ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated 2 months, 3 weeks ago
Last updated 2 months, 2 weeks ago
ይህ ስለ Manchester United መረጃዎችን የሚያገኙበት የ Telegram ቻናል ነው 🇪🇹
--------------------------------------------------------------
☞︎| ስለ ማንቸስተር ዩናይትድ ትኩስ መረጃዎች
☞| ቀጥታ ስርጭቶች ከየስታድየሞቹ
☞| የዝውውር ዜናዎች
☞| ስለ ማንችስተር ዩናይትድ ታሪኮች
📩 ለማስታወቂያ ስራ DM :- @Marcoabdu
Last updated 1 month, 1 week ago
ከሸዋሮቢት ከተማ ወደ ደብረብርሃን አመራር አጅቦ ሲንቀሳቀስ የነበረ የአድማ ብተናና መከላከያ ሠራዊት ተደመሠሠ!
አማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ
የካቲት 2/2017 ዓ.ም
የአማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ መሃመድ ቢሆነኝ ኮር አስቻለው ደሴ ክፋለጦር 4ኛ ሻለቃ ከሸዋሮቢት ወደ ደብረብርሃን የብልፅግና ከፍተኛ አመራሮችን አጅቦ ሲንቀሳቀስ በነበረ በጠላት ፓትሮል ላይ የደፈጣ እርምጃ በመውሰድ የጠላት ሀይልን ደምስሶታል። አመራሮቹን በ6 ፓትሮል አጅቦ ዲሽቃና ዙ-23 ያጠመደው የጠላት ሃይል ከሸዋሮቢት ከተማ ሳይርቅ ልዩ ቦታው ፍርፍር በተባለ ቦታ የአርበኛ መከታው ቀኝ እጆች በደፈጣ ጠብቀው አርግፈውታል።
በሌላ ግንባር የአማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ የአፄ አምደ ጽዮን ኮር 7ለ70 ክፍለ ጦር የኦሮሞ ብሄረሰብን ምሽግ አድርጎ ከሚነሳው የጠላት ሀይል ጋር ገጥሞ ከፍተኛ ድል ተቀዳጅቷል። የጠላት ቡድን ሀይሉን አሰባስቦ ውጊያ ቢክፍትም የአማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ስር የሚገኘው 7ለ70 ክፍለ ጦር በተለያየ አቅጣጫ የጠላትን ሃይል በመግጠም ከፍተኛ ኪሳራ አድርሶበታል። በዚህ ቀጠና በአውደ ውጊያ የተመታው የብልፅግና ሠራዊት በኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን ውስጥ ከተደበቀው ከሸኔ ጋር በጥምረት ውጊያ የከፈተ ቢሆንም በተባበረ ክንድ በአማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ አናብስቶችና የጦር ጠበብቶች እየተደቆሰ ይገኛል።
ድል ለአማራ ፋኖ
አማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ
ከአማራ ፖለቲከኞች እና ሊሂቃኖች ስህተት አንዱ የክልሉን መቀመጫ መሃል አማራ ባህርዳር ማድረጋቸው ነዉ ፡፡
ወደ ሃገሪቱ ሴንተር ቀርቦ በማእከላዊ ሃገር ላይ ጫና ማሳደር ሲገባ እንዲሁም አንዳንድ የክልሉን ፅህፈት ቤቶች አዲስአበባ ላይ ማድረግ ሲገባ ከማእከላዊ ቦታ እርቆ መቀመጥ የክልሉን የፖለቲካዊ አቅም ገድሎል ፡፡
አሁንም ሊታሰብበት የሚገባ እና የክልሉን መቀመጫ ወደ ደብረብርሃን ማዘዋወር ይገባል ባይ ነን ፡፡
ሃሳባችሁን ስጡበት
ለአማራ ህዝብ ነፃነት ደም እና አጥንታቸዉን ሊከሰክሱ የተዘጋጁ ተርብ የአማራ ልጆች ፣
ጭቆና ያንገሸገሻቸዉ ተገፍተዉ የወጡ አፍላ የአማራ ወጣቶች ፣
ማንነቴን አትግፉ ህዝባችን በሰላም ወጥቶ ሰርቶ ይባላ ያሉ ጫካ ቤቴ ብለዉ ነፍጥ ያነገቡ የአማራ መፃኢ እድል ወሳኝ ወጣት ፋኖዎች ፡፡፡
አንድነት ወዴት አለህ ፣ ቆራጡ መሪስ ከየት ነህ እያሉ ነዉ ፡፡
መጪዉ ጊዜ ለአማራ ብሩህ ነዉ ፡፡
ሸዋ‼️****
የ አማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ የመንዝ ማማ ወረዳን (ሞላሌን) ተቆጣጥሯል
ካላኮርማ ክፍለጦር ራያ ቆቦ ሮቢት ከተማን በመቆጣጠር ታላቅ ድል ተጎናፀፈ::የአማራ ፋኖ በወሎ ተጠናክሮ በቀጠለው የህልዉና ተጋድሎ በፋኖ ዘውዱ ዳርጌ የሚመራው ካላኮርማ ክፍለጦር ወልድያና ቆቦ ከተማ መካከል ዋና መስመር ላይ የምትገኘዉን ራያ ቆቦ ሮቢት ከተማን በመቆጣጠር ታላቅ ድል ተጎናፀፈ:
ሸዋሮቢት ከፍተኛ ዉጊያ እየተደረገ ነዉ
ወቅታዊ መግለጫ
የአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ ከሰም ክፍለ ጦር ነበልባል ብርጌድ በሚንቀሳቀስባቸው የምንጃር ሸንኮራ ወረዳ ካሉት 31 ቀበሌዎች ውስጥ 28ቱን ፋኖ የተቆጣጠረ ሲሆን ባለው የአፓርታይድ የአብይ አህመድ መንግስት 3 የከተማ ቀበሌዎችን ነው ከሞላ ጎደል የተቆጣጠራቸው ስለሆነም ከሚቆጣጠራቸው ከነዚህ ቀበሌዎች ውስጥ ያሉትን የአማራ ወጣቶች አዝመራ በመሰብሰብ ላይ ከሚወቁበት አውድማ ላይ ጭምር በማፈስ እስትንፋሴን ያስቀጥሉልኛል ብሎ ላሰበው የመጨረሻ ጦርነት ለመዘጋጀት ወረዳው ላይ የአስር ቀን ስልጠና በማሠልጠን ላይ ይገኛል።
ስለሆነም መላው የወረዳው ህዝብም ሆነ የታፈሡ ሠዎች ማወቅ ያለባቸው ነገር ያፈሳቸውን ሰዎች ፦
የሸዋውን ወደ ጎንደር ፣ የጎንደሩን ወደ ሸዋ ፣ የወሎውን ወደ ጎጃም ፣ የጎጃሙን ወደ ወሎ በማዞር ወይም በማቀያየር እቅዱን እንዲያስፈፅሙለት እየሠራ እንደሚገኝ እና ስልጣነ መንበሩን በድሃ ልጅ ደም ማራዘም ሳይታለም የተፈታ መሆኑን ህዝቡ ጠንቅቆ እንዲያውቀው ስንል የጥንቃቄ መልዕክታችንን እያስተላለፍን ፦
አሁን ህዝቡ እራሱን ከአፈሳ ለመከላከል የጀመረውን ግብግብ አጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል።
የብልፅግናው አገዛዝ በማህበረሰቡ ላይ ከምንጣፍ ጎታቹ የአብይ ሠራዊትና ከጋሻ ጃግሬዎቹ ጋር በገጀራ ፥ በዱላ ፥በመጥረቢያና በቢላዋ እራሱን እየተከላከለ ሁሉም በሚባል ደረጃ ማህበረሰቡ ቤትና ንብረቱን ትቶ በዱርና በጫካ መኖሪያውን አድርጓል ።
በመሆኑም እርስ በእርስ ከሚያጋድለን አረመኔአዊ አባገነን መንግስት መንጋጋ ለመላቀቅ ሰልጣኙ ከወረዳችን እንዳይወጣ መላው ማህበረሰባችን መንገድ በመዝጋት እና አመፅ በማንሳት ሠራዊቱን በመበተን ወደ ነበልባል ብርጌድ እንድትቀላቀሉ እና የአብይ አህመድን አባገነናዊ መንግስትን በአፋጣኝ ወደ ግብዓተ መሬቱ እንድናስገባ ስንል ጥሪአችንን እናቀርባለን።
-
ከነበልባል ብርጌድ ሚድያና ኮሚኒኬሽን
ፋኖ መምህር አጥናፉ አባተ
©Ethio 251
መረጃ ‼️
"እባካችሁ የዘራነውን እንኳን እንሰብሰብ " የአማራ ክልል ገበሬዎች ተማፅኖ ነዉ
በአዲስአበባ እና በኦሮሚያ ክልል የነበረዉ ወጣቶች በጅምላ አፍሶ ወደ ወታደራዊ ማስልጠኛ ማስገባት አሁን ላይ በአማራ ክልል ሁሉም አካባቢዎች ተስፋፍቶ ወጣት ሽማግሌ ሳይባል በግዳጅ ወደ ማስልጠኛ እየገባ መሆኑ ተሰምቶል ፡፡
በተለይ ገበሬዎች የመኸር ሰብል መሰብሰቢያ ወቅት ቢሆንም በግዳጅ ታፍነዉ ወደ ወታደራዊ ግዳጅ እየተላኩ ነዉ ተብሎል ፡፡
የመንግስት ሚሊሻዎች ወደ መኖሪያ መንደሮች፣ ትምህርትቤቶች ፣ የሀይማኖት ተቆማት በመሄድ ወጣቶችን በማሰር ወደ ወታደራዊ ማስልጠኛዎች በግዳጅ እንደሚልኩ ነዉ የተነገረዉ
በአዲስ አበባ ኣያት አርባ ዘጠኝ አካባቢ በተለምዶ ውሃ ታንከር በሚባለው አካባቢ የቦንብ ጥቃት ድረሶ 3 ፖሊስ አባላት መገደላቸው ተስምቶል
የተመለከትነው ዘግናኝ ቪዲዮ የሽብር ጥግ ማሳያ ነው። በአንጻሩ መንግሥታዊ መዋቅሩ ድርጊቱን ለፖለቲካ ትርፍ ያዋለበት መንገድ የሚወገዝ ተግባር ነው።
(በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ከእናት ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ)
ከሰሞኑ በማኅበራዊ ሚዲያ ሲዘዋወር የተመለከትነውና ከየት መጣውን ለማጣራት ጥረት እያደረግን ያለውን ምስል ወድምጽ(video) እጅግ ዘግናኝና በጽኑ ቃል የሚወገዝ ተግባር ሆኖ አግኝተነዋል። ፓርቲያችን ድርጊቱ በማን፣ የትና መቸ እንደተፈጸመ ለማጣራት ጥረቶችን እያደረገ ሲሆን በዚሁ አጋጣሚ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽንና ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ በተለመደው መልኩ በገለልተኝነት ጥረታቸውን አድርገው ለሕዝብ ይፋ እንደሚያደርጉ ጽኑ እምነታችን ነው።
ከዚኹ ጋር ተያይዞ እጅግ ጥርጣሬ ውስጥ የሚያስገቡና ከዚኽ ዘግናኝ ድርጊት ጀርባ ምን የተደገሰ ነገር አለ? ብለን እንድንጠይቅ የሚያደርጉ አንዳንድ ኹነቶችን ታዝበናል። ወለጋ የደም ምድር፣ የእልቂት ሜዳ ሲሆንና በመቶዎች የሚቆጠሩ ዜጎች በዘግናኝ ኹኔታ በአንድ ጀምበር ሲያልቁ፤ መላው የኦሮሚያ ሕዝብ የቀን ገዥና የጨለማ ገዥ እየተፈራረቀበት ቁምስቅሉን ሲያይ፣ ልጆቹን ሲነጠቅ፤ አፋርና ሶማሌ ሥርዓቱ በፈጠረው ግጭት ወገኖቻችን በመቶዎች ሲሞቱ፤ እዚኹ አፍንጫችን ሥር ምሥራቅ ሸዋ በአንድ ሌሊት 43 ሰው ቤት ተዘግቶ ሲቃጠል፤ ሞጆ ወረዳ ላይ አረጋዊ ካህን ከነቤተሰባቸው ለዘር እንዳይተርፉ ወንዝ ዳር እንደበግ ሲታረዱ፤ የዝቋላ አቦ ገዳማውያን አባቶች ተቆራርጠው ጭምር ሲገደሉ፤ ደራ ላይ የመስጅድ ኢማም ከነቤተሰባቸው ለዘር እንዳይተርፉ በዘግናኝ ኹኔታ ሲገደሉ፤ በመላው አማራ ሰው በተገኘበት ይገደል ተብሎ የታወጀ እስኪመስል ድረስ ነብሰ ጡሮችና ሕጻናት ሲያልቁ፤ ትግራይ የሞት ጥላ አንዣቦ በረሃብና በሰው ሠራሽ መንገድ ሕጻናት ጭምር ሲያልቁ፤ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ በአራቱም ማዕዘናት በየቀኑ ሊባል በሚችል መልኩ ለመስማትም ለማየትም በሚዘገንን መልኩ እልቂት ሲፈጸም ምንም እንዳልተፈጠረ አሸሸ ገዳሜ ሲደልቁ የኖሩ የመንግሥት ሚዲያዎች በዚህ ጉዳይ ብቻ እንዴት ከደስታ እንቅልፋቸውና ፈንጠዝያቸው ነቅተው ሙሾ አውራጅ ሆኑ? "ለሞቱት ዛፍ እንተክላለን" እያለ በሞት ላይ ሲዘብት የነበረው መንግሥት እንዴት ተሰምቶት ሀዘን ተቀመጠ? ኦሮሚያ የደም መሬት ሲሆን የሕዝቡን ብሶት ተጋርቶ የማያውቀው፣ አትግደሉን እያለ ልጆቹን ቀንበር ጠምዶ ለወጣው ሕዝብ ጠብ የሚል መፍትሔ ያልሰጠውና ሲጠየቅም ጆሮ ዳባ ልበስ የሚለው የክልሉ መንግሥት እንዴት አኹን ነቅቶ ሕዝብን በሕዝብ ላይ የሚያነሳሳ መግለጫ አወጣ? የሚሉት በውል መታየት ያለባቸው ሰበዞች ሆነው አግኝተናቸዋል። ከዚህ አስነዋሪ ድርጊት ጀርባ ማን ነው ያለው የሚለውንም ፍንጭ ይሰጡ ይሆን ወይ? ብለን እንድንጠይቅ አስገድዶናል።
ዘግናኝ ድርጊቱን አውግዞ፣ ተገቢው ማጣራት ተደርጎበት አጥፊዎችን ለፍርድ አደባባይ ማቅረብ፣ ድርጊቱም በምድራችን ዳግም እንዳይከሰት ተባብሮ መሥራት ሲገባ ሀኪም አጥቶ በጽኑ ደዌ ተይዞ የሚሰቃየውን ፖለቲካችንን መንግሥታዊ መዋቅሩና መንግሥት የሚዘውራቸው ሚዲያዎቹ ጊዜያዊ የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት ሲባል ያደረጉት እሳት ላይ ቤንዚን ማርከፍከፍና እልቂት ጠመቃ ውሎ አድሮ ከተጠያቂነት እንደማያድን በእርግጥ መናገር ይቻላል።
በአንጻሩ ከዚህ በፊት ጽንፍ በወጣ የፖለቲካ አቋማቸው የምናውቃቸው ግለሰቦች ተው ባይ ሆነው መታየታቸው እጅጉን የሚደነቅ ተግባር ሆኖ አግኝተነዋል። ኢትዮጵያ የሚያስፈልጋት ይሄው ስክነትና ፖለቲካዊ መቀራረብ መሆኑን በተግባር ለማስተማር ጅምር ሙከራዎች ታይተዋል። በመሆኑም
፩. እናት ፓርቲ ድርጊቱንና የድርጊቱን ፈጻሚዎች በጽኑ ያወግዛል፤ በገለልተኛ አካል ተጣርቶም ፍትሕ እንዲሰፍን አጥብቆ ይጠይቃል።
፪. መንግሥትና የመንግሥት ሚዲያዎች ለጊዜያዊ የፖለቲካ ትርፍ ሲባል ሕዝብን በሕዝብ ላይ ማነሳሳት እንዲያቆሙ እናሳስባለን።
፫. መንግሥትን ጨምሮ ኹሉም ታጣቂ ኃይሎች ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ እንደገለጽነው ንጹሓን ዜጎችን ዒላማ ማድረግ የጦር ወንጀል መሆኑንና ይዋል ይደር እንጂ ተጠያቂነትን እንደሚያስከትል በመረዳት ከዚህ መሰል ጥፋት እንዲታቀቡ አጽንዖት ሰጥተን እናሳስባለን።
እግዚአብሔር አገራችን ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ይጠብቅ!
እናት ፓርቲ
ኅዳር ፲፭ ቀን ፳፻፲፯ ዓ.ም
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated 2 months, 3 weeks ago
Last updated 2 months, 2 weeks ago
ይህ ስለ Manchester United መረጃዎችን የሚያገኙበት የ Telegram ቻናል ነው 🇪🇹
--------------------------------------------------------------
☞︎| ስለ ማንቸስተር ዩናይትድ ትኩስ መረጃዎች
☞| ቀጥታ ስርጭቶች ከየስታድየሞቹ
☞| የዝውውር ዜናዎች
☞| ስለ ማንችስተር ዩናይትድ ታሪኮች
📩 ለማስታወቂያ ስራ DM :- @Marcoabdu
Last updated 1 month, 1 week ago