Janderebaw Media

Description
የኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ትውልድ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በጠቅላይ ቤተ ክህነት የማኅበራት ማደራጃ መምሪያ ዕውቅና የተሰጠው መንፈሳዊ ማኅበር ነው::

የሚከለክለኝ ምንድን ነው?
Advertising
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 2 months, 1 week ago

Last updated 6 days, 22 hours ago

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ ? @Esat_tv_comment_bot

??ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ??

Last updated 2 months, 3 weeks ago

3 days, 4 hours ago
Janderebaw Media
3 days, 4 hours ago
Janderebaw Media
3 days, 4 hours ago
Janderebaw Media
1 week, 2 days ago
በጃን ማዕተብ የተሰናዳውን "ወደ ኦርቶዶክስ መመለስ" …

በጃን ማዕተብ የተሰናዳውን "ወደ ኦርቶዶክስ መመለስ" የተሰኘውን ዘጋቢ ፊልም በጃንደረባው ሚድያ አሁን መመልከት ይችላሉ:: ኦርቶዶክስ ማለት ርትዕት የቀናች ማለት እንደመሆኑ ወደ ኦርቶዶክስ መመለስ ማለት "ወደ ርትዕት ሃይማኖት መመለስ" ማለት ነው::

በዚህ ዘለግ ያለ ፊልም ላይ ወደ እናት ቤተ ክርስቲያን የተመለሱ ልጆች "ለምን ሔዱ? ለምን መጡ? እንዴት እንመናቸው?" የሚሉ አንገብጋቢ ጥያቄዎችና በአጠቃላይ ተቅዋማዊ ዕቅበተ እምነት ላይ ዝርዝር መረጃዎች ቀርበዋል:: ስለ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን አገልግሎት የምትጨነቁ የሚመለሱ ሰዎችም አመላለሳቸው ምን መምሰል እንዳለበት የሚገዳችሁ ሁሉ ይህንን ዘለግ ያለ ዘጋቢ ፊልም በትዕግሥት ተመልከቱ::

https://youtu.be/HqyhPq_Jf-g

1 week, 2 days ago
+ 70 ነፍሳት ወደ ቤተ ክርስቲያን …
  • 70 ነፍሳት ወደ ቤተ ክርስቲያን ተጨመሩ +

| ጃንደረባው ሚድያ | ኅዳር 2017 ዓ.ም.|
አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ

በኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ትውልድ - ጃን ማዕተብ በኩል 70 ወጣቶች ወደ ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን በልጅነት ጥምቀትና በቄደር ጥምቀት ተመለሱ::
ጃን ማዕተብ ሥራ ከጀመረ ጊዜ አንሥቶ በአንድ ለአንድ (የገፅ ለገፅ) የትምህርት መንገድ የተማሩት እነዚህ ንዑሰ ክርስቲያን ከእስልምና ከፕሮቴስታንት ከካቶሊክ እና እምነት የለሽነት የተመለሱ መሆናቸውን የጃን ማዕተብ የንዑሰ ክርስቲያን ክትትል አስተባባሪ ዶ/ር ቤተልሔም ገልጻለች::

"በወላጆቻቸው ፣ በትዳር አጋሮቻቸውና በወዳጆቻቸው ጥቆማ ወደ እኛ የሚመጡትን ወጣቶች በመጀመሪያ ያሉበትን የግንዛቤ ደረጃ የመመዘኛ ቃለ መጠይቅ ካደረግንላቸው በኋላ በየርእሰ ጉዳዩ በጠነቀቁ (specialize ባደረጉ) መምህራን አንድ ለአንድ እንዲማሩ በማድረግ መምህረ ንስሓ በማገናኘት እስከጥምቀት ድረስ የማብቃትና የመከታተል ሥራዎችን ስንሠራ ቆይተናል" ያሉት የጃን ማዕተብ ሰብሳቢ ዲ/ን እርሱባለው ኩምሳ "ከተጠመቁት መካከል በሚገባ ተምረው በንዑሰ ክርስቲያን አገልግሎት ላይ ከእኛ ጋር ማገልገል የጀመሩም አሉ" በማለት ገልጸዋል::

ወደ ቤተ ክርስቲያን ማኅበር የተቀላቀሉት ወጣቶች መካከል በሔዱባቸው ቦታዎች እስከ ሰባኪነት የደረሱና አንዳንዶቹም "የተሐድሶ" ሥልጠና ሠጪዎች የነበሩም እንዳሉበትና ለወራት በአንድ ለአንድ ትምህርትና ሱባኤ ጉባኤ በመማር ላይ እንደሚገኙ ተገልጾአል:: ከእነዚህም መካከል አስቀድሞ በዘማሪነት ሲያገለግል የነበረውና ወደ ተሐድሶ ተወስዶ የነበረው ዘማሪ ሐዋዝም ላለፉት ስምንት ወራት በጃን ማዕተብ ሲማር ቆይቶ በይፋ ወደ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በቄደር ጥምቀት ተመልሶ ለአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ይፋዊ የይቅርታ ደብዳቤውን አቅርቦአል::

ጃን ማዕተብ በብዙ ድካም የሠራውን የፕሮጀክት ምክረ ሃብ በመተግበርም በቀጣይ ጉዳይ ተኮር የሆኑ የዕቅበተ እምነት ጉባኤያትና ዐውደ ጥናቶችን በማዘገጀት ሒደት ላይ መሆኑን የገለጸው ዲ/ን እርሱባለው "ተቅዋማዊ ዕቅበተ እምነት" ላይ ማተኮርና የንዑሰ ክርስቲያን የመግቢያ ትምህርት ዶክመንት የማዘጋጀት ሥራዎችም እየተሠሩ መሆኑን ገልጾአል::

በጃን ማዕተብ የተሰናዳው "ወደ ኦርቶዶክስ (ወደ ቀናችው ሃይማኖት) መመለስ" የተሰኘ ዕቅበተ እምነታዊ ዘጋቢ ፊልም ዛሬ ማታ በጃንደረባው ሚድያ ቻናል ይለቀቃል::

#የሚከለክለኝ_ምንድን_ነው
#በፍጹም_ልብህ_ብታምን_ተፈቅዶአል
#ወደ_ኦርቶዶክስ_እንዳልመለስ_የሚከለክለኝ_ምንድን_ነው

1 week, 3 days ago
Janderebaw Media
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 2 months, 1 week ago

Last updated 6 days, 22 hours ago

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ ? @Esat_tv_comment_bot

??ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ??

Last updated 2 months, 3 weeks ago