ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated 2 weeks, 6 days ago
Last updated 2 weeks, 1 day ago
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot
🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹
Last updated 1 month ago
ከየትኛውም ዩኒቨርስቲ የምትመረቁ ወንድምና እህቶች፤ መብሩክ ብያለሁ። አላህ ራሳችሁንም፣ ቤተሰባችሁንም፣ ኡማውንም የምትጠቅሙበት ያድርግላችሁ። ግን አደራ! ከገደብ ያለፈ የምርቃት ድግስ ውስጥ አትግቡ። ኋላ ሥራ ሲጠፋ ሼም ያሲዛል። ከወዲሁ እንድትጨናነቁ ሳይሆን ከመጠን በላይ ከመደገስ ይልቅ ሳንቲሟን ያዝ አድርጓትና ፒሲ የሌለህ ገዝተህ የተማርከውን ፊልድ ተግባር ተኮር አድርገውና ሥራ ወዲያውኑ ጀምር።
Application is now open in the monthly scholarship in the Kingdom of Saudi Arabia ?? for Bachelor, Master and PhD.
Funding provided:
?️ Monthly salary 1900 riyals
?️Preparation Allowance (will be given once upon attendance).
?️ Comprehensive health insurance throughout the period of the grant.
?️ Provision of housing and utilities.
?️ Providing supported meals to the candidate.
?️ Allowance to charge books (at graduation).
?️ Providing the candidate with round trip tickets annually to and from the mother country.
?️️Enjoying all the activities and trips of the university.
Details and the application link are in the comments ⬇️
Good luck to all
The sound system in the Haramain !
More than 8000 speakers transmit the Adhan, the Iqāmah, Salahs and the Khutbahs from Al Masjid Al Haram, its courtyards and surroundings.
Whereas in Al Masjid Al Nabawī, 2900 speakers are distributed throughout the Haram.
Around 22 microphones are distributed in Al Masjid Al Haram whereas in Al Masjid Al Nabawī there are 31.
There are 3 sound systems in the Haramain, just in case they fail.
- The main sound system
- The backup sound system
- The emergency sound system
More than 170 technicians look after the sound system in the Haramain, and they adjust the system from the Imams and the Muadhins microphone according to what is appropriate for everyone to hear.
(በአሁኑ ዘመን የተቸገረን መርዳት አስቸጋሪ ደረጃ ላይ ደርሷል!)
||
✍ በአሁኑ ወቅት የበርካታ ሰዎችን መታመም ሰበብ በማድረግ እርዳታ በማሰባሰብ ሽፋን በተለያዬ መልኩ የሚያጭበረብሩ ሰዎች መብዛታቸው ትክክለኛ ተረጂዎች እንዳይረዱ መሰናክል ሆኗል።
ለናሙና ያክል፦
①) መኪና ተከራይተውና ሐሰተኛ የሕክምና ማስረጃ ይዘው «ወንድማችን ታሞብን ነው!» በማለት በተለያዩ ወረዳዎች እየተዟዟሩ ከማኅበረሰቡ ከታች በፎቶው የምትመለከቱትን ብር ያጭበረበሩ ሰዎች እጅ ከፍንጅ መያዛቸውን የወላይታ ሶዶ ከተማ ፖሊስ አሳውቋል።
አሁን የነዚህ ሰዎች ድርጊት በትክክል ሰው ታሞባቸው በመኪና ተዟዙረው ድጋፍ የሚያሰባስቡ ሰዎች በሙሉ በጥርጣሬ ዓይን እንዲታዩ የሚያደርግ ነው።
እነዚህን በሦስት ከፍለን እንያቸው፦
ሀ) የሆነ ወቅት ላይ የታመመን ህፃን ወይም ሰው ሆስፒታል ተኝቶ የሚያሳይ ወይም ህመሙን አሳዛኝ በሆነ መልኩ የሚገልፅ ፎቶ አያይዘው፤ ከስር የግላቸውን የባንክ አካውንት አያይዘው በሶሻል ሚዲያ በማሰራጨት የሚሸቅሉ አሉ። ምናልባትም ያ የለጠፉት ፎቶ የሆነ ወቅት ላይ ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ተፖስቶ ገንዘብ የተሰባሰበበት ይሆናል። ግን የተሰባሰበለት ሰው ብሩ ሞልቶለት ታክሞ ድኖ ይሆናል ወይም አላህ ከወሰነም ሞቶ ይሆናል። እነርሱ ግን ያንን እንደ አዲስ ፖስተው በነርሱ አካውንት እንድገባ ያደርጋሉ። ሰውም የተፖሰተውን አሳዛኝ ፎቶ ተመልክቶ ውስጡ ስለሚያዝን ሳያጣራ ይሰድቃል።
*
ለ) የተፖሰተው ፎቶ ወይም ቪድዮ እውነተኛ ይሆናል። በተለይም ቲክቶከሮችና ዩ ቲዩበሮች እዚያ ታማሚ ዘንድ ይሄዱና ቀርፀውት በፖስትና በቀጥታ ስርጭት ገቢ ያሰባስቡለታል። ግን የሚሰባሰብበት አካውንት የራሳቸው አካውንት ነው። ወይም እዛው ተመካክረው የሚተዋወቁት አጭቤዎች በግሩፕ የከፈቱት አካውንት ነው። በኋላ ለታማሚ ትንሽ ነገር ጣል ያደርጉለታል። ምክንያቱም ምን ያክል እንደተሰባሰበ መረጃው ስለሌለው የሰጡትን አምኖ ይቀበላል፤ ያንኑስ ማን አየበት በሚል መንፈስ!
አንዳንዶች ግን በተለይም አሁን ከትናንት በፊት ቲክቶክ ላይ የተከሰተው፤ «ያሰባሰብንለት ልጅ አይድንም ብዬ ብሩን አጥፍቼዋለሁ!» ብሎ በአደባባይ ሲናገር የተቀዳውን ቪድዮ በጆሮዬ ሰምቻለሁ። አለፍ ሲልም ብሩ 350 ሺህ ብር እንደሆነና "ወጣት ነኝ፣ ሰይጣን አሳስቶኝ ነው፣ አካውንቴን ሽጬ እከፍላለሁ!» ብሏል። ውርደት ከነ ግርማ ሞገሱ!
*
ሐ) ለአላህ ብለው ሳይሆን ጉዳዩን እንደ ቢዝነስ አድርገውት በኮሚሽን የሚያሰባስቡ አሉ። ማለትም በፌስቡክ ወይም በቴሌግራም ወይም በቲክቶክ ወይም በዩ ቲዩብ… በርካታ ተከታታይ ያላቸው ግለሰቦች ሰው የታመመበት ሰው ወይም ራሱ የታመመው ሰው ለሕክምና ተቸግሮ አሰባስቡልኝ ሲላቸው «እሺ! ግን ከሚሰባሰበው ገንዘብ ላይ 20%ቱን ልትሰጠን ትስማማለህ ወይ?» ይሉታል። ከዚያ አማራጭ ስለሌለው እሺ ይላል። ህዝቡ በዚህ መልክ እንደሚሠሩ ስለማያውቅ ዝም ብሎ ይሰጣል። ግን ከፊሉ ገንዘብ ለአሰባሳቢው ነው። ይህ ሥራ 100% ሐራም ነው ለማለት ባልደፍርም ግን ብልግና ነው። ወይ በዛ መልኩ እንደምትሠሩ ማሳወቅ አለባችሁ። የተጨነቀን ሰው ከኪሳችሁ አውጥታችሁ መርዳት ባትችሉ እንኳ በነፃ ብታስተባብሩለት ምን ትጎዳላችሁ? ከአላህ አጅር ማግኘት አትሹም?
አላህ ቢጠይቃችሁስ? ወጣት ናችሁ፤ የሶሻል ሚዲያ ጡረተኛ ከመሆን ሠርታችሁ አትበሉም?
ለካ ለዛ ነው ብዙዎች ሰው ታሞባቸው እንዳሰባስብላቸው ሲጠይቁኝ ወይም ሰውም ሆነ መኪና ጠፍቶባቸው አፋልጉኝ እንድለጥፍላቸው ሲጠይቁኝ፤ «የሚያስፈልግ ነገር ካለ እናሟላለን!» ይላሉ። ለካ በሌሎች ስለሚጠየቁ እኔም የምጠይቃቸው መስሏቸው ነው።
♠
✔ መፍትሄ፦
①) በማይታወቅ ሰው ለተፖሰተ አፋልጉኝ ሳታጣሩ አትሰድቁ። የሚታወቅ ቢሆንም በደንብ የሚታመን መሆኑን እወቁ። በተለይ ኮሚሽን ባልኳችሁ ዘዴ በርካታ የምታውቋቸው ሰዎች ጭምር ይሠራሉ። ወላሂ! ብነግራችሁ ታፍራላችሁ። የማትጠብቁት ሰው ሁላ ተዘፍቆበታል።
በነዚህ አጭበርባሪዎች የተነሳ በትክክል መረዳት ያለባቸው እንዳይጎዱና መተማመን ጠፍቶ መጨካከን እንዳይመጣ፤ እያጣራን እንርዳ እላለሁ። ውስጣቸውን ሳይሰቀጥጠው የአሳዛኝ ታማሚ ሰውነ ገንዘብ የሚያጭበረብሩና በሐሰት የሚለምኑ ሰዎችንም አላህ ልቦናቸውን ለሐቅ ይከፍትላቸው።
♣
ወንድማችሁ፦ ሙራድ ታደሰ
========
ኦገስት 20, 2024 G.C.
ሚያዚያ 13, 2016 E.C.
||
t.me/MuradTadesse
ዓሊሞች'ኮ አይናገሩ!?
«ከሁለት የወጣ ጎመን አትሁኑ!» ይላል ያ'ገራችን ሰው።
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated 2 weeks, 6 days ago
Last updated 2 weeks, 1 day ago
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot
🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹
Last updated 1 month ago