ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated 2 months, 3 weeks ago
Last updated 2 months, 2 weeks ago
ይህ ስለ Manchester United መረጃዎችን የሚያገኙበት የ Telegram ቻናል ነው 🇪🇹
--------------------------------------------------------------
☞︎| ስለ ማንቸስተር ዩናይትድ ትኩስ መረጃዎች
☞| ቀጥታ ስርጭቶች ከየስታድየሞቹ
☞| የዝውውር ዜናዎች
☞| ስለ ማንችስተር ዩናይትድ ታሪኮች
📩 ለማስታወቂያ ስራ DM :- @Marcoabdu
Last updated 1 month, 1 week ago
በነጻ የአይን ሞራ ግርዶሽ ህክምና የ151 ዜጎችን የአይን ብርሃን መመለስ መቻሉ ተገለፀ!
ወራቤ ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ከሀበሺስታን ዴቬሎፕመንት ኤንድ ኮኦፕሬሽን አሶሴሽን ጋር በመተባበር ከታህሳስ 13 ጀምሮ ሲሰጥ የቆየው የነፃ የአይን ምርመራ እና የአይን ሞራ ግርዶሽ ቀዶ ህክምና አገልግሎት ለ151 ዜጎች ህክምና በማድረግ ብርሃናቸውን በመመለስ መጠናቀቁ ተገልጿል።
የወራቤ ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የአይን ህክምና ክፍል ኃላፊ አቶ ምናለ ደበበ በዘመቻው ለ3 ሺህ ዜጎች የአይን ምርመራው መደረጉንና የአይን ሞራ ግርዶሽ ያለባቸውን 151 ዜጎች በመለየት ቀዶ ህክምና እና የመድኃኒት እደላ መዳረጉን ተናግረዋል።
አገልግሎቱ የተሰጣቸው ዜጎች ከተለያዩ የክልሉ አካባቢዎች እንደመጡ በመጠቆምም በርካቶች በአይን ሞራ ግርዶሽ ምክንያት የአይን ብርሃናቸውን አጥተው እንደሚኖሩ ገልጸዋል።
የአይን ሞራ ግርዶሽ ሳይታከም ከቆየ ለአይነ ስውርነት ያጋልጣል ያሉት ኃላፊው በጊዜ ከታከመ የሚድን በመሆኑ ችግሩ ያለባቸው አካላት ምርመራ ማድረግና መታከም እንዳለባቸውም አክለው ገልጸዋል ማለታቸውን ከሆስፒታሉ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ከ60 ሀገራት በላይ ይሳተፉበታል ተብሎ የሚጠበቀው 2ኛው አለም አቀፍ የቁርኣን እና አዛን ውድድር በኢትዮጵያ የመግባያ ትኬት ሽያጭ መጀመሩ ተገለፀ!
በኢትዮጵያ የዘመን ቀመር የፊታችን ጥር 25/2017 ዓ.ል በአዲስአበባ ስታዲየም ለማካሄድ ቀነ ቀጠሮ የተያዘለት ሁለተኛው አለም አቀፍ የቁርኣን እና የአዛን ውድድር የመግቢያ ትኬት ሽያጭ መጀመሩ እና አጠቃላይ ዝግጅቱን አስመልክቶ የውድድሩ አብይ ኮሚቴ በዛሬው ዕለት መግለጫ ሰጥቷል።
ከተለያዩ ሀገራት በርካታ እንግዶች በውድድሩ ላይ ለመሳተፍ ኢትዮጵያ ለመምጣት ዝግጅታቸውን መጨረሳቸውን የተገለፀ ሲሆን እንግዶች ለማስተናገድ ብሎም ውድድሩን በተሻለ መልኩ ለማካሄድ የፋይናንስ ድጋፍ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ የመግቢያ ትኬት ለሽያጭ መዘጋጀቱ ተገልጿል።
በመሆኑም በመላው ኢትዮጵያ እንዲሁም በውጭ አለም የሚኖሩ ሙስሊሞች እንዲሁም የቁርኣን ውድድሩን መታደም የሚፈልጉ ሁሉ ትኬት በመግዛት ተሳታፊ እንድሆኑ ጥሪ ቀርቧል።
ሀገራችን ኢትዮጵያን ከአለም አቀፉ ማህበረሰብ ጋር ይበልጥ ለማስተዋወቅ ሰፊ ድርሻ ይኖረዋል በተባለው በዚህ ታላቅ አለም አቀፍ የቁርአን ውድድር አሜሪካ ካናዳ እንግሊዝ እና ሳዑዲ አረብያን ጨምሮ ከ60 በላይ ሀገራት ተሳታፊ ይሆናሉ ተብሏል።
የዘንድሮው ውድድር ለየት የሚያደርገው ኢስላማዊ አደብን በጠበቀ መልኩ አለም አቀፍ የሴቶች የቁርአን ውድድር በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚካሄድ መሆኑ ተገልጿል።
ውድድሩን ስኬታማ ለማድረግ አብይ ኮሚቴው የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የበላይ ጠባቂነት እንዲሁም የመንግስት ባለድርሻ አካላትና ዘይድ ኢብኑ ሳቢት የቁርአን ማህበር አስፈላጊውን ስራ እያከናወኑ መሆናቸው የተገለፀ ሲሆን ሙስሊም ማህበረሰብ፣ ሚዲያዎች፣ የማህበረሰብ አንቂዎችና የሚመለከታቸው ግለሰቦች አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርጉ ጥሪ ቀርቧል።
የመግቢያ ትኬቶቹን በሁሉም የሂጅራ ባንክ ቅርንጫፎች፣ በአዋሽ ባንክ እና በኦሮሚያ ኮፕሬትቭ ባንክ ማግኘት እንደሚቻል ተገልጿል።
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት እና የሰላም ሚኒስቴር በሀገራዊ የሰላም ግንባታ ሥራዎች ላይ በጋራ እንደሚሠሩ ተናገሩ!
ሁለቱ ተቋማት ይህን ያሳወቁት የጠቅላይ ምክር ቤቱ ፕሬዚደንት የክብር ዶክተር ሼይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ የሰላም ሚኒስትር ክቡር መሐመድ ኢድሪስን ዛሬ በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው ባነጋገሩበት ወቅት ነው።
የጠቅላይ ምክር ቤቱ ፕሬዚደንት ክቡር ሼይኽ ሐጂ ኢብራሒም ቱፋ እና የሰላም ሚኒስትሩ ክቡር አቶ መሐመድ ኢድሪስ በሀገሪቱ የተጀመረውን ሰላም አጠናክሮ ማስቀጠል በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ሐሳብ ተለዋውጠዋል፡፡
ፕሬዚደንቱ አዲስ የተሾሙት የሰላም ሚኒስትር ክቡር አቶ መሐመድ ኢድሪስ ጠቅላይ ምክር ቤቱን ለመጎብኘትና በሰላም ጉዳይ ላይ ለመወያየት በመምጣታቸው በራሳቸውና በጠቅላይ ምክር ቤቱ ስም አመስግነዋል።
ሥራውን ከጀመረ ሁለት ዓመት ከመንፈቅ ዕድሜ ያስቆጠረው የለውጡ መጅሊስ የነበሩበትን የተለያዩ ዕዳዎች በመክፈል ትልልቅ ፕሮጀክቶችን እውን ለማድረግ በከፍተኛ እንቅስቃሴ ላይ እንደሚገኝ ክቡር ፕሬዚደንቱ ተናግረዋል።
የሙስሊሙን አንድነት እና የአገራችንን ሰላም ለማጠናከር ጠቅላይ ምክር ቤቱ የተለያዩ ሥራዎችን እየሠራ እንደሚገኝ የጠቀሱት ክቡር ፕሬዚደንቱ ምክር ቤቱ የሚኒስቴሩ አጋር በመኾን ይህን ሥራ ይበልጥ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል።
ክቡር ሚኒስትሩ በበኩላቸው የጠቅላይ ምክር ቤቱ ፕሬዚደንት ክቡር ሼይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ አገራችንን ኢትዮጵያን በዓለም አቀፍ መድረኮች ላይ ለማስተዋወቅና የሙስሊሙን ብሎም የአገርን ስም ከፍ ለማድረግ እየሠሩ ያሉትን ሥራ አድንቀዋል።
በአፋር እና በሶማሊ ወንድማማች ሕዝቦች መካከል የነበረውን የቆየ የሰላም እጦት ለመቅረፍ ጠቅላይ ምክር ቤቱ የሠራው ሥራ ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገበ መኾኑን የጠቀሱት ክቡር ሚኒስትሩ፣ በቀጣይም ምክር ቤቱ ሁሉን አቀፍ የሰላምና የልማት ሥራዎችን አጠናክሮ እንዲቀጥል አሳስበዋል።
የሃይማኖት አገር በኾነችውና በርካታ የችግር መፍቻ ባህሎችና ልምዶች ባላት አገራችን ላይ ዜጎች በሰላም እጦት ሳቢያ ለችግር መዳረግ እንደሌለባቸው ክቡር ሚኒስትሩ ተናግረዋል።
አሁን ያለው ሰላም እንዲጎለብት፣ እየታዩ ያሉ የሰላም ፈተናዎች እንዲፈቱና ችግሮቻችን በሙሉ ዘላቂ መፍትኄ እንዲያገኙ በጁምዓ ሶላት ወቅት አገራዊ የሰላም ጥሪ እና ዱዓ እንዲደረግ ጠቅላይ ምክር ቤቱ መልዕክት እንዲያስተላልፍ ሚኒስትሩ ጥሪ አቅርበዋል።
በመንግሥት በኩል ለሰላም የሚከፈል ማንኛውም ዋጋ እንደሚከፈል የጠቀሱት ክቡር ሚኒስትሩ የሰላም ሚኒስቴርም ከሁሉም የእምነት አባቶች እና ተቋማት ጋር በትብብር እንደሚሠራ በአጽንዖት ተናግረዋል።
በጠቅላላይ ምክር ቤቱ ፕሬዚደንት ቢሮ በተደረገው በዚህ ውይይት ላይ የጠቅላይ ምክር ቤቱ የዓሊሞች ጉባዔ ምክትል ሰብሳቢና የፈታዋ እና ምርምር ተጠሪ ዶክተር ጀይላን ኸድር፣ ምክትል ፕሬዚደንትና የሐጅና ዑምራ ዘርፍ ተጠሪው ሼይኽ አብዱልዓዚዝ ሼይኽ አብዱልወሊ፣ ሌሎች የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላትና የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
◾️ መረጃው የኢ/እስ/ጉ/ጠ/ም/ቤት ነው።
ውድ የተከበራቹህ የቻናላችን ቤተሰቦች በሙሉ
ዛሬ አንድ ለበርካቶች ጥያቄ መሰረት እንደ ፍላጎታቹህ ለ10 ቀናት እና ከዛ በላይ በኡምራ ፕሮግራም መቆየት ለምትፈልጉ እነሆ እንኳን ደስ አላቹህ ይላቹሀል ኢትዩ ቱር ትራቭል
? ከጥር 8ጀምሮ በፈለጉት የፓኬጅ አይነት በመካና በመዲና የምቆዩበት ልዩ የኡምራ ፓኬጅ በኢትዩ ቱር ኤንድ ትራቭል ተዘጋጅቶል
በተመጣጣኝ ዋጋ እና በልዩ መስተንግዶ ልዩ የዒባዳ ግዜን ማሳለፍ ከፈለጉ የኛ ቤተሰብ ይሁኑ
? ልዩ ጥቅል ከ ኢትዮ ቱር ?
ከጥር 8 ጀምሮ
ለ7 ቀን(3ቀን መካ 3 ቀን መዲና)
ለ 12 ቀን (8ቀን መካ 4ቀን መዲና)
ለ 15 ቀን (10 ቀን መካ 5ቀን መዲና)
?ምንሰጣቸው አገልግሎቶች?
✅ የኡምራ ቪዛ
✅ ቲኬት
✅ ሆቴል
✅ ትራንስፖርት
✅ ምግብ እና ላውንደሪ
✅ የሳኡዲ ሲም ካርድ
ለበለጠ መረጃ
+251946555777
+251946888777
8924(አጭር ኮድ)
ቤተሰብ ተጨንቋል ከቤት ከወጣ ቀናት አልፈውታል ግን እስካሁን አልተመለሰም።ቢላል ኸሊል ይባላል ያለበትን የምታወቁ ወይም ካያችሁት ከስር በተቀመጠው ስልክ ለቤተሰቡ በመጠቆም እንዲሁም ይህን ልጥፍ ሼር በማድረግ ብንተባበር መልካም ነው።
0910189442
ውዴታ እኮ
አቡበክር የሆነ ሰሀባ ምን ያስለቅስሀል የአባ በክር ብሎ ሲጠይቀው ...?የአላህ መልዕክተኛ ﷺ ሲያለቅሱ አይቼ አለቀስኩ አለ
ውዴታ እኮ የአላህ መልዕክተኛ ﷺ
"በአኢሻ አትጉዱኝ " እንዳሉት ነው ።
የአላህ መልዕክተኛ ﷺ ለእናታችን አኢሻ የኔ ውዴታ ላንቺ ገመድ ላይ የተቆጠረ ቆጠሮ ነው ማንም የማይፈታው ። እናታችንም እየሳቀች አልፎ አልፎ ቆጠሮው እንዴት ነው ብላ ትጠይቃቸዋለች እሷቸውም እንደዛው ነው ይሎት ነበር ﷺ ﷺ
"ካፕቴን በመሆን ኢትዮጵያን ካደጉት ሀገራት ተርታ ማሰለፍ እንፈልጋለን"
የመወዳ ስኩል ተማሪዎች
- ሀሩን ሚድያ፣ ታህሳስ 3/2017
የአለም አቀፍ ሲቪል አቭየሽን ድርጅትና የኢትዮጽያ ሲቪል አቭየሽን ባለስልጣን 80ኛ ዓመት ክብረ በዓል ኘሮግራም ላይ በሂጃባቸው ደምቀው ተሳታፊ የነበሩት የመወዳ ስኩል ተማሪዎች ወደፊት ብቁ ካፒቴን በመሆን ኢትዮጵያን በአቪየሽን ዘርፍ ካደጉት ሀገራት ተርታ ማሰለፍ እንደሚፈልጉ በዝግጅቱ ላይ ለነበሩት የክብር እንግዶች ገልፀዋል።
በዝግጅቱ ላይ በሂጃባቸው ደምቀው የቀረቡት የመወዳ ስኩል ተማሪዎች የተለያዩ አቭየሽንን የሚገለፁ መልዕክቶችን ያስተላለፉ ሲሆን ወደፊት በኢትዮጵያ አየር መንገድ በመስራት የሀገራቸውን ስም ማስጠራት እንደሚፈልጉ ተናግረዋል።
የአለማቀፍ አቭየሽን ድርጅትና የኢትዮጵያ ሲቪል አቭየሽን ባለስልጣን 80ኛ ዓመት ክብረ በዓልና የአፍሪካ አቭየሽን ኤክስፖ መክፈቻ ስነ-ስርአት ህዳር 30/2017 ዓ.ል በደማቅ ሁኔታ መካሄዱ ይታወሳል።
በመክፈቻው ፕሮግራም ላይ የትራንስፖርትና ሎጅስቲክ ሚንስትር ዶ/ር አለሙ ስሜ የአለም አቀፍ ሲቪል አቭየሽን ድርጅት የምስራቅ አፍሪካ ሪጅናል ዳይሬክተር ሚስ ሉሲ ምቡጉዋ፣ የኢትዮጵያ አቭየሽን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ጀኔራል የሆኑት አቶ ጌታቸው መንግስቴና ሌሎች የኢትዮጵያ አቭየሽን ባለስልጣናትና ሰራተኞች ተገኝተው ነበር።
የኢትዮጲያ አየር መንገድ አሁን እየተከተለው ከሚገኘው አሰራር አንፃር ከጉልበት በላይ የሆኑ አጭር ቀሚሶችን መልበስ እና ጸጉርን ማስያዝ (መልቀቅ) እንደስራ ግዴታ የሚታይ ሲሆን ይህ ህግ የእነዚህን ልጆች ህልም ሊያጨልም ስለሚችል የሚመለከተው አካል አፋጣኝ መፍትሄ እንዲሰጥም ተጠይቋል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ተገቢውን መስፈርት አሟልተው ያለፉ ሙስሊም ሴት እህቶች "በሂጃባቸው ምክንያት ከስራ እንዳይታገዱ በዘላቂት እፈታለሁ" ያለ ቢሆን እስካሁን ተፈፃሚ አለመሆኑ ይታወቃል።
© ሀሩን ሚድያ
ማስታወቂያ/Promotion ማሰራት የምትፈልጉ አናግሩኝ
@Faysul
የጽዮናውያን ወረራ ከጋዛ ሰርጥ በስተደቡብ በምትገኘው በካን ዩኒስ በተፈናቃዮቹ ድንኳኖች ላይ ኢላማ ካደረገ ብኋላ አስከሬናቸው የተቃጠሉ የፍልስጤም ህጻናት አስክሬን ተገኝቷል።
ኢላሂ አቤት አቻቻልህ ያረብ
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated 2 months, 3 weeks ago
Last updated 2 months, 2 weeks ago
ይህ ስለ Manchester United መረጃዎችን የሚያገኙበት የ Telegram ቻናል ነው 🇪🇹
--------------------------------------------------------------
☞︎| ስለ ማንቸስተር ዩናይትድ ትኩስ መረጃዎች
☞| ቀጥታ ስርጭቶች ከየስታድየሞቹ
☞| የዝውውር ዜናዎች
☞| ስለ ማንችስተር ዩናይትድ ታሪኮች
📩 ለማስታወቂያ ስራ DM :- @Marcoabdu
Last updated 1 month, 1 week ago