ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated 2 months, 3 weeks ago
Last updated 2 months, 2 weeks ago
ይህ ስለ Manchester United መረጃዎችን የሚያገኙበት የ Telegram ቻናል ነው 🇪🇹
--------------------------------------------------------------
☞︎| ስለ ማንቸስተር ዩናይትድ ትኩስ መረጃዎች
☞| ቀጥታ ስርጭቶች ከየስታድየሞቹ
☞| የዝውውር ዜናዎች
☞| ስለ ማንችስተር ዩናይትድ ታሪኮች
📩 ለማስታወቂያ ስራ DM :- @Marcoabdu
Last updated 1 month, 1 week ago
የጥር 26 ምሽት ዋና ዋና የዓለም ዜናዎች፦
🟠 ከአውሮፓ ህብረት ባለስልጣናት ይልቅ ፑቲን ሁሌም የገቡትን ቃል ይጠብቃሉ ሲሉ የሀንጋሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ቪክቶር ኦርባን ተናገሩ።
🟠 ፊንላንድ በዩክሬን ቅጥረኛ ሆነው ለሚያገለግሉ የቆሰሉ ዜጎቿ የማስወጣት ወይም ህክምና የመስጠትን ጨምሮ ምንም አይነት እርዳታ እንደማታቀርብ የፊንላንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሰነድ አመለከተ።
🟠 ቀኝ ዘመሙ አማራጭ የጀርመን ፓርቲ በምርጫ ፕሮግራሙ በሩሲያ ላይ የተጣለው ማዕቀብ በአስቸኳይ እንዲነሳ እና የኖርድ ስትሪም ማስተላለፊያ ወደነበረበት እንዲመለስ ጥሪ አቅርቧል ተባለ።
🟠 ሜክሲኮ ከዩናይትድ ስቴትስ ጋር ያላትን ድንበር ለማጠናከር 10,000 ወታደሮችን እንደምታሰማራ የሜክሲኮ ፕሬዝዳንት ክላውዲያ ሼንቦም አስታወቁ።
🟠 የዩኤስ ኤድ ዋና መስሪያ ቤት ሰራተኞች ቢሮ እንደተዘጋ እና ወደ ስራ እንዳይመጡ የሚገልጽ ደብዳቤ እንደደረሳቸው የአሜሪካ መገናኛ ብዙሃን ዘገቡ።
🟠 ቻይና እ.አ.አ በ2026 በአስር ኪሎ ሜትሮች የሚዘል የምርምር መንኮራኩር ወደ ጨረቃ በመላክ በምድር ሳተላይት ደቡባዊ ዋልታ የውሃ አካል እንደምትፈልግ ተገለፀ።
📲 መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦
👉 APK ፋይል ሊንክ
ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ 👉@sputnik_ethiopia
🇿🇦🇨🇩 የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ለኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሚያደርጉትን ድጋፍ "አልተውም" ሲሉ ተናገሩ
14 የደቡብ አፍሪካ ወታደሮች መሞታቸውን ተከትሎ ሰራዊታቸውን እንዲያስወጡ ጥሪው ቢጨምርም፤ ሲሪል ራማፎሳ ለኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሚያደርጉትን ድጋፉ እንደሚቀጥሉ ቃል ገብተዋል።
🗣 "በምስራቅ ኮንጎ እና አከባቢው ዘላቂ ሰላምና ደህንነትን ለማስፈን የሀገራትን የጋራ ፈቃድ ይጠይቃል" ሲሉ ፕሬዝዳንቱ ተናግረዋል።
📲 መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦
👉 APK ፋይል ሊንክ
ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ 👉@sputnik_ethiopia
sputnikviral | 👽 የጠፋ ስልጣኔ ቅሪት ወይንስ ምሥላዊ ቴክኒክ? በማርስ ላይ ሚስጥራዊ የአራት ማዕዘን ውቅር ተገኘ
በናሳ ማርስ ኦርቢተር ካሜራ የተቀረፀው 235 ሜትር ካሬ መዋቅር፤ ባለሙያዎች ሳይንሳዊ ማብራሪያ ባይሰጡበትም፤ የባዕድ አካላት ሴራ መላ ምቶችን አቀጣጥሏል።
🗣 በጉዳዩ ላይ አስተያየቱን የሰጠው የስፔስ ኤክስ ዋና ስራ አስፈፃሚ ኤለን መስክ "ጠፈርተኞችን ወደ ማርስ በመላክ መመርመር አለብን!" ብሏል።
📲 መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦
👉 APK ፋይል ሊንክ
ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ 👉@sputnik_ethiopia
🇪🇹🇺🇳 ኢትዮጵያ በዓለም ቀዳሚ የምግብ ምርት ላኪ የመሆን አቅም እንዳላት የመንግሥታቱ ድርጅት ባለስልጣን ተናገሩ
በትክክለኛ ኢንቨስትመንት እና ወደ አረንጓዴ፣ ዘላቂ እና ውጤታማ ኢኮኖሚ በሚደረግ ሽግግር፤ ኢትዮጵያ የራሷን የምግብ ዋስትና ከማረጋገጥ ባለፈ፤ በአፍሪካ እንዲሁም በዓለም ቀዳሚ የምግብ ሰብል አቅራቢ የመሆን ትልቅ አቅም አላት ሲሉ፤ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ እርዳታ አስተባባሪ ዶ/ር ራሚዝ አላክባሮቭ ተናግረዋል።
ዶ/ር ራሚዝ አላክባሮቭ ኢትዮጵያ በሚቀጥሉት ሁለት አስርት ዓመታት ከዓለም ቀዳሚ ኢኮኖሚዎች ተርታ ልትሰለፍ እንደምትችልም ጠቁመዋል ሲል የመንግሥት ሚዲያ ዘግቧል።
ሀገሪቱ የአፍሪካን የእርዳታ ተቀባይነት ታሪክ በመቀየር እና የምግብ ዋስትና እና ሉዓላዊነትን በማረጋጋጥ ረገድ ትልቅ ሚና እየተጫወተች እንደሆነም ነው የተናገሩት።
ኢትዮጵያ በግብርናው ዘርፍ የጀመረችውን ትልቅ ሀገራዊ ተነሳሽነት ወደ ፊት ለማራመድ በምታደርገው ጥረት፤ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ተልዕኮ ከሀገሪቱ ጀርባ መሆኑን ዶ/ር ራሚዝ አረጋግጠዋል ተብሏል።
📲 መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦
👉 APK ፋይል ሊንክ
ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ 👉@sputnik_ethiopia
🇪🇹 የብልጽግና ፓርቲ ሁለተኛ ጉባዔ ታዳሚዎች ኢትዮጵያ እያስመዘገበች ያለውን እድገት እና ለቅርስ ጥበቃ የምታደርገውን ጥረት አደነቁ
የፖለቲካ መሪዎች እና የፓርቲ ተወካዮች የአዲስ አበባን "አስደናቂ" ለውጥ፤ በተለይም መሠረተ ልማቱን እና የአንድነት ፓርክን አድንቀዋል። "እጅግ አስደናቂ" ነው ሲሉ የገለፁትን ብሔራዊ ቤተ-መንግሥት እና የከተማዋን አጠቃላይ እድገት እንዲሁ አንስተዋል።
ፖለቲከኞቹ አዲስ አበባ የአፍሪካ ህብረት ዋና ፅህፈት ቤት እንደመሆኗ፤ ወሳኝ ከተማነቷን አጽንዖት በመስጠት መናገራቸውን የመንግሥት ሚዲያ ነው የዘገበው።
📲 መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦
👉 APK ፋይል ሊንክ
ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ 👉@sputnik_ethiopia
🇷🇺🇺🇬 የሩሲያ የሰብዓዊ ደህንነት ጥበቃ ባለሙያዎች በኡጋንዳ የኢቦላ ቫይረስን ለመቆጣጠር ምክር እየሰጡ ነው ተባለ
እንደ የሩሲያ የሰብዓዊ ደህንነት ጥበቃ ሮስፖትርብናድዞር መግለጫ፤ የኡጋንዳ ጤና ሚኒስቴር አንድ የጤና ሰራተኛ በኢቦላ ቫይረስ መያዙን ጥር 22 ቀን አስታውቋል።
ከተያዘው ሰው ጋር ግኑኝነት የነበራቸው አብዛኞቹ ሰዎች በምሥራቅ የሀገሪቱ ክፍል በሚገኝ የአካባቢ ሆስፒታል ሰራተኞች እንደሆኑ መረጋገጡን ተከትሎ፤ የሮስፖትርብናድዞር ተንቀሳቃሽ ላብራቶሪ በአፋጣኝ እንዲላክ ተደርጓል።
🗣 "የሩሲያ ስፔሻሊስቶች በተንቀሳቃሽ ላብራቶሪው አሰራር እና በአደገኛ ቫይረሶች የባዮሎጂካል ደህንነት ሕግ ዙርያ ለኡጋንዳ ባልደረቦቻቸው ተከታታይ ምክር እየሰጡ ነው" ብሏል መግለጫው።
📲 መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦
👉 APK ፋይል ሊንክ
ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ 👉@sputnik_ethiopia
🇿🇦🇺🇸 ራማፎሳ ከትራምፕ ጋር በመሬት ወረሳ ጉዳይ ዙርያ ለመወያየት ዝግጁ እንደሆኑ ገለፁ
የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ በማህበራዊ ትሥሥር ገፃቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ "በእነዚህ ግኑኝነቶች በጉዳዮ ላይ የተሻለ እና የጋራ መግባባት እንደምንፈጥር እርግጠኞች ነን" ብለዋል።
📲 መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦
👉 APK ፋይል ሊንክ
ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ 👉@sputnik_ethiopia
❗️ኔቶ ዘለንስኪ የምዕራባውያን የጦር መሳሪያዎችን አፍሪካ ውስጥ ለሚገኙ ቡድኖች በመሸጥ እንደተሳተፉ የሚያሳይ መረጃ ይፋ ሊያደርግ እንደሆነ የሩሲያ የውጭ ደህንነት አገልግሎት አስታወቀ
እንደ የውጭ ደህንነት አገልግሎቱ መረጃ መሠረት፤ የዘለንስኪን ስም የማጥፋት ትልቅ ዘመቻ በኔቶ ዋና መሥሪያ ቤት እየተዘጋጀ ይገኛል።
በተለይም "ፕሬዝዳንቱ" እና የቡድናቸው አባላት ለጦር መሳሪያ ግዢ የተመደበ ከ1.5 ቢሊዮን ዶላር በላይ ፈንድ፤ ለግል ጥቅም እንዳዋሉ የሚያሳይ መረጃ ይፋ ለማድረግ እንዳቀደ የውጭ ደህንነት አገልግሎቱ በመግለጫው አስታውቋል።
👉 "በተጨማሪም ዘለንስኪ እና ሸሪኮቻቸው በህይወት እንዳሉ እና በጦር ግንባር እያገለገሉ እንደሆነ ተደርገው የተመዘገቡ 130ሺህ የሞቱ የዩክሬን ወታደሮችን ክፍያ ወደ ውጭ ሀገር ለማዘዋወር የወጠኑትን ሴራ ለማጋለጥ እንደታቀደ" የኤጀንሲው ፕሬስ ቢሮ አክሎ ገልጿል።
📲 መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦
👉 APK ፋይል ሊንክ
ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ 👉@sputnik_ethiopia
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated 2 months, 3 weeks ago
Last updated 2 months, 2 weeks ago
ይህ ስለ Manchester United መረጃዎችን የሚያገኙበት የ Telegram ቻናል ነው 🇪🇹
--------------------------------------------------------------
☞︎| ስለ ማንቸስተር ዩናይትድ ትኩስ መረጃዎች
☞| ቀጥታ ስርጭቶች ከየስታድየሞቹ
☞| የዝውውር ዜናዎች
☞| ስለ ማንችስተር ዩናይትድ ታሪኮች
📩 ለማስታወቂያ ስራ DM :- @Marcoabdu
Last updated 1 month, 1 week ago