Tofik Bahiru

Description
Advertising
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 2 months, 1 week ago

Last updated 6 days, 22 hours ago

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ ? @Esat_tv_comment_bot

??ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ??

Last updated 2 months, 3 weeks ago

3 weeks, 3 days ago

ሰይዲና አቡሁረይራ [ረዲየላሁ ዐንሁ] የአላህ መልክተኛ [ﷺ] እንዲህ ማለታቸውን ዘግበዋል: ‐
«አላህ ጀነትን ከፈጠረ በኋላ ጂብሪልን [ዐለይሂ ሰላም] «ሂድና ተመልከታት!» አለው።

ጂብሪል ተመለከታትና እንዲህ አለ: ‐ «በልቅናህ እምላለሁ! ስለርሷ የሰማ ማንም ሰው ወደርሷ መግባቱ አይቀርም።»

ከዚያም አላህ ነፍስ በምትጠላው ነገር ከበባትና «ሂድና ተመልከታት» አለው። ሂዶ ተመለከታትና «በልቅናህ እምላለሁ! ማንም እርሷ ውስጥ አይደባም ብዬ ሰጋሁ!» አለ።

እሳትን የፈጠረ ጊዜም ጂብሪልን «ሂድና እያት» አለው። ሄዶ ተመለከታትና «በልቅናህ እምላለሁ! ስለርሷ የሰማ ማንም ሰው እርሷ ውስጥ አይገባም።» አለ።

ከዚያም አላህ ነፍስ በምትወዳቸው [እኩይ] ስሜቶች ከበባትና «ሂድና ተመልከታት» አለው።

ጂብሪልም ተመለከታትና እንዲህ አለ: ‐ «በልቅናህ እምላለሁ! ማንም ሰው እርሷ ውስጥ ከመግባት አይተርፍም ብዬ እሰጋለሁ።» አለ።»
ኢብኑ አቢዱንያ ዘግበውታል።

1 month ago

ሙቀዲመቱ ባፈድል
📗 ክፍል ሠላሳ አንድ:‐ የዒድ ሶላት (ሶላቱል‐ዒደይን)
📆 ጥቅምት 24/ 2017 ዓ. ል.

1 month ago

በርካቶቻችን በቀልብ ድርቀት ፈተና ውስጥ ወድቀን በጭካኔ ህመም እየተሰቃየን ይሆናል።
አንዳንድ ሰዎች ግን ፈተናቸው ተቃራኒ ነው። በቀልብ ልስላሴና በቀልብ ቅጥነት ስር ወድቀው የሚሰቃዩ አሉ። የነርሱ ስቃይ ከባድ ነው!
:
መከረኛ በሆነው በዚህ ዓለም ውስጥ ቀልበ ቀጭን መሆን ከባድ ነው። የሰብዓዊው ፍጡር እንግልት በጠናበት በዚህ ዓለም እዚህም እዚያም ለሚወድቀው ነፍስ ማዘን መራር ነው። ፀሀይ ወጥታ እስከምትጠልቅ ስንት ዓይነት የሰዎችን ስቃይና ሰቆቃ እናያለን?
ቀልበ ቀጭኖች የሌሎችን ስቃይ እንደራሳቸው ስቃይ ይመለከታሉ። በሰው ሃሳብ ይብሰለሰላሉ። በጭንቀታቸው ይብሰከሰካሉ። በሰዎች ህመም ይታመማሉ። ከምላሳቸውና ከኪሳቸው እምባቸው ይቀድማል።
ሩኅሩኅ ናቸው። ለሰዎች መልካምን ይመኛሉ። በሰው ላይ በሚደርስ ክፉ ነገር ይጨነቃሉ። ሰዎች በእጦት ከተረበሹ እነርሱም ያላቸውን ሰጥተው በእጦት ከሚሰቃዩት ጋር ራሳቸውን ይቦድናሉ። የሚሰጡት ካጡም መለገስ ባለመቻላቸው በመቆጨት በለቅሶ ይመለሳሉ።
:
እነዚህ ሰዎች ጥቂቶች ናቸው። በህይወቴ ከሦስት የማይበልጡ ሰዎች ከነዚህ እንደሚመደቡ እመሰክርላቸዋለሁ። ምቾትን አያውቋትም። በእርግጥ በዓለሙ ስቃይ ይሰቃያሉ። ነገርግን ስቃያቸው ቢበረታም የጀነት ናቸው። እንደውም ያለ ሂሳብ ጀነት ከሚገቡት የበሯ ከፋቾች ናቸው! በክብር የሚገቡበት የግል በርም ሳይኖራቸው አይቀርም!
የአላህ መልክተኛ [ﷺ] እንዲህ ብለዋል: ‐ «ልባቸው እንደ ወፍ ልብ የሆኑ ሰዎች ጀነት ይገባሉ!»
በዚህ ሐዲስ ላይ «የወፍ ልብ ያላቸው» የተባሉት ሩኅሩኅ ሰዎች ናቸው ተብሏል በአንድ ተፍሲር።
አላህ ርኅራኄን ይስጠን!
https://t.me/fiqshafiyamh

3 months, 2 weeks ago

ሙስሊሞች የአላህ ነቢይን [] ለመጥራት ሲፈልጉ ሊከተሉት የሚገባን ስነስርዐት በማስመልከት በቀጥታ ከአላህ የተሰጡ ደንቦች አሉ። እነርሱም የሚከተሉት ናቸው: ‐

? ﴿يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا لَا تَرْفَعُوا أَصْوَاتَكُمْ فَوْقَ صَوْتِ النَّبِيِّ وَلا تَجْهَرُوا لَهُ بِالْقَوْلِ كَجَهْرِ بَعْضِكُمْ لِبَعْضٍ أَنْ تَحْبَطَ أَعْمَالُكُمْ وَأَنْتُمْ لَا تَشْعُرُونَ﴾.

«እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ድምጾቻችሁን ከነቢዩ ድምጽ በላይ ከፍ አታድርጉ፡፡ ከፊላችሁም ለከፊሉ እንደሚጮህ በንግግር ለርሱ አትጩሁ፡፡ እናንተ የማታውቁ ስትኾኑ ሥራዎቻችሁ እንዳይበላሹ (ተከልከሉ)፡፡»

? ﴿إِنَّ الَّذِينَ يُنَادُونَكَ مِنْ وَرَاءِ الْحُجُرَاتِ أَكْثَرُهُمْ لَا يَعْقِلُونَ وَلَوْ أَنَّهُمْ صَبَرُوا حَتَّى تَخْرُجَ إِلَيْهِمْ لَكَانَ خَيْرًا لَهُمْ﴾.

«እነዚያ ከክፍሎቹ ውጭ ኾነው የሚጠሩህ አብዛኞቻቸው አያውቁም፡፡ ወደእነርሱም እስክትወጣ ድረስ እነርሱ በታገሱ ኖሮ ለእነርሱ በላጭ በኾነ ነበር፡፡ አላህም እጅግ መሓሪ አዛኝ ነው፡፡»

? ﴿يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا لَا تَقُولُوا رَاعِنَا وَقُولُوا انْظُرْنَا وَاسْمَعُوا﴾.

«እናንተ ያመናችሁ ሆይ! (ለነቢዩ) ራዒና አትበሉ፡፡ ተመለከትን በሉም፡፡ ስሙም፤ ለከሓዲዎችም አሳማሚ ቅጣት አላቸው፡፡»

? ﴿یَـٰۤأَیُّهَا ٱلَّذِینَ ءَامَنُوۤا۟ إِذَا نَـٰجَیۡتُمُ ٱلرَّسُولَ فَقَدِّمُوا۟ بَیۡنَ یَدَیۡ نَجۡوَىٰكُمۡ صَدَقَةࣰۚ ذَ ٰ⁠لِكَ خَیۡرࣱ لَّكُمۡ وَأَطۡهَرُۚ فَإِن لَّمۡ تَجِدُوا۟ فَإِنَّ ٱللَّهَ غَفُورࣱ رَّحِیمٌ﴾.

«እናንተ ያመናችሁ ሆይ! መልክተኛውን በተወያያችሁ ጊዜ ከመወያየታችሁ በፊት ምጽዋትን አስቀድሙ፡፡ ይህ ለእናንተ መልካም ነው፡፡ አጥሪም ነው፡፡ ባታገኙም አላህ መሓሪ አዛኝ ነው፡፡»

? ﴿لَّا تَجۡعَلُوا۟ دُعَاۤءَ ٱلرَّسُولِ بَیۡنَكُمۡ كَدُعَاۤءِ بَعۡضِكُم بَعۡضࣰاۚ﴾.

«በመካከላችሁ የመልክተኛውን ጥሪ ከፊላችሁ ከፊሉን እንደ መጥራት አታድርጉት፡፡»

#ሶሉ #ዐለነቢ

3 months, 2 weeks ago

ተወዳጃችን [] እንዲህ ይላሉ: –
«ሰኞና ሐሙስ ቀን የጀነት ደጃፎች ይከፈታሉ። እናም አላህ በእርሱ ላይ ምንም የማያጋራ ሰውን በሙሉ ምህረት ይሰጣል፤ በእርሱና በወንድሙ መካከል ቂም የቋጠረ ሰው ሲቀር። አላህም: ‐ 'እነዚህን እስከሚታረቁ ድረስ አቆይዋቸው' ይላል።»
ሙስሊም ዘግበውታል።
:
አስፈሪ ነው። ነገርግን ዐፍዉ በመባባል አደጋውን መሻገር ይቻላል!

3 months, 2 weeks ago

ሱፍያን ኢብኑ ዑየይና [ረዐ] እንዲህ ብለዋል: —
«አምስቱን ሶላቶች የሰገደ ሰው በእርግጥ አላህን አመሰገነ። ከሶላት በኋላ ለወላጆቹ ዱዓ ያደረገ ሰው በእርግጥ አመሰገናቸው።»
ተፍሲር አል‐ቁርጡቢ
t.me/fiqshafiyamh

3 months, 2 weeks ago

ጠቢቡ ሰይዲና ሉቅማን ልጃቸውን ሲመክሩ እንዲህ አሉ: ‐

«ልጄ ሆይ!…
ክፉ በክፉ ይጠፋል የሚልህን ሰው አትስማ።
የሚለው እውነት ከሆነ እስኪ ሁለት እሳቶችን ያንድድና አንዱን በሌላው ያጥፋ!
እሳትን ውሃ እንደሚያጠፋው ክፋትንም መልካምነት ብቻ ያጠፋዋል!»
t.me/fiqshafiyamh

3 months, 2 weeks ago

⚀ ዛሬ ሱረቱል‐ከህፍ ቀርተሃል?
⚁ የጁሙዐ የሰለዋት ዊርድህን ሞልተሃል?
:
የሁለቱም ምላሽ አልሰራሁም ከሆነ እስከ መግሪብ ሁለቱንም ማሳካት ትችላለህና ብትሞክረውስ?!…

3 months, 3 weeks ago

ከዚህ ቀደም በክፍል 9 እና 10 መካከል የተዘለለ ደርስ እንደነበረ ብዙ ተከታታዮች አመልክታችሁን ነበር። በእርማት ሂደት ውስጥ በስህተት ተዘሎ ነበር። እነሆ አሁን ተገኝቶ አጋርተናችኋል። ደርሱ "ባቡ አን‐ነጃሳት" ብሎ የሚጀምር ነበር። በትኩረት ስለምትከታተሉን እናመሰግናለን።

አላህ ተጠቃሚ ያድርገን!

3 months, 3 weeks ago

በ͟አ͟ን͟ድ͟ ወ͟ቅ͟ት͟ እ͟ን͟ዲ͟ህ͟ ተ͟ፅ͟ፎ͟ ነ͟በ͟ር͟

ህዝባችን ይታመማል፤ ነገርግን አይሞትም።
ያንቀላፋል፤ ነገርግን አይተኛም።
ይታለል ይሆናል፤ ነገርግን አይረታም።
:
ከዚህ ቀደም ብዙ አልፏል። በሀዘንና በመከራ የጀመረው የነቢዩ [ﷺ] ትግል፣ ሶሐቦች ነፍስ ከደም የከፈሉበት ውጣ ውረድ፣ በአባቶቻችን ሰቆቃ የተላለፈ የእምነትና የፅናት ምሳሌ፣ በመጨረሻም የሁሉም አበርክቶና ከፍታ በብዙዎች ይዘነጋል!
እያንዳንዱ እምባ ያመነጨው የስኬት ባህር፣ እያንዳንዱ የደም ጠብታ የፈየደው ብሩህ ድል፣ የልሂቃን እንግልት የፈነጠቀው ደማቅ ፀሀይ…
በርካቶች ዘንድ ላይታይ ተደፍኗል። ዛሬ በኢስላም ልጆች ሳይቀር ተዘንግቶ ተስፋም ይቆረጣል!
እነዚያም! ዛሬ መታመማችንን ሲያዩ አፈር ምሶ ግብዐታችንን እንደፈፀመ ቀባሪ፣ በጉድጓድ ውስጥ ከድነውን ጥለውን የሄዱ፣ ከታሪክ ጋር ላንታይ የሰወሩን ይመስላቸዋል!
:
ብዙ ጊዜ በርካቶች ይህንን አድርገዋል። ሙእሚኖች ተላቅሰው "ህዝባቸው" መሞቱን አምነው ተዕዚያ ተቀምጠዋል። መናፍቃንና የሐቅ ጠላቶች አፈር ሲምሱ የቆዩበትን አቧራቸውን ከእጃቸው አራግፈው በድል ደስታ ተራጭተዋል! ይህ ብዙ ጊዜ ተደጋግሞ ተከስቷል!…
:
የኢስላም ታሪክ ፀሀፊው ኢብኑል‐አሲር የታታሮችን በደል ለመፃፍ የሚሆን ጠንካራ ልብ አጥቶ ረዥም ጊዜ ሲቆዝም ቆይቷል። የጠላትን ጭካኔና የሙስሊሙን ኡማ ውርደት ከምፅፍስ «እናቴ ባትወልደኝ ኖሮ! ከዚህ ቀደም ሞቼ ተረስቼ በነበር!» በማለት ጥልቅ ሀዘኑን ገልጿል። «በታሪክ ላይ በየትኛውም! ህዝብ ላይ ያልደረሰ ግፍ» በወቅቱ መከሰቱን አስታውቋል።
ነገርግን ኢብኑል‐አሲር ዛሬ ቢኖር ተታሮች በሙስሊሞች ታሪክ ውስጥ ተውጠው፣ በርካቶች የኢስላም አገልጋዮች ሆነው ማለፋቸውንም ይዘግብ ነበር!
:
ኡመተል‐ኢስላም ለበርካታ ጊዜያት እንዳይኖር ታስቦ ቢደቆስም ወገቡን ቀጥ አድርጎ በሁለቱም እግሮቹ በመቆም አበርክቶውን ቀጥሏል! ለሰው ልጅ መልካም የቆመ መሆኑን በማይረሳው የእዝነት ስልጣኔው ብዙውን ጠቅሟል፤ አቅንቷል፤ አንቅቷል፤ አሰልጥኗል።
:
ኡመቱ ዛሬ መታመሙን አትይ! ለዘመናት በርካታ ጊዜ ታሟል። ህመምን የመቋቋም አቅሙ ብርቱ ስለሆነ ግን በድጋሚ ተነስቷል።
:
ህዝቤ ሆይ! ተወዳጅ፣ ተዋሐድ፣ ንቃ፣ ከዝቅታህ ተነስና ትልልቅ ነገሮችን አልም!…
ተስፋ አትቁረጥ!
ኢስላም ሊያኖር እንጂ ሊጠፋ አልመጣም!
በዙርያው ዐቅለኞችን እንቅልፍ የሚነሳ ሴራ እየተዶለተ ቢሆንም እንኳን የአላህ ፀሀይ ነውና ዝንተዐለም ይኖራል፤ አይከስምም።
[هُوَ ٱلَّذِىٓ أَرْسَلَ رَسُولَهُۥ بِٱلْهُدَىٰ وَدِينِ ٱلْحَقِّ لِيُظْهِرَهُۥ عَلَى ٱلدِّينِ كُلِّهِۦ وَلَوْ كَرِهَ ٱلْمُشْرِكُون]
«እርሱ ያ አጋሪዎቹ ቢጠሉም መልክተኛውን በመምሪያ (መጽሐፍ) በእውነተኛው ሃይማኖትም (በኢስላም) ከሃይማኖት ሁሉ በላይ ይፋ ሊያደርገው የላከ ነው፡፡»

We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 2 months, 1 week ago

Last updated 6 days, 22 hours ago

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ ? @Esat_tv_comment_bot

??ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ??

Last updated 2 months, 3 weeks ago