ኑሮ ለለውጥ

Description
የተሻለ ነገን ዛሬ ላይ እንፍጠር 😊
ሃሳብ አስተያየትዎን @sura7338phel ብለው ያድርሱን
Advertising
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated hace 3 semanas, 5 días

Last updated hace 3 semanas

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated hace 1 mes, 1 semana

2 months, 1 week ago

📍ፔሩሉስ የተባለ ቀራጺ ባለእጅ ነበር። ካላጣው መሣሪያ ሰዎችን የሚጠብስና የሚያቁላላ የመዳብ ኮርማ ተጨንቆና ተጠቦ አበጀ። አገኘሁ ብሎ ፋላሪስ ለተባለ ጨካኝ ግሪካዊ ገዥ "እንሆ በረከት" በማለት ሰጠው። ፋላሪስ ይህን የመዳብ ኮርማ ሲያይ ተገረመ፤ ለአማልክቱ እጅ መንሻ፥ መባ አደረገው። ይህ የመዳብ ኮርማ በሆዱ በኩል ይከፈታል። ሰው በውስጡ ይጠበስበታል። በስተ ጉሮሮው በኩል ደግሞ ሰውዬው እየጮኸ ሲሰቃይ ይህን ድምፅ ወደ ኮርማ ድምፅ የሚቀይር ሽቦ ተበጅቶለታል።

💡ታዲያ ፔሩሉስ ሆዬ የኮርማውን ሆድቃ እየከፈተ "ፋላሪስ ሆይ፥ ያሻህን ሰው በኮርማው ውስጥ ጠርቅምበትና በሥሩ እሳት ልቀቅበት፥ ሰውዬው የሰቆቃ ድምፅ ሲያሰማ አንተ "እምቧ" የሚል የኮርማ ድምፅ ትሰማለህ” አለው። ፋላሪስም ይህን ካደመጠ በኋላ "ቀራፂ እንኪያስ ፔሩሉስ ሆይ፥ ና፥ አንተ መጀመሪያ ግባና አሠራሩን አሳየና" በማለት ግልፅ እንዲያደርግለት ፔሩሉስን በማታለል ወደ መዳቡ ኮርማ ይገባ ዘንድ ግድ አለው። ፔሩሉስ "እኔ ምንተዳዬ፥ ለሚቃጠለው ይብላኝለት" እያለ ጕረሮውን እየጠራረገ ገባ።

♦️ፋላሪስ የፔሩሉስ መሣሪያ አሽሙር ሳይመስለውም አልቀረም። ጨካኝ ሕፃናትን እንኳን ሳይቀር የሚበላ ርህራሄ የሌለው ገዢ ነበርና። ፔሩሉስም እንደ ገባ ይሄው ጨካኝ ገዥ በሥሩ የሚንቀለቀል እሳት ለቀቀበት። በመዳቡ ኮርማ ሆድ ውስጥ ያለው ፔሩሉስ ሆዱ ተላወሰ። ላንቃው እስኪበጠስ የምሩን ጮኸ።

ፋላሪስ "የታባቱንስ ይህ ከብት፤ ጨካኝ ነህ ማለቱም አይደል" እያለ ከዚያ የመዳብ ኮርማ ሩሑ ሳይወጣ አስወጣው። ያስወጣውም አዲሱ መዳብ ከጅምሩ እንዳይጨቀይበት ብሎ ነው። ከዚያም ከገደል አፋፍ አውጥቶ ወረወረው። የፔሩሉስ ዕጣ ፈንታ ይህ ሆነ።

💡በዚህ መሣሪያ የብዙዎች ሕይወት ተቀጠፈ። ጭስስ ብሎ የታቃጠለ ዐጥንታቸውም እንደ አልቦና አንባር ያገለግል ጀመር። የሚገርመኝ ይህ አይደለም። በፋላሪስ ላይ ቴሌማኹስ የተባለ ሌላ ጨቋኝ ገዢ ተነሣበት። እርሱንም ይዞ ከመዳቡ ኮርማ ከተተው፤ አቃጠለውም።

🔑እናም አማካሪ ሆይ፥ ስትመክር ጠንቀቅ ብለህ ምከር። ገዢ ሆይ፥ በጭካኔ መንገድ መሄዱ ይቅርብህ።

ናምሩድ

ማለፊያ የሆነች ማክሰኞ ተመኘን❤️

@selam

2 months, 2 weeks ago

🛑‘የእኔ’ እንደምትለዋ ቃል ጣፋጭ ቃል የለችንም ፣ በየትኛውም ዕለታዊ የንግግር ብፌያችን ላይ የማትቀር ጨው ናት… ሁሉም ውስጥ አለች… ‘የኔ’ የባለቤትነት ማስረገጫም ናት ፣ ቤቱ የእኔ ነው፣ ዛፉ የእኔ ነው፣ ስራው የእኔ ነው፣ ብሩ የእኔ ነው፣ ሰፈሩ የእኔ ነው ፣ ሃገሩ የእኔ ነው፣ እውቀቱ የኔ ነው ፣ ሃሳቡ የኔ ነው…. ሺህ ምንተ ሺህውን ሁላ ጠቅልላ የእኔ /የእኛ የምታሰኝ አግላይ ነፍስያ አለች።

የኔታችን ከፋ ስትል ደግሞ ህይወት ያለውን ሰው እንደ ንብረት አድርጎ እስከማሰብ ይዘልቃል፣ የኔ ነው እሱ/እሷ እያልን እንደፈለግን የምንዘውረው የባለቤትነት ስሜት  አለ።

🔷የኔ ስለምትሉት ነገር በደንብ አስቡ እስኪ ፣ በስማችሁ የተመዘገበ ሃብት፣ እናንተን የሚያስጠራ ንብረት፣ የእርሱ/ሷ የሚባል አንድ ቁስ፣ እናም ያ ነገር የእናንተ የሆነበትን በቂ ምክንያት አስቡ እስኪ፣ ያላችሁበት የስልጣን ወንበር፣ በኑረት ውስጥ የቋጠራችሁት ጥሪት ፣ በላቤ በወዜ ያገኘሁት የምትሉት ወረት ፣ ድንገት ከእጃችሁ የገባ በረከት… ብቻ አንድ የኔነት.........

♦️እውነት ለመናገር  ምንም የላችሁም ፣ ኑረት የመዋጮ ውጤት ነው… እያንዳንዱ ስምረት ብዙ አለሁ ባይነትን ከጎኑ ይዟል። የሰው ልጅ ከእናቱ እቅፍ እስከ ቃሬዛ ሽክፍ ድረስ በመዋጮ ነው የሚጓዘው። ለብቻው መጥቶ፣ ለብቻው ኖሮ፣ ለብቻው የተሻገረ አንድ ስንኳ የለም፣  አለኝ የምትለውን ነገር ከመነሻው ጠገግ እስከ መድረሻው ጥግ ብታጠናው የኔ ያስባለህን አመክንዮ ባዶነት ትረዳለህ ፣ ከእኛ የሆነ አንዳች የለም ፣ በዙሪያችን ካለው ምልዓት ነው እንዳፈተተን የሸከፍነው፣ የእኛ ስለሆነ የተጨመረ ነገር አይደለም፣ ከነበረው ላይ ነው የተቀዳው።

🔷ታዲያ እኛ ዘንድ ስለምን ተጠጋ?… መንገድ ነን እኛ፣ ለሌሎች መድረሻ ቦይ ፣ እኛ ዘንድ ያለው ሌሎች ዘንድ እስኪደርስ ነው። አንባሪዎች ነን ፣ ባላደራ እንደማለት ነው። ከፍም ዝቅም ብሎ እኛን የተጠጋው ለጎደለው በእኛ በኩል እንዲደርስ ነው። እናም… ሃብታም አይደለም ያለው – ብዙ ሰጪ እንጂ፣ ድሃ አይደለም ያለው ጥቂት ሰጪ እንጂ፣ ምንም ሁን ግን የምትሰጠው አለህ ፣ ማንም ሁን የምትቀበለው አለህ፣ አንተ ለኑረት መጻተኛ ነህ ፣ አለቀ።

🔑ያፈራኸው ሃብት፣ ያካበትከው እውቀት፣ የኖርክበት ቀዬ፣ ያለፍክበት መንገድ፣ የታወቅህበት ፈለግ፣ ያቀረብከው ማዕድ፣ የተጠለልከው ታዛ፣ የተሰጠህ ማዕረግ፣ የጨበጥከው ሥልጣን ፣ የሁሉም እጅ አለበት።

💡ዲዮጋን ፈላስፋ ነው..."ምናምኒት የሌለው" ፈላስፋ፣ በዘመኑ የነበሩ ኃያላን መሪዎች ሳይቀሩ ለአማካሪነት የሚፈልጉት፣ የሚያውቁት በተገኘበት ቃሉን ለመስማት የሚሻሙበት፣ ዝናውን ከሩቅ የሰሙ ሀገር አቋርጠው ወንዝ ተሻግረው ሊያደምጡ የሚሹት ድንቅ የዘመኑ ፈላስፋ። ግን ደግሞ ምንም "የሌለው" ዓይነት… 'ንብረት' ከተባሉ ንብረቶቹ ውሻ፣ አንድ ከቀፎ የተሰራ ማደሪያና ውሃ መጠጫ ቅል ናቸው። ቅሉንም አንድ ቀን ወንዝ ሲሻገር፣ አንድ ሌላ ሰው በርከክ ብሎ በእጆቹ ውሃ እየጠለቀ ሲጠጣ ስላየው "ለካስ ቅልም ትርፍ ኖሯል?" ብሎ ጥሎታል...

📍ታላቁ እስክንድር አለምን በሙሉ እየተቆጣጠረ፡ ቆሮንጦስ ሲደርስ፡ እሱን ለማየትና ለማመስገን ሁሉም ሰው ተሰበሰበ፤ ዲዎጋን ግን አልመጣም። ታላቁ እስክንድር ለማየት የፈለገው ግን ዲዎጋንን ነበር። ንጉሱ ከኋላው በጣም ብዙ ሰው አስከትሎ እየሄደ ሳለ አቀበቱ ላይ ተንጋሎ ፀሐይ ሲሞቅ ዲዎጋንን አገኘው።

እስክንድርም ሰላምታ ካቀረበለት በኋላ እንዲህ አለው፦ ”ዲዎጋን!ስላንተ ጥበብ ብዙ ሰምቻለሁ። የማደርግልህ ነገር ይኖራል?“
”አዎ“ አለ ዲዎጋን ” ጸሀይዋን ስለጋረድከኝ ወደ ጎን ዞር በልልኝ“ አለው። ለሰማይና ለምድሩ የከበደውን ታላቁን ንጉስ በንቀት ስለተናገረ ብለው የእስክንድር ወታደሮች ሊቆራርጡት  ሰይፋቸውን ሲመዙ እስክንድር ግን "ተውት አትንኩት እኔ እስክንድርን ባልሆን ኖሮ ዲዎጋንን መሆን እመርጥ ነበር" አላቸው።

🔷ሕይወት ከቁሳዊው ዓለም ጀርባ ካረገዘችው ትክክለኛው እኔነት ውስጥ ካልሆነ በቀር ከውልደት እስከ ሥጋ ሞት በተዘረጋው አፍታ ውስጥ የምታጋብሰው ንብረት አልያም ስልጣን ያንተ አይደለም። ያንተ የሆነው የማይጠፋው ነው። ከኑረት ፈለግ ላይ የሥጋ ሞት ሲነጥልህ አብሮ የማይነጠለው፣ የመንፈስ ከፍታህ፣ የነፍስ ልዕልናህ ነው፣ ይህ ሃብት ሌባ ሲዘርፈው አልታየም፣ ብልና ዝገት ሲበላው አልታየም፣ እሳትና ጎርፍ ሲያወድመው አልታየም፣ የመድኅን ዋስትናም አይፈልግም፣ እውነተኛ ሃብትህ እርሱ ብቻ ነው፣ ሌላው ሁሉ ትርፍ ነው።

♦️ምንም ነገር ይኑርህ ምንም ነው… ልክ እንደ ቅዠት፣ አሁን ላይ ቁም ፣ ምንድነው ያለህ? እጅህ ላይ ያለው ከትናንት ያደረና በየትኛውም ቅጽበት ሊጠፋ የሚችል ነው።በነግ ተስፋህ ላይ የተንጠለጠለው ስለመምጣቱ የማታውቀው ምኞት ነው… አሁን ምንድነው ያለህ?… ምንም… አንተ ብቻ ነህ ያለኸው፣ ከእጅህ ያለውን ግን የኔ ነው እንዳልከው አጥተኸዋል፣ ቋሚ አይደለምና። **መልሰህ የምትሰጠውን ከእጅህ ታቆያለህና አንተ ባለጸጋ ነህ!!

ደምስ ሰይፉ**

@selam

2 months, 2 weeks ago
SEED !

SEED !

Seed እንደሚታወቀው በ Binance list የመሆን እድሉ 100% ያለቀ ይመስላል ምክኒያቱም Binance lab invest እንዳደረገበት አብዛኛው የ Crypto ዙሪያ ዜናዎች ዘግበውታል

SEED ምንድነው?

- Seed ከ Web3 ፕሮጀክት ጋር የተቆራኘ Gaming እና Social interaction ፕሮጀክት ነው. Airdrop በመሆን በገነባው ፕሮጀክት መሰረት በ November 2024 ለ ተጠቃሚዎች Token ይሰጣል

- Seed Total supply cap 20 ሚልየን ነው, ይህም ፋርም ስታደርጉ ብዙ ቁጥር ለመስራት ትቸገራላችሁ ነገር ግን Active መሆን ከቻላችሁ ጥሩ እድል ነው, በተለይ Bird hunt አድርጎ እዛው ላይ መሸጥ ብዙ ነጥብ እንድትሰበስቡ ያደርጋል

Snapshot እና listing በኖቬምበር መጨረሻ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል

ለመጀመር 👉 t.me/seed_coin_bot/app?startapp=304572310

2 years, 1 month ago
2 years, 11 months ago

ህይወታችንን ቆም ብለን እንመልከት ... የቱ ጋር ነን?
አለም ሲኒማ
ከ 2:30 - 6:30
ቦታ ለማስያዝ
@always4n4b29
ይጠቀሙ

We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated hace 3 semanas, 5 días

Last updated hace 3 semanas

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated hace 1 mes, 1 semana