YeneTube

Description
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Advertising
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 2 months, 1 week ago

Last updated 6 days, 22 hours ago

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ ? @Esat_tv_comment_bot

??ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ??

Last updated 2 months, 3 weeks ago

5 days ago

በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ የመንግስት ሰራተኞች በቅርቡ ከስራ ሊቀነሱ እንደሆነ ታውቋል

ከሰሞኑ የፀደቀው የመንግስት ሰራተኞች አዋጅ "ተቋማት ተልዕኳቸውን በብቃት እንዲፈፅሙ የሚያስችል ነው" ቢባልም ከአዋጁ ጋር ተያይዞ በርካታ የመንግስት ሰራተኞች ከስራ ሊቀነሱ እንደሚችሉ ስማችን አይጠቀስ ያሉ ሁለት የመንግስት ምንጮች ለመሠረት ሚድያ ተናግረዋል።

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ሃብት ልማት ሥራ ስምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ዶ/ር ነገሪ ሌንጮ በአዋጁ አላማና አስፈላጊነት ዙሪያ ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተው በነበሩበት ወቅት ስለ ሰራተኛ ቅነሳው ያነሱት ነገር ባይኖርም በመንግስት አቅጣጫ ከተያዘባቸው ጉዳዮች አንዱ "ከሚያስፈልገው በላይ የመንግስት ሰራተኛ አለ" የሚለው ዋናው መሆኑን ምንጮቹ ጠቅሰዋል።

በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ዋና ተጠሪ ሚንስትር አቶ ተስፋዬ በልጅጌ ሂደቱ የግለሰቦችን መብት ያለአግባብ እንዳይጎዳ ሚዛኑን አስጠብቆ በመሄድ ረገድ ተገቢው ጥንቃቄ ይደረጋል ቢሉም በርካቶች ከስራቸው እንደሚቀነሱ እንደማይቀር ታውቋል።

የረቂቅ አዋጁን ይዘት በአግባቡ ባለመረዳት በአንዳንድ የሚዲያ ተቋማት የተዛቡ መረጃዎች እየተላለፉ እንደሆነ የሚናገሩት ዶ/ር ነገሪ በበኩላቸው ግልፀኝነት በሚያስፈልጋቸው ጉዳዮች ላይ በመወያየት ረቂቅ አዋጁን የበለጠ ለማዳበር እና ህዝቡ ትክክለኛ መረጃ እንዲያገኝ ለማድረግ ይደረጋል ብለዋል።

አዋጁ እንደ ፍርድ ቤት፣ አቃቤ ህግ፣ ፖሊስ፣ መከላከያ፣ እና ደህንነትን የመሳሰሉ ተቋማት ውስጥ የብሄር ስብጥር ለማድረግም ያለመ መሆኑን የጠቁሙት ምንጮች አዋጁ "የብሔር ብሔረሰቦች ብዙሃነት እና አካታችነት ስርዓትን ይገነባል" በሚል በመንግስት እንደታሰበ አስረድተዋል።

የዚህን የመንግስት ሰራተኞች ቅነሳ የሚጠቁም ነገር ግን ብዙ ሰው ልብ ያላለው አንድ መረጃ በአንድ የመንግስት ሚድያም ተለቆ ነበር።

"ሲቪል ሰርቪሱ ሀገሪቷ ከምትሸከመውና አገልግሎቱ ከሚፈልገው በላይ የበዛ መሆኑ ተጠቆመ" የሚል መረጃ ባለፈው ሳምንት በኢትዮጵያ ፕረስ ድርጅት ተሰራጭቶ የነበረ ሲሆን በአሁኑ ወቅት ያለው የሲቪል ሰርቪሱ ቁጥር ሀገሪቷ ከምትሸከመውና አገልግሎቱ ከሚፈልገው በላይ የበዛ መሆኑን ዶ/ር ነገሪ መናገራቸውን ዘግቦ ነበር።

ዶ/ር ነገሪ በዚህ ንግግራቸው እንደጠቀሱት "በየመንግሥት መሥሪያ ቤቱ ያለው የሠራተኛ ቁጥር በጣም በርካታ ነው። ሀገሪቷ ከምትሸከመውና አገልግሎቱ ከሚፈልገው በላይ የበዛ ነው። ከአደረጃጀት አንጻር ሲታይም በአንድ መሥሪያ ቤት ውስጥ መዋቅሩ የሚሸከመው ብዙ የሰው ኃይልን ነው፤ በተሸከመ ቁጥር ደግሞ የሚያገኘው ጥቅም አናሳ ነው" ብለው ነበር።

ሀላፊው አክለውም "የመንግሥት ሠራተኞች የብዛታቸውን ያህል የሚሠሩት አገልግሎት የሚያረካ አይደለም፣ የተወሰኑ ይሠራሉ፤ ሌሎቹ ግን የተወሰኑ ሠራተኞች በሠሩት ትከሻ ላይ ተንጠላጥለው ይኖራሉ" በማለት የሰራተኛ ቅነሳ መኖሩን በተዘዋዋሪ መንገድ ጠቁመው ነበር።

@Yenetube @Fikerassefa

5 days ago

የዳኝነት ክፍያን እስከ 500 ፐርሰንት የሚጨምረው ህግ ዛሬ ፀደቀ

የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የዳኝነት ክፍያን ለመወሰን የወጣው ረቂቅ ደንብ በዛሬው እለት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፀደቀ ሲሆን መሠረት ሚድያ የተመለከተው ይህ የክፍያ ወሰን እስከ 500 ፐርሰንት ጭማሪ ተገልጋዮች ላይ ይጥላል።

ደንቡን ማሻሻል ያስፈለገው የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ከዚህ ቀደም የሚጠቀሙበት የዳኝነት ገንዘብ አከፋፈል ለ72 ዓመታት ማሻሻያ ሳይደረግበት የቆየ መሆኑ የተገለፀ ቢሆንም እስከ 500 ፐርሰንት ጭማሪ ማድረጉ በተለይ አሁን ላይ ካለው የኑሮ ውድነት ጋር ተያይዞ ለብዙዎች አስገራሚ ሆኗል።

መሠረት ሚድያ የተመለከተው እና በቅርቡ በነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ እንደሚወጣ የሚጠበቀው ዛሬ የፀደቀው የዳኝነት ክፍያ ከዚህ በፊት ለሁለት ሚልዮን ብር የክስ ገንዘብ መጠን ይከፈለው የነበረው 23,000 ብር ወደ 82,000 ብር ጨምሯል።

ይህ የተጋነነ ክፍያ ሰዎች ፍትህ ለማግኘት ወደ ፍትህ ተቋማት እንዳይሄዱ እንቅፋት ሊሆን እንደሚችል ከወዲሁ እየተጠቆመ ይገኛል።

መሠረት ሚዲያ
@Yenetube @Fikerassefa

5 days, 11 hours ago

የከተማ መሬቶች በሶስት ዓመት ጊዜ ውስጥ ሙሉ በሙሉ በሊዝ የመሬት ስርዓት ውስጥ መካተት እንዳለባቸው ተጠቆመ

በኢትዮጵያ ከተሞች ያሉ መሬቶች በሶስት ዓመት ጊዜ ውስጥ ሙሉ በሙሉ በሊዝ የመሬት ስርዓት ውስጥ መካተት እንዳለባቸው ተሻሻሎ በቀረበው የከተማ መሬትን በሊዝ ለመያዝ በቀረበው ረቂቅ አዋጅ ላይ ተጠቆመ።

በዛሬው ዕለት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የከተማ፣ መሰረት ልማት እና ትራንስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የከተማ መሬት ይዞታ እና መሬት ነክ ንብረት ለመመዝገብ እና የከተማ መሬትን በሊዝ ለመያዝ ተሻሽሎ የቀረቡ ረቂቅ አዋጆች ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር እየተወያየ ይገኛል።

በተሻሻለው አዋጅ ውስጥም የከተማ መሬት ሊዝን በተመለከተ ከኅዳር 18/2004 በኋላ ያለፈቃድ የተያዙም ሆነ ፈቃድ ባላገኙ መሬት ላይ ያሉ ግንባታዎችን ጭምር በማፍረስ መንግስት የመሬት ይዞታዎቹን እንደሚረከብ ተመላክቷል።

እንዲሁም በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ከተሞች በሶስት ዓመት ጊዜ ውስጥ ሙሉ በሙሉ በሊዝ የመሬት ስርዓት ውስጥ መካተት እንዳለባቸው በተሻሻለው በረቂቅ አዋጅ ላይ መካተቱን ለሚመለከታቸው አካላት ተብራርቷል።

@Yenetube @Fikerassefa

1 week, 4 days ago

ቻይና ኢኮኖሚዋን ለማነቃቃት መግቢያ ቪዛ የማያስፈልጋቸው ሀገሮችን ቁጥር ልታሳድግ ነው!

ቻይና የቱሪዝም እና የንግድ ተጓዦችን ቁጥር በማሳደግ የተቀዛቀዘውን ኢኮኖሚዋን ለማነቃቃት ለዘጠኝ ተጨማሪ ሀገራት ዜጎች ካለቪዛ እንዲገቡ ልትፈቅድ መሆኗን አስታወቀች፡፡የቻይና ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ሊን ጂያን ዛሬ ዓርብ እንዳስታወቁት እአአ ከህዳር 30 ጀምሮ ከቡልጋሪያ፣ ሮማኒያ፣ ማልታ፣ ክሮኤሺያ፣ ሞንቴኔግሮ፣ ሰሜን መቄዶኒያ፣ ኢስቶኒያ፣ ላቲቪያ እና ጃፓን ተጓዦች ለሠላሳ ቀናት ቆይታ ያለ ቪዛ ሊገቡ ይችላሉ።

ይህ ካለፈው ዓመት ጀምሮ ያለቪዛ መግባት የተፈቀደላቸውን ሀገራት ቁጥር ወደ 38 ያሳድገዋል።ከዚህ ቀደም ከቪዛ ነጻ ፈቃድ የነበራቸው ሦስት ሀገራት ብቻ ሲሆኑ የእነሱም ፈቃድ በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ወቅት ተሰርዞ እንደነበረ ይታወሳል፡፡የጃፓን ከቪዛ ነጻ ሀገራቱ ውስጥ መጨመር፣ ቻይና በታይዋን ጉዳይ ከቶኪዮ በተደረጉ ጠንከር ያሉ ንግግሮች የተነሳ ሻክሮ የነበረውን ግንኙነት ለማሻሻል እየፈለገች መሆኗን ሊጠቁም እንደሚችል ተነግሯል፡፡

ጃፓን ከወረርሽኙ በፊት ከቪዛ ነፃ ከሚገቡት ሶስት ሀገራት አንዷ ነበረች፡፡ የጃፓን የካቢኔ ፀሃፊ ዮሺማሳ ሃያሺ እንደገና እንዲጀመር መንግሥታቸው በተደጋጋሚ ሲወተውት እንደነበረ ገልጸዋል፡፡ቻይና ከቪዛ ነፃ የመግባት ሂደትን በየደረጃው በማስፋፋት የአውሮፓ ሀገራትን ጨምራ በቅርቡ የተማሪዎችና እና የምሁራን ጉብኝቶችን በማሻሻል የህዝብ ለህዝብ ልውውጥ ላይ ትኩረት አድርጋለች።

ታይላንድ እና ሌሎች ሀገራት ቱሪዝምን ለማበረታታት ለቻይና ተጓዦች ከቪዛ ነጻ ፖሊሲዎችን ተግባራዊ አድርገዋል፡፡በዚህ ዓመት ከሀምሌ እስከ መስከረም በነበሩት ሦስት ወራት 8.2 ሚሊዮን የውጭ ዜጎች ቻይና የገቡ ሲሆን 4፡9 ሚሊዮን የሚሆኑት ከቪዛ ነጻ ተጠቃሚዎች መሆናቸውን የአሶሴይትድ ፕሬስ ዘገባው አመልክቷል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa

1 week, 5 days ago

20 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ህዝብ  መንገድ  ላይ ይፀዳዳል ተባለ

በኢትዮጵያ ከ20 ሚሊዮን በላይ ህዝብ  ጥራቱን ከጠበቀ ሽንት ቤት ዉጭ መንገድ ላይ   ይፀዳዳል ተብሏል ፡፡

በጤና ሚኒስቴር አካባቢ ጤና ፕሮግራም ዴስክ ሃላፊ አቶ አለሙ ቀጀላ በአለም ጤና ድርጅት እና በዩኒሴፍ በ2022 በተደረገ ጥናት መሠረት 17 ፐርሰንት የሚሆነዉ የኢትዮጵያ ህዝብ ከመፀዳጃ ቤት ዉጭ መንገድ ላይ ይፀዳዳል ብለዋል ፡፡

በዚህም ህዝቡ ለኮሌራ እና መሰል  በሽታዎች  ተጋላጭነቱ እንደጨመረ ተነግረዋል ።

ጤና ሚኒስቴር የተለያዩ ስትራቴጅዎችን ቀርጾ ህዝቡ መሰረታዊ መፀዳጃ ቤት እንዲጠቀም እየሰራ መሆኑ አቶ አለሙ ቀጀላ ገልፀዋል ፡፡

በአለም አቀፍ ደረጃ የሚከበረዉ የእጅ መታጠብ እና መፀዳጃ ቤት ቀን በኢትዮጵያ ለ ስምንተኛ ጊዜ በተለያዩ የግንዛቤ ማስጨበጫ ፕሮግራሞች እየተከበረ ይገኛል።

Via:- አዩዘሀበሻ
@Yenetube @Fikerassefa

1 week, 5 days ago

ሩሲያ ከድምጽ ፍጥነት አሥር እጥፍ የበለጠ የሚጓዝ ሚሳኤል እንዳላት አስታወቀች

የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን አዲሱ የሞስኮ ሙከራ የተደረገበት ባሊስቲክ ሚሳኤል አስር እጥፍ ከድምፅ ፍጥነት እንዳለው በሰከንድ 3 ኪ.ሜ እንደሚጓዝ አስታውቀዋል።

ፍጥነት አስፈላጊ ነው ምክንያቱም ሚሳኤል በፈጠነ ቁጥር ኢላማውን የጠበቀ ይሆናል። ኢላማውን ለመምታት በፈጠነ መጠን የመከላከያ ሰራዊት ምላሽ የሚሰጥበት ጊዜ ይቀንሳል በማለት አክለዋል። በእርግጥ እንደዚህ አይነት ሚሳኤሎች አደጋዎችን እንዳያስከትሉ ለመከላከል የሚቻል ሲሆን ነገር ግን ፍጥነቱ እየጨመረ በሄደ መጠን የመከላከል ስራውን የበለጠ እያከበደው ይሄዳል። ለዚህም ነው ፕሬዚዳንት ፑቲን ይህን አዲስ አይነት ሚሳኤል በማወጅ ፍጥነት ላይ አፅንዖት ሰጥተው የተናገሩት። የዩናይትድ ስቴትስ ባለስልጣናት ይህንን አዲስ የሙከራ ስርዓት ቀድሞውኑ እንደሚያውቁት እና ዩክሬን እና አጋሮቿን ለማዘጋጀት ሲሉ ገለፃ እንዳደረጉ አስታውቀዋል።

ይህ መጠነ ሰፊ ግጭት ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ ሩሲያ ወደ 12 ሺ የሚጠጉ ሚሳኤሎች በዩክሬን ግዛቶች ላይ አወንጭፋለች።  ከእነዚህ ውስጥ 80 በመቶ የሚሆኑት በዩክሬን አየር ስርዓት ተጠልፈዋል። ነገር ግን እነዚህ ፈጣን የባለስቲክ ሚሳኤሎች ከአየር መቃወሚያ እና ከሌሎች የመከላከያ ስርዓቶች ውጪ ለማድረግ የታሰቡ ናቸው።ሩሲያ በዩክሬን ላይ ትናንት ሀሙስ ባደረሰችው የባለስቲክ ሚሳኤል ጥቃት ምክንያት የሰሜን አትላንትቲክ ጦር ቃልኪዳን ኔቶ እና ዩክሬን አስቸኳይ ውይይት በሚቀጥለው ሳምንት በብራስልስ እንደሚያደርጉ ይጠበቃል። የናቶ-ዩክሬን ምክር ቤት ስብሰባ ማክሰኞ የሚካሄድ ሲሆን የኪየቭን የእንሰብሰብ ጥያቄ ተከትሎ እንደሚደረግ የፈረንሳዩ የዜና ወኪል አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ያነጋገራቸው ባለስልጣናት ገልጸዋል።

እ.ኤ.አ. በሀምሌ 2023 የተመሰረተው ምክር ቤት በኔቶ አባላት እና በዩክሬን መካከል የጋራ አካል ነው። ወታደራዊ ህብረትን ለመቀላቀል ፍላጎት ያለው - እንዲሁም የጦርነት ቀውስ ሲያጋጥን የምክክር አማራጭ ሆኖ ይሠራል ።የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ ሩሲያ ትናንት በዲኒፕሮ አዲስ የባላስቲክ ሚሳኤል መጠቀሟ የጦርነቱን ከባድነክ ያሳያል ብለዋል። "ዛሬ በዩክሬን ላይ የባሊስቲክ ሚሳኤል መጠቀሟ ሩሲያ ለሰላም ምንም ፍላጎት እንደሌላት ተጨማሪ ማረጋገጫ ነው" ሲሉ ዘለንስኪ በሰጡት መግለጫ ላይ ተናግረዋል። ጥቃቱ የሩስያ መሪ ቭላድሚር ፑቲን ጦርነቱን ለማባባስ የወሰዱት "ሁለተኛ እርምጃ" ነው ሲሉ ዘለንስኪ ገልፀዋል።

ዘለንስኪ አክለው ፑቲን "ከቻይና፣ ብራዚል፣ የአውሮፓ ሀገራት፣ አሜሪካ እና ሌሎች የሚደረጉ የሰላም ጥሪዎችን ችላ በማለት" ከአንድ ሺህ ቀናት በፊት የተጀመረውን ግጭት ለማራዘም ሁሉንም ነገር እያደረጉ ነው ብለዋል። "አለም የአፀፋ ምላሽ መስጠት አለበት" ፤ "በሩሲያ ድርጊት ላይ ጠንካራ ምላሽ አለመስጠት እንዲህ አይነት ባህሪ ተቀባይነት ያለው እንዲመስል መልእክት ያስተላልፋል" በማለት ተናግረዋል። ሩሲያ በኃይል ብቻ ወደ እውነተኛ ሰላም መገደድ አለባት ፤ ይህ ካልሆነ ግን ማለቂያ የሌላቸው የሩሲያ ጥቃቶች ፣ ዛቻዎች እና አለመረጋጋት በዩክሬን ላይ ብቻ ሳይሆን በሌሎች ላይም የሚከተል ነው ሲሉ ገልፀዋል።

#ዳጉ_ጆርናል
@Yenetube @Fikerassefa

2 weeks, 4 days ago

ለ24ኛ ጊዜ የተዘጋጀው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ የተወሰኑ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚሆኑ አዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ።

በርካታ የሀገር ውስጥና የውጪ ሀገራት ተሳታፊዎች ፣ አምባሳደሮች ፣ ተጋባዥ አትሌቶች የሚታደሙበት መነሻና መድረሻውን መስቀል አደባባይ ያደረገው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ያዘጋጀው የሩጫ ውድድር ህዳር 8 ቀን 2017 ዓ/ም በአዲስ አበባ ይካሄዳል፡፡ ውድድሩ ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ የተወሰኑ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚሆኑ አዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

ለጋራ ደህንነት ሲባል ፍተሻ እንደሚኖር የውድድሩ ተሳታፊዎች ተገንዝበው አስፈላጊውን ትብብር ማድረግ እንዳለባቸው ፖሊስ ገልፆ የወድድሩ ተሳታፊዎች በሚያልፉት አካባቢ የሚኖሩ ነዋሪዎች እንደ ከዚህ ቀደሙ ከፀጥታ ኃይሉ ጎን በመቆም ትብብራቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ አዲስ አበባ ፖሊስ ጥሪውን እያስተላለፈ ውድድሩ የከተማችንን ዋና ዋና መንገዶች የሚያካልል በመሆኑ ሩጫው ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ የተወሰኑ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚሆኑ አዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቆ ውድድሩ በሰላም እንዲጠናቀቅ የፀጥታ አካላት አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅት አጠናቀው ስራ መጀመራቸውን አዲስ አበባ ፖሊስ ገልጿል።

ከውድድሩ ዓላማ ውጪ ህገ-ወጥ ተግባራትንና መልእክቶችን ማስተላለፍ የውድድሩን መንፈስ የሚረብሽ ስለሆነ አዘጋጅ ተቋሙ እና ተሳታፊዎች ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ እንደለባቸው እያሳሰበ ውድድሩ ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ፡-

-ከኦሎምፒያ አደባባይ ወደ መስቀል አደባባይ (ኦሎምፒያ አደባባይ )
- ከጥላሁን አደባባይ ወደ ሳንጆሴፍ መብራት (ጥላሁን አደባባይ ) ለከባድ ተሽከርካሪ አጎና ሲኒማ
- ከአፍሪካ ህብረት መብራት ወደ ሜክሲኮ አደባባይ (ጥይት ቤት መስቀለኛ )
-ከፓርላማ መብራት ወደ ኮንሰን መታጠፊያ (ፓርላማ መብራት )
- ከኮንሰን መታጠፊያ ወደ ገብርኤል (ኮንሰን መታጠፊያ )
ከጥይት ቤት ወደ ገብርኤል በጀርባው (ጥይት ቤት መታጠፊያ )
ከሴቶች አደባባይ ወደ ካዛንቺስ (ሴቶች አደባባይ )
- ከሴቶች አደባባይ ወደ ካዛንቺስ ቶታል (ሴቶች አደባባይ )
- ከ22 አደባባይ ወይም ዘሪሁን ህንፃ ወደ ዑራኤል አደባባይ (ዘሪሁን ህንፃ መስቀለኛ )
- ከፒኮክ አዲሱ መንገድ ወደ ዑራኤል አደባባይ (ፒኮክ መብራት)
- ከጋዜቦ አደባባይ ወደ ደንበል (ጋዜቦ አደባባይ)
- ከቂርቆስ ቤ/ክርስቲያን መስቀለኛ ወደ ለገሃር መብራት (ቂርቆስ ቤ/ክርሰቲያን ነርክ ተራ )
- ከላንድ ማርክ ሆስፒታል መታጠፊያ ገነት ሆቴል ወይም ወደ ገነት መብራት (ላንድ ማርክ ሆስፒታል መስቀለኛ )
- ከጠማማ ፎቅ ወደ ሜክሲኮ አደባባይ (ጠማማ ፎቅ መስቀለኛ )
- ከአፍሪካ ህብረት መብራት ወደ ሜክሲኮ አደባባይ (ሜክሲኮ ጥይት ፋብሪካ መስቀለኛ )
- ከፈረሰኛ መብራት ወደ ጨፌ ሜዳ (ፈረሰኛ መብራት )
- ከሞላ ማሩ መስቀለኛ ወደ ጌጃ ሰፈር (ጌጃ ሰፈር መስቀለኛ )
- ከከፍተኛ ፍ/ቤት አደባባይ ወደ ሜክሲኮ አደባባይ (ከፍተኛ ፍ/ቤት አደባባይ)
- ከሠንጋ ተራ 40/60 ወደ ሠንጋ ተራ መብራት (ሠንጋ ተራ 40/60 መታጠፊያ)
- ከጎማ ቁጠባ መብራት ወደ ብ/ቲያትር (ጎማ ቁጠባ መብራት)
- ከሜትሮሎጂ መታጠፊያ ወደ ፖስታ ቤት መብራት (ሜትሮዎሎጂ መታጠፊያ )
- ከጥቁር አንበሳ ሼል ወደ ኢምግሬሽን (ጥቁር አንበሳ ሼል)
- ከጎላ ሚካኤል መስቀለኛ ወደ ኢምግሬሽን (ጎላ ሚካኤል መስቀለኛ)
- ከቴዎድሮስ አደባባይ ወደ አገር አስተዳደር መብራት (ቴዎድሮስ አደባባይ)

ከንጋቱ 11:30 - ሰዓት ጀምሮ ውድድሩ እስከሚጠናቀቅ የተጠቀሱት መንገዶች የሚዘጉ ሲሆን በተጨማሪም በተገለፁት መስመሮች ላይ ቅዳሜ ከምሽቱ 12:00 ሰዓት ጀምሮ መኪና ለአጭርም ይሁን ለረጅም ጊዜ ማቆም የተከለከለ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ እያስታወቀ የፖሊስን አገልግሎት ለማግኘት 011 1110111 ወይም ነጻ የስልክ መስመር 991 መጠቀም እንደሚቻል ፖሊስ አስታውቋል።

@YeneTube @FikerAssefa

2 weeks, 4 days ago
**በቋሚ ደመወዝ ለሚተዳደሩ ሰራተኞች የሥራ ግብር …

በቋሚ ደመወዝ ለሚተዳደሩ ሰራተኞች የሥራ ግብር እንዲቀነስ መጠየቁ ተገለጸ!

በቋሚ ደመወዝ ለሚተዳደሩ ሰራተኞች የሥራ ግብር መቀነስን ጨምሮ ሌሎች እርምጃዎች እንዲወሰዱ ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድን በደብዳቤ መጠየቃቸውን የኢትዮጵያ ሠራተኛ ማህበራት ኮንፌደሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ካሣሁን ፎሎ ገለጹ።የኮንፌደሬሽኑ ፕሬዘዳንት አቶ ካሣሁን ፎሎ ለአሜሪካ ድምጽ እንደገለጹት የብር የመግዛት አቅም መዳከም ጋር ተያይዞ ቋሚ ደመወዝ የሚያገኙ ሰራተኞች ለከፍተኛ የኑሮ ፈተና እየተዳረጉ እንደሚገኙ ገልጸዋል።

"በተለይም ዝቅተኛ ገቢ የሚያገኘው ሰራተኛ ቀን ቀን እየሠራ ማታ ማታ ሆቴሎች ላይ ፍርፋሪ እየለመነ እያደረ ነው።" ያሉት ፕሬዝዳንቱ የኑሮ ጫናው በተለይ በኢንዱስትሪ ፓርኮች ተቀጥረው በሚሰሩ ኢትዮጵያውያን ላይ ያያለ መሆኑን ጠቁመዋል።

አክለውም ከዚህ በፊት በሰራተኞች የኑሮ ሁኔታ ዙርያ ከጠቅላይ ሚንስትር ዓብይ አህመድ ጋር ተደጋጋሚ ውይይቶች መደረጋቸውን አስታውሰው ነገር ግን እነዚህ ውይይቶች ይበል የሚያሰኝ ውጤት አለማስገኘታቸውን ተናግረዋል።በመሆኑም የሥራ ግብር መቀነስን ጨምሮ ሌሎች የኑሮ ፈተናውን ሊያቀሉ የሚችሉ ኢኮኖሚያዊ እርምጃዎች እንዲወሰዱ ጠቅላይ ሚንስትሩን በድጋሚ በደብዳቤ መጠየቃቸውን አመላክተዋል።

Via Addis Standard
@YeneTube @FikerAssefa

2 weeks, 4 days ago
ጤናወ በእጀወ በቤትወ የጤና በረከት የተለያዩ …

ጤናወ በእጀወ በቤትወ የጤና በረከት የተለያዩ መፍትሄ ያጡ ችግሮች እናም በሽታወችን እንዴት አባቶች እና እናቶች ባቆዩነን ቅመማቅመም ቅጠል ስር ፍሬ እና ጥበብ መታከም መፈወስ ከችግራችን መውጣት እንዴት እንደምንችል እምንረዳበት የምንችለው  ቻናል ነው ይቀላቀሉ በየቀኑ የምንለቃቸውን ጠቃሚ መረጃ ተካፋይ ይሑኑ ሸር ያድርጉ
👇
https://vm.tiktok.com/ZMhNYSvDS/       ለበለጠ መረጃ
0912718883
0917040506 በቴሌግራም በውስጥ መስመር የሚፈልጉትን ያስቀምጡ
👉አድራሻችን አዲስ አበባ አየር ጤና ካራቆሬ ወደመድኀኒአለም 200ሜትር ገባ ይበሉ
ቁጥር 2ባህርዳር ቀበሌ 11ዲያስፖራ በአሮየው 
አስፓልት መስጊዱ ፊት ለፊት ያገኙናል ይምጡ
ይፈወሱ
https://www.tiktok.com/t/ZMhN2XcBE/

በማንኛውም አገልግሎት ውጤቱን እንዳዪ ክፍያ ይፈፅማሉ

3 weeks, 4 days ago

ኦቪድ ሪል ስቴት ከራይድ ትራንስፖርት ጋር የራይድ ቤተሰብ መንደርን ለመገንባት ከተፈራረመ ከአንድ ወር በኋላ የመሠረት ድንጋይ አስቀመጠ።

ኦቪድ ሪል ስቴት ለራይድ ሹፌሮች የሚሆን የራይድ ቤተሰብ መንደር በገላን ጎራ ከተማ ለመገንባት ስምምነት መፈራረሙ ይታወሳል።ራይድ ትራንስፖርት እና ሰዋሰው መልቲሚዲያ ለሚያስገነቡት ዘመናዊ የራይድ መንደር ዛሬ ጥቅምት 30 ቀን 2017 ዓ.ም በገላን ጉራ ከተማ በይፋ የመሠረት ድንጋይ አስቀምጠዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን የአማራጭ ቤቶች ልማት ፕሮግራም ዳይሬክተር ኢንጅነር ታምራት አክሊሉ፤በመንግስትና የግል አጋርነት ከሚሰሩ ፕሮጀክቶች መካከል ከኦቪድ ጋር በትብብር እየተሰሩ ካሉ ፕሮጀክቶች የራይድ መንደር ግንባታ አንዱ መሆኑን አንስተው፤ መንግስት ከመሬት አቅርቦት ጀምሮ ሌሎች አማራጮችንም በማቅረብ እንደሚደግፍ ገልጸዋል።ኦቪድ ሪልስቴት አዲስ እየተገነባ በሚገኘው የገላን ጎራ ከተማ ውስጥ ለራይድ አሽከርካሪዎች እና ከሰዋሰው መልቲሚዲያ ጋር ለተፈራረሙ አርቲስቶች በአጭር ጊዜ ቤቶችን ገንብቶ ለማስረከብ ነው የተስማማው።

በዚህ ስምምነት ከሰዋሰው መልቲሚዲያ ጋር የተፈራረሙ አርቲስቶች በቅናሽ የቤት ባለቤት መሆን እንደሚችሉም ነው የተገለጸው።ኦቪድ ግሩፕ ከሚያደርገው የቤት ዋጋ ቅናሽ በተጨማሪ ሰዋሰው መልቲሚዲያ የፋይናንስ ድጋፍ እንደሚያደርግ ተገልጿል።ኦቪድ ግሩፕ ከ90 ሺህ በላይ ቤቶችን በተለያዩ ሳይቶች እየገነባ መሆኑን የገለፁት የኦቪድ ሪል ስቴት ዋና ስራ አስፈፃሚ ዮናስ ታደሰ፤ 60 ሺህ የሚሆኑት በገላን ጎራ ከተማ መሆናቸውን ገልጸዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን የአማራጭ ቤቶች ልማት ፕሮግራም ዳይሬክተር ኢንጅነር ታምራት አክሊሉ፤ ኦቪድ ከሚሰራቸው ቤቶች 30 በመቶ ድርሻ እንዳለው ገልፀው ፤ 18 ሺህ ቤቶች የመንግስት መሆናቸውን አንስተዋል።ዳይሬክተሩ መንግስት እነዚህን ቤቶች ለልማት ተነሺዎች ፣ ለቆጣቢዎች እና ለሌሎች የሚሰጥ መሆኑንም ገልፀዋል።ኦቪድ ግሩፕ ከሁለቱ ተቋማት ጋር በገባው ስምምነት መሠረት 5 ሺህ ቤቶችን በ2 ዓመት ጊዜ ውስጥ ሰርቶ እንደሚያስረከብ አስታውቋል።

Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa

We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 2 months, 1 week ago

Last updated 6 days, 22 hours ago

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ ? @Esat_tv_comment_bot

??ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ??

Last updated 2 months, 3 weeks ago