ኢትዮ መረጃ - NEWS

Description
ኢትዮጵያን መውደድ ባትችል አትጥላት

ማክበር ባትችል አታዋርዳት
ማራመድ ባትችል አታዘግያት
መጠበቅ ባትችል አትበትናት።
ይህን በማድረግ ታሪክ ባትሠራም ታሪክ አታበላሽም።

ለአስታየት @ethio_merjabot
@B_promotor
Advertising
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 2 months, 1 week ago

Last updated 6 days, 22 hours ago

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ ? @Esat_tv_comment_bot

??ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ??

Last updated 2 months, 3 weeks ago

6 days, 14 hours ago
“ በአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራው ቡድን …

“ በአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራው ቡድን ህወሓትን በአመፅ ለመበተን ወጣቶችን እያሰለጠነ ነው” አማኑኤል አሰፋ

በደብረጽዮን ገብረሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት ባካሄደው ጉባኤ ምክትል ሊቀመንበር ሆነው የተመረጡት አቶ አማኑኤል አሰፋ  መግለጫ ሰጥተው ነበር።

በዚህ መግለጫቸው ላይ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ በባለፈው ጉባኤ ከሥልጣን የተነሱ በመሆናቸው “ፕሬዝደንትነታቸውን አንቀበልም” ብለዋል።

አቶ አማኑኤል “የጊዚያዊ አስተዳደሩ አመራሮች ህወሓትን በአመፅ ለመበተን ወጣቶች እያሰለጠኑ ናቸው” ሲሉ ወንጅለዋል።

“ የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ለሁለት ዓመት ያለ እቅድ እየተመራ ይገኛል “  በማለትም ገልፀዋል ።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news

6 days, 14 hours ago
ኢትዮ መረጃ - NEWS
1 week ago

#ጠብታው ሲጠራቀም  

በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ምስራቅ በለሳ ወረዳ የሚገኘው ሙትአንሳ  ማር  ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም ልዩ በረከት ያለበት ስፍራ ነው፡፡

ከዓለት መሀል በመነኮሳት ፀሎት ብቻ በሚቆረጥ የማር እምነትና ድውያን ከመፈወስ አልፎ ሙት ያስነሳ ድንቅ ጸበል ያለበት፤ ከዘጠና በላይ ገዳማውያን የተጠለሉበት፣ ስለ ዓለምና ስለ ሀገራችን ሌት ተቀን የሚጸልዩበት ቅዱስ ስፍራ ነው፡፡

ይሁንና መነኮሳቱና ገዳማውያኑ ተፈጥሯዊና ሰው ሰራሽ ችግሮች እየተፈታተኗቸው ነው፡፡ አከባቢው ተፈጥሮ ፊቷን አዙራበት ድርቅ በመኖሩ ጭው ያለ ምድረ በዳ ሆኋል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ በአካባቢው ያለው ጦርነት በየጊዜው ይጎበኟቸው የነበሩ ፀበልተኞች ፈጽመው እንዲሸሹና ገዳማውያኑ ያለምንም ጠያቂ በትልቅ ችግርና ፈተና ውስጥ እንዲገኙ አድርጓቸዋል፡፡

ከፀሎትና ከድካም መልስ የሚጠለሉበት በአታቸውን ማጽናት የሚችል እገዛ፣ ከፆም መልስ የሚቀምሱትን አፍ መሻሪያና የአመት ልብስ ልናቀርብላቸው ይገባል። በዚህ የበረከት ስራ ገዳሙንና አባቶችን ብቻ ሳይሆን በጸሎታቸው ሀገራችንንም ለመጠበቅ አስተዋጽኦ እናደርጋለን፡፡ የእያንዳንዳችን ጠብታ ድጋፍ ሲጠራቀም ዋጋ አለው፣ የሕሊና እርካታም እናገኛለን፡፡

ድጋፍ ለማድረግ፦ሙትአንሳ  ማር  ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት  ገዳም

ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444

የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444

2 weeks ago
ኢትዮ መረጃ - NEWS
2 weeks ago
ኢትዮ መረጃ - NEWS
2 weeks ago

#ከዓይን ሲርቅ የሚደርቀው እንቁላል…

“ሐልዎተ እግዚአብሔር” የእግዚአብሔርን መኖር ከምናውቅባቸው ነገሮች አንዱ ፍጥረታትን መመልከት እንደሆነ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን አባቶቻችን ያስተምሩናል፡፡

ይህ ሁሉ ስፍር ቁጥር የሌለው ፍጥረት አስገኚ፣ ፈጣሪ ባይኖረው ከዓለም ጅማሬ እስካለንበት ዘመንና እስከ ዓለም ፍጻሜ ስርዓቱን ጠብቆ ባልኖረም ነበር ይሉናል፡፡

ያውም ከድንቅ ተፈጥሯዊ ባሕርዩ ጋር፡፡ በዚህ ድንቅ ተፈጥሯዊ ባህርይ ከሚታወቁት ፍጥረታት አንዷ ግዡፏ የአእዋፋት ዝርያ ሰጎን ናት፡፡

ሰጎን እንቁላል ከጣለች በኋላ እስኪፈለፈል ድረስ አይኗን ከእርሱ ላይ አታነሳም፡፡ ምግብ ፍለጋ ስትሔድም ወንዱን አስጠብቃ ነው፡፡ አይኗን አንስታ ረጅም ጊዜ ከቆየች ይደርቅና አይፈለፈልላትም፡፡

የመፈልፈያ ጊዜያቸው ሲደርስም ከውጪ ሆና ቅርፊቱን ታንኳኳለች፣ እነርሱም ከውስጥ ሆነው ያንኳኳሉ፡፡ ድምጽ ታሰማቸዋለች፣ እነርሱም መልሰው ድምጽ ያሰማሉ፡፡ ይህን ጊዜ እንቁላሉን ሰብራ ታወጣቸዋለች፡፡

ስታንኳኳ ካላንኳኩ፣ ድምጽ ስታሰማቸው ድምጽ ካላሰሙ ጊዜያቸው ገና ነው አሊያም ሞተዋል፣ ወይም እንቁላሉ ባዶ ነው ብላ ስለምታስብ ትታቸው ትሔድና በዚያው ይደርቃል፡፡

እኛም እንደ ጫጩቶቹ ነን፡፡ አባታችን እግዚአብሔርም የከከበበን የኃጢአት ቅርፊት ሰብሮ የሚያወጣን ዘወትር አይኖቹን ከኛ የማያነሳ ጠባቂያችን ነው፡፡

ይህ እንዲሆን ግን ቅርፊቱን ሲያንኳኳ እኛም በኃጢአት ውስጥ እንኳን ብንሆን አድነኝ ብለን መልሰን እናንኳኳ፤ ድምጽ ሲያሰማ፣ ሲጠራን፣ ተመለሱ ሲለን የእሺታ፣ የመዳን ፍላጎት ድምጽ እናሰማው፡፡

አዎ ቅርፊቱን አንሳልኝ መውጣት፣ መራመድ፣ በጽድቅ ስራ መብረር እፈልጋለሁ እንበለው፡፡ በዘመነ ስጋዌው በዚህ ምድር ሲመላለስ ፈውስ ፈልገው ወደርሱ የሚመጡትን “ልትድን ትወዳለህን? ብሎ ይጠይቅ የነበረው በፈቃዳችን ስለሚሰራ ነው፡፡

መዳን፣ እንደ ሰጎኗ ጫጩቶች ከቅርፊቱ መውጣት፣ በበጎ ምግባር፣ በትሩፋት መጓዝ የምንችልበት እድል ተሰጥቶናል፡፡

ይህን ድንቅ ምስጢር የሚገልጹልን የመዳንን መንገድ እንድንከተል በጸሎታቸው የሚያስቡንን፣ የኃጢአት ቅርፊቷን የምትጭንብንን ይህቺን ዓለም ንቀው የመነኑትን ገዳማውያንና ቅዱሳት መካናትንም እናስብ፡፡ ጥሪውን እንድንሰማ፣ ለማንኳኳቱም መልስ እንድንሰጥ ይርዳን፡፡

ድጋፍ ለማድረግ፦ሙትአንሳ  ማር  ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት  ገዳም

ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444

የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444

3 weeks, 1 day ago
ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ዜጎች በአይን ብሌን …

ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ዜጎች በአይን ብሌን ጠባሳ ምክንያት የአይን ብርሀናቸውን ማጣታቸው ጥናት አረጋገጠ

በኢትዮጵያ በተደረገ የዳሰሳ ጥናት ከግማሽ ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ዜጎች በአይን ብሌን ጠባሳ ምክንያት የአይን ብርሀናቸውን አጥተው የአይን ብሌን ንቅለ ተከላ እየተጠባበቁ ናቸው ተብሏል።

እስካሁን ድረስም ንቅለ ተከላ የተደረገላቸው ዜጎች ቁጥር ከ3ሺህ በላይ እንደሆነና ብርሃናቸውን ማግኘታቸውንም ተገልጿል።

ይሁን እንጂ ካለው ፍላጎት አንጻር ሲታይ የለጋሾች ቁጥር እጅጉን አናሳ መሆኑንም ነው የተነገረው።

በመሆኑም ህዳር ወር አለም አቀፍ የአይን ብሌን ለጋሾች ወር በመሆኑ የብርሀን ስጦታ በመስጠት የወገኖቻችን ህይወት እንቀይር በሚል መሪ ቃል ለመጀመርያ ጊዜ በኢትዮጵያ ይከበራል።

በዚህም የሀገር መሪዎች፣ታዋቂ ሰዎች፣ የማህበረሰብ አንቂዎች፣ ጋዜጠኟች፣ የሀይማኖት መሪዎች እና የሀገር ሽማግሌዎችን ቃል በማስገባት ወሩን በሙሉ ሊከበር ነው።

የዓይን ብሌን ጠባሳ የሰው ልጆችን ሙሉ ለሙሉ ማየት የተሳናቸው ሊያደርግ እንደሚችል ገልጸው ነገር ግን ሕክምና ካገኘ ሊድን የሚችል ተናግረዋል።

የዓይን ጠባሳ ሊድን የሚችለው ሰዎች ከህልፈታቸው በኋላ በሚለግሱት የዓይን ብሌን መሆኑን ተናግረው ኅብረተሰቡ ዓይን ብሌኑን እንዲለግስ ጥሪ አቅርበዋል።

ይህንንም ተከትሎ ስለ ዓይን ብሌን ልገሳ በማስተማር ከህልፈት በኋላ የአይን ብሌናቸውን እንዲለግሱ የማድረግ ሥራ እየተሰራ መሆኑን ተገልጿል።

ተቋሙ ከጊዜ ወደ ጊዜ የሚሰጣቸው አገልግሎቶች እያደጉ ቢመጡም የፍላጎትና የአቅርቦት አለመመጣጠን ችግር መኖሩን ተቋሙ ጠቁሟል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news

3 weeks, 1 day ago

በኢየሩሳሌም መቅደስ ደጃፍ ላይ ስምንት ሙዳየ ምጽዋት ይቀመጥ ነበር። ክብር ይግባውና ጌታችን መድኃኔዓለም በሴቶች መግቢያ በኩል ባለው ሙዳየ ምጽዋት አጠገብ ቆሞ፣ ሁሉን በሚያውቅ ባህርይው ስጦታውንና ስጦታው የተሰጠበትን ልብ ያይ ነበር። አንዳንዶች ለዝና ሰጡ፣ ሌሎች ስጦታቸውን ኑሮአቸውን ሊያናጋ እንደማይችል በማሰብ ሰጡ።

አንዲት ድሃ መበለት ግን በቤትም በእጇም የነበራትን ሁለት ሳንቲም በሙሉ ሰጠች። ከእነዚህ ከሁለት ሳንቲሞች ውጪ በምድር ላይ ምንም ጥሪት ሀብት የላትም። በዚህ ጊዜ ጌታ "እውነት እላችኋለሁ፣ ይህች ድሃ መበለት ከሁሉ አብልጣ ጣለች እነዚህ ሁሉ ከትርፋቸው ወደ እግዚአብሔር መዝገብ ጥለዋልና ይህች ግን ከጉድለቷ የነበራትን ትዳርዋን ሁሉ ጣለች" አለ፡፡

ይህ በቅዱስ ሉቃስ ወንጌል ምዕራፍ 21፣1-4 የሰፈረው ይህ ቃል የመስጠትን ምንነት ጌታችን በሚገባ ያስረዳበት ነው፡፡ ሁሉ የእርሱ ሲሆን በቸርነትና በልግስና ከሰጠው ላይ ስጡኝ ብሎ ይለምናል፡፡

የዚህች መበለት በጌታችን የተደነቀ መስጠት ብዙ ይነግረናል፡፡ አለማስተዋል እንጂ እንኳን ገንዘባችን እኛ ራሳችን ዋጋ የተከፈለብን የእግዚአብሔር ገንዘቦች ነን።
አንዳንዶቻችን ከሰጠን የሚጎድልብን እየመሰለን እንሰስታለን፣ እግዚአብሔር ግን ስጡኝና ፈትኑኝ፣ የጎደለውን ባልሞላ በረከቱን ባላበዛ ታዘቡኝ ይለናል። ደግሞም ስጦታ ከጉድለት እንጂ ከትርፍ አይደለም።

ስጦታችን ካልተሰማን ገና አልሰጠንም ማለት ነው። እናም ማትረፍ ከፈለግን ከጉድለታችንም ቢሆን በፍቅር እንስጥ። በተለይ በአስቸጋሪ ሁኔታ ክረምቱን እያሳለፈ ላለው ገዳምና አባቶች እጃችንን እንዘርጋ፡፡

ድጋፍ ለማድረግ፦ሙትአንሳ  ማር  ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት  ገዳም

ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444

የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444

3 weeks, 1 day ago

ትራምፕ በአንቶኒዮ ብሊንከን ቦታ ማንን ይሾማሉ?

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የፕሬዝዳንቱ የውጭ ጉዳይ ዋና አማካሪ ሆኖ ያገለግላል። ሚኒስትሩ የፕሬዝዳንቱን የውጭ ጉዳይ ፖሊሲዎች ያከናውናል።

ታዲያ በዚህ ቁልፍ ቦታ አዲስ ተመራጩ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ማንን ይሾማሉ በሚለው ጉዳይ ሚዲያዎች ዘገባዎችን እያወጡ ነው። ተሿሚው ማን ሊሆኑ ይችላሉ? በአፍሪካ ቀንድ የሚኖራቸው ተጽዕኖስ ምን ሊመስል ይችላል?

ዶናልድ ትራምፕ የፍሎሪዳውን ሴናተር ማርኮ ሩቢዮን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አድርገው ይሾማሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ዘገባዎች አመላክተዋል።

ትራምፕ በመጨረሻዎቹ ደቂቃ ሃሳብ ይቀይሩ ካልሆነ በስተቀር አሁን ባለው ሁኔታ ግን ስራውን ለሴናተሩ ሩቢዮ ለማቅረብ እያቀዱ መሆናቸው ታውቋል።

ትራምፕ የሀሳብ ለውጥ ሊያደርጉ ይችላሉ፤ ነገር ግን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቦታን ለሩቢዮ የወሰኑ መሆናቸውን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ነግረውኛል ሲል ዘ ኒው ዮርክ ታይምስ ዘግቧል።

ለሪፐብሊካኖቹ ቅርበት አለው የሚባልለት ፎክስ ኒውስ የተሰኘው ሚዲያም ዘግቦታል። በትራምፕ በኩልም ሆነ በሩቢዮ እስካሁን ማረጋገጫ ሀሳብ አልተሰጠም።

በፈረንጆቹ 2010 ለመጀመሪያ ጊዜ ለሴኔት የተመረጡት ሩቢዮ በኩባ፣ ኢራን እና ቻይና ላይ ባላቸው ጠንካራ አቋም ይታወቃሉ።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን ከትራምፕ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ጋር በመስማማት ተመራጩ ፕሬዝዳንት የሩስያ - ዩክሬን ጦርነት እንዲያበቃ ያቀረቡትን ጥሪ በማስተጋባት “መደምደሚያ ላይ መድረስ አለበት” የሚል አቋም ሲያንጸባርቁ ተስተውለዋል።

የማርኮ ሩቢዮ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር መሆን ለአፍሪካ ቀንድም ጠቃሚ ሊሆን እንደሚችል ተገምቷል። ሩቢዮ ስለ ቀጣናው ጠንቅቀው የሚያውቁ መሆናቸው ይነገራል።
@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news

We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 2 months, 1 week ago

Last updated 6 days, 22 hours ago

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ ? @Esat_tv_comment_bot

??ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ??

Last updated 2 months, 3 weeks ago