ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated hace 3 semanas, 5 días
Last updated hace 3 semanas
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot
🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹
Last updated hace 1 mes, 1 semana
.
● የልቤ v ሰራቂ ●
የውበቷ እንቁ ውቧ ፅጌረዳ
ደምቃ እንደወጣች ገና በማለዳ
አብራት ከወጣችው ከፀሀይዋ ልቃ
ልቤን ወሰደችው ካካሌ ፈልቅቃ
የምን ልቤ ብቻ የምን አካላቴ
በፍቅሯ የነደደው መላ እኔነቴ
የፍቅር ጀግናናት አይደፍሩትን ደፋር
ጥልፉ የጣለችኝ በውበቷ አድባር
ከልቤ ካንጀቴ እኔ እዬወደድኳት
በፍርሃት ተውጬ ፍቅሬን ስገልፅላት
በፈጣሪ ፀጋ በውበቷ ኮርታ
አሻፈረኝ ብላ ሄደች ጀራባ ሰታ
የወንድነቴ ጥግ ተሰበረ ወሽመጡ
የማረገው ጠፋኝ አልገባኝም ቅጡ
ኸረ ወቸው ጉዴ አሁን ምን ተሻለኝ?
ከሷ ተነጥዬ መኖር አይቻለኝ
ቀን በቀን ስናፍቅ ልቤ ሲፈልጋት
እንዲው ጥላኝ ስትሄድ ፍቅሬ አልከበዳት
በፍቅሯ ብመንን ካአጀብ ተነጥዬ
መቼም አልጫናት የኔ ሁኚ ብዬ
ውደደኝ ሳትለው ልቤ ከወደዳት
እንዴትስ አድርጌ ሸንጎ ልገትራት
ቀንቶኝም የማያወቀው ደርሶ የኔ ዕጣ
እሷን አገኝ ብዬ እኔው ራሴን ልጣ?
✍ቶፊቅ መሀመድ
━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
ፍቅር በእኛ @selefikir
➳➳➳ ከወደዱት ለሌሎች ሼር ያድርጉ!! ➢➢➢
▓▓▓▓▓▓▓ ምክር ▓▓▓▓▓▓▓
የምድር ላይ ቆይታህ ትርጉም አልባ እንዳይሆን, በተሰጠህ የህይወት ደረጃ ፈጣሪህን አመስግን, ለስህተትህ ይቅርታ መጠየቅ ሽንፈት አይደለምና ይቅርታ መጠየቅን ልመድ ,ካለፈው ስተትህ ተማር, አጉል እልህ ዋጋ እንዳያስከፍልህ ተጠንቀቅ , መልካም መሆን አይጎዳምና መልካም ሁን , በህይወትህ የውሳኔ ሰው ሁን, በተቻለህ መጠን እሚቆጭህን ነገር ለማድረግ አትሞክር ,
━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
? Admin @Tes_b37
ፍቅር በእኛ @selefikir
➳➳➳ ሼር ያድርጉ!! ➢➢➢
? Admin @Tes_b37
ልክ እንደ አእዋፍ ሰማይ ላይ
መብረረን ተማርን ፣ ልክ እንደ አሳ
ባህር ውስጥም መዋኘትን ተማርን. . .
ነገር ግን እስከ አሁን ድረስ ልክ እንደ
ወንድማማቾች ምድር ላይ መራመድን
መማር አቃተን!
ተስፋ....✍
@Tes_b37
? መልካም ምሽት ለሁላችንም ?
ፍቅር በእኛ
@selefikir
. የደስታ ቀን !
ቀናችንን እኛ እንሰራዋለን ፡፡ እያንዳንዱ ቀን በራሱ ጥሩ ወይንም መጥፎ ሁኖ አይመጣም ይልቁንስ ኹለቱንም እድል ይዞ ወደእኛ ይመጣል ፡፡ ስለዚህ ደስታና ሀዘን ባብዛኛው የውሳኔያችን ውጤት ስለሆነ በየቀኑ ባለን ነገር ለመደሰት እንወስን ፡፡ የሕይወታችን የሚገጥሙን ማዕበሎችም እኛን ለማጠንከርና ለማሳደግ ስለሆነ በጥሩ አጋጣሚ ተስፋ ሳንቆርጥ እንጠቀምባቸው፡፡
መልካም ቀን ይሁንላችሁ
# Share # Share
?Admin @Tes_b37
ፍቅር በእኛ @selefikir
.
. . . ሁሉም ሰው በህይወት ሚያቆየው ምክንያት ይኖረዋል ፤ ነገን የተሻለ እናልማለን . . . ነገ ለመኖራችን ምክንያት እንጂ ዋስትና የለንም ፤ ምክንያቶችን በተስፋ እንጠብቃለን. . .
ተስፋ......✍
@Tes_b37
ፍቅር በእኛ
@selefikir
.
ብዙ ነገሮች በህይወታችን ሲመጡ የራሳቸው ምክንያት አላቸው፡፡ . . . ሰዎች እንደዚ ነን ከዳር ቆመን በምላሳችን ሰዎችን መጣልና ማንሳት የዕለት ተለት ስራችን ነው፡፡ ቢያንስ ለምን? ብለን እንኳን ጠይቀን ምክንያታቸውን ለመስማት እንሞክር፡፡ ምክንያቱም ሁሉም ነገር የራሱ የሆነ እውነት ስላለው፡፡
ተስፋ....✍
@Tes_b37
❤️ፍቅር በእኛ❤️
@selefikir
ሚስቴ ስላት ሚስትህ አይደዉም አለችኝ ባልሽ ነኝ ስላት ባሌ አይደለህም አለችኝ እኔ አይኔን ጨፍኜ ሳምናት ማትታመን አንተ ነህ አለችኝ በተግባር ሁሉን ከፍቼ ባሳያት እና ብነግራት ላለመታመኔ አቀረበችልኝ ምክንያት እሺ የቱ ነው ጥፍቴ ሁሉን ነገር ግልፅ ማድረጌ ለነገሩ እንኳንም ቀረችብኝ ምን ይታወቃል አምላኬ ንፁህነቴን አይቶ የተሻለ የምታምነኝ ልሰጠኝ ይሆናል። እንዲህም አይደል የሚባለው ከትላንት ዛሬ ይሻላል ከዛሬ ደግሞ ነገ...
❤️ ፍቅር በእኛ ❤️
@selefikir
?Admin @Tes_b37
ጄን ትባላለች። እድሜዋ 30 ነው። የሳንባ፣ የጉበት እና የአከርካሪ አጥንት ካንሰር
አለባት። ሀኪም የመኖርሽ ተስፋ 2 ከመቶ ብቻ ነው ብሏታል። ከአንድ አመት ባነሰ
ጊዜም እንደምትሞት ተነግሯታል። ይህንን የሰማው ባለቤቷ በፍቺ ተሰናብቷታል።
ብቻዋን ቀርታለች። ጄን ይህን ሁሉ የአለም መከራ ተሸክማ በደስታና በተስፋ
እንደምትኖር ለማሳየት America Got Talent በተባለ ግዙፍ መድረክ ላይ ቀርባ It
is Ok የሚል ሙዚቃ በማቅረብ እንኳን ለራሷ ለምድራዊው ህይወት እንግልቱ ሁሉ
“ምንም ሆነ ምን ሁሉም ለበጎ ነው” የሚል አስተማሪ መልዕክት አስተላልፋለች። --
የፕሮግራሙ ዳኛ ሳይመን እንኳ እንባውን መቆጣጠር አልቻለም ነበር። -- ነገ ደስተኛ
እሆናለሁ ብለህ ዛሬ ነገሮች እንዲጎዱህ አትፍቀድ፣ በየትኛውም ውጣ ውረዶች ውስጥ
ሆነህ ዛሬን ደስተኛ ሆነህ እለፍ ስትል ለሞት ወራት የተቆጠረላት ጄን መክራለች። “I
have two percent chance to servival but two per-cent is not a zero!
Two per-cent is something and I wish people all knew this.” ብላለች።
የፕሮግራሙ መሪም በዚህ አመት ልንሰማው የሚገባን ድንቅ መልዕክት ነው በማለት
አለም በኮረና ቫይረስ እያሳለፈች ያለውን የቀቢጸ ተስፋ ህይወት አስታውሷል። የእኔም
መልዕክት ይሄው ነው፦ ዛሬን በፍቅርና በደስታ እንኑር!
?Admin @Tes_b37
ፍቅር በእኛ @selefikir share
.
ትላንት በህይወትህ ያለፈውን መጥፎ ቀን
ማጥፋትም መቀየርም
መስረዝም አትችልም የምትችለው መቀበል ብቻ ነው።
ትላንትን ኣምነህ ተቀብለህ ዛሬን በደስታ ኑር። አስተውል ዛሬ ኣዲስ
ቀን ነው ከቀኑ ጋር ኣዲስ መሆን ያንተ ፋንታ ነው። !!
የተወለወለ ቤት በጨቀየ ጫማ ብትገባ ወለሉን ታበላሽዋለህ ልክ
እንደዛው በትላንት መጥፎ ሀሳብ ዛሬን ከተቀበልከው ዛሬህ የተበላሸ ይሆናል ።
ተስፋ...✍
@Tes_b37
? ፍቅር በእኛ ?
@selefikir
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated hace 3 semanas, 5 días
Last updated hace 3 semanas
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot
🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹
Last updated hace 1 mes, 1 semana