Dive into the Ultimate Free Library: Your One-Stop Hub for Entertainment!

Janderebaw Media

Description
የኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ትውልድ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በጠቅላይ ቤተ ክህነት የማኅበራት ማደራጃ መምሪያ ዕውቅና የተሰጠው መንፈሳዊ ማኅበር ነው::

የሚከለክለኝ ምንድን ነው?
Advertising
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated hace 1 día, 17 horas

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated hace 5 días, 6 horas

Last updated hace 5 días, 19 horas

1 month, 1 week ago
የጽሙና ጊዜ አለህ?

የጽሙና ጊዜ አለህ?

| ጃንደረባው ሚድያ | መጋቢት 2016 ዓ.ም.|

✍🏽 ዲያቆን አቤል ካሣሁን እንደ ጻፈው

በጸሎት ጊዜ ሐሳቡ እየተበተነበት የተቸገር አንድ ደቀ መዝሙር ወደ አረጋዊ አባት ሄዶ ስለሆነው ነገር ይነግራቸዋል። እኛም አረጋዊ ልጁን በምሳሌ ሊያስተምሩት ስለ ፈለጉ ከፊቱ ውኃ አመጡ። ከዚያም በውኃው ላይ ጠጠር በመወርወር ልክ የሚርገበገብ ሞገድ ሲፈጠር ያን ደቀ መዝሙር ፊቱን በውኃው ውስጥ እንዲያይ ጠየቁት። ተማሪውም በውኃው ውስጥ ጥላ የሚመስል ነገር እንጂ መልኩን ማየት እንዳልቻለ ነገራቸው። ቀጥለውም አረጋዊው ውኃው እስኪረጋጋ ጠብቀው "አሁንም መልሰህ ተመልከት?" አሉት። አየ፤ "አሁን ልክ እንደ መስታወት ውኃው ፊቴን እያሳየኝ ነው" አላቸው። አረጋዊውም "ልጄ ሆይ፣ አንተም እንዲሁ ሂድና ራስህን አረጋጋ። ያን ጊዜ በጸሎትህ ውስጥ መጽናናትን ታገኛለህ" አሉት። (Paradise of the holy fathers)

ሙሉውን ያንብቡ

1 month, 1 week ago
እንዳላነብ የሚከለክለኝ ምንድን ነው?

እንዳላነብ የሚከለክለኝ ምንድን ነው?

1 month, 1 week ago

ይህንን checklist ይጠቀሙ

1 month, 1 week ago
እንዳላነብ የሚከለክለኝ ምንድን ነው?

እንዳላነብ የሚከለክለኝ ምንድን ነው?

1 month, 2 weeks ago
ነገረ አእዋፍ

ነገረ አእዋፍ

| ጃንደረባው ሚድያ | መጋቢት 2016 ዓ.ም.|

✍🏽 ቀሲስ ታምራት ውቤ እንደጻፉት

መጽሐፈ ዘፍጥረት የአምስተኛውን ቀን ፍጥረታት ሲተርክ “እግዚአብሔርም አለ፡- ውኃ ሕያው ነፍስ ያላቸውን ተንቀሳቃሾች ታስገኝ፤ ወፎችም ከምድር በላይ ከሰማይ ጠፈርም በታች ይብረሩ” በማለት ይጀምራል፡፡ ዘፍ 1፡20 አእዋፍ ጌታ እግዚአብሔር ከውኃ ከፈጠራቸው መካከል ናቸው፡፡ ከውኃ ተፈጥረው የተሰጣቸው ተፈጥሯዊ ጸጋ ደግሞ “ከምድር በላይ” እንዲበርሩ ነው፡፡ በዚህ የዘፍጥረት ተረክ ውስጥ ጌታ እግዚአብሔር ስለ እኛ ሕይወት ምን ታላቅ ምሥጢር ሊነግረን እንደ ወደደ ለማየት እንሞክራለን፡፡

ከምድር መጥቀው እንዲበርሩ የተፈጠሩት አእዋፍ የተገኙ ከውኃ መሆኑ፤ ውኃ የጥምቀት ከውኃ የተገኙትም የጥሙቃን (የክርስቲያኖች) ምሳሌ ናቸው ይሉናል አበው፡፡ ጌታችን ስለ ምሥጢረ ጥምቀት ለኒቆዲሞስ ሲነግረው “ከሥጋ ተወለደ ሥጋ ነው፤ ከመንፈስም የተወለደ መንፈስ ነው፡፡ ዳግመኛ ልትወለዱ ያስፈልጋችኋል ስላልሁህ አታድንቅ፡፡ ነፋስ ወደሚወደው ይነፍሳል፤ ድምጹንም ትሰማለህ፤ ነገር ግን ከወዴት እንደ መጣ ወዴትም እንዲሄድ አታውቅም፤ ከመንፈስ የተወለደ ሁሉ እንዲሁ ነው” ብሎታል፤ ምሥጢሩን ለጊዜው ሊረዳው ባይችልም፡፡ ዮሐ 3፡6-8 ከመንፈስ የተወለዱ ሁሉ በምን ደረጃ ሊኖሩ በአዲስ ተፈጥሮ ከውኃና(በሚታይ) ከመንፈስ እንደ ተወለዱ አበሠረን፡፡

ሙሉውን ያንብቡ

1 month, 2 weeks ago
ነጻ የሚያወጣ ፍቅር

ነጻ የሚያወጣ ፍቅር

|ጃንደረባው ሚድያ | መጋቢት 2016 ዓ.ም.|

✍🏽 ዮርዳኖስ ዘሪሁን እንደጻፈው

ንፁህ እና እውነተኛ ፍቅር ለምንወደው ሰው ያለ ምንም ገደብ ታላቅ ነፃነትንና ሰላምን ይሰጣል። ይህም ሰላም እና ነፃነት የሚፈጠረው ከምንም በላይ አብልጠን የምንወደው ሰው ከቶ በኛ ቁጥጥር ውስጥ እንዲሆን ባለመፍቀዳችን ነው። ማለትም አንድን የምንወዳትን ወፍ በማሰርያ ውስጥ አስረናት የኛ እንድትሆን ከማድረግ ይልቅ እንደልቧ እንድትበር ፈቅደን ነገር ግን ቤት አዘጋጅተንላት በነጻነት በራሷ ፍላጎት ተመልሳ ወደሰራንላት ቤት እንድትመጣ ነፃነትን መስጠት እንደማለት ነው።

ሙሉውን ያንብቡ

1 month, 2 weeks ago
እንዳላነብ የሚከለክለኝ ምንድን ነው?

እንዳላነብ የሚከለክለኝ ምንድን ነው?

1 month, 3 weeks ago
ኑሮን ስለ ማቅለል

ኑሮን ስለ ማቅለል

| ጃንደረባው ሚድያ | መጋቢት 2016 ዓ.ም.|

✍🏽 ቀሲስ ታምራት ውቤ

"ሰው ለምቾትና ለተቀማጠለ ሕይወት ራሱን አሳልፎ ሲሰጥ ለንስሓ ያለው ቁርጠኝነት ይቀንሳል፡፡ ''
(ፍና ቅዱሳን - ገጽ 51)

ብዙ ጊዜ በምቾት የተቀማጠለ ሕይወትን እና ኑሮን ቀለል ባለ (በዘመናዊ ዘይቤ) መኖር የሚሉትን ሃሳቦች ቀላቅለን እናያቸዋለን ፡፡ ነገር ግን ሁለቱ ሃሳቦች የሚለያዩ ይመስለኛል፡፡ ስለሆነም እኛ እየኖርን ያለነው (ለመኖር የምንጥረው) የትኛውን ዓይነት ኑሮ ነው? በአካል፣ በነፍስና በአስተሳሰብ መኖር የሚገባንስ እንዴት ነው?

መልስ፦ ሰው ለምቾትና ለተቀማጠለ ሕይወት ራሱን አሳልፎ ሲሰጥ ለንስሓ ያለው ቁርጠኝነት ይቀንሳል? እውነት ወይም ሐሰት መሆኑን ለማወቅ ሩቅ መሔድ አይጠበቅብንም ራሳችንን ማየት እንጂ። አበው "ዝናም ዘነበ ቢለው፥ በየደጅህ እየው" እንዲሉ በየራሳችን ሕይወት ስናየው እውነት ነው ምቾትና የተቀማጠለ ሕይወት ምን ያህል ለንስሐ ልምሾ እንደሚያደርገን ማየት እንችላለን።

ሙሉውን ያንብቡ

1 month, 3 weeks ago
Janderebaw Media
2 months ago
የዐቢይ ጾም ቅበላ ድግስ

የዐቢይ ጾም ቅበላ ድግስ
የካቲት 24-2016 ዓ.ም - ቀጥታ ስርጭት

https://www.youtube.com/watch?v=bgTDNyZ1Y2U

We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated hace 1 día, 17 horas

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated hace 5 días, 6 horas

Last updated hace 5 días, 19 horas