Unlock a World of Free Content: Books, Music, Videos & More Await!

YeneTube

Description
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Advertising
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated hace 1 día, 17 horas

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated hace 5 días, 6 horas

Last updated hace 5 días, 19 horas

3 weeks, 2 days ago

የኦነግ የፖለቲካ ኦፊሰር አቶ በቴ ኡርጌሳ ተገድለው፤ አስክሬናቸው ተጥሎ ተገኘ!

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) የፖለቲካ ኦፊሰር አቶ በቴ ኡርጌሳ የትውልድ ከተማቸው በሆነችው መቂ ከተማ ተገድለው አስክሬናቸው ተጥሎ ተገኘ።ለደኅንነታቸው ሲባል ስማቸውን የማንገልጸው የአቶ በቴ ኡርጌሳ የቅርብ ጓደኛ ለቢቢሲ እንደተናገሩት አቶ በቴ በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን በምትገኘው መቂ ከተማ የተገደሉት ትናንት ሰኞ ሚያዚያ 1/2016 ዓ.ም. እኩለ ለሊት ላይ ነው።

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ፓርቲ የፖለቲካ ኦፊሰሩን ግድያን በተመለከተ እስካሁን ያለው ነገር ባይኖርም የፓርቲው የሕዝብ ግንኑነት ኃላፊ አቶ ለሚ ገመቹ በፌስቡክ ገጻቸው ላይ “በቴ የሆነውን ማመን አቅቶኛል” ሲሉ ጽፈዋል።አቶ በቴ የካቲት አጋማሽ ላይ በቁጥጥር ስር ውለው ለሁለት ሳምንታት ያህል በእስር ከቆዩ በኋላ በ100 ሺህ ብር የገንዘብ ዋስትና የተለቀቁት ከአንድ ወር ገደማ በፊት የካቲት 30/2016 ዓ.ም. ነበር።

ቢቢሲ ያነጋገራቸው የፖለቲከኛው የቅርብ ጓደኛ እንደሚሉት፤ አቶ በቴ በመቂ ከተማ አርፈው ከነበረበት የሆቴል ክፍል ውስጥ ተይዘው እንዲወጡ ከተደረጉ በኋላ ተገድለው አስክሬናቸው መንገድ ላይ ተጥሎ ተገኝቷል።በአቶ በቴ ኡርጌሳ ላይ ግድያን ማን እንደፈጸመው እንደማያውቁ የገለጹት ይህ ግለሰብ፤ በአሁኑ ወቅት በመቂ ከተማ የቴሌኮም አገልግሎት በመቋረጡ ተጨማሪ መረጃ ማግኘት አዳጋች እንደሆነባቸው ጨምረው ተናግረዋል።

አቶ በቴ በፖለቲካ ተሳትፏቸው ምክንያት በተደጋጋሚ ለእስር ሲዳረጉ የቆኡ ፖለቲከኛ ሲሆኑ ከጥቂት ሳምንታት በፊትም ከአንድ ፈረንሳይዊ ጋዜጠኛ ጋር በአዲስ አበባ በቁጥጥር ስር ውለው ነበር።አቶ በቴ ኡርጌሳ ሐሙስ የካቲት 14/2016 ዓ.ም ከፈረንሳዊው ጋዜጠኛ አንቷን ጋሊንዶ ጋር በአዲስ አበባ ስካይ ላይት ሆቴል ቁጭ ብለው እየተነጋገሩ ሳለ በቁጥጥር ስር ውለው ከሁለት ሳምንታት እስር በኋላ ተለቀዋል።

በወቅቱ መንግሥት የ“አፍሪካ ኢንተለጀንስ” ጋዜጠኛው እና የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) የፖለቲካ ኦፊሰር በቁጥጥር ስር የዋሉት “ከፋኖ እና ኦነግ ሸኔ ጋር በመተባባር ሁከት እና ብጥብጥ ለማስነሳት በመንቀሳቀሳቸው ነው” ብሎ ነበር።በኦሮሞ የተቃውሞ ፖለቲካ ውስጥ ጉልህ እንቅስቃሴ በማድረግ የሚታወቁት እና በፓርቲያቸው ውስጥ ተጽእኖ ፈጣሪ የሆኑት አቶ በቴ ከዚህ ከቀደምም ለተደጋጋሚ እስር ሲዳረጉ ቆይተዋል።

Via BBC
@YeneTube @FikerAssefa

3 weeks, 2 days ago
YeneTube
3 weeks, 2 days ago

በዓለም ገበያ የነዳጅ ዋጋ በከፍተኛ መጠን ናረ!

ለጋዛው ጦርነት ከተኩስ አቁም ስምምነት ለመድረስ፣ በእስራኤል እና በሃማስ መካከል ሲካሄድ የነበረው ድርድር ያሳደረው ተስፋ መመናመን እና ሜክሲኮ ለዓለም ገበያ በምታቀርበው ድፍድፍ የነዳጅ ዘይት መጠን ላይ ተጨማሪ ቅነሳ ለማድረግ የያዘችውን እቅድ ተከትሎ በዛሬው ዕለት የዓለም የነዳጅ ዋጋ መናሩ ተዘግቧል።

ትናንት ሰኞ ካይሮ ላይ የተካሄደውን አዲስ ዙር የተኩስ አቁም ድርድር ተከትሎ በዓለም ገበያ የነዳጅ ዋጋ የማሽቆልቆል አዝማሚያ ማሳየት ቢጀምርም፤ የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚንስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ፣ ጦራቸው በጋዛዋ የራፋህ ግዛት ጥቃት የሚፈከፍትበት ‘ቀን ተቆርጧል’ ካሉ በኋላ፣ የአካባቢው ውጥረት ‘ይረግባል’ በሚል አሳድሮት የነበረውን ተስፋ እያመከነ መሆኑን ተንታኞች ተናግረዋል።

የግጭቱ አለማብቃት ሌሎች አገሮችንም ወደ ጦርነት እንዳይስብ፤ በተለይም ደግሞ ዋናዋ የሃማስ ደጋፊ እና በዓለሙ የነዳጅ አምራች አገሮች ድርጅት፣ ለዓለም ገበያ በሚቀርበው የነዳጅ መጠን በሦስተኛ ደረጃ ላይ የምትገኘውን ኢራንን ወደ ጦርነቱ እንዳያስገባ ያሳደረው ሥጋት እንዲቀጥል ማድረጉ ተዘግቧል።

በተጨማሪም የሜክስኮው መንግስታዊ የነዳጅ ኩባንያ ‘ፔሜክስ’ በቀኑ ለዓለም ገበያ ከሚያቀርበው 330ሺሕ በርሜል መጠን ያለው ነዳጅ በመቀነስ ተጨማሪ ነዳጅ ለአገር ውስጥ ማጣሪያዎች ለማቅረብ የያዘው ዕቅድ አሳሳቢውን ሁኔታ ይበልጥ እንዳባባሰውም ተመልክቷል። ውሳኔውም ኩባንያው ለዩናይትድ ስቴትስ፣ ለአውሮፓ እና ለእስያ ተቀባዮቹ ያቀርብ የነበረውን ድፍድፍ የነዳጅ ዘይት መጠን በአንድ ሶስተኛ ይቀንሰዋል ተብሏል።ፔሜክስ አዲሱን ውሳኔውን ይፋ ከማድረጉ አስቀድሞም በያዝነው የሚያዝያ ወር ውስጥ በየቀኑ ከሚያቀርበው የነዳጅ ዘይት መጠን በ436ሺሕ በርሜል ቀንሶ ነበር።

Via VoA
@YeneTube @FikerAssefa

1 month ago
**በመሬት አገልግሎት ላይ ተጥሎ የነበረው እግድ …

በመሬት አገልግሎት ላይ ተጥሎ የነበረው እግድ ተነሳ!

ላለፉት ሦስት ወራት እግድ ተጥሎበት የነበረው የመሬት አገልግሎት ካለፈው ሰኞ መጋቢት 23 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ መነሳቱ ተገለጸ።

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በተጠናው የመዋቅር ጥናት መሠረት የሰራተኞች ድልድል ተካሂዶ ምደባ እስከሚካሄድ ድረስ ከጥር  21 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ላለፉት ሦስት ወራት ታግዶ የቆየው የመሬት አገልግሎት፣ የዜጎችን መብት የጣሰ እንደነበር በመናገር  ተገልጋዮች ሲያማርሩ ቆይተዋል።

አስተዳደሩ እንደገለጸው አጠቃላይ የሰራተኛ ድልድሉ በመጠናቀቁ ከቀን ከመጋቢት 23 ቀን2016 ዓ.ም ጀምሮ የመሬት አገልግሎት የተጀመረ መሆኑን አስታውቋል።

Via Reporter
@YeneTube @FikerAssefa

1 month ago
የዓለማቀፉ ገንዘብ ድርጅት (አይ ኤም ኤፍ) …

የዓለማቀፉ ገንዘብ ድርጅት (አይ ኤም ኤፍ) ልዑካን ቡድን ከኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣናት ጋር ባደረገው ውይይት የመንግሥትን አገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ መርሃ ግብር መደገፍ በሚቻልበት ኹኔታ ዙሪያ ብዙ እድገት መታየቱን ገልጧል።

ውይይቱ፣ ዓለማቀፉ የገንዘብ ድርጅት እና ዓለም ባንክ በቀጣዩ ወር መጨረሻ ገደማ በሚያደርጉት ስብሰባ ላይ እንደሚቀጥል ቡድኑ ትናንት ሌሊት ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። የድርጅቱ ልዑካን ቡድን በአዲስ አበባ ከመጋቢት 10 እስከ መጋቢት 24 /2016 ቆይታ ማድረጉን ገልጧል። አበዳሪ አገራት የኢትዮጵያ መንግሥት እስካለፈው የፈረንጆች ወር መጨረሻ ከድርጅቱ ጋር የብድር ስምምነት ላይ ካልደረሰ፣ ለአገሪቱ እስከ ቀጣዩ የፈረንጆች ዓመት ያራዘሙትን የብድር መክፈያ ጊዜ እንደሚሰርዙ እስጠንቅቀው ነበር። መንግሥት ከድርጅቱ የጠየቀው ብድር 3 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር ነው።

[ዋዜማ]
@YeneTube @FikerAssefa

1 month ago
**ከ8ሺህ በላይ የሆኑ የብልፅግና ፓርቲ አባላት …

ከ8ሺህ በላይ የሆኑ የብልፅግና ፓርቲ አባላት ተባረዋል ተባለ፡፡
በዘንድሮው የበጀት ዓመት በስድስት ወር የስራ አፈፃፀም ላይ በተደረገ ግምገማ ከ8 ሺህ በላይ የብልፅግና ፓርቲ አባላት ላይ እርምጃ መወሰዱን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ገልጸዋል፡፡ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ይህን የገለፁት በትላንትናው ዕለት ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር በነበራቸው ቆይታ ፤ከፓርቲዎች በብልሹ አሰራር ዙሪያ ለተነሳላቸው ጥያቄ ምላሽ በሰጡበት ወቅት ነው፡፡

ከ8 ሺህ በላይ የሚሆኑት የብልፅግና ፓርቲ አባላት እንደ ስራቸው አስተዳደራዊ እርምጃ ከመውሰድ በተጨማሪ እስከ ማባረር የደሰረ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡መጋቢት 2015 ዓ.ም ፓርቲው ባካሄደው ጉባዔ ላይ የፓርቲው ፕሬዝዳንት ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ፤ ፓርቲው በኢትዮጵያ ታሪክ ከዚህ በፊት ከነበሩ ፓርቲዎችና ድርጅቶች በቁጥርም፥ በአደረጃጀትም፥ በሀሳብም የተለየ ፓርቲ መሆኑንም መግለጻቸው የሚታወስ ነው፡፡

በወቅቱ ፓርቲው በመላው ሀገሪቱ ከ11 ሚሊየን በላይ አባላት እንዳው በመግለፅ፤ ሁሉም ብሄሮች በሚገባቸው ልክ የተወከሉበት ፓርቲ መሆኑንም አስታውቀዋል።ገዢው ፓርቲ ብልፅግና ባለስልጣናት መካከል የክህሎት፣ የመቀራረብና የአስተሳሰብ አንድነት ያመጣል የተባለ ስልጠናና ውይይት በሁሉም ክልሎች ማካሄዱ የሚታወስ ነው፡፡

Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa

3 months ago
**አሜሪካ ለተገደሉባት ወታደሮቿ በቀል ሶሪያ እና …

አሜሪካ ለተገደሉባት ወታደሮቿ በቀል ሶሪያ እና ኢራቅ ውስጥ ጥቃት ፈጸመች!

አሜሪካ በሶሪያ እና ኢራቅ ውስጥ በሚገኙ ከኢራን ጋር ግንኙነት አላቸው የተባሉ ቡድኖችን ዒላማ ያደረጉ ጥቃቶችን አርብ ሌሊት መፈጸሟ ተገለጸ።ይህ ጥቃት ባለፈው እሁድ ዮርዳኖስ ውስጥ በሚገኝ የአሜሪካ ጦር ሰፈር ላይ በኢራን የሚደገፉ ታጣቂዎች በፈጸሙት የድሮን ጥቃት ለተገደሉ ሦስት ወታደሮቿ ሞት አጸፋ ነው።

አሜሪካ ኢራቅ እና ሶሪያ ውስጥ በሚገኙት ዒላማዎች ላይ ጥቃት የፈጸመችው ከግዛቷ በተነሱ ረጅም ርቀት ተጓዥ በሆኑ ቦምብ ጣይ አውሮፕላኖች መሆኑ ተገልጿል።የአሜሪካ ሠራዊት ማዕከላዊ ዕዝ እንዳስታወቀው ጥቃቱ የተፈጸመባቸው በሁለቱ አገራት ውስጥ የሚገኙ ዒላማዎች በኢራን የሚደገፉ ታጣቂዎች የሚጠቀሙባቸው ናቸው።

አርብ ሌሊት ሦስት ኢራቅ ውስጥ አራት በሶሪያ በሚገኙ ስፍራዎች ላይ በተፈጸመው ጥቃት የኢራን እስላማዊ አብዮታዊ ዘብ ጓድ፣ ቁዱስ የተባለው ኃይል እና ተባባሪ የሆኑ ሌሎች ቡድኖች የሚገኙባቸው ስፍራዎች ናቸው።በጥቃቱ ከአሜሪካ ምድር የተነሱ ረጅም ርቀት የሚጓዙ ቦምብ ጣይ አውሮፕላኖች እና ሌሎችም የጦር አውሮፕላኖች ሲሳተፉ፣ ከ85 በላይ ዒላማዎች ከ125 በሚበልጡ ዒላማቸውን ለይተው በሚመቱ የጦር መሳሪያዎች ተመትተዋል።

በጥቃቱ ዒላማ የሆኑት የታጣቂ ቡድኖቹ የማዘዣ፣ የመረጃ እና የቁጥጥር ማዕከላት፣ ሮኬቶች እና ሚሳኤሎች የተጠመዱባቸው ስፍራዎች፣ የድሮኖች ማከማቻ ቦታዎች እና የአቅርቦት ማዕከላት መሆናቸውን የአሜሪካ ሠራዊት እስታውቋል።አርብ ሌሊት በበርካታ ቦታዎች ላይ ለ30 ደቂቃዎች በተፈጸመው የመጀመሪያው የአጸፋ ጥቃት የደረሰውን ጉዳት መጠን ለማወቅ የአሜሪካ ሠራዊት ዛሬ ቅዳሜ ግምገማ እንደሚያደርግ ተነግሯል።

Via BBC
@YeneTube @FikerAssefa

3 months ago
**በሀገር ዓቀፍ ደረጃ ከሁለት ሳምንት በኋላ …

በሀገር ዓቀፍ ደረጃ ከሁለት ሳምንት በኋላ ለሚሰጠው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመውጫ ፈተና የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተጠናቀቁ መሆናቸውን ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል።

ከየካቲት 6 እስከ 9 ቀን 2016 ዓ.ም ለሚሰጠው ፈተና ከ112 ሺህ በላይ ነባርና አዳዲስ ተማሪዎች ምዝገባ ማድረጋቸውን በሚኒስቴሩ የከፍተኛ ትምህርት ጥራትና ብቃት ማሻሻያ ዴስክ ኃላፊ ሰዒድ መሃመድ ተናግረዋል።

የፈተና ጥያቄዎች ፣ የኮምፒውተር ፣ ፈተና የሚሰጥባቸው የትምህርት መስኮች ልየታን ጨምሮ አብዛኛዎቹ የዝግጅት ስራዎች እየተጠናቀቁ መሆኑን ነው ኃላፊው የገለፁት።

ባለፈው ዓመት በፈተና አሰጣጥ ሂደትያጋጠሙ ችግሮች ዘንድሮ እንዳይደገሙ በቂ ዝግጅት መደረጉን አቶ ሰኢድ ተናግረዋል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa

3 months ago

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ከፓርላማ አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች፤ በመጪው ማክሰኞ ምላሽ ሊሰጡ ነው

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ከፓርላማ አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች፤ በመጪው ሳምንት መጀመሪያ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በመገኘት ምላሽ እና ማብራሪያ እንደሚሰጡ ምንጮች ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናገሩ። የፓርላማ አባላቱ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚቀርቡ ጥያቄዎችን አስገብተው ያጠናቀቁት በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ነው።

“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ያነጋገረቻቸው ሶስት የፓርላማ አባላት፤ ጥያቄዎችን እንዲያቀርቡ የተሰጣቸው ቀናት ብዛት ሶስት ብቻ እንደነበር ገልጸዋል። በዚህም መሰረት የፓርላማ አባላቱ ከባለፈው ሳምንት ቅዳሜ ጥር 18 ጀምሮ እስከዚህ ሳምንት ሰኞ ጥር 20 ድረስ ጥያቄዎቻቸውን ማስገባታቸውን አስረድተዋል።

በ2008 ዓ.ም የወጣው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአሰራር እና የአባላት ስነ ምግባር ደንብ፤ “ማንኛውም የቃል መልስ የሚፈልግ ጥያቄ የሚያቀርብ አባል፤ ጥያቄውን ቢያንስ ከአስር ቀናት በፊት ለአፈ ጉባኤው በጽሁፍ ማሳወቅ አለበት” ሲል ይደነግጋል። የፓርላማው አፈ ጉባኤ፤ ከምክር ቤቱ አባላት የቀረቡላቸውን ጥያቄዎች መርምረው የመቀበል ወይም ውድቅ የማድረግ ስልጣን በደንቡ ተሰጥቷቸዋል።

Via Ethiopian Insider
@Yenetube @Fikerassefa

4 months, 4 weeks ago

CPJ ጋዜጠኛ በላይ ማናዬ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈታ ጠየቀ!

ዓለም አቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች (CPJ) የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ያለ አንዳች ክስ በቁጥጥር ስር አውለውታል ያለውን የኢትዮ ኒውስ ዋና ኤዲተር ጋዜጠኛ በላይ ማናዬን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱ ጠየቀ።ጋዜጠኛ በላይ ማናዬ ከሦስት ሳምንታት በፊት በፀጥታ ኃይላት የተያዘው ያለ አንዳች ማብራሪያ ነው ሲል ዓለም አቀፍ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋቹ ትናንት ባወጣው መግለጫ ዐስታውቋል።ጋዜጠኛ በላይ ማናዬ ሰኞ፤ ኅዳር 3 ቀን፣ 2016 ዓ.ም በቁጥጥር ስር የዋለው የፖሊስ የደንብ ልብስ ባልለበሱ ፖሊሶች እና ሌሎች የፀጥታ አካላት መሆኑን ዓለም አቀፍ ተቋሙ ዘግቧል።

በላይ የተያዘው የግል የዩቱዩብ ዜና ማሠራጪያው «ኢትዮ ኒውስ» ከሚገኝበት ጽ/ቤቱ አቅራቢያ እንደሆነ የጋዜጠኛው ባለቤት ወ/ሮ በላይነሽ ንጋቱ እና የኢትዮ ኒውስ ተባባሪ መስራች በለጠ ካሳ መናገራቸውን ዓለም አቀፍ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋቹ (CPJ) ገልጿል።በላይ በምን ምክንያት ተይዞ ወደ ኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ቢሮ እንደተወሰደ እንደማያውቅ በእስር ቤት ለጎበኙት ለባለቤቱ ተናግሯል።

ሆኖም የተያዘው በአማራ ክልል ካለው ጦርነት እና ከተደነገገው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዳይያያዝ ፍራቻ እንዳለው ማከሉ ተነግሯል ። መሰል እስር «ኢትዮጵያ ውስጥ ሌሎች ጋዜጠኞች በማናቸውም ጊዜ ነጻነታቸው ሊገፈፍ እንደሚችል መልእክት ያስተላልፋል» ሲሉ የሲፒጄ ከሰሐራ በታች የአፍሪቃ ተወካይ ሙቶኪ ሙሞ ተናግረዋል።በአስቸኳይ እንዲፈታም ጠይቀዋል።ጋዜጠኛ በላይ ማናዬ እና ኢትዮ ኒውስ ስለ አማራ ክልል ጦርነት እና የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች በስፋት እና በተደጋጋሚ በመዘገብ ይታወቃሉ።

Via DW
@YeneTube @FikerAssefa

We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated hace 1 día, 17 horas

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated hace 5 días, 6 horas

Last updated hace 5 días, 19 horas