የግቢ ጉባኤያት ምሩቃን ዓለም አቀፍ ኅብረት

Description
ሰላም እንደምን ሰነበታችሁ? ይህ ቻናል የተከፈተው በማኅበረ ቅዱሳን የግቢ ጉባኤያት አገልግሎት መንፈሳዊ ትምህርት ሲከታተሉ ቆይተው ከግቢ ጉባኤያት ለተመረቁ በመላው ዓለም ለሚገኙ አባላት ሲሆን በዚህ ቻናል የሚተላለፉ መልዕክቶች፣ ትምህርታዊ ጽሑፎች እና ልዩ ልዩ የፕሮጀክት ሐሳቦች በማኅበረ ቅዱሳን ዋናው ማእከል አማካኝነት ሲሆን ምሩቃን ወደዚህ ቻናል እንዲቀላቀሉ የበኩልዎትን ድርሻ ይወጡ።
Advertising
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated hace 3 semanas, 5 días

Last updated hace 3 semanas

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated hace 1 mes, 1 semana

1 month ago
[የአርማንያ ሰማዕት |አርሴማ|](https://youtu.be/94wfdG3stKc?si=F8wkB7hMt2KEYQ93)

https://youtu.be/94wfdG3stKc?si=F8wkB7hMt2KEYQ93

የአርማንያ ሰማዕት |አርሴማ|
ለሰማያዊ ክብር በወንጌል|፪| ያስጌጠሽ
ለቃሉ ምስክር አምላክ  የጠራሽ።
የአርማንያ ሰማዕት|፪|  አርሴማ አንች ነሽ፣

          አዝ...........
የምሥጢር ዋሻ ነሽ የሰማይ ሙሽራ፣
በዓለማት ሁሉ ክብርሽ የሚያበራ።
ምግባር|፪| እና እምነትን አስተባብረሽ ይዘሽ፣
በመንግሥተ ሰማይ አክሊል ተቀዳጀሽ።
አዝ.........
በእውነት ቢያምርም የሰው ልጅ ውበቱ፣
ምግባር ከታጣበት በሰማይ አባቱ።
ያልሆነለት|፪| እሱ ውበት ሃይማኖቱ፣
ብለሽ ተናግረሻል ይቀራል በከንቱ።
አዝ.....
የጽናት ምስክር  ለቃለ ወንጌሉ ፣
ከሁሉ ይበልጣል  የፈጣሪ ኃይሉ።
ጸንተው|፪| ለሚኖሩ በሃይማኖታቸው ፣
አርሴማ እናታችን አብነት ሆንሻቸው።
አዝ........
ለሰማያዊ ክብር ሰለሆንሽ ምክንያት፣
እኛ እንልሻለን የሁላችን  እናት።
ለምናምን|፪| ሁሉ በምልጃ ኪዳንሽ፣
ምሕረትን አሰጪን ለምነሽ ከአምላክሽ።

1 month ago

አገልግሎቴን አከብራለሁ!
በእያንዳንዳችን ሕይወት ውስጥ “አገልግሎት” የሚለው ቃል በተለያየ መልኩ ሊገለጽ ይችላል፡፡ ሰው በግሉ፣ ከቤተ ሰቡ እንዲሁም ከማኅበረሰቡ ጋር ከሚያከናውናቸው ተግባራት ውስጥ “አገልግሎቴ” ብሎ የሚያስባቸው ምግባሮች ሊኖሩት ይችላሉ፡፡ ለዚህም ዕውቀት ይኑረው አይኑረው ለማወቅ ቢያዳግትም ከቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ ግን አገልግሎትን ማወቅ፣ መረዳትና መተግበር እንዲችል ግንዛቤ መፍጠር ተገቢ ነው፡፡
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ “የሰው ልጅ ሊያገለግል ነፍሱንም ለብዙዎች ቤዛ ሊሰጥ መጣ” በማለት በቅዱስ ወንጌል እንደ ነገረን ክርስቶስን የምንመስልበት፣ እርሱን ወደ መምሰል የምናድግበት፣ ነፍሳችንን ለእርሱ የምንሰጥበት የሕይወት መንገድ ነው። (ማቴ. ፳፥፳፰) ስለ ብዙዎቹ በሥጋም፣ በነፍስም፣ በመንፈስም መዛል ራስን ቤዛ አድርጎ በመስጠት የሰዎችን መንፈሳዊ ብስለት፣ ሥጋዊ ጥንካሬ እንዲያገኙ እግዚአብሔርን ደስ የምናሰኝበትና ከእግዚአብሔር ጋር የምንገናኝበት ሕይወት ነው። በቤተ ክርስቲያን አገልግሎት የምናገለግለው ሌሎችን ሰዎች ነው። ለሊሎች መኖር ሌሎችን ማገልገል ደግሞ ክርስቶስን መምሰል ነው።
ከምንም በላይ አስቀድሞ አገልግሎት ለአምላካችን እግዚአብሔር የሚፈጸም ነው፤ ሰውን በአርአያውና በአምሳሉ ሲፈጥረው በምስጋናና በውዳሴ ከመላእክት ጋር አንድ ሆነው ስሙን እንዲቀድሱ ክብሩን እንዲወርሱ ነው፡፡ ስለዚህም ሕገ እግዚአብሔርን እየጠበቅን፣ ሥርዓቱን እየፈጸምንና በመንፈሳዊ ሕይወት ውስጥ ለራስም ሆነ ለሌሎች የምናከናውነው በጎ ምግባር አገልግሎት እንለዋለን፡፡ ከጸሎት ጀምሮ የምንጾመው ጾም፣ የምንሰግደው ስግደት፣ የምንመጸውተው ምጽዋትና ለቤተ ክርስቲያን የምናቀርበው መባ ሁሉ ለፈጣሪያችን የሚቀርብ ነውና አገልግሎት ነው፡፡
በመንፈሳዊ ሕይወታችን በአንድም ይሁን በሌላ ምክንያት በጎውን አስበን ልንተገብር የምንችልው ስለ እግዚአብሔር ቅዱስ ቃል ማወቅና ተግባራዊ ክርስትናን መረዳት ስንችል ነው፡፡ በመሆኑም ከሁሉም ነገር በፊት የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት ጠንቅቆ ማወቅ ይገባል፡፡ የፈጣሪያችንን ቅዱስ ፈቃድና ትእዛዝ ለመፈጸም የሚረዳንን አገልግሎታችንን ልናውቅና ልናከብርም ይገባናል፡፡

ለአገልግሎት የሚሰጥ ክብር
ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ለሮሜ ሰዎች በላከው መልእክቱ “ለእናንተም ለአሕዛብ እናገራለሁ። እኔ የአሕዛብ ሐዋርያ በሆንሁ መጠን ሥጋዬ የሆኑትን አስቀንቼ ምናልባት ከእነርሱ አንዳንዱን አድን እንደሆነ አገልግሎቴን አከብራለሁ” በማለት እንደተናገረው በክርስቶስ ክርስቲያን የተባልን ሰዎች ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት ተቀባይነትና ተወዳጅነት ያለውን አገልግሎት እናከብር ዘንድ አለን፡፡ (ሮሜ ፲፩፥፲፫)
“አገልግሎቴን አከብራለሁ” ስንልም አገልግሎት የተሰጠን ሹመት ስለሆነ ሹመትን አለማክበር ደግሞ ከክብር ያወርዳል፤ ቅጣት ያመጣል፤ ከንጉሡ ማዕድና ከቤተ ክርስቲያን ኅብረት የሚለይ ስለሆነ አገልግሎትን ማክበር መንፈሳዊ ግዴታ ነው። የቂስ ልጅ የሚሆን ሳኦል ምንም እንኳን ሹመትን ወድዶ፣ ፈልጎ የተሾመ ባይሆንም የጠፉትን የአባቶቹን አህዮች ለመፈለግ እንደሄደ በእግዚአብሔር ፈቃድ በነቢዩ ሳሙኤል ተቀብቶ ቢነግሥም ከቅጣት እንዳልዳነ መጽሐፍ ቅዱስ በ፩ኛ ሳሙኤል ምዕራፍ ፱ ይነግረናል።
የቂስ ልጅ ሳኦል እግዚአብሔር በትልቅ ሕዝብ ላይ ሹሞት ሳለ ሹመቱን በአግባቡ ባለ መጠቀሙ እግዚአብሔር ናቀው፤ አቃለለው፤ መንግሥቱን አሳልፎ ሰጠበት። ዛሬም እግዚአብሔር እኔና እናንተን መርጦ በራሳችን ላይ እንዲሁም በሌሎች ሰዎች ላይ እንደ እየ አቅማችን መጠን ሹሞናል። ለዚህ ከመረጠን ደግሞ ሹመትን አክብሮ መታዘዝ ማገልገል የሁላችን ግዴታ ነው።
አገልግሎት ክርስቶስ ለእርሱ ላለን ፍቅር ማረጋገጫ አድርጎ ያቀረበልን ነው። ቅዱስ ጴጥሮስን ትወደኛለህ? በማለት ሦስት ጊዜ በመጠየቅ “ከወደድከኝ በጎቼን ጠብቅ” እንዳለው ሁሉ እኛም በአገልግሎት አባግዕ የተባሉ ምእመናንን ራሳችንን ጨምሮ በመጠበቅ (ጠብቆም ላልቶም ይነበብ) የተሰጠንን ኃላፊነት ልንወጣ ይገባናል። (ዮሐ.፳፩፥፲፯)
የማያነግሡት ንጉሥ የማያከብሩት ክቡር ማንም የማያበድረው ባለ ጸጋ ሲሆን አገልግሎታችንን ባናከብር ለእግዚአብሔር የሚቀርበት ኖሮ ሳይሆን እንድናገለግል የፈቀደልን፣ ኃይሉን፣ ጥበቡን፣ ማስተዋሉን የሰጠን፣ አበው በእራት ላይ ዳረጎት እንዲሉ በጸጋ ላይ ጸጋ በክብር ላይ ክብር የሚጨምርልን ከፍጹም ፍቅሩ የተነሣ ነው።
ይቆየን!

1 month ago
[የአበውን ርስት አንሰጥም](https://youtu.be/8UWUkNFHHCE?si=NoRSZtySzwCisiQW)

https://youtu.be/8UWUkNFHHCE?si=NoRSZtySzwCisiQW

የአበውን ርስት አንሰጥም

የአበውን ርስት /አንሰጥም/(፪) አሳልፈን
እንኖራለን ጸንተን መስቀል ተሸክመን(፪)
እንኖራለን በእምነት ተደግፈን

ያ ኢይዝራኤላዊው ናቡቴ በሰማርያ
የወይኑ ፍሬ ናት የማንነቱ መለያ
አክአብ ድንበርተኛው በወይኗ ጎምጅቶ
ነቃቅሎ ሊጥላት ሊያጠፋት ሽቶ
ያችን መልካም እርሻ ባድማ ሊያደርጋት
ሊገዛት ወደደ በእጥፍ ሊለውጣት

አዝ= = = = =

ተኩላው ለምድ ለብሶ ገብቶ ከበረትሽ
አድብቶ ቢሰራም እንዲፈርስ ስርአትሽ
በሃይማኖት ቆመን ድል እንነሳዋለን
በርትዕት ተዋህዶ የኖሩትን ይዘን

አዝ= = = = =

ጠላት ቢከፋብን ያለ በደላችን
በብዙ መከራ ቢከበብ ዙሪያችን
በእመ ብርሃን ምልጃ ሁሉን እናልፋለን
በእግዚአብሔር ቸርነት በርስት እንኖራለን

አዝ= = = = =

ዛሬም በእኛ ዘመን አክአብ ተነስቷል
ርስት ድንበራችንን ቀን በቀን ይገፋል
እኛም ናቡቴ ነን ሰማዕት እንሆናለን
የተዋህዶን ርስት እናስከብራለን/(፪)"

3 months, 2 weeks ago
**አደራ አለብኝ!**ዓለም አቀፍ የግቢ ጉባኤ ምሩቃን …

አደራ አለብኝ!ዓለም አቀፍ የግቢ ጉባኤ ምሩቃን ኅብረት ጉባኤ

የ2017 ዓ.ም 1 ኛ ዙር ቨርቹዋል ጉባኤቀን፡ መስከረም 26/2017 ዓ.ም

ሰዓት፡ ምሽት 2፡00-3፡00

ሁሌም በየወሩ በግቢ ጉባኤያት ምሩቃን ዓለም አቀፍ ኅብረት የቴሌግራም ቻናል

https://t.me/gibigubayat_mirukan_hibret

3 months, 3 weeks ago
[ንትፈሣሕ ዮም](https://youtu.be/GnvpjUnQD_0?si=FtJC4WYm5nfeeqCW)

https://youtu.be/GnvpjUnQD_0?si=FtJC4WYm5nfeeqCW

ንትፈሣሕ ዮም

ወንሕነኒ ንትፈሣሕ ዮም ወንግበር በዓለ
በዛቲ ዕለት በዓለ እግዚእነ።
አዝ.........
የድኅነት ምክንያት የሕይወት መገኛ፣
ምልክታችን ነው የተሰጠን ለእኛ።
መስቀል ኃይላችን ነው ለሁሉ ሚያበራ፣
ነጻ የወጣበት አዳም ከመከራ።
አዝ....
ሥጋው ተቆርሶበት ደሙ የፈሰሰበት፣
ጥንተ ጠላታችን ድል የተነሣበት።
አምላክን የቻለ   መስቀል ዕፀ ሕይወት፣
የነጻነት አርማ አዳም የዳነበት።
አዝ........
ያዕቆብ ባረከ ኤፍሬም  ምናሴን።
በመስቀል አምሳያ ዘርግቶ እጆቹን።
ቀድሞ በነቢያት ምሥጢር ያናገረ፣ 
አማሌቃውያንን እንዲያ  ያሳፈረ።
አዝ..........
ኃይል ያጎናጽፋል የመስቀሉ ምሥጢር ፣
የሙሴ ጦር ጋሻ ጠላት ሚያሳፍር።
ለቀደመ ክብር ዳግም አበቃቸው፣
የመስቀል ምልክት ኅይል ጸወን ሆናቸው።
አዝ.....
ወልድ ቢያፈስበት ደሙን በመስቀሉ፣
ተክሶ ቀረለት የአዳም በደሉ።
እኛ እናከብራለን አምነናል በቃሉ፣
ሕይወት ስለሰጠን ነገረ መስቀሉ።

3 months, 3 weeks ago
3 months, 4 weeks ago
4 months ago
የግቢ ጉባኤያት ምሩቃን ዓለም አቀፍ ኅብረት
4 months ago
የግቢ ጉባኤያት ምሩቃን ዓለም አቀፍ ኅብረት
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated hace 3 semanas, 5 días

Last updated hace 3 semanas

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated hace 1 mes, 1 semana