Sharp Swords // ስለታማ ሰይፎች

Description
↪️ አግራሞቴን በብዕር

የእይታን አድማስ የሚያሰፉበት፣
➝የጥሩነት ጥሩነት የሚያውቁበት፣
➝የመጥፎነትን መጥፎነት የሚያውቁበት፣
➝ለነገሮች ያሎትን ምልከታ የሚያሳድግ።
➝ደግነትን የሚዘክሩ፤ ክፋትን የሚያወግዙ ብሎም የሚጠሉ።
➝አንዳንዴ ደስታ፤ አንዳንዴ ደግሞ ሀዘን የሚቦርቅበት።
●የተደበላለቁ ስሜቶችን ባማረ የስነ-ፅሑፍ ዘይቤ የሚቀርብበት የናተው መድረክ!

በናተው ወንድም:- በረሻድ ሙዘሚል
Advertising
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 1 day, 23 hours ago

Last updated 3 days, 5 hours ago

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated 2 weeks, 1 day ago

1 month ago
Sharp Swords // ስለታማ ሰይፎች
1 month ago
Sharp Swords // ስለታማ ሰይፎች
1 month ago
Sharp Swords // ስለታማ ሰይፎች
4 months ago

⚙️ የሚጠልቅ ፀሐይ ☀️

ብዙ ጊዜ እኛ የሰው ልጆች ብዙዎቻችን ማለት በሚቻል ሁኔታ አንድ ነገር ከተከናወነ ወይም ከተከሰተ በኋላ ስንጨነቅና ስንጠበብ ይታያል።

ውስጣችን ላይ ብዙ ጥያቄዎች ይመላለሳሉ።
➘ ለነዚህ ጥያቄዎች ለአንዳዶቻቸው መልስ ሲኖራቸው ለአንዳዶቻቸው መልስ ሳይኖራቸው እንዲሁም ደግሞ አንዳዶቻቸውን ጭራሹንም የማንረዳበት ሁኔታ ሊፈጠር ይችላል ይፈጠራልም ጭምር።

ውስጣችን ላይ ከሚመላለሱት ጥያቄዎች ውስጥ መልሳቸውን ያወቅናቸው ቢሆን እኳን በድጋሚ ራሳችንን ከመጠየቅ አንቆጠብም።
“እንዲህ ለምን ሆነ”፣
“እንዲህ የሆነው በዚህ ምክንያት ነው”፣
“እንዲህ ቢሆን ኖሮ ለኔ የተሻለ ነበር”፣
“እንዲህ የተከሰተው በነ እገሌ ክፉነት ነው”፣
“ከነ እገሌ ርቄ እነ እገሌን ቀርቤ ቢሆን ኖሮ አኔ ላይ እንደዚህ አይነት በደል አይፈፀምብኝም ነበር” እያለን “በቢሆን ኖሮ” ዓለም ራሳችንን ከልለን እንኖራለን።

“ቢሆን ኖሮ” የምትለዋ ሀረግ መርዘኛ ናት፣ እኛን በቢሆን ኖሮ ዓለም ውስጥ እያኖረች ተዋርደን፣ ዝቅ ብለን፣ በቁማችን ሞተን፣ ህልማችንን ቀብረንና ዓላማ ? ቢስ እንድንሆን ታደርገናለች።

➝ ወዳጆቼ ይችህ “ቢሆን ኖሮ” መርፌ ? ናት፤ ሰበብ ሆና ከበሽታ የምታድን መርፌ ሳትሆን በሽተኛ እንድንሆን መምታደርገን ናት‼️
➝ ወንድምና እህቶቼ ይቺህ “ቢሆን ኖሮ” በቅዠት ዓለም ውስጥ እንድንኖር የምታደርገን በቅዠት የተለከፈች በሽታም ናት።
➝ ጓደኞቼ ይችህ “ቢሆን ኖሮ” በህይወት ስንኖር ተስፋ ካለን የፀሐይና የጨረቃ ብርኃን እንዳለ ረስታ በጨለማ ህይወት የምታኖረን ጨለምተኛ አስተሳሰብም ጭምር ናት‼️

➻ አዎ በርግጥ ፀሐይ በሆነ ሰዓት ትጠልቃለች ለዛውም በአይናችን እያየን አየሩ እየጨለመ ነው የምትጠልቀው ከዛም ጨለማ (ምሽት) የሚተካው!
ነገር ግን ወዳጆቼ ይቺህ ፀሐይ እኮ እንደ ፈጣሪ ፍቃድ ነገ ተመልሳ መውጣቷ አይቀሬ ነው።

➽ ታዲያ ለምን እኛ እንቅፋቶች በገጠሙን ሰዓት እቅፋቶችን የህይወታችን የአኗኗር ዘይቤ አንዱ አካል አድርገነው ወደፊት የማንቀጥለው⁉️
➽ ታዲያ ለምን ፀሐይ ተመልሳ መውጣቷ የማይቀር መሆኑን እያወቅን ጨለማውን በትዕግስት ማለፍ የሚያቅተን።

⚙️ እኔ ይህን እያልኩ አደለም እኛ ለይ የሚደርሱ ወይም ሊደርሱ የሚችሉ እንቅፋቸቶ በጣም ቀላል ናቸው፤ እኔ ይህን እያልኩ ነው በፈጣሪ እምነት ኖሮን የምንታገስ ከሆነ የማናልፈውና በድል የማንወጣው ችግር እዚህ ዓለም ላይ ፈጣሪ አልፈጠረም አይፈጥርምም።

እናም እላችኋለሁ .........
● ለሚጠልቀው ፀሐይ አናስብ፤ ድጋሚ ፀሐዩ ሲወጣ ምን ማድረግ እንዳለብን እንወቅ እናስተውል ጭምር።

✍️ በረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል

ለአስተያየት: t.me/ReshadMuzemil

══════════════
??ሉን?*?*? share?**

Join our channel

t.me/Grade9Info

t.me/Grade8Info

t.me/Grade7Info

t.me/Grade5and6Info

t.me/AcademicEducations

t.me/BasicComputer_Skills

4 months, 1 week ago

? ተቃውሞ

ከድጋፍ በላይ ተቃውሞ ለውጥ ለመፍጠር ያግዛል!

ከሚሰጡን ምላሾች ከአውንታዊነት(Positivity) ይልቅ አሉታዊነት (Negativity) እኛ ላይ ትልቅ ለውጥ ያመጣል‼️

➽ ሁሌ ከተጨበጨበልን ጉድለታችንን ላናውቀው እንችላለን በዚህም አልበቃ ብሎ - - - - - 

➝ልክ እንደሆነን ፣
➝ሙሉ እንደሆንን
➝ ጉድለት የሚባል ነገር እንደሌለብን
➝ መሻሻልና መቀየር እንደሌለብን ሊሰማን ይችላል!

ያ ደግሞ አዲስ ነገር ለማወቅና ለመጨመር አንጓጓም፤ በአንድ መስመር ላይ ብቻ እንሄዳለን!!!

➽ ይሄኔም ልባችን ላይ ኩራት እያደገ፣ ውስጣችን በእብሪት እየተሞላ፣ አዕምሯችን ውስጥ መጥፎ አመለካከት ስር እየሰደደ ይመጣና በዙሪያችን ላሉ ሰዎች መጨነቅና ማሰብ እናቆማለን።

➝ በዚህም አያበቃም ትላንት የነበረን ማንነት መጥፎ ሆነ ጥሩ ለይተን ሳናውቀው በደፈናው በራሳችን ዓለም ውስጥ እንኖራለን! ይህ ደግሞ ከኛ ውጭ ያለን አመለካከትና ዕይታ ስህተት የኛው አመለካከትና ዕይታ ደግሞ ትክክል መስሎ እንዲታየን ያደርጋል።

ተቃውሞ፣ ትችት፣ እንዲሁም የአስተያየትና የጥያቄ መብዛት ሲከሰት መልስ ለማግኘት ሌላ እይታ ልንመለከት እንችላለን! ያ ደግሞ በእጅጉን ትላንት ላይ በቃን ብለን እንዳንቆምና ዛሬ ላይ ፈርጣማዎች እንድንሆን ያግዘናል!!! ይህ እገዛም በህይወታችን ውስጥ ትልቅ የሆነ ለውጥ ያመጣልናል። ከሰውም ሆነ ከራሳችን በገኘናቸው (በቀሰምናቸው) መልካም አመለካከቶችና ዕይታዎች ራሳችንን ሆነ ሰውን እንቀይርባቸዋለን!!

በዚህም አያበቃም ትላንት ትክክል መስሎ ይታዩን የነበሩ የህይወት መስመሮች ትክክል ወይም ስህተት መሆናቸውን ዛሬ ላይ ለይተን እንድናውቅ ያደርጉልናል‼️

ስለዚህም ይህን እንላለን - - - - -

ከሚሰጡን ምላሾች ከአውንታዊነት(Positivity) ይልቅ አሉታዊነት (Negativity) እኛ ላይ ትልቅ ለውጥ ያመጣል‼️
ከድጋፍ በላይ ተቃውሞ ለውጥ ለመፍጠር ያግዛል‼️

ወቀሳዎች በፍርኃት ሳይሆን ጥንካሬን ይወልዱልንና በስኬት ያጎናፅፉናል‼️

ከተለያዩ ሰዎች የታዘብናቸው ወይም የቀሰምናቸው የተለያዩ ዕይታዎች በርካታ ነገሮችን እንድናስተውልና “ አሃ ” ለካ እንዲህ ነው እንድንል ያስችሉናል‼️

▪️ያኔም ነው ነገሮችን በተረዳንና ባስተዋልን ጊዜ ይቺህ “አሃ” ከኛ ውስጥ የምትወለደው‼️
▪️ ያኔም ነው ያሰመርነው ወይም የተሰመረልን መሥመር እና እየሄድነበት ያለው ወይም ሰዎች ያመላከቱን መንገድ ቀጥተኛ ይሁን ወልጋዳ፤ ትክክል ይሁን ስህተት አበጥረን ማወቅ የምንችለው‼️

*✍️ በረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል*
════════════════

ለአስተያየት: t.me/ReshadMuzemil ??ሉን?*? share?*

Telegram: t.me/SharpSwords1 Tiktok: tiktok.com/@sharpswords1 Ummalife:** ummalife.com/ReshadMuzemil

LinkedIn: linkedin.com/in/reshad-muzemil-139b97320

4 months, 1 week ago

? አግራሞቴን በብዕር

በመኖርህ ውስጥ ስለምትኖርላቸው ሰዎች ውለታ ታስባለህ፤ በአንፃሩ ስለምትኖርላቸው ሰዎች እጣፋንታም ትጨነቃለህ!!

➶ ህይወት ፍቅርን ታስተምርሃለች!!
በልምድ ጉዞህ ውስጥ ሰውን በማንነቱ መምረጥ ትችላለህ፤ ማን መውደድ እንዳለብህ ትገነዘባለህ!!
የተለያዩ ክሰሰተቶች ብዙ ነገር ያስተምሩሃል
እነዛ ክስተቶች ....
እንዳንዴ የተፈጠረው ነገር ምን እንደሆነ እንድታውቅ እድሉን ይሰጡሃል፣
አንዳንድ ጊዜ ግን በብርሃን ፍጥነት ይከሰቱና የተፈጠረው ነገር ምን እንደሆነ ሳታውቅ ትቀራለህ፣
አንዳንድ ጊዜ በደስታ በዓበል ያስዋኙሃል፣
አንዳንዴ ደግሞ በሀዘን ዝም ጭጭ ያስብሉሃል!!

ክስተቶቹም ሲገርሙ.........

◆ ብቻ ግን በነዚህ በተለያዩ ክስተቶች መሀል የእውነት አንተን የሚወድህ ማን እንደነበረም ታውቃለህ። ክስተቶቹ ሰዎችን ያበጥሩልሃል። ምርጫህን ለይ!!

*✍️ በረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል*
════════════════

ለአስተያየት: t.me/ReshadMuzemil ??ሉን?*? share?*

Telegram: t.me/SharpSwords1 Tiktok: tiktok.com/@sharpswords1 Ummalife:** ummalife.com/ReshadMuzemil

LinkedIn: linkedin.com/in/reshad-muzemil-139b97320

4 months, 1 week ago

? መነፅራችንን አውልቀን ከቆሻሻ እንጨምረው!

➤ በአለም ላይ ሁሉም ሰው ነው፤ ቢሆንም ሁሉም የተለየ ማንነትና መታወቂያ አለው‼️

ይህ ማለት ደግሞ:-

● ከኛ የተለየ አመለካካት ያላቸው፣
● ከኛ የተለየ እይታ ያላቸው፣
● ከኛ የተለየ የአኗኗር ዘይቤ ያላቸው፣
● ከኛ የተለየ የፍትህ አሰጣጥ መንገድ ያላቸው፣
● ከኛ የተለየ ውሳኔ ያላቸው፣
● ከኛ የተለየ ሀሳብና አስታየት ያላቸው፣
● ከኛ የተለየ ችሎታ፣ ክህሎት፣ ብቃትና ጥበብ ያላቸው፤ አለም ላይ እጅግ በጣም ብዙ ናቸው!!

ነገር ግን ታዲያ ይህ ማለት አደለም፤ እነሱ ስህተት ናቸው እኛ ደግሞ ትክክል!

ይህ ማለት አደለም፤ የነሱ የእይታ አድማሳቸው የጠበበ የኛ ደግሞ የሰፋ!
▼ ምናልባትም ሁለታችንም ልክ ነን፤ ነገር ግን እርሰ በርስ ስለምንናናቅ ብቻ የአንዳችን ውሳኔ አንዳችን አይመቸንም!
▼ የአንዳችን ፍርድ ሌሎቻችን ላይ ትክክል ያልሆነ መስሎን ፍርደ-ግምድል ይመስለናል!
▼ ጠንከር ያሉ መልካምና ሰናይ ተግባር የሆኑ ስራዎች ራሱ የደካሞች ምልክት ይመስለናል!

◉  ውስጣችንን እልከኝነት፣ አልሸነፍ ባይ ጅልነት፣ ኩራትና ፣ ‟እኔ ብቻ ነኝ አዋቂው” የሚባል «አላዋቂነት» ፣
◉ “እኔ ነኝ የበላዩ” እሱ እንዴት ሀሳብ ሊሰጠኝ ይችላል የሚል የጅሎች አስተሳሰብ፣

◉ ከኔ ስር ያሉ ሰዎች ያሉት ከኔ ስር ነውና የነሱን ሀሳብ አልቀብልም የሚል ‟እብሪት˝ እንደ ወረርሽን እርሰበርስ ተዛምቶብን ጤነኛ የሆኑ አመለካከቶች ራሱ ስህተት ይመስሉናል። መልካምና ከድንቅም በላይ የሆኑ ስራዎች ራሱ ‟የሰይጣን ስራ” መስሎ ይታየናል!

➻ ችግሩ የእይታችን አድማስ ጠቦ፣ የመነፅራችን ቀጡር አንሶ ወደ ዜሮ ተቀይሮ፤ ሌሎች ስራዎችንም በዜሮ እያባዛ ውጤቱንም ዜሮ እያደረገው መሆኑን ሳናስተውል እንቀራለን!
➻ “የበላያቸው” ነኝ የሚለው እብሪታችን ወደታች እየጎተተን መሆኑን ሳንገነዘብ መቁማችን እንሞታለን!

↪️ እንደ ብርኃን ብልጭታ ጥርሳችንን እያሳየን፤ ፈገግ ያልን መስሏቸው እነሱ መሳቅ ሲጀምሩ እናስለቅሳቸዋለን!

↪️ ለጥቅማችን ብለን *ባበራነው ሻማ እነሱ ብርኃን አገኘን፣ ብርኃን ከወዲያ ብልጭ አለ ብለው፤ በብልጭታዋም በታዬቻቸው ልክ ስራ መስራት፣ ያለምንም ምላሽ ሰዎችን ማፍቀር(መውደድና ማክበር)፣ ደካሞችን መርዳት፣ መልካም ትውልድን ማፍራት፣ ማህበረሰብን ማገልገል ሲጀምሩ፤ ያቺንም ትንሿን ብልጭታ መልሰን እናጠፋባቸዋለን!

➻ እኛ መልካም የሆኑ ህልሞችን ማለማችንን ትተን ሌሎችም እንዳያልሙ የመብረቅ ጋጋታ እንሆንባቸዋለን!

➻ ጤነኛ ህልሞችን ማለም ትተን በጤነኞች በሽታ እንሆንባቸዋለን!

➻ ተደጋግፈን፣ ተዋደን፤ በፍቅር አንድ ላይ አብረን የስኬት ማማ ላይ መድረስ ሲገባን፤ ደካማ መስለው የታዩንን ሰዎች ስንወቅስና ስንጨፈልቅ እንከርማለን‼️

➻ ጀልባችን ውኃ ከሌለበት ቦታ እንድትሰምጥ እናረጋታለን!

ከዚህ ሁሉ ግን የሚበጀን.......

⓪‟እኔ ብቻ ነኝ አዋቂው”
⓪“እኔ ነኝ የበላዩ”
⓪ “እኔ ብቻ ነኝ ጠንካራው” ፤፤ ከሚሉ ቢቀነሱ፣ ቢደመሩ፣ ቢካፈሉ፣ ቢባዙ ውጤታቸው ዜሮ(⓪) ከሚሆኑ፤ ‟እብሪቶች˝........

...ደክመንም፣ ብዙ መንገድ ተጉዘን፣ ላባችንን አጠፍጥፈን፣ ጉልበታችንን ጨርሰን የገዛነው ቁጥሩ ዜሮ የሆነ የዕይታ መነፅር ካለ አውልቀን ከቆሻሻ እንጨምረው!! ፤
◉ አረ እንደውም ሌላ ሰው እንዳያገኘው አድርገን ቆፍረን እንቅበረው‼️

*✍️ በረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል*
════════════════

ለአስተያየት: t.me/ReshadMuzemil ??ሉን?*? share?*

Telegram: t.me/SharpSwords1 Tiktok: tiktok.com/@sharpswords1 Ummalife:** ummalife.com/ReshadMuzemil

We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 1 day, 23 hours ago

Last updated 3 days, 5 hours ago

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated 2 weeks, 1 day ago