ምስለ እኔነት🤩

Description
ቃል ህይወት አለው.....ምድርም በፍጥረቷ ፡ሰማይንም በኑረቱ አቁሟልና'
እናም በኖርኩትም ባየውትም ስሜትን እና እኔነትን ለመግለፅ ይህ ገፅ ተመስርቷል።
Advertising
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated hace 3 semanas, 5 días

Last updated hace 3 semanas

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated hace 1 mes, 1 semana

3 weeks, 3 days ago
1 month ago

የምትወዱት ሰው ያለምንም አሳማኝ ምክንያት ሲለያቹ ....የቀረባቹ ሰው ሁሉ ሚርቃቹ ይመስላቹህ እና ሰው መሸሽ ይሆናል ግባቹ

🖌121

1 month ago

የሰሞኑ የመብራት ጉዳይ ጨጓራን አልፎ አንጀቴን ሳያቃጥል በፊት ነበር የነቃሁት.....እንደው ያለ ልምዴ ፓኮ ሻማ ስለገዛው እንደ ጥንዶች እራት አራት ማዕዘን ቤቴን ባንድ ክር ከብቤ እራቴን እየበላው ሳላስበው ሻማው አልቆ ጠፋ.....

ሲታየኝ ሻማው ሳይሆን ክሩ ነው ያለቀው።።።የጉድ ሀገር አሉ....እንዴት እና በምን ይሆን የሰሩት
ብቻ አንድ ነገር ትዝ ቢለኝ በጨለማ አልጎመጉም ጀመር

ትላንት ቀን አንድ ቦታ "ሻማን ማን አቃጠለሽ ቢሏት ፤አቅፌ የያዝኩት ክር"አለች አሉ።።።ማን እና ምን አስቦ እንደጠየቃት ባላውቅም ለኔ ተቋጭቶ ያላለቀ ሀረግ እንደሆነ ገባኝ ።።።ሻማም ገብቷት ይሆናል ሳትናገር የቀረች አይመስለኝም ።።።ያ ክር መኖሯ እና መጥቀሟ እንደሆነ ።።።።።።እርግጥ አይካድም መጥፊያዋ ነው ዳሩ ግን ፍጥረቷ ብርሀን ስትሰጥ መቅለጥ ከሆነ የኑረት አላማዋን እየተገበረላት እንደሆን ሳይሰሟት ቀርተው እንጂ ነግራቸዋለች......
ያለ ክሯ ማንም እንደማይፈልጋት
ደርሶም እርሱም ነዶ እንጂ ኖሮ እንደማያቀልጣት አልገባቸውም መሰል.....

ብቻ ሻማዬ ሳትሆን ክሯ ተጠናቃ ብርሀን አልባ እና መቅለጡ ጥቅም የማይሰጥ ተራ ቁመናን መላበስ አይደለም የርሷ ፍጥረት
ያቀፋት ሲያቃጥላት እና አብሮ ሲወስዳት ነው ሁሉም የሚፈልጋት.......
እኔም ቀየርኳት....ስለማታስፈልግ.....
ከፈረደበት ካርቶን ክር ያቀፈ ሻማ አውጥቼ እራቴን እየበላው.....
ብቻ አንዳንድ ቅጽበታዊ ሀሳብ ሳይታወቅ የትልልቅ ነገሮች ምላሽ ይሆን አይደል.....ህ......እንደዛ

ኢሊ ዲያ

3 months, 4 weeks ago

ሁሉም ልብ ላይ መቃብር አለ ???

3 months, 4 weeks ago

?**ብር እጃችሁ ላይ አልበረክት ለሚላችሁ

የሩዝ ውሀ...ፌጦ...የወይራ ዘይት ከጦስኝ ከርቤና አሪቲ ጋር ቀላቅሎ መጉመጥመጥና? የአሳ ሀሞት...በእርጎ ቀላቅሎ ነጣ ባለ በነጠላ ቅዳጅ ነክሮ በአፍንጫ መሳብ አ4ቴ ጥሩ ፍቱን መፍትሄ ነው ? አመሰግናለሁ ❤️**

3 months, 4 weeks ago

..."አባዬ" (ልጅ)

..."አቤት" (አባት)

..."በግ አስተኝተን፡ አርደን፡ ደሙን አፍሥሰን፡ በጥብስ እና በቅቅል አርገን ስንበላው ነፍሱን በማጥፋታችን ሀጥያት አይሆንብንም?"(ልጅ)

..."ምን ስትል አሰብከው ልጄ? እረ አይሆንብንም።" (አባት)

..."እንዴ አባዬ እየገደልን አደለ እንዴ፡ እንዴት ሀጥያት አይሆንብንም?" (ልጅ)

..."ምን መሰለህ ልጄ... እንዴት ላስረዳህ?... ሞት እኮ በር እንጂ መጨረሻ አይደለም፡ በጉን ስንበላው በኛ ውስጥ መኖሩ ይቀጥላል እንጂ ጨርሶ አይሞትም" (አባት)

..."እረ እረ አባዬ ደሞ እንደዚ አለ እንዴ?" (ልጅ)

...."አዎ! እውነት ስልህ ፥ ያው የበላነው ተስማምቶን ሀይል እና ጉልበት አግኝተን፡ አካላዊ እድገት እያመጣን አይደል የምንኖረው ፡ ያ ታድያ እኮ በኛ ኖረ ማለት ነው ልጄ" (አባት)

..."እሺ እና ጋሽ ጀንበሬ እንደውም ባለፈው በለሊት ወደስራ ሲሄዱ ጅብ የበላቸው ጅብ ሆነው እየኖሩ ነው ማለት ነው አባዬ?" (ልጅ)

..."ወይ ጉድ ዛሬ እንደው ምን ጉድ ውስጥ ነው የገባሁት...ማነሽ 'አልማዝ ነይ እስኪ ይሄን ልጅ ወደዛ ወስደሽ ገላግይኝ'...አልሞት አልኩህ?" (አባት)

..."ምን አልክ አባዬ?" (ልጅ)

..."ምንም ወዲህ ነው የእራት ሰዓት ደርሷል እናትህን ወስደሽ አብይው እያልኳት ነው....'አንቺ አልማዝ ነይ እኮ ነው ምልሽ'. ..አትሰማኝም እንዴ?" (አባት)

..."እና ንገረኛ አባቴ ጋሽ ጀንበሬ ጅብ ሆነዋል ማለት ነው? የባቢ አባት ጅብ ናቸው ማለት ነው?" (ልጅ)

..."ሆሆ! ደሞ ነገ ት/ት ቤት ሄደህ 'የባቢ አባት ጅብ ሆኑ እንጂ አልሞቱም ብሏል አባዬ' ልትል ነው ሆሆ! ደሞ ከጎረቤቶቼ አቆራርጠኛ! በል በል የለም ያልኩህን እርሳው በቃ እንደውም ሀጥያት ነው ከንግዲህ በግ የሚባል አናርድም።. ..ግልግል እንደውም ተወዷል...ሆ! በገዛ እጄ...ቆይ እዛ ት/ት ቤት ምን ስትማሩ ነው የምትውሉት?" (አባት)

..." እርሳው? አባዬ ደሞ አንዴ ነግረኸኝ እንዴት ነው ምረሳው?...ደሞ ት/ት ቤት ሳይሆን አንተ እኮ ነህ የነገርከኝ በግን ስንበላው እኛን እንደሚሆን...ት/ት ቤት ምን አጠፉ....ህእ!" (ልጅ)

..."ማ? እኔ አልወጣኝም! አይወጣኝምም!. ..ምን ይላል ይሄ...በል ጥፋ ከዚ. ..ድራሽ አባክ ይጥፋና...አትሄድም!".....

By Mikiyas Beshada Kebede

@wegoch
@wegoch
@paappii

4 months ago

Nowadays, Cheaters are posting about loyalty, while Loyal ones are posting jokes.??

4 months, 1 week ago

ወደድክም ጠላህም ፍቅር እንደ ጤዛ ብን ብላ የምትጠፋ ቅፅበታዊ ምትሃት ከሆነች ቆየች።?

We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated hace 3 semanas, 5 días

Last updated hace 3 semanas

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated hace 1 mes, 1 semana