ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated hace 3 semanas, 5 días
Last updated hace 3 semanas
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot
🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹
Last updated hace 1 mes, 1 semana
...
መፅሐፍ ቅዱስ Infallible የሚሆነው Infallible የሆነችው ቤተ/ክን ስለሰጠችን ነው ሲለን የከረመው ሰውዬ ያኔ ስትሰጠው ተሳስታለች መሠል ይኸው አሁን ደግሞ ሪቪዥን እየጠየቀ ነው። በእርግጥም ስህተት እንዳለ ተረድቷል ማለት አይደል ታድያ ?!
ቆይ እሱን ተውትና እንደው ከሰጠችው ራሱ የትኛዋ ቤተ/ክን ነች የምትሰጠው ?
የኢትዮጲያ ቤተ/ክ ነች ካለ እሷ ልትሳሳት ትችላለች። ስለዚህ 81ዱን ብትሰጠውኳ ልትሳሳት የሚችል አካል ነው የሰጠው ማለት ነው። ስለዚህ በራሱ ክራይቴሪያ ወድቆ Infallible የሆነ መፅሐፍቅዱስ ጨርሶውኑ ሊኖራቸው አይችልም ማለት ነው። ሊሳሳት የሚችል አካል ሊሳሳት የማይችለውን ልትሰጥ አትችልም ብሎናልና! በእርግጥ ትሳሳታለች ብሎ የነገረንም እራሱ ነው። 💀
ስለዚህ Eccumenical Council ነው እየጠበቀ ያለው ? ካልሆነስ ከእኛ ምን ለየው ?
ዘይገርም ነውኮ ዘንድሮ ...
ከልደት በኋላ አንደኛ እሁድ
የወንጌልና የመልእክት ክፍል
ማቴዎስ 2
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹³ እነርሱም ከሄዱ በኋላ እነሆ፥ የጌታ መልአክ በሕልም ለዮሴፍ ታይቶ፦ ሄሮድስ ሕፃኑን ሊገድለው ይፈልገዋልና ተነሣ፥ ሕፃኑንና እናቱንም ይዘህ ወደ ግብፅ ሽሽ፥ እስክነግርህም ድረስ በዚያ ተቀመጥ አለው።
¹⁴-¹⁵ እርሱም ተነሥቶ ሕፃኑንና እናቱን በሌሊት ያዘና ከጌታ ዘንድ በነቢይ፦ ልጄን ከግብፅ ጠራሁት የተባለው እንዲፈጸም ወደ ግብፅ ሄደ፥ ሄሮድስም እስኪሞት ድረስ በዚያ ኖረ።
¹⁶ ከዚህ በኋላ ሄሮድስ ሰብአ ሰገል እንደ ተሣለቁበት ባየ ጊዜ እጅግ ተቆጣና ልኮ ከሰብአ ሰገል እንደ ተረዳው ዘመን በቤተ ልሔምና በአውራጃዋ የነበሩትን፥ ሁለት ዓመት የሆናቸውን ከዚያም የሚያንሱትን ሕፃናት ሁሉ አስገደለ።
¹⁷-¹⁸ ያን ጊዜ በነቢዩ በኤርምያስ፥ ድምፅ በራማ ተሰማ፥ ልቅሶና ብዙ ዋይታ፤ ራሔል ስለ ልጆችዋ አለቀሰች፥ መጽናናትም አልወደደችም፥ የሉምና የተባለው ተፈጸመ።
¹⁹ ሄሮድስም ከሞተ በኋላ፥ እነሆ፥ የጌታ መልአክ በግብፅ ለዮሴፍ በሕልም ታይቶ፦
²⁰ የሕፃኑን ነፍስ የፈለጉት ሞተዋልና ተነሣ፥ ሕፃኑን እናቱንም ይዘህ ወደ እስራኤል አገር ሂድ አለ።
²¹ እርሱም ተነሥቶ ሕፃኑንና እናቱን ያዘና ወደ እስራኤል አገር ገባ።
²² በአባቱም በሄሮድስ ፈንታ አርኬላዎስ በይሁዳ እንደ ነገሠ በሰማ ጊዜ፥ ወደዚያ መሄድን ፈራ፤ በሕልምም ተረድቶ ወደ ገሊላ አገር ሄደ፤
²³ በነቢያት፦ ናዝራዊ ይባላል የተባለው ይፈጸም ዘንድ፥ ናዝሬት ወደምትባል ከተማ መጥቶ ኖረ።
ገላትያ 4
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁴ ነገር ግን የዘመኑ ፍጻሜ በደረሰ ጊዜ እግዚአብሔር ከሴት የተወለደውን ከሕግም በታች የተወለደውን ልጁን ላከ፤
⁵ እንደ ልጆች እንሆን ዘንድ፥ ከሕግ በታች ያሉትን ይዋጅ ዘንድ።
⁶ ልጆችም ስለ ሆናችሁ እግዚአብሔር አባ አባት ብሎ የሚጮኽ የልጁን መንፈስ በልባችሁ ውስጥ ላከ።
⁷ ስለዚህ ከእንግዲህ ወዲህ ልጅ ነህ እንጂ ባሪያ አይደለህም፤ ልጅም ከሆንህ ደግሞ በክርስቶስ የእግዚአብሔር ወራሽ ነህ።
Is to be deep in history to cease to be Protestant? When it comes to the venerating of icons, to be deep in history is, emphatically to the contrary, to cease to be Roman Catholic or Eastern Orthodox. For the witness of the early church is unanimously and thunderingly opposed to the practice, in consistency with the witness of Scripture.
Yet the seventh ecumenical council, which both the Roman Catholic and Eastern Orthodox traditions regard as infallible, casts anathemas widely and liberally at all who abstain from the practice (or “knowingly communicate” with those who do!).
This is not a case of doctrinal development, but doctrinal U-turn: The seventh ecumenical council reversed the view of the early church on the veneration of icons. Unfortunately, traditions that consider Nicaea II to represent infallible teaching cannot reform its teaching. It is, by definition, irreformable. The Protestant tradition, by contrast, offers us a pathway of meaningful return to the practice and theology of the early church, as well as to that of later contexts like the Council of Frankfurt. It also allows us to obey the second commandment.
Further, it obligates no anathemas. Therefore, it is the Protestant position on icon veneration that is not only deep in history, but biblical and catholic.
Gavin Ortlund, What it means to be Protestant , p 192
የመዳን ቀንዴ ጌታዬ
አምላኬ ያስነሳው ለእኔ
ከአብ ጋር ያስተራረቀኝ
ዘወትር የሚማልድልኝ
ውዴ የመዳን ቀንዴ
ውዴ የመዳን ቀንዴ
...
ሊቀካህን ሆኖልኛል ሊቀካህን
ሊቀካህን ሆኖልኛል ሊቀካህን
እናንተ ፕሮቴስታንቶች ቤተክርስቲያን 2ተኛው ወይ 3ተኛው ክፍለዘመን ላይ ጠፍታ 16ተኛው ክፍለዘመን ላይ ጌታ ታደጋት ብላችሁ እንዴት ታምናላችሁ ... ? ብላችሁ የምትወቅሱን ኦርቶዶክስ ወንድሞቻችን ይኸው መልሳችንን ተመልከቱስኪ እንዲህ አቅርቤላቹሀለው ... 😁 .... 👇👇👇👇
እናንተ ፕሮቴስታንቶች ቤተክርስቲያን 2ተኛው ወይ 3ተኛው ክፍለዘመን ላይ ጠፍታ 16ተኛው ክፍለዘመን ላይ ጌታ ታደጋት ብላችሁ እንዴት ታምናላችሁ ... ?
ብላችሁ የምትወቅሱን ኦርቶዶክስ ወንድሞቻችን ይኸው መልሳችንን ተመልከቱስኪ እንዲህ አቅርቤላቹሀለው ... 😁
.... 👇👇👇👇
እንኳን ለጌታችን ልደት የመታሰቢያ በአል አደረሳችሁ!
ይህ የአምላክ ሰው ሆኖ መወለድ ፍጥረታዊ ሰው ሊረዳው የማይችለው ፤ በመንፈስቅዱስ ብርሀን ብቻ ልንታመነው የምንችለው ፤ ከአምላክ መገለጦች ሁሉ የመጨረሻውና የመሰጠረው መገለጥ ነው።
▣ ለምን ቃል ስጋ ሆነ ?
ሀጥያታችንን ሊሸከምና ለእኛ ይገባ የነበረውን የሞት ቅጣት(ደሞዝ) ከፍሎ ከዘላለም ፍርድ ነፃ ሊያወጣን በዚህም ደግሞ የዘላለምን ህይወት የመውረስ መብት ሊቸረን ነው! ይህም በእኛ በፕሮቴስታንቱ ስነመለኮቶ ወስጥ ፅድቅ | Justification ብለን የምንጠራው ነው። ስጋዌን ያስገደደው (Necessitate ያደረገው) ስለዚህም ዋናውና ቀዳሚው አላማ (Cause) የሆነው ይህ የፅድቅ ጉዳይ ነው!
▣ እግዚአብሄርን ለዚህ ውሳኔ ምን ምክንያት ሆነው ?
እግዚአብሄር አምላክ ሰው እንዲሆን ግድ ያሰኘው ብቸኛ ምክንያት በሀጥያታችን ሙታንና ፍርድ የተገባን ሆነን ላለነው ለሰው ልጆች ያለው ፍቅር ብቻና ብቻ ነው!
▣ ግን ስጋዌ ከዚህ የዘለለ ምስጢር አለው ?
ይህ ምስጢር በመስቀል የመሞቱንና እኛን ከማዳኑ አንፃር ብቻ የሚተረጎም አይደለም። ከላይ የስጋዌ አላማና ግብ ሆኖ የተገለፀው ፅድቅ ምንምኳ የስጋዌው ትልቁና ዋነኛው ግብ ቢሆንም ነገር ግን ፅድቁን የመስራቱና ለእኛም የመስጠቱ የመጨረሻ አላማና ግብ (Telos) የእግዚአብሄርን ባህሪ ወይም የእግዚአብሄርን ህይወት ተካፋይ ለመሆን ነው! ስለዚህ በድህነት አስተምህሮ ውስጥ ፅድቅ በራሱ የመጨረሻው ነጥብ አይደለም። እርሱ ራሱ ግብ አለው!
ስለዚህ ይህ ማለት :
➾ የፅድቅ (Justification) ግቡ በእግዚአብሄር ህይወት ውስጥ ያለ ተካፋይነት ነው!
➾ The end Goal of Justification is participation in the life of God.
ይህንን የፅድቅ የመጨረሻ ግብ አባቶች Theosis እንዲሁም Divinization ብለው ይጠሩታል። ይህም በእዚህ በምድር ባለን ህይወትም ሆነ ከመጨረሻው ፍርድ በኋላ ከጌታ ጋር ባለን ህይወት ጨርሰን የምንሆነው ወይም የምናጠናቅቀው ነገር ባይሆንም ነገር ግን በዚህ በምድር በቅድስና ጉዞ (Sanctification) እለት እለት እየተላበስን የምንመጣውና ከከበርንም በኋላ (After Glorification) በሙላት የእግዚአብሄርን ህይወት የምንካፈልበት እንዲሁም ያለማቋረጥ እየጠለቀ በሚሄድ መልኩ Experiance የምናደርግበትም ነው።
ታድያ ቃል በዚህ በስጋዌው ይህን ለእኛ የመጨረሻ ግብ የሆነውን ያንን ሰው ፕሮቶታይፕ ሆኖ በአካልና በስጋ የገለጠበት ነው። ጳውሎስም በሮሜ 8: 29 ላይ ስለዚህ ሲናገር የእግዚአብሄር የማዳኑ የመጨረሻው ግብና አላማ የልጁን መልክ መምሰል ነው ይለናል። ይህንንም በመጥራት ፤ በማፅደቅና በማክበር በኩል ፈፀመው!
በውድቀት ምክንያት ባህሪው ደቆ ለሀጥያትም ባሪያ ሆኖ የተገዛው የሰው ልጅ ከዚህ ፍፁም የሚገላግለው መድሀኒት የእራሱ የእግዚአብሄር ህይወት ነው! ስለዚህ ስጋዌው ይህንን መድሀኒት ለራሳችን Appropriate (Apply) የምናደርግበትን መብት (አስተውሉ! ስለመብት (Title) ነው እያወራሁ ያለሁት!) የምናገኝብን ስራ ለመስራት የተገለጠበት ብቻ ሳይሆን ፤ ያ ሙሉ ለሙሉ አለምን ሀጥያትንና ሞትን አሸንፎ እግዚአብሄርን የመሰለውና ባህሪውንም የሚያንፀባርቀውን የእርሱን ማንነት ለእኛ በቅርበት የገለጠበትም ጭምር ነው። እኛም በእርሱ በኩል (In participating in his Status) ከዛም ደግሞ በእርሱ ውስጥ (In an Onthological Participation in his Nature) አለምን ሀጥያትንና ሞትን እናሸንፋለን!
መልካም በአል!
ስገምት ስገምት አብዛኞች ኦርቶዶክስ ወንድሞቻችን Apostolic Succession (AS) ማለት ማንኛውም አይነት ቅብብሎች ይመስላቸዋል መሠል። ማለትም ለምሳሌ ክርስቶስ ሐዋርያቱን ሾመ ፤ ሐዋርያቱ ኤጲስቆጶሳትን ሾሙ ፤ የተሾሙትም ታማኝ የሆኑ ተከታይ ኤጲስቆጶሳትን ሾሙ ፤ እያለ እያለ ሄደ .. ታድያ ይህንን በማሳየት ብቻ Apostolic Succestionን ጨርሰው ያስረገጡ የሚመስላቸው ሰዎች አሉ።
ያው ግን ይህ ስለ AS ጨርሶ አለማወቅ ነው። ይህንንማ በየትም የፕሮቴስታንት ቤተእምነት ውስጥ ሆነህ መቀበል ትችላለህ ፣ ትቀበላለህም። ቀይ መስመር ሆኖ የሚለያየንን ፕሮፐር የሆነ የሐዋርያት ቅብብሎሽ (AP) አስተምህሮ ትርጉም ከዚህ በፊት አብራርቼ አስቀምጫለሁ። አራት መሠረታዊ ነጥቦች አሉት። ቀጣዩን ሊንክ ተጠቀሙና ተመልከቱት!
ሌላው ደግሞ እንደው በOrdinary የቤተ/ክን ህይወት ውስጥ ማንም ብድግ ብሎ ራሱን መሾምና ሳክራመንትን Administer ማድርግ ይችላል ብለንም እንደምናምን እና በቃ ምንም መስፈርት የሌላቸው አድርገውን የሚስሉንም አሉ። ይህም ስህተት ነው። ጌታ ይርዳቸው!
Side Note :
እንደው ምናልባት ትክክል ከሆነኳ በተወሰኑ ሉተራንና በአንግሊካን ዘንድ AP የሚታመን መሆኑን አትዘንጉት! 'ወይ ዜሮ ወይ መቶ , ምረጥ!' በሚል የሚሰሩት ፋልስ ዳይኮቶሚ ለማያውቁቱ ካልሆነ በቀር በእኛ ዘንድ አያዋጣቸውም!
ጋይስ እንዴት ናችሁሳ ? ያው እንደምታዩት በአጭር ጊዜ ውስጥ 3k ገብተናል። እንኳን ደስ አለን። 👊 ገና ደግሞ እንበዛለን። 😁
እስከዛሬ ለሰዎች ሼር እያደረጋችሁ ጀማችንን እንዲቀላቀሉን ላደረጋችሁና እያደረጋችሁ ላላችሁ ወንድም እህቶች ፤ ለተቀላቀላችሁንም ጭምር ፈጣሪ ያክብርልኝ።
ይህ አገልግሎት እንዲሰፋ የሁላችንንም መረባረብ የሚጠይቅ መሆኑ ምንም ጥያቄ የለውምና አሁንም በተቻለን አቅም በዙሪያችን ላሉ ለሰዎች በማሳወቅ ፣ በመጋበዝ ፤ ሼር በማድረግ እንድናሰፋው አደራ እላለሁ።
ምናልባት ደግሞ ይህን አስመልክቶ ከዚህ በፊት እንዳደረግነው ሰብሰብ እንበልና እነዚህ እነዚህ ላይ እናውጋ የሚል ሀሳብ ካላችሁ እስኪ አሳውቁኝ እናደርገዋለን።😁
ድኛለሁ፣ እየዳንሁ ነው፣ ወደፊትም እድናለሁ በሚለው ሰሞናዊ የሶሻል ሚዲያ ትምህርታችሁ ላይ ግን ፓትሪስቲካዊ ማስረጃ እያየን አይደለም😁😁 እስቲ እርዱን እባካችሁን ስራችንንም አቅልሉልን😄
ከመጸሃፍ ቅዱስ በ16ኛ ክፍለ ዘመን መነጽር ከምታስተምሩን እባካችሁን ከአበው እያመሳጠራችሁ፣ በጉባኤ ውሳኔዎች እያስደገፋችሁ፣ በቤተ እምነታችሁ የእምነት ድንጋጌ እያመሳከራችሁ እባካችሁን እኛ የጠፋን በጎቹን ተጣሩን😀
ከመጸሃፍ ቅዱስ ብቻ እያስተማራችሁ ከመሰረታዊ መርሆቻችሁ ፈቀቅ አትበሉ። ደግሞ ድኛለሁ፣ እየዳንሁ ነው ያልከው ግለሰብ ናና እስቲ በና ሶላ ፊዴን የማትቀበልበት ሰማያዊ ምስጥርህን ንገረኝ😁
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated hace 3 semanas, 5 días
Last updated hace 3 semanas
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot
🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹
Last updated hace 1 mes, 1 semana