ከመጻሕፍት ዓለም - Book shelf 📗📚📖

Description
"ስለመጻሕፍት ከመጻሕፍት መንደር እንዘምራለን!"
Advertising
We recommend to visit

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ ? @Esat_tv_comment_bot

??ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ??

Last updated 1 month, 1 week ago

Last updated 2 months, 1 week ago

እንኳን ደህና መጡ‼

✔ማስታወቂያ ለማሰራት እና ጥቆማ ለመስጠት በዚህ ይጠቀሙ ☞https://t.me/WasuMohammed

✔ ቻናሉን ለመቀላቀል Join ☞http://t.me/Wasulife

ከልብ አመሰግናለሁ♥?

Last updated 2 months ago

2 days, 12 hours ago
የተከፈለበት ማስታወቂያ!

የተከፈለበት ማስታወቂያ!

ውሸት ነው ሲባል…Notcoin ከፈለ … Pixelverse የፍንጥር ሰጠ … Avacoin መላ በጠሰ…Dogs ጨላ አንበሸበሸ። Hamster እና Cats ትንሽም ቢሆን ሰጥተዋል። ስሙኝ። ትርፍ ጊዜያችሁን እርባን በሌለው ነገር ላይ ከምታጠፉ ቴሌግራም ላይ በኤርድሮፕ ገንዘብ ስሩበት። አንድ ነገር አለ። በጣም የሚጠቅም ወይም ቅድሚያ የምትሰጡት ስራ ወይም ተግባር ካለ ግዜያችሁን እዛ ላይ ማዋል ይገባል። ምንም ጥያቄ የለውም። ነገር ግን በዋዛ ፈዛዛ ሚባክን ካለ ግን ቢያንስ እዚህ ላይ ቢውል መልካም ነው። ምንም ግንዛቤ የሌለው ቅድሚያ ስለክሪፕቶ ወይም ኤርድሮፕ ጥናት እንዲያደርግ ይመከራል። ከዛ የተመቸው ይስራ ያልተመቸው ባላየ ይለፈው። አሁን ምጋብዛችሁ። የተረጋገጠ ቶን ከፋይ Airdrop ነው!

Ton ማለት የቴሌግራም መገበያያ ገንዘብ ነው። በወቅታዊ ምንዛሬ 1 Ton = 5 dollar አከባቢ ነው። ጓደኞቻችሁን በመጋበዝ ብቻ Ton ማግኘት ትችላላችሁ። ይሄ ከሌላው የሚለየው minimum withdrawሉ 0.1 ton መሆኑ ነው። ከዛ Verify በሆነ የTelegram Wallet በኩል የሰራነውን Ton ወደ ብር በቀላሉ ቀይረን ማውጣት እንችላለን። ይሄም 100% እውነት ነው። መልካም አዲስ ዓመት! ጆይን ለማለት…

👇👇👇

https://t.me/AblyBot/join?startapp=ref1067310339

4 days, 6 hours ago

የትምህርት ነገር

… …

የትምህርትን ሥርዓት በማሻሻል ብቻ በትምህርት ረገድ ለውጥ ማምጣት አይቻልም፤ ብቻ የምትለዋን አስምሩባት። መልካም የትምህርት ሥርዓት አቅርቦቱን እንደሚያሻሽለው ጥርጥር የለውም። በትምህር ፍላጎት ላይ የሚኖረው ተጽዕኖ ግን ውስን ነው።

ሰው ለምን ይማራል? ለምንስ መማር አለበት?

ይህን ጥያቄ መመለስ የትምህርት ፍላጎትን ለመረዳት ወሳኝ ነው። ትክክለኛው መልስ ሰው ለመሆን የሚለው ነው፣ ምሉዕ ሰው። ትምህርት ሰው ራሱን ፈልጎ የሚያገኝበት ጉዞ ነው። በዚህ ሂደት ከተፈጥሮ፣ አካባቢው፣ መሠሉ እና ሁለንተና ጋር ያለውንና የሚኖረውን መስተጋብር ይረዳል። ይህ ነበር የትምህርት ዕሴት መሆን የነበረበት።

በዚህ ረገድ፣ ትምህርት በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ አበርክቶ አልነበረውም ባይባልም፣ እጅግ ውስን ነው።

ከዚህ ይልቅ የትምህርት ፋይዳ፣ ከሥራ ቅጥር ጋር በእጅጉ የተቆራኘ ነው። ትምህርት ልጆች በቀጣይ ህይወታቸው ኑሯቸውን የሚመሩበትን ገቢ ለማግኘት የሚያስችል እውቀትና ክህሎት ማስጨበጫ መሳሪያ ሆኖ ቆይቷል። ይህ እንግዲህ ውጤታማ ከሆነ ነው። በዚህ ረገድ የኛ ሀገር ትምህርት ውራ ነበር ማለት ይቻላል። ከትምህርት ይልቅ አጫጭር ስልጠናዎችና የሥራ ላይ ልምምዶች የላቀ ዋጋ አላቸው።

ሌላኛው የትምህርት ፋይዳ የስብዕና ግንባታ ነው። አነሰም በዛ የሀገራችን ትምህርት ለዚህ ዓላማ ጠቀሜታ ሲሰጥ ቆይቷል።

… …

የትምህርት አሥርዓት መሻሻል የተሻለ የትምህርት አቅርቦት እንዲኖር ያደርጋል። ፍላጎትንም በተወሰነ ደረጃ ያበረታታል፣ ራስን የመፈለግ፣ እውቀትና ክህሎት የማስጨበጥ እና ስብዕናን የመገንባት ሚናውን በአግባቡ ስለሚወጣ።

ብዙ ሰው ግን ልጆቹን የሚያስተምረው የወደፊት ህይወታቸው መልካም እንዲሆን በማሰብ ነው። ይህ ደግሞ በሌሎች ጉዳዮች ላይ የተመሰረተ ነው።

መንግስት ዋነኛ ቀጣሪ በሆነበት እና የቅመስፈርቱም ብቃት ባልሆነበት ሁኔታ የመማር ፍላጎት ይገታል፣ እውቀትና ክህሎትን የመሻት ጉጉት ይዳከማል።

ዜጎች በነፃነት በኤኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ውስጥ የሚሳተፉበት ዕድል በጠበበበት ሀገር፣ ሰዎች ለትምህርት የሚሰጡት ዋጋ ይቀንሳል። በነፃነት የማሰብ፣ የመኖር፣ የማምረት እና የንብረት ባለቤት የመሆን መብቶች በሚደፈጠጡበት አገር፣ እውቀትና ክህሎት ዋጋቸው ይኮስሳል።

… …

ምን ለማለት ነው?

አጠቃላይ የአገራችን ፖለቲካዊና ኤኮኖሚያዊ ሥርዓት ሳይስተካከል፣ ትምህርትን ማሻሻል የማይቻል እንኳ ባይሆን እጅግ ከባድ ነው።

© Ja Liberty

3 weeks, 5 days ago

አሚታብ ማለት ለህንዳውያን ምን ማለት እንደሆነ ታውቁታላችሁ ፡ አሁን አሁን እንኳን የጤናው ነገር አሪፍ ነው ። በአንድ ወቅት ግን አለፍ አለፍ እያለ ህመም ብጤ ይሰማው ነበር ።
....
እና አንዳንዴ ህመሙ ባስ ብሎበት ሆስፒታል መግባቱ ከተሰማ. . የሆስፒታሉ ዙሪያ ፡ መንገዱ ሁሉ እዛው ውለው ፡ በሚያመሹ የአሚታብ አድናቂዎች ይሞላል ።
...
አሚታብ እንግዲህ ይህ ነው ። እና ሰሞኑን በአንድ የቲቪ ሾው ላይ ሲናገር. .. ትንሽ ዘና ለማለት ወደ ለንደን ሄጄ ነበር አለ. ..
....
እና አሚታብ በለንደን ቆይታው ፡ አንዳንድ ነገሮችን ሊሸማምት ወደ ገበያ ይወጣል ።
....
ከዛም ብራንድ የሆኑ ውድ ልብሶችን ወደሚሸጥ መደብር ገብቶ ልብሶችን ክራቫቶችን ሲያይ ከቆየ በኋላ አንዱን ውድ ክራቫት መርጦ ፡ ለሚሸጠው ሰው ያሳየውና ፡ ይህንን ፈልጌ ነበር ። ፓክ አርግልኝ አለው ።
....
የመደብሩ ሻጭ አሚታብ ጠቅልልኝ ያለውን ከራቫት እያሳየው " ይህንን ነው ? " ብሎ ደግሞ ጠየቀው
አዎ እሱን ነው ጠቅልለው ሲለው ልጁ ..... ይሄ ህንድ ከረባቱ ርካሽ መስሎታል እንዴ ? በሚል አይነት አስተሳሰብና አነጋገር. ..

" አይ እሱ ይወደድብሀል ሌላ ምረጥ " አለው

አሚታብ ጠየቀ ፡ ስንት ነው ዋጋው
" 120 ፓውንድ "

Ok እንደዛ ከሆነ ....... ይህንን ጨምረህ የተለያየ ከለር አድርግና አስር ከረባት ጠቅልልልኝ በማለት ሂሳቡን ከፍሎ ፡ ከረባቱን ይዞ ወጣ ።
....
እና አሚታብ ንግግሩን ሲያጠቃልል ፡ በርግጥ ልጁ ማን እንደሆንኩ ላያውቅ ይችላል ። ሆኖም ሀብት ወይም ዝና ... ኖራችሁ ... አልኖራችሁ. .. ብቻ. . ማንም ብትሆኑ ........

ሰወች ዝቅ አድርገው እንዲያዩዋችሁ በፍፁም እድል አትስጡ ! ሲል መክሯል ።

( የአሚታብ የቅዳሜ መልእክት ነው ። መልካም ቅዳሜ )

© Wasihune Tesfaye

3 months ago

አደራቸውን ሊወጡ ዝግጁነቱ ያላቸው፣ ጀግኖች ሆነው ሳለ፣ ... አደራ በላ ለመሆን ተገደዋል። እየቻሉ፣ ግን አልቻሉም። እንዳይችሉ ሆነዋል። ....

ይህ የአሜሪካ ሲክሬት ሰርቪስ ታሪክ... በሚወጡ፣ በሚወርዱ አልፎ ሂያጅ መሪዎችና ባለሥልጣናት እጅ ፍዳቸውን የሚበሉ፣ በቁጭት የሚንገበገቡ፣ ቀን የሚጠብቁ፣ የብዙ ሀገሮች ጀግኖች ታሪክ ይመስለኛል።

ሃቅ። ትክክለኝነት። ፍትህ። ቅንነት። ህሊና። ለሰዎች ሁሉ። የት እና መቼ ይሆን... የምትወጣው? ... እና ይህችን ዓለም ውብ፣ ምቹ የምናደርጋት? — አላውቅም።

ምናልባት አንድ ቀን።

ምናልባትም ደግሞ ... በወዲያኛው ዓለም... ?!

"Man is born free, but everywhere he is in chains." — Jean Meslier

("ሰው ነፃ ሆኖ ይወለዳል፣ በሁሉ ቦታ የሚታየው ሰው ግን፣ በሠንሰለት የተጠፈረ ነው!")

ፈጣሪ ሰንሠለታችንን ይፍታልን!

ኢትዮጵያችንን አብዝቶ ይባርክ።

ደራሲዋን አመስግኜ፣

አበቃሁ።

© Assaf Hailu

3 months ago

እና በውጤቱ ስሙ አፈርድሜ የጋጠው ሲክሬት ሰርቪስ ቀን ወጣለት። ኬኔዲ በተገደለባት ዕለት ለፕሬዚደንቱ ጥበቃ የተሠማሩት 34 የሲክሬት ሰርቪስ አባላት ብቻ ነበሩ። እነዚያ አባላት ብቻቸውን፣ ተሰልፎ የወጣን 200ሺ ሰው መመለስ አይችሉም። መሣሪያውም። ቁሳቁሱም። ቴክኖሎጂውም። ብቃቱም። የገንዘብ አቅሙም የላቸውም።

ኬኔዲ ሲገደሉ፣ የሲክሬት ሰርቪሱ ዓመታዊ ባጀት 2.3 ሚሊዮን ዶላር ብቻ ነበር። በአጠቃላይዋ አሜሪካ የነበሩ በሲክሬት ሰርቪሱ የደሞዝ ሮስተር ላይ ያሉት ሰዎች ቁጥራቸው ከ700 ያነሰ ነበረ። ከዚያ ኬኔዲ ተገደሉ። ጭራሽ ወንድማቸውም ሮበርት ኬኔዲ ተደገሙ።

አሜሪካኖች ከዓለም በሁሉነገሩ ግዙፉንና ብቃት ያለውን ሲክሬት ሰርቪስ ሊገነቡ በገንዘብ፣ በሰው ኃይል፣ በሥልጣንና ሥራዎቹ ዓይነት፣ በሁሉነገሩ እንደ አዲስ አደራጅተው፣ አግዝፈው አዋቀሩት።

ሲክሬት ሰርቪስ የአየር በረራ እንቅስቃሴዎችን ካልተቆጣጠረ የፕሬዚደንቱን ህይወት ካልታሰበ ጥቃት መከላከል እንደማይችል አመኑ። የአቪዬሽን ክፍል ተቋቋመለት።

ሲክሬት ሰርቪሱ አሜሪካን ለመጎብኘት የሚመጡ መሪዎችንና ባለሥልጣናት እና ቤተሰቦቻቸውንም በሠላም ገብተው እስኪወጡ የመጠበቅ ሥራ ተደረበለት። ለዚያም ክፍል ተቋቋመለት።

ደሞ አንድ የጠላት ሀገር ዋይትሃውስን በሚሣኤል ወይ በኒውክሊየር፣ ወይ በኬሚካል፣ ወይ በቫይረስ ቢያጠቃውስ? የሰይጣን ጆሮ ይደፈን። ለእነዚህም እያንዳንዳቸው ልዩ ጉዳዮች ልዩ ክፍሎች ተቋቋሙለት። አሸባሪዎችና ሰርጎ-ገቦች መጥተው ጥቃት ቢያደርሱስ? ለእነርሱም ልዩ ክፍሎች ተቋቋሙ።

በውጭ ሀገር ያሉ ኤምባሲዎቻችንና ስታፎቻችንስ? እነሱንስ ማን ከጥቃት ይጠብቃቸው? ለእነሱም ልዩ ክፍል ተቋቋመለት። እንዴ! በአውሮፕላን የሚጓጓዙ፣ በየአውሮፕላን ጣቢያዎቻችን የሚተራመሱ መንገደኞቻችንስ? ለእነሱም በሲክሬት ሰርቪሱ ውስጥ ራሱን የቻለ ልዩ ክፍል ተቋቋመላቸው።

ተቀጣጣይ ፈንጂስ በመንገድ ላይ ቢጠመድ? የኤሌክትሪክ ማመንጫዎችን፣ ግድቦችን፣ የመንግሥት ግዙፍ ሕንፃዎችን፣ የኒውክሊየር ኃይል የሚያመነጩ ፕላንቶችንስ? ለእነሱም በሲክሬት ሰርቪሱ ውስጥ ራሳቸውን የቻሉ ክፍሎች ተቋቋሙለት።

ሲጀምሩ የተነሱለት የፋይናንስ ደህንነትን ማስጠበቅ ራሱ ከፎርጂድ ብር ማጭበርበር የትናየት አልፎ የሳይበር ጥቃትና የኤሌክትሮኒክስ ማጭበርበሮች ላይ ደርሷል። ለእነሱም ደግሞ ራሳቸውን የቻሉ ክፍሎች። ....

እንዲህ እንዲህ እያለ የሲክሬት ሰርቪስ ሥራዎችና ኃላፊነቶች ከጊዜ ወደ ጊዜ ተለጠጡ። ማለቂያ አልገኝላቸው አለ።

ዛሬ ላይ - ይህ መፅሐፍ ሲታተም - ሌሎችን ሳይጨምር - የአሜሪካ ሲክሬት ሰርቪስ የራሱ የሠለጠኑ የቴክኒክ፣ የምርመራና የመስክ አባላቱ ቁጥር ከ7,000 በላይ አሻቅቧል። መደበኛ ይፋዊ ዓመታዊ ባጀቱ ብቻውን 2.2 ቢሊየን ዶላር ነው። እጅግ ግዙፍ ኃላፊነቶችን የተሸከመ፣ እጅግ ግዙፍ ተቋም።

አሁን ደሞ ምን አስቸገረው? በብዙ እጥፍ አድጎ፣ ተለጥጦ፣ የሹሙ ብዛት፣ የሥራው ብዛት፣ የቢሮክራሲው ብዛት፣ ወዘተ. ደግሞ በፕሬዚደንሺያል ጥበቃ ሥራው ላይ እጅግ ከፍ ያለ አሉታዊ ተፅዕኖ አመጣበት።

አበሻ "ችግር ነው!" የሚለው ለካ ወዶ አይደለም - ያስብላል። ቁጥሩና አቅሙ፣ ባጀቱና ኃላፊነቱ ሲያንስም መከራ! ሲበዛም መከራ! ድሮ በቅጥነቱ፣ አሁን ደሞ በሁሉነገር ላይ የሚገባ ሆኖ በመንቦራቀቁ የተነሳ፣ ... አሁንም ሥራውን በትክክል ለማከናወን በብዙ አቅጣጫ bottlenecks የጠለቀለት (መዓት ተረከዞች አንገቱ ላይ የቆሙበት) እያለ፣ እንደሌለ ለመሆን የተገደደ ተቋም ሆኗል በማለት - ብዙውን የሲክሬት ሰርቪስ የውስጥ ገመናዎች እየዘረገፈች ታስነብበናለች።

በሥልጣን በየወጣው መሪ ሁሉ ያሻውን በሙያና በችሎታ፣ በልምድና በብቃቱ ሳይሆን - ቀልቡ የወደደውን፣ በትውውቅ፣ በልምምጥ፣ በምልጃ ሥልጣን የሚሰጥበትና የሚነሳበት፣ የመጣው መሪ ሁሉ እንደግሉ ንብረት ባሻው መንገድ የሚጠመዘዝና ፍዳውን የሚያበላው፣...

ምርጥና ለህይወታቸው የማይሳሱ ብዙ ቆራጥ ጀግኖችን ታቅፎ፣ ግን ሥራውን በአግባቡ እንዳይሠራ ከእግር-እስከራሱ የተተበተበ፣ ከአናቱ የሞሰነ፣ እጅእግሩ የተሳሰረ - እና አሁንም ሆነ ወደፊት በዚህ አያያ- የማለለትን የፕሬዚደንቱን ህይወት ከጥቃቶች የመጠበቅ አቅሙ የሌለው የይስሙላ፣ የድራማና የአደባባይ ትዕይንት ተቋም ሆኗል - በማለት አጥብቃ ትተቸዋለች።

በነገራችን ላይ፣ ይህ መፅሐፍ ሲፃፍ፣ ሲክሬት ሰርቪሶች ከነበሩበት ከትሬዠሪ መዋቅር እንዲወጡ ተደርገው፣ በአዲስ መዋቅር በሆምላንድ ሰኪዩሪቲ ዲፓርትመንት ሥር እንዲሠሩ ተደርገዋል። (ከሴፕቴምበር 11ዱ ጥቃት በኋላ፣ ማለትም በትንሹ ቡሽ ጊዜ)። ግን ችግራቸው ከመሻሻል ይልቅ ተባባሰ። ባይ ነች።

ይህች መርማሪ ጋዜጠኛ ይህን መፅሐፍ ለማዘጋጀት 180 የቀድሞና አሁንም በሥራ ላይ ያሉ የሲክሬት ሰርቪስ አባላትን በምሥጢር ስምና ማንነታቸውን ደብቃላቸው ምሥጢራቸውን ዘርግፈውላት በማስረጃ ነው የምትናገረው። ከ10ሺህ ሰነዶች በላይ አገላብጬያለሁ ትላለች። ለሕዝብ ይፋ ያልሆኑ ሰነዶች ጭምር። ጉድ ነው!

በመጨረሻ - በአሜሪካ የደህንነት ተቋማትና በተለይም በሚሠሯቸው ለሕዝብ ይፋ ባልወጡ ሸፍጦችና እንከኖቻቸው ላይ ከዘጋቢነት አልፋ ራሷን ወደ ውስጥ-አዋቂ ምሁርነት ያሸጋገረችው ይህች ልባም ጋዜጠኛ ካሮል ሊዮኒግ፦

"እኔ ይህን ሁሉ ደክሜ የምፅፈውም፣
እነዚህ ለሀገራቸው ነፍሳቸውን ለመስጠት
ያልሳሱ የሲክሬት ሰርቪሱ አባላት ምሥጢ
ራቸውን የሚነግሩኝም - ሁላችንም - ይህ
ተቋም ከችግሮቹ ተላቅቆ - በትክክል
ሥራውን እንዲሠራ ለማድረግ ካለን
ምኞትና ካደረብን ቁጭት የተነሳ ነው።
እንጂ የሀገራችንን ምሥጢር የመዝራት
ሱስ ኖሮብን አይደለም..."

ትላለች ደጋግማ! በአፅንዖት። ጊዜና ቦታው ከዚህ በላይ ለመቀጠል አልፈቅብሎኝ እንጂ፣ እኔም በበኩሌ የዚህችን መሳጭና ውብ አዋቂ ብዕረኛ፣ ስለያንዳንዱ ፕሬዚደንት፣ እና ከሲክሬት ሰርቪሱ ጋር ስለነበረው አካሄድ፣ የግድያ ሙከራዎች፣ የሲክሬት ሰርቪስ ሰዎች በየዕለቱ ስለሚታዘቧቸው የዋይትሃውስ ውስጥ ቅሌቶች፣ እና ብዙ ጠቃሚ ሃሳቦች... ብዙ፣ እጅግ ብዙ ፅፋለች።

ይህን መፅሐፍ እያነሳሁ፣ እየጣልኩ - በመሐል ሌላ ቀልቤን የሚስብ መፅሐፍ እየመጣብኝ - አንብቤ ለመጨረስ ወደ ስምንት ወር ገደማ የፈጀብኝ ይመስለኛል። ጊዜ ቢኖር፣ አንዴ ከተነሳ፣ የማይከደን መፅሐፍ ነበር።

ሰሞኑን ዶናልድ ትራምፕ በፔንስልቫንያ ላይ በ20 ዓመቱ ወጣት ሲተኮስባቸው፣ ሲክሬት ሰርቪሶች ሰዉ እየነገራቸውም ቀድመው ከጥይት ሊያስጥሉት አልቻሉም እያለ ብዙ ሰው ሲወቅሳቸው ስሰማ፣ ይህች ጋዜጠኛ ካሮል ሊዮኒግ፣ እና ይህ ድንቅ መፅሐፏ ትዝ ብለውኝ ነው ሃሳቡን ለማጋራት የተነሳሁት።

የሲክሬት ሰርቪሶቹ ታላቅ ዓላማ፣ የመሪዎቻቸውንና የሕዝባቸውን ሕይወት - የገዛ ህይወታቸውን እንደሻማ አቅልጠውም ቢሆን - ከጥቃት ለማዳን፣ ከሞትና ከሽብር ለመታደግ፣ እና ሕዝባቸው በሙሉ እምነት እንደልቡ ወደፈለገው ወጥቶ መግባት እንዲችል ለማድረግ ነበር።

መፈክራቸው የተጣለባቸውን ግዴታ ሁሉ ያለድካም በ"Zero Fail" (ያለምንም እንከን) መወጣት ነበር። ዓላማቸው ዲሞክራሲያቸውን ከሸፍጥ እጆች መጠበቅ ነበር። ....

ግን በብዙ ማነቆዎች ተይዘዋል። ብዙ ፍርጃዎችን ተሸክመዋል። ብዙ እንዳይራመዱ አድርጎ የተበተባቸው የፖለቲከኞችና የባለጊዜዎች ሠንሠለት አለ። ታላቅ አቅማቸው ተገድቧል። ህልማቸው ታስሯል።

3 months ago

የአሜሪካ "ሲክሬት ሰርቪስ"

— አነሳስና አወዳደቅ

ይህ መፅሐፍ ለሶስት ጊዜያት እጅግ ታዋቂውን የፑሊትዘር ሽልማት በተቀዳጀችው የዋሺንግተን ፖስቷ መርማሪ ጋዜጠኛ በካሮል ሊዮኒግ የተፃፈ እጅግ አስደናቂ የምርመራ ውጤት ነው።

ከታተመ ሶስት ዓመት (በ2021) የሆነው ይህ መፅሐፍ ማጣቀሻዎቹን ሳይጨምር ወደ 532 ገፆች አሉት።

ይህች ጆርናሊስት በተለይ ኤድዋርድ ስኖውደን በይፋ እስኪያጋልጠው ድረስ በህቡዕ አሜሪካውያንን እና መላውን ዓለም በሥለላ ሥር በመክተት በቢሊየን የሚቆጠሩ መረጃዎችን ይሰበስብ የነበረውን ኤንኤስኤ (ናሽናል ሰኪዩሪቲ ኤጀንሲ) ለሕዝብ ያጋለጠችና፣ በዚያም በርከት ያሉ የዕውቅና ሽልማቶችን የተጎናፀፈች እጅግ ደፋር፣ ማራኪ አፃፃፍን የተላበሰችና ሲበዛ አዋቂ ኤክስፐርት ፀሐፊ ነች ካሮል ሊዮኒግ።

በዚህ መፅሐፏ የአሜሪካን ፕሬዚደንቶች ህይወት ከአጥቂዎች አደጋ ሲጠብቅ የኖረውን የፀጥታ ተቋም (ሲክሬት ሠርቪስን) ከተፀነሰበት ከአብርሃም ሊንከን ዘመን አንስታ፣ እስከ ትራምፕ ሥልጣነ-ዘመንና እስካሁንም፣ ወደፊትም የሠራቸውን ሥኬቶች፣ ያሉበትን ጉድለቶች፣ ጫናዎች፣ የአቅም ውሱንነቶች፣ ሸፍጦች በሚገርም የተባ ልሣን ዝርዝር መረጃዎቿን ታዥጎደጉድልናለች።

በዚህ መፅሐፍ ሲክሬት ሰርቪስ ሀ ብሎ የተቋቋመው በአሜሪካ የእርስበርስ ጦርነት ወቅት (በአብርሃም ሊንከን ዘመን በ1862 ላይ) የጦርነቱ ግርግር ያመቻቸው ጥቂት ጭራቸው የማይያዝ ስማርት ሌቦች፣ የአሜሪካንን ፎርጅድ ዶላሮች በተራቀቀ ዘዴ እያተሙ በማሠራጨት ሚሊየኖችን ማፈስ በጀመሩበት ወቅት እንደሆነ ታሪክ እየተጠቀሰ ተብራርቷል።

አሜሪካኖች ሁሉም ነገር ወደ ጦር ግንባር ብለው በጦርነት ይጨፋጨፋሉ። ፎርጂድ አታሚዎቹ ደግሞ አጋጣሚውን ተጠቅመው በመላ ሀገሪቱ በየቀኑ እስከ መቶ ሺህ ዶላር (በአሁን ተመን በየቀኑ 1.5 ሚሊዮን ዶላር ማለት ነው) እንደ አሸን እያተሙ ያልለፉበትን ሃብት ያፍሳሉ።

እነዚህ ፎርጀሮች የራሳቸው አዘዋዋሪዎች (በታኝ ጋንጊስተሮች) አሏቸው። የታጠቁ ጠባቂዎች ከፖሊስ እየተዋጉ ይከልሏቸዋል። የጥቅም ተካፋይ ሀብታሞች ከጎናቸው አሰልፈዋል። በጦርነቱ አጋማሽ ላይ (በ1863 እ.ኤ.አ.) ከአሜሪካ አጠቃላይ ገንዘብ ግማሹ ፎርጂድ ሆነ።

ስለሆነም አብርሃም ሊንከን ከፖሊስና ከመደበኛ ሠራዊቱ ተለይቶ የፋይናንስ ማጭበርበርን ብቻ የሚከታተልና እያደነ የሚይዝ ልዩ የፀጥታ ግብረሃይል አቋሙ። የግብረሃይሉን ተጠሪነት ደግሞ ለገንዘብ ሚኒስቴር (ትሬዠሪ ሴክሬተሪ) እንዲሆን አድርገው አደራጁት።

በጣም የሚገርመው ነገር ልክ አብርሃም ሊንከን በትያትርቤት ውስጥ እያሉ በተገደሉባት ዕለት ጠዋት ላይ፣ ይሄ ሲክሬት ሰርቪስ ከገንዘብ ማጭበርበር ክትትል በተጨማሪ፣ የፕሬዚደንቱንና ከፍተኛ ባለሥልጣናቱን ደህንነት የማስጠበቅ ሥራም ደርቦ እንዲሠራ ሥልጣን የሚሠጠውን ደንብ (ድንጋጌ) ፈርመው፣ ከትሬዠሪ ሴክሬተሪያቸው ጋርም መክረው፣ የዚያኑ ዕለት ትያትር ቤት ሄደው በአንድ ደቡቦችን በሚደግፍ ተዋናይ በሽጉጥ ጥይት አናታቸውን ተመተው ሞቱ።

እና - ትላለች ካሮል ሊዮኒግ - ይህ የሲክሬት ሰርቪስ የደህንነት ተቋም የተቋቋመ ዕለት የፕሬዚደንቱን የደም ግብር በልቶ ነፍስ የዘራ ተቋም ነው። በዚያ ወቅት የነበሩት የፀጥታ ሠራተኞች አስር አይሞሉም ነበር።

እንዲህ እያለ እየዳኸ ሥራውን ቀጥሎ፣ ከሊንከን በመቀጠል ሥልጣን ላይ የወጡ ሌሎች ተጨማሪ ሁለት ፕሬዚደንቶችንም ከገዳዮች እጅ ማስጣል አልሆነለትም።

ፕሬዚደንት ጋርፊልድ በሲክሬት ሰርቪስ ሰዎች ፊት ሲገደሉ፣ ቆይቶ ደግሞ ፕሬዚደንት ማኪንሌይ በ1901 ላይ በአንድ የዲትሮይት አናርኪስት ጥይት ሲገደሉ - ሁለቱንም ከሞት ማስጣል አልቻለም 24 ሰዓት የፕሬዚደንቶቹን ህይወት ነቅቶ የመጠበቅ ኃላፊነት የተሰጠው ይህ የአሜሪካ ሲክሬት ሰርቪስ።

ከዚያም አልፎ በ1912 ላይ ፕሬዚደንት ቴዲ ሩዝቬልት በአንድ የሙት መንፈስ ግደለው ብሎ በህልሜ ተናገረኝ በሚል የወጣለት ያሜሪካ ቱጃር እጅ በሁለት ጥይት ሲመቱም ከጥቃት ሊከላከላቸው አልቻለም።

በዚህ ጊዜ ግን አሜሪካኖች የመሪዎቻቸው ደህንነት እጅግ አሳሰባቸው። ስለሆነም የሰው ኃይል ቁጥሩን፣ ሥልጠናውንና ባጀቱን ከፍ አድርገው በአዲስ መልክ ኃይለኛና ብቃት ያለው የፕሬዚደንታቸው ሕይወት ዋስትና መድኅን የሆነ ሲክሬት ሰርቪስ ለመፍጠር ጥረት አደረጉ።

ቁጥራቸውንም ወደ 36 ከፍ አደረጉት። ስለዚህ ፕሬዚደንቱ በየዕለቱ በፈረቃ በአንዴ ስድስት ስድስት እየሆኑ፣ በፈረቃ በሚሠሩ፣ የሲክሬት ሰርቪስ የደህንነት ዕቅድ አውጪዎች (ዲቴይለሮች)፣ ኦፊሰሮች፣ እና ኤጀንቶች) 24 ሰዓት እንዲጠበቅ አደረጉ።

ምክትል ፕሬዚደንቱም ደግሞ አደጋ እንደተደቀነበት አውቀው፣ ለፕሬዚደንቱ ብቻ ሳይሆን ለእርሱም ጥበቃ እንዲደረግለት ሁለት ሰው ተመደበለት። ቀስ በቀስ ደሞ ለፕሬዚደንቶቹ የቤተሰብ አባላትም ጥበቃ መስጠት ጀመሩ። ቀስ በቀስ ደግሞ አድማሳቸውን በማስፋት ለየክፍለሃገሩ ገቨርነሮች (ሀገረገዢዎች) ጭምር የጥበቃ አገልግሎት ጀመሩ።

እንዲህ እያለ የሲክሬት ሰርቪሱ የደህንነት ተቋም በፕሬዚደንት ጆን ኤፍ ኬኔዲ የሥልጣን ዘመን ላይ ሲደርስ፣ በመላዋ አሜሪካ ያሉት ልዩ የሲክሬት ሰርቪስ ጓዶች አባላት (ዲቴይለርስ) ቁጥር በጠቅላላ ተደምረው 64 ብቻ ነበሩ። ይሄ ማለት ግን በየከተማው መደበኛ ፖሊስ የሚደረግላቸውን ተጨማሪ ድጋፍ ሳይጨምር ነው።

ኬኔዲ ብዙ ጠላትና ዛቻ ያስተናገዱ መሪ ሆኑ። ደሞ በዚህ ግባ፣ ውጣ የሚባለውን ምክር የማይቀበሉ፣ መቀመጥ የማይወዱ፣ ከሕዝቡ ጋር በየቦታው መገናኘት፣ መጨባበጥ፣ በየፕሮግራሙ መገኘት፣ ንግግር ማሰማት የማይሰለቻቸው ፍጥረት ነበሩ።

ያ ደግሞ የሲክሬት ሰርቪሱን ሥራ እጥፍ ድርብ አደረገበት። ለአደጋ ተጋላጭነታቸው ከሲክሬት ሰርቪሱ ውሱን አቅም በላይ ሆኖ ነበር። እንዲያም ሆኖ ለምሣሌ፣ የዕፅዋትና እንስሳትን ብክለት አላስቆሙም ብላ፣ መንገድ ጠብቃ ኬኔዲ ላይ ተኩሳ ልትገድላቸው ሽጉጥ ከመዘዘች አንዲት መነኩሴ እጅ አስጥለውታል።

ሌላ ጊዜ ደግሞ ጥቁሮችን ከእኛ ከነጮች እኩል አንድ ምግብ ቤት ግቡ፣ ባንድ ት/ቤት ልጆቻችሁን አስተምሩ እንዴት ይለናል በሚል ንዴት ተነሳስተው፣ በኩምቢ መኪናቸው 25 እስር ደማሚት ፈንጂ ጭነው ኬኔዲን ባገኙት ቦታ ዶጋአመድ ሊያደርጉት ሲከታተሉት ከነበሩ፣ የ73 ዓመት ጡረተኛ ወታደር እጅም ከመጥፋት ታድገውታል።

በመጨረሻ ግን አቅማቸው አልፈቀደም። የሲአይኤና የፓርቲው ረዥም የሴራ እጆችም አሉበት በሚል እስከዛሬ ብዙዎችን ያከራክራል። በመጨረሻ ፕሬዚደንት ኬኔዲ በዳላስ ሄደው ከፎቅ ላይ ባነጣጠረ የቀድሞ ወታደር የነበረ ሰው በተተኮሰባቸው ጥይት፣ በመኪናቸው ውስጥ እንዳሉ በሚስታቸው ፊት ተገደሉ።

ከፊትና ኋላ ሆነው ያጀቡትም፣ መኪናዋን ያሽከረክሩ የነበሩትም እነዚሁ ከጅብ የማያስጥሉ የሲክሬት ሰርቪስ ሰዎች ነበሩ - ትለናለች በጣም በዝርዝር እየተረከች ይህች ጋዜጠኛ ካሮል ሊዮኒግ። እንዲያም ሆኖ የፕሬዚደን CAT (Counter Assault Team - ወይም የፀረ-ጥቃት ቡድን) ባደረገው ፈጣን ምላሽ፣ "ገዳዩን" ይዞ በፍጥነት ተረሽኗል። እውነተኛ ገዳዩ እሱ አይደለም የሚሉም አሉ።

ኬኔዲ ሲገደል ግን የሲክሬት ሰርቪሱ ስም ገደል ውስጥ ገብቶ ተቀበረ። ስሙ አደፈ። ዝናው ጨቀየ። ግን ታሪክም ተቀየረ። አሜሪካኖች በኬኔዲ መሞት ጨሱ። ሕዝቡ በአጠቃላይ በመንግሥት ላይ በተቃውሞ ተነሳ። የሰዉን ሁሉ ቀልብ የሳበ አንድ ወጣት መሪ ቢመጣ፣ እሱም ተገደለ። አሜሪካኖች በመብከንከንና በንዴት ተንቀጠቀጡ።

3 months ago

የሰው ልጅ የሰራው ግዙፍ ስህተት በሃይማኖት ሲሰላች መንፈሳዊ ባህሪውን እርግፍ አድርጎ መተዉ ነው። ሃይማኖት በተለያዩ ምክንያቶች ሰውን ከፈጣሪው፣ ከመለኮታዊ ባህሪው ጋር ማገናኘቱ አልተሳካለት ይሆናል። በውስጡ የተሰገሰጉት charlatans መንፈሳዊ ፍለጋውን ወደ ሸቀጥ ቀይረውት በእግዚአብሔር ስም ነግደው ይሆናል። በአጠቃላይ የሃይማኖት አቀራረብ በእግዚአብሔር ፍቅር ሳይሆን በዘለአለማዊ የገሃነም እሳት ምእመኑን በማስፈራራት በእግዚአብሔር ፍቅር ሳይሆን በሰይጣን ፍርሃት የተከታዮቻቸውን መንፈሰ መርዘው ይሆናል። ታዲያ ይኼኔ ትምህርት ቤቱ ካልተስማማህ ትምህርት ቤት ትቀይራለህ እንጂ መማር አታቆምም። አስመሳይ ቄሶችን፣ ፓስተሮችን፣ ሼሆችን ትርቃቸዋለህ እንጂ መንፈስህን አትተወውም። ሃይማኖት ሰው ሰራሽ ነው። መንፈስ ግን የፈጣሪ የእጅ ስራ ነው። ዘለአለማዊ ነው። ለጥቂት የሃይማኖት ነጋዴዎች ብለህ ከዘለአለማዊ መንፈስህ ጋር እስከወዲያኛው አትፋታም። ሃይማኖት ሌላ መንፈሳዊነት ሌላ። ሰው ከሃይማኖት ተለይቶ ሊኖር ይችላል። ከመንፈሱ ውጪ ግን ለቅጽበት እንኳን መሆን አይችልም። እኛ እኮ መንፈስ ያለን ፍጥረቶች ሳንሆን መንፈሱን እራሱኑ ነን። ከራስ ተሸሽቶ ወዴት ይደረሳል። እንዲያውም መንፈሳዊነታቸውን የሚክዱት አንዱ የምእራባውያንን አዲስ ስልጣኔ አይሉት ስይጣኔ አመጣሽ ዘይቤ ያስታውሰኛል። transgender የሚሉት። ወንድ ሆኖ ይወለድና ቲኔጀር ሲኮን when they hit puberty ግራ መጋባት ይጀምራል። I identify as female ብሎ ያውጃል። በቃ ከአሁን ወዲህ ሴት ነኝ። ተፈጥሮው ሁሉ የወንድ ነው። በእርግጥ ሰርጀሪ አለ። ብዙ አካላዊ ለውጦችን ማድረግ ይቻላል። ህግም ረቅቋል። የመንግስት ፖሊሲው ይደግፈዋል። ተፈጥሯዊ ወንድነቱን ሊቀይር የሚችል አንዳችም ምድራዊ ሃይል ግን የለም። የኤቲስቶችም ነገር እንዲሁ ነው። እግዚአብሔር ሲፈጥራቸው በውስጣቸው የመለኮት እስትንፋስ እፍ ብሎ በአምሳሉ ነው የፈጠራቸው። ኤቲስቶች የእግዚአብሔርን ህልውና ሲክዱ እኮ በውስጣቸው ያለውን መለኮታዊ ባህሪ ጭምር አብረው እየካዱ እኮ ነው። የእግዚአብሔር መንፈስ እኮ በሁላችንም ውስጥ ያለ መሰረታዊ ባህሪያችን ነው። ኤቲስት ሽምጥጥ አድርጎ የሚክደው ይሄን ተፈጥሮውን ነው። የትራንጀንደሮችን ልዩ የሚያደርገው የሴት ነኝ ባዩን ወንድነት፣ ወይም የወንድ ነኝን ባይዋን ሴትነት በአካላቸው በግልጽ ማየት ስለምንችል ነው። ከልብስ ባሻገር፣ ከሜክአፕ ስር ተፈጥሯዊ ጾታ አይቀየርም። የኤቲስቶችም መለኮታዊነት ሊካድ እንጂ ሊሸገግ አይችልም። በእርግጥ መለኮት ረቂቅ ነው። በአይን ሊታይ አይችልም። እዚህ ወይም እዚያ ነው ያለው ተብሎ በእጅ ሊጠቆም አይችልም። በውስጡ ያ ረቂቅ መንፈስ እንዳለ የማይረዳ ከመካከላችን አንድም የለም። በአፋችን እንጂ በግብራችን ልንክደው አንችልም። መኖራችን ራሱ የዚህ ተአምር ውጤት መግለጫ ነው። ነፍስ ብሎ ነገር የለም ብሎ በአፉ ሙሉ የሚክደው ወንድ ሆኖ ሳለ ሴት ነኝ ብሎ ተፈጥሮውን ከሚክደው ከንቱነት ለይቼ አላየውም።

እኔ በህይወቴ ብዙ የማይመስሉ፣ ውሃ የማያነሱ፣ ትርጉም የማይሰጡ ቲዎሪዎችን ሰምቼያለሁ። እንደ ኤቲዝም ግን አስቂኝና ቀሽም ሃሳብ ሰምቼ አላውቅም። እግዚአብሔር የለም ማለት እኔ ራሱ የለሁም ብሎ ከመለፈፍ ምንም አይለይም። አዎ እግዚአብሔር ተአምር ነው። ሁላችንም ውስጥ ያለ ተአምር። ህይወት ተአምር አይደል እንዴ?! ከህይወት የበለጠ ተአምር የለም። ተአምር መብረር፣ በውሃ ላይ መራመድ ወይም ውሃን ወደ ወይንጠጅ መቀየር አይደለም። ተአምር ይህ ህይወት የሚሉት ረቂቅ ነገር እና እሱን የሞሉት ፍቅር፣ ሳቅ፣ ደስታ ወዘተ ያሉ እጹብ ድንቅ ስሜቶች ናቸው። ይኼኔ የእግዚአብሔር ህልውና ከትንፋሻችን የቀረበ የማይጠራጠሩት እውነት መሆኑ ይገለጽልናል። እናም ሃይማኖትን ተዉት። ቅዱስ መጻህፍትን፣ ጽድቅና ኩነኔን፣ ገነትና ገሃነምን ሁሉንም እርሱት። መቼም የማይጠገበውን ህይወት፣ ረቂቁን ፍቅር ወዘተ አስታውሱት። ያኔ የእግዚአብሔር ህልውና ለጥርጣሬ የሚቀርብ ጉዳይ አይሆንም። አይ እግዚአብሔር የለም የሚለውን ጅል ሃሳብ ግን እርግፍ አድርጋችሁ ተዉት።

© Tewodros Shewangizaw

3 months ago

ከማንኛውም ሰው ጋር በሰከንዶች ሽርፍራፊ የምንገናኘው በሞገድ ነው። በኢነርጂ ነው። እግዚአብሔር ሌላ ምንም አይደለም። መጠንአልባ ግዙፍ ተአምራዊ ኢነርጂ ነው። እንግዲህ ኤቲስቶች የሚክዱት ይሄንን ኢነርጂ ነው። ወደ ቅድሙ ዱአሊቲ ባህሪ ልመልሳችሁና ነገሮች ሁሉ ሁለቱም ባህሪ ነው ያላቸው። ይሄንንም ግዙፍ እውነት አንስታይን E=mc² ብሎ አብርሆትን በሚፈጥር ቀመር አስተሳስሮታል። ግኡዙና ረቂቁ ላይዬያዩ የተጋመዱ ነገሮች ናቸው። ቁስአካል ወደ ኢነርጂ ወይም ሃይል፣ ሃይልም ወደ ቁስአካል ይቀየራል። ሲንጉላሪቲ ላይ መጀመሪያ የነበረው በጣም ደቃቅ ነጥብ መጠንአልባ ኢነርጂ የነበረው መለኮት ወይም እግዚአብሔር ነው። ይህ ነው ተለጥጦ የምናየውን፣ የምንዳስሰውን አለም ያስገኘው። ድሮ Conservation of matter የሚባል ጽንሰሃሳብ ነበር። ቁስ አይፈጠርም፣ አይጠፋም። ከአንዱ ወደ ሌላው ቅርጽ ይቀይራል እንጂ። ይሄ ጽንሰሃሳብ ግን ፉርሽ ሆኗል። ቁስ ኢነርጂ ሊሆን እንደሚችል የአንስታይን ቀመር ገልጧል። አቶሚክ ቦምብ የተሰራው በዚህ እውቀት ነው። በእጅ የሚያዝ መጠነኛ ቦምብ ፈንድቶ ሂሮሽማና ናጋሳኪን ድምጥማጣቸውን ያጠፋው፣ በሰከንዶች ሽርፍራፊ በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ ሰዎች የሞቱት የቦምቡ ቁሶች በውስጣቸው አምቀው በያዙት እልፍ ሃይል ነው። ውጉዝ ከማርዮስ እንዳትሉኝ እንጂ እነዛን ሰዎች የገደለው ኢነርጂ ነው፣ እግዚአብሔር ነው። ደሞስ ከእግዚአብሔር ሌላ የሚገድል አለ እንዴ?! ሞትና ህይወት የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታ ናቸው። ህይወት የሚሰጠው እግዚአብሔር ነው መልሶ በሞት ህይወትን የሚነጥቀው። ታዲያ የሚሞተው ስጋ እንጂ ነፍስ አይደለም። ለዛ ነው ሞት ትራጄዲ የማይሆነው። ነፍስ ዘለአለማዊ ናት። በሌላ ቅርጽ መኖሯን ትቀጥላለች። ወደ ሌላ ጉዳይ አልሻገርና ወደ ቀደመው ልመለስና ሳይንስ ባለፉት ብዙ አመታት ብዙ ርቀት መጥቷል። አያቶቻችን ያልተረዱትን ብዙ ነገር አሁን ተረድተናል። ግን ከተረዳነው ገና ያልተረዳነው ይበልጣል። ሳይንስ አሁንም እንጭጭ ነው፣ ለጋ ነው፣ ገና ድክድክ ማለት የጀመረ ህጻን ነው። ገና እየዳኸ ነው። ገና መናገር፣ መራመድ፣ መሮጥ፣ መብረር አልጀመረም። ታዲያ በዚህ ጩጬ ሳይንስ ረቂቁን፣ ግዙፉን፣ ተአምራዊውን ተረድተን እንደጨረስን ማስመሰል የማይነፋ አካሄድ ነው። በየግዜው ጂኒየሶች እየተወለዱ ትንሽ ወደ ትልቁ እውነት ፈቀቅ ያደርጉናል። ግን ግዙፉ እውነት በጣም ሩቅ ነው። መቼም የሚደረስበት አይደለም። ልክ እንደ asymptote ነው። አሲምቶት በሂሳብ ይጠጌ አይነኬ ብለን የምንገልጸው ኮንሰፕት ነው። ስሙ በራሱ ገላጭ ነው—ትጠጋዋለህ እንጂ መቼም አትነካውም። የእግዚአብሔርም ነገር እንዲሁ ነው። እንቀርበዋለን እንጂ መቼም በፍጹም ምሉእነት ተረድተን አንጨርሰውም። Infinityን አስቡት። የቁጥር መጨረሻ ስንት ነው? ዘለአለም ስንቆጥር ብንከርም የማይደረስበት ነው። የሲንጉላሪቲ ጽንሰሃሳብ አርቃቂዎችም ብለውታል። ቢግ ባንግ ቲዎሪን ተረቋል። በፊዚክስ ጽንሰሃሳብና ቀመር ማስረዳት ተችሏል። ሲንጉላሪቲን ግን በፍጹም። እንደራሳቸው ቃል Singularity is where all the laws of physics fail. መለኮትን በፊዚክስ ህግጋት ማብራራት አይቻልም። ኤቲዝም በአጭሩ ሲንጉላሪቲን መረዳት ስላልቻለ እግዚአብሔር የለም ብሎ መደምደም ነው። ሌላ ሚስጥር የለውም። የኤቲዝም ከንቱ ድፍረት ሁሉንም ነገር በሎጂክ፣ በሳይንስ መረዳት እችላለሁ ብሎ መነሳቱ ነው። ግን ከሎጂክ ባሻገር፣ ከሳይንስ በላይ ብዙ ነገሮች አሉ—ፍቅር፣ ሙዚቃን፣ ውበትን የትኛው ሳይንስ ሊገልጣቸው ይችላል? እነዚህ ነገሮች በባህሪያቸው እንዲተነተኑ አይደለም የተፈጠሩት። በረቂቅ መንፈሳችን እንድንደሰትባቸው ነው። በቃ እግዚአብሔር እኮ ሌላ ነገር አይደለም። እነዚህ ረቂቅ ነገሮች ናቸው። እናም ውብ ሙዚቃ፣ እውነተኛ ፍቅር፣ ልብ የሚያጠፋ ውበት፣ ረቂቅ ተፈጥሮ፣ ምትሃት አለ። እግዚአብሔር አለ። በአይናችን የማናያቸው፣ በጆሮዋችን የማንሰማቸው፣ፐ በእጃችን የማንዳስሳቸው ብዙ ረቂቅ፣ ውብ ነገሮች አሉ። የእግዚአብሔር ቅንጣቶች ናቸው። እግዚአብሔር ራሱን ለሁላችንም ከሚገልጥባቸው እልፍ መንገዶች መካከል ናቸው። ሳይንስ ራሱ ስለ ስድስተኛው ስሜት፣ ስለ ሶስተኛው አይን፣ ስለ ፒቱታሪ እጢ ይነግረናል። የማይታየውን የምናይበት፣ የማይሰማውን የምንሰማበት፣ ረቂቁን የምናስተውልበት፣ ከመለኮት ጋር የምንገናኝበት የእኛው አካል ነው። ሁላችንም ረስተነው ነው እንጂ እኛ እኮ ሰዋዊ ልምምዶች ያሉን መንፈሳዊ ፍጥረቶች እንጂ መንፈሳዊ ልምምድ ያለን ሰዋዊ ፍጥረቶች አይደለንም። መንፈስ ነን። የላቀው፣ የበለጠው፣ የረቀቀው ደግሞ መንፈሳዊ ባህሪያችን ነው። ኤቲዝም ማለት ሌላ ምንም ሳይሆን ይሄንን መሰረታዊ ረቂቅነታችንን ከዶ ተራ ግኡዝ መሆን ነው። ተራነትን መቀበል ነው። ተአምራዊ ማንነታችንን ችላ ብሎ በመደዴነት መወሰን ነው። በመጨረሻ ስሙን የረሳሁት አንድ ሳይንቲስት እንዲህ ይላል፦

"ሚጢጢ ሳይንስ ከእግዚአብሔር ታርቃለች። ጥልቅ ሳይንስ ግን ይበልጥ ወደ እግዚአብሔር ያቀርባል"

የሁላችንም የሳይንስ እውቀት አሁንም ገና ሚጢጢ ነው። በዚህች ደቃቅ እውቀታችን ተመርተን ነው ደረታችንን ነፍተን እግዚአብሔር ብሎ ነገር የለም ብለን የምንደመድመው። ሳይንሳዊ አውቀታችሁን ችላ በሉትና መንፈሳችሁን አዳምጡት። በሳይንሳዊ መረዳት ብቻ እግዚአብሔርን መቼም አትደርሱበትም። ሳይንስ ባህሪው አይፈቅድለትም። የትኛውም ሳይንሳዊ ጽንሰሃሳብ ሲንጉላሪቲን ወይም መለኮትን ሊገልጽ አይቻለውም። ሳይንስ በባህሪው ቁሳዊ ነው። ጠቢባን አበው እሾህን በእሾህ ይላሉ። እግዚአብሔር መንፈስ ነው። እኛም እግዚአብሔር በአምሳሉ ረቂቅ መንፈስ አጎናጽፎናል። የምናውቃቸውን ሳይንሳዊ ጽንሰሃሳቦች ሁሉ ወደ ጎን ገፍተን እሾህን በእሾህ፣ እግዘብሔርን በመንፈሳችን፣ መለኮትን በረቂቅ ባህሪያችን ለመረዳት፣ ለመለማመድ መትጋት አለብን። ይሄ ነው ብቸኛው መንገድ። አለበለዚያ መለኮትን እንደ ማንኛውም ተራ ቁስ በላቦራቶሪ ለማየት ከፈለግን ከታሪካችን የሞኝነት ቁንጮ ተለይቶ አይታይም። መለኮት ተራ አይደለም። እኛም ሁላችንም ደግሞ ከመለኮት ውጪ ተራ ነን። የሰውን ልጅ በድን እኮ ላቦራቶሪ ወስዳችሁ ብትሸነሽኑት የናይትሮጅን፣ ካርበን፣ ኦክሲጅን፣ አርገን ወዘተ ክምር ነን። ተራ የኢለመንት ክምር ነን። ልዩ የሚያደርገን በሁላችንም ውስጥ ያለው ረቂቅ የማይታይ የማይዳሰስ መለኮት ነው። እንግዲህ ኤቲስት እኔ ተራ የካርበንና ናይትሮጅን ክምር ነኝ ብሎ የሚያምን አሳዛኝ ፍጥረት ነው። መብቱ ነው ግን What a waste. የሰው ልጅ ሙሉ ተፈጥሮና ብቃቱን ቢያውቀው አሁን ተቀብሎት የሚኖረው ተራ ህልውናው እንዴት ባሳፈረው። በአጭሩ ኤቲስት ማለት እጅግ የላቀ ጂኒየስ አእምሮ እያለው በትምህርቱ ሰነፍ የሆነ ተማሪ ነው። ሰነፍ ተማሪነቱን መቀበሉ እውነታውን አይቀይረውም። ሁላችንም ጂኒየሶች ነን። ሁላችንም ረቂቅ መንፈሶች ነን። ሁላችንም ባህሪ መለኮት ነን። ሁላችንም ከአማልክት አንዱ ነን። ግን እንደ አውሬ እንጠላላለን፣ እንደ አውሬ እንገዳደላለን፣ ባለ ብሩህ አእምሮ ሳለን እንደ ሰነፍ ተማሪ የህይወት ፈተናን እንወድቃለን። ግን ተአምራዊ ብቃታችንን ዘወትር የሚያስታውሰን ስውር ድምጽ በሁላችንም ውስጥ አለ። እናዳምጠው፣ እንከተለው፣ እንደ አማልክት ሳለን እንደ መደዴ አንኑር።

We recommend to visit

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ ? @Esat_tv_comment_bot

??ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ??

Last updated 1 month, 1 week ago

Last updated 2 months, 1 week ago

እንኳን ደህና መጡ‼

✔ማስታወቂያ ለማሰራት እና ጥቆማ ለመስጠት በዚህ ይጠቀሙ ☞https://t.me/WasuMohammed

✔ ቻናሉን ለመቀላቀል Join ☞http://t.me/Wasulife

ከልብ አመሰግናለሁ♥?

Last updated 2 months ago