Why Pay for Entertainment? Access Thousands of Free Downloads Now!

Murad Tadesse (Official Channel)☪️🇪🇹

Description
ትክክለኛው ኢስላማዊ አስተምህሮ፦
1) ከቁርኣን፣
2) ከሐዲሥ፣ [በሰለፎች አረዳድ]
3) ከታማኝ ዑለማዎችና
4) ከትክክለኛ ቂያስ ተጠናቅሮ ይቀርብበታል።
√ አዳዲስና ወቅታዊ ኢስላማዊ የሆኑ ጉዳዮችም ይዳሰሳሉ።
√ አላማዬ በዲኔ ላይ ያለውን የመረጃ ክፍተት መሙላት ነው።

ማንኛውም አስተያዬት ሲኖራችሁ @Murad_Tadesse ላይ አስፍሩት።

ስህተትም ባያችሁ ጊዜ አርሙኝ።
ጀዛኩሙል`ሏህ ኸይራ!
Advertising
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated hace 1 día, 17 horas

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated hace 5 días, 6 horas

Last updated hace 5 días, 19 horas

6 days, 23 hours ago
Murad Tadesse (Official Channel)☪️🇪🇹
6 days, 23 hours ago
The sound system in the Haramain …

The sound system in the Haramain !

More than 8000 speakers transmit the Adhan, the Iqāmah, Salahs and the Khutbahs from Al Masjid Al Haram, its courtyards and surroundings.

Whereas in Al Masjid Al Nabawī, 2900 speakers are distributed throughout the Haram.

Around 22 microphones are distributed in Al Masjid Al Haram whereas in Al Masjid Al Nabawī there are 31.

There are 3 sound systems in the Haramain, just in case they fail.
- The main sound system
- The backup sound system
- The emergency sound system

More than 170 technicians look after the sound system in the Haramain, and they adjust the system from the Imams and the Muadhins microphone according to what is appropriate for everyone to hear.

1 week, 6 days ago
Murad Tadesse (Official Channel)☪️🇪🇹
1 week, 6 days ago
Murad Tadesse (Official Channel)☪️🇪🇹
1 week, 6 days ago

የጥንቃቄ መልዕክት

(በአሁኑ ዘመን የተቸገረን መርዳት አስቸጋሪ ደረጃ ላይ ደርሷል!)
||
በአሁኑ ወቅት የበርካታ ሰዎችን መታመም ሰበብ በማድረግ እርዳታ በማሰባሰብ ሽፋን በተለያዬ መልኩ የሚያጭበረብሩ ሰዎች መብዛታቸው ትክክለኛ ተረጂዎች እንዳይረዱ መሰናክል ሆኗል።

ለናሙና ያክል፦
①) መኪና ተከራይተውና ሐሰተኛ የሕክምና ማስረጃ ይዘው «ወንድማችን ታሞብን ነው!» በማለት በተለያዩ ወረዳዎች እየተዟዟሩ ከማኅበረሰቡ ከታች በፎቶው የምትመለከቱትን ብር ያጭበረበሩ ሰዎች እጅ ከፍንጅ መያዛቸውን የወላይታ ሶዶ ከተማ ፖሊስ አሳውቋል።

አሁን የነዚህ ሰዎች ድርጊት በትክክል ሰው ታሞባቸው በመኪና ተዟዙረው ድጋፍ የሚያሰባስቡ ሰዎች በሙሉ በጥርጣሬ ዓይን እንዲታዩ የሚያደርግ ነው።

  • ②) ከቅብር ጊዜ ወዲህ የቴክኖሎጂውን መሻሻል ተከትሎ ሌላኛው የማጭበርበሪያ መድረክ የሆነው ማኅበራዊ ሚዲያ ነው። በውሸት ውስወሳና ጅንጀና የተሻለ ገንዘብና ሥራ ታገኛላችሁ በሚል የሚያጭበረብሩ ዘርፈ ብዙ ስካመሮች እንዳሉ ሆነው፤ በተቸገሩ ሰዎች ሽፋን ኪሳቸውን የሚያደልቡም የትየለሌ ናቸው።

እነዚህን በሦስት ከፍለን እንያቸው፦
ሀ) የሆነ ወቅት ላይ የታመመን ህፃን ወይም ሰው ሆስፒታል ተኝቶ የሚያሳይ ወይም ህመሙን አሳዛኝ በሆነ መልኩ የሚገልፅ ፎቶ አያይዘው፤ ከስር የግላቸውን የባንክ አካውንት አያይዘው በሶሻል ሚዲያ በማሰራጨት የሚሸቅሉ አሉ። ምናልባትም ያ የለጠፉት ፎቶ የሆነ ወቅት ላይ ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ተፖስቶ ገንዘብ የተሰባሰበበት ይሆናል። ግን የተሰባሰበለት ሰው ብሩ ሞልቶለት ታክሞ ድኖ ይሆናል ወይም አላህ ከወሰነም ሞቶ ይሆናል። እነርሱ ግን ያንን እንደ አዲስ ፖስተው በነርሱ አካውንት እንድገባ ያደርጋሉ። ሰውም የተፖሰተውን አሳዛኝ ፎቶ ተመልክቶ ውስጡ ስለሚያዝን ሳያጣራ ይሰድቃል።
*
ለ) የተፖሰተው ፎቶ ወይም ቪድዮ እውነተኛ ይሆናል። በተለይም ቲክቶከሮችና ዩ ቲዩበሮች እዚያ ታማሚ ዘንድ ይሄዱና ቀርፀውት በፖስትና በቀጥታ ስርጭት ገቢ ያሰባስቡለታል። ግን የሚሰባሰብበት አካውንት የራሳቸው አካውንት ነው። ወይም እዛው ተመካክረው የሚተዋወቁት አጭቤዎች በግሩፕ የከፈቱት አካውንት ነው። በኋላ ለታማሚ ትንሽ ነገር ጣል ያደርጉለታል። ምክንያቱም ምን ያክል እንደተሰባሰበ መረጃው ስለሌለው የሰጡትን አምኖ ይቀበላል፤ ያንኑስ ማን አየበት በሚል መንፈስ!

አንዳንዶች ግን በተለይም አሁን ከትናንት በፊት ቲክቶክ ላይ የተከሰተው፤ «ያሰባሰብንለት ልጅ አይድንም ብዬ ብሩን አጥፍቼዋለሁ!» ብሎ በአደባባይ ሲናገር የተቀዳውን ቪድዮ በጆሮዬ ሰምቻለሁ። አለፍ ሲልም ብሩ 350 ሺህ ብር እንደሆነና "ወጣት ነኝ፣ ሰይጣን አሳስቶኝ ነው፣ አካውንቴን ሽጬ እከፍላለሁ!» ብሏል። ውርደት ከነ ግርማ ሞገሱ!
*
ሐ) ለአላህ ብለው ሳይሆን ጉዳዩን እንደ ቢዝነስ አድርገውት በኮሚሽን የሚያሰባስቡ አሉ። ማለትም በፌስቡክ ወይም በቴሌግራም ወይም በቲክቶክ ወይም በዩ ቲዩብ… በርካታ ተከታታይ ያላቸው ግለሰቦች ሰው የታመመበት ሰው ወይም ራሱ የታመመው ሰው ለሕክምና ተቸግሮ አሰባስቡልኝ ሲላቸው «እሺ! ግን ከሚሰባሰበው ገንዘብ ላይ 20%ቱን ልትሰጠን ትስማማለህ ወይ?» ይሉታል። ከዚያ አማራጭ ስለሌለው እሺ ይላል። ህዝቡ በዚህ መልክ እንደሚሠሩ ስለማያውቅ ዝም ብሎ ይሰጣል። ግን ከፊሉ ገንዘብ ለአሰባሳቢው ነው። ይህ ሥራ 100% ሐራም ነው ለማለት ባልደፍርም ግን ብልግና ነው። ወይ በዛ መልኩ እንደምትሠሩ ማሳወቅ አለባችሁ። የተጨነቀን ሰው ከኪሳችሁ አውጥታችሁ መርዳት ባትችሉ እንኳ በነፃ ብታስተባብሩለት ምን ትጎዳላችሁ? ከአላህ አጅር ማግኘት አትሹም?
አላህ ቢጠይቃችሁስ? ወጣት ናችሁ፤ የሶሻል ሚዲያ ጡረተኛ ከመሆን ሠርታችሁ አትበሉም?

ለካ ለዛ ነው ብዙዎች ሰው ታሞባቸው እንዳሰባስብላቸው ሲጠይቁኝ ወይም ሰውም ሆነ መኪና ጠፍቶባቸው አፋልጉኝ እንድለጥፍላቸው ሲጠይቁኝ፤ «የሚያስፈልግ ነገር ካለ እናሟላለን!» ይላሉ። ለካ በሌሎች ስለሚጠየቁ እኔም የምጠይቃቸው መስሏቸው ነው።


መፍትሄ፦
①) በማይታወቅ ሰው ለተፖሰተ አፋልጉኝ ሳታጣሩ አትሰድቁ። የሚታወቅ ቢሆንም በደንብ የሚታመን መሆኑን እወቁ። በተለይ ኮሚሽን ባልኳችሁ ዘዴ በርካታ የምታውቋቸው ሰዎች ጭምር ይሠራሉ። ወላሂ! ብነግራችሁ ታፍራላችሁ። የማትጠብቁት ሰው ሁላ ተዘፍቆበታል።

  • ②) በቀጥታ የታመመውን ሰው በብረት ዓይናችሁ ካላያችሁ ወይም ያዬ የምታምኑት ሰው ካልነገራችሁ በመኪና ለሚዞሩትም ቢሆን አትስጡ። የሆነ ፎቶ ስለተለጠፈ ወይም ታማሚ ተብሎ የሆነ ሰው መኪናው ውስጥ ስለተኛ ብቻ እውነት ነው ማለት አይደለም። አንዳንዱ እግሩን በጀሶ ጠግኖ በውሸት የታመመ መስሎ ተኝቶ የተጋለጠ አለ።
    በዚህ መልኩ ለሕክምና ከሚያስፈልገው በላይም የሚያሰባስብ አለ። እንዳውም የሆነ ቀልድ ላይ «መኪናህን መታከሚያ ገንዘብ ላሰባስብበት አከራየኝ ያለህ ሰው፤ በሳምንቱ "ስንት ትሸጠዋለህ?" ሲልህ…!» የሚል አይቻለሁ። ሁሉንም አይመከትም።

በነዚህ አጭበርባሪዎች የተነሳ በትክክል መረዳት ያለባቸው እንዳይጎዱና መተማመን ጠፍቶ መጨካከን እንዳይመጣ፤ እያጣራን እንርዳ እላለሁ። ውስጣቸውን ሳይሰቀጥጠው የአሳዛኝ ታማሚ ሰውነ ገንዘብ የሚያጭበረብሩና በሐሰት የሚለምኑ ሰዎችንም አላህ ልቦናቸውን ለሐቅ ይከፍትላቸው።


ወንድማችሁ፦ ሙራድ ታደሰ
========
ኦገስት 20, 2024 G.C.
ሚያዚያ 13, 2016 E.C.
||
t.me/MuradTadesse

2 months, 2 weeks ago
ዓሊሞች'ኮ አይናገሩ!***👌***

ዓሊሞች'ኮ አይናገሩ!👌

«ከሁለት የወጣ ጎመን አትሁኑ!» ይላል ያ'ገራችን ሰው።

2 months, 2 weeks ago

ትክክለኛ ጓደኛህን እንደት መለየት ትችላለህ⁉️

ትክክለኛ ጓደኛህ ማን እንደሆነ ማወቅ ከፈለግክ ወደ ሰፈር (ጉዞ) አብረኸው ውጣ። በተለይም ስንቅ የሚያልቅበት ጉዞ፣ አድካሚ የእግር መንገድ ያለው፣ ከሃገር ውጭ… ወዘተ ሊሆን ይችላል።

ጠቢቦቹ እንዲህ ይላሉ፦

إذا أردت أن تكتشف صديقاً سافر معه፣
ففي السفر ينكشف الإنسان يذوب المظهر وينكشف المخبر..
ولماذا سمي السفر سفراً إلا لأنه عن الأخلاق والطبائع يسفر.

ሰፈር "ሰፈር" የተባለው የሰውየው ጸባይና ተፈጥሮ አብረው ስለሚሳፈሩ ትክክለኛ ማንነቱ የሚገለጥበት ስለሆነ ነው። ከላይ ከላይ ሲያሳይ የነበረው ሽንገላ ያኔ ፍንትው ብሎ ትክክለኛ መሠረታዊ ማንነቱ ይታያል።

سُمّي السفر سفرًا لأنه يُسْفرُ عن أخلاق الشخص فيَعود لطبْعه ويرجع لأصل خُلِقه، كما أن السفر تجربة مثيرة ووسيلة حقيقية لمعرفة الصديق الصدوق، فالصداقة من أسمى المشاعر التي يعيشها الإنسان، ولا يمكن التعبير عنها بكلمات، لأنها تأتي من الصدق والوفاء والإخلاص، ومبنية على الحبّ والمودة، تتميز بمشاركة الأفراح والأتراح، وبتجردها من المصلحة والنفاق وسوء النية،

ጓደኝነትን በተመለከተ ከተባሉ ትክክለኛ አባባሎች መካከል ይህን እናገኛለን፦
لذلك نجد أصــدق ما قيل عنـها «احْذر عدوّك مرّة وصديقك ألف مرّة، فإن انقــلب الصديـق فهو أعلم بالمضرّة»،

«ጠላትህን አንድ ጊዜ ተጠንቀቅ፤ ጓደኛህን ግን 1000 ጊዜ ተጠንቀቅ። ምክንያቱም ፊቱን ካዞረ አንተን የበለጠ የሚጎዳህን ነገር ያውቃል (የቅርብ ሰውህ ስለሆነ ደካማ ጎንህን ጠንቅቆ ያውቃል)።

والله ولي التوفيق.

ደግሞ እርስ በርሳችሁ የጎረጥ ተያዩ አሏችሁ¡

እኔ ካነበብኩት ለመጠቆም ያክል ነው። ግን ጓደኛን በሰፈር ጊዜ ፈትነው የሚለው የማያወላዳ እውነታ ነው!

||
t.me/MuradTadesse

2 months, 2 weeks ago

በዚህ እንስሳ ጉዳይ አላህን አትፈራም⁉️

ሐዲሡን ያስተላለፈው የጀዕፈር ኢብኑ አቢ ጧሊብ ልጅ ዐብደ-ል'ሏህ ነው፤ አላህ መልካም ሥራውን ይውደድለትና።
በአንድ ወቅት የአላህ መልዕክተኛ ﷺ አንፈራጠውኝ ጋልበን እየሄድን ሳለ ወደ አንድ ባለቤትነቱ የአንሷር ሰው ወደ ሆነ ማሳ ጉዳያቸውን ለመፈጸም ሲገቡ፤ አንድ ግመል ከማሳው አጥር ውስጥ አለ። እርሰቸውን ﷺ የተመለከተ ጊዜ በናፍቆት ስቅስቅ ብሎ ለቆይታ ያክል አለቀሰ፤ ዓይኖቹም እምባ አቀረሩ።

እርሳቸው ወደ ግመሉ ጠጋ አሉና ጀርባውን ሲያሻሹት፤ ለቅሶውን አቆመ። «ማነው የዚህ ግመል ባለቤት?» አሉ አዛኙና ውዱ ነቢይ – የጌታዬ ሰላምና እዝነት በርሳቸው ላይ ይስፈንና።

ከአንሷሮች የሆነ አንድ ወጣት መጣ። «የኔ ነው!» አንቱ የአላህ መልዕክተኛ ሆይ! ﷺ አላቸው።

«በዚህ እንስሳ ጉዳይ አላህን አትፈራም⁉️» አሉት። «አላህ ላንተ ትቆጣጠረው ዘንድ ያገራልህን? አንተ እንደምታስርበውና (ከአቅሙ በላይ እያሠራህ) እንደምታደክመው ስሞታ ነግሮኛል!» አሉት።
[አሕመድ: 1745፣ አቡ ዳውድ 2549]

ወልሏሁ-ል-ሙስተዓን!

በኛ ሃገር በተለይም በጋሪ ሥራ ላይ የተሰማሩ ወንድሞች ፈረሶችን በጣም ሲያሰቃዯቸው ይስተዋላል። ተጠቅመው ይጥሏቸዋል፤ ያስርቧቸዋል፣ ከአቅም በላይ ይጭኗቸዋል፣ በግርፋትና እንግልት ያሰቃዯቸዋል።

አላህ ይጠቀሙባቸው ዘንድ ባገራላቸው ፈረሶች ጉዳይ አላህን አይፈሩምን⁉️

አየህ ግን እስልምናን! አይደለም ለሰው ልጅ ለእንስሳ ሳይቀር የሚያዝኑ፣ ስሞታቸውን የሚረዱ ውድና አዛኝ ነቢይ የሆኑት የሙሐመድ ﷺ ኡመቶች ነን። እኛን በፍትሕ ጉዳይ መወንጀል ወንጀል ነው።

አላህ ሆይ! የትኛውንም ፍጡርህን ከመደበል ጠብቀን።

የሐዲሡ ዐረብኛ ይህ ነው።

(أردَفَني رسولُ اللَّهِ صلَّى اللَّهُ علَيهِ وسلَّمَ خَلفَهُ ذاتَ يومٍ، فأسرَّ إليَّ حَديثًا لا أحدِّثُ بِهِ أحَدًا من النَّاسِ، وَكانَ أحبُّ ما استَترَ بِهِ رسولُ اللَّهِ صلَّى اللَّهُ علَيهِ وسلَّمَ لحاجَتِهِ هَدفًا، أو حائِشَ نَخلٍ، قالَ: فدخلَ حائطًا لرَجُلٍ مِن الأنصارِ فإذا جَملٌ، فلَمَّا رأى النَّبيَّ صلَّى اللَّهُ علَيهِ وسلَّمَ حنَّ وذرِفَت عيناهُ، فأتاهُ النَّبيُّ صلَّى اللَّهُ علَيهِ وسلَّمَ فمَسحَ ذِفراهُ فسَكَتَ، فقالَ: مَن ربُّ هذا الجَمَلِ، لمن هذا الجمَلُ؟ فَجاءَ فتًى منَ الأنصارِ فَقالَ: لي يا رسولَ اللَّهِ فَقالَ: أفلا تتَّقي اللَّهَ في هذِهِ البَهيمةِ الَّتي ملَّكَكَ اللَّهُ إيَّاها؟ فإنَّهُ شَكا إليَّ أنَّكَ تُجيعُهُ وتُدئبُهُ!)

||
t.me/MuradTadesse

2 months, 3 weeks ago

ሰለፎች በሸዕባን ወር

በሸይኽ ዐብዱ ያሲን (ረሒመሁ-ል'ሏህ)

©: Video Credit: Nesiha Tv

We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated hace 1 día, 17 horas

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated hace 5 días, 6 horas

Last updated hace 5 días, 19 horas