ከዚም ከዚያ ጉዞ ወደ መልካምነት!

Description
እዚህ Channel ላይ ያስተምራሉና ያዝናናሉ ብዬ የማስባቸውን ማንኛውም አይነት ፅሁፎች ከተለያዩ ቦታዎች እየለቀምኩ አቀርባለሁ። ስታነብ ታውቃለህ፣እራስህን ትመለከታለህ፣ክፉና ደጉን ትለያለክ። እዚህ የሚለቀቁ ፅሁፎች እኔ የተናገርኳቸው እና የፃፍኳቸው ብቻ አይደሉም። ከመፃፍ፣ከሶሻል ሚዲያ እና ከተለያዩ ሰዎች የሰበሰብኳቸው ጭምር ናቸው።
Any comment @jer21
Advertising
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 2 months, 1 week ago

Last updated 6 days, 22 hours ago

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ ? @Esat_tv_comment_bot

??ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ??

Last updated 2 months, 3 weeks ago

9 months, 3 weeks ago

?ሰላም ለእናንተ ይሁን እንዴት አደራችሁ?

"በተቻለኝ መጠን ሁሌ የምሰብካት ስብከት አለችኝ፣ የምሬን! ጠዋት ስትነቃ ተመስገን በል! በረከቶችህን ቁጠር፣ ርዕሷ ነች ይህቺ!!"

"ጧት ስትነሳ ተመስገን በል፣ ምክንያቱም ሞተህ ልታድር ትችል ነበራ! ከአልጋ ወርደህ ስትቆም ተመስገን በል፣ በሆነ ምክንያት የአልጋ ቁራኛ ሆነህ ልትቀር ትችል ነበር!!"

"ከዛ ደግሞ ተነስተህ ስትንጠራራ ተመስገን በል! መንጠራራት ደስ አይልም፣ ተንጠራርተህ ድብርትህን ስታስለቅቅ? ድብርትን እንዲህ ማስለቀቅ እንድትችል አድርጎ የፈጠረህን፣ ይኼን የሰጠህን ተመስገን አትልም?"

"ቀጥለህ የፊኛና የጎረቤቱን ጥያቄ ታስተናግዳለህ ተመስገን በል! አንዱ ወይም ሌላው እንቢ ሊልህ ይችል ነበራ። ሽንትህን ወጥሮህ ስትሸና የሚኖርህን ጤንነትና ዕረፍት ያላቸውን ዋጋስ?"

"መሽናት ባትችል የሚያስከትልብህ ጭንቀትና ህመምስ? የጠጣኸው ውሃ ሽንት ሆኖ መውጣቱ ይሄ የማናውቀው ተዓምር ውስጣችን በመስራቱ ተመስገን አትልም?"

"ከዛ በሗላ ወጥተህ ስትሄድ መንገዱ ሁሉ ጤና ነው፤ ታክሲው፣ ሰዉ፣ ምኑ፣ ለማኙ፣ መነኩሴው... ስታይ ተመስገን በል! ምክኒያቱም ሰጥ አርጋቸው የሚባሉ ጄኔራል ጨለማን ተገን አድርገው በታንክ ገብተው ሀገሩ ፀጥ ብሎ ቢቆይህስ? ምን ታደርግ ነበር?"

"የምግብ ጉዳይስ፣ ተመስገን! እያልክ ብላ። ዊልያም ሼክስፒር እንደሚለው 'እግዜር ምግብ ይሰጥና ሆድ ይከለክላል፤ ወይ ሆድ ይሰጥና ምግብ ይከለክላል' ሊሆንብህ ይችል ነበራ። ለአንተ ግን ጤነኛ ሆድም የሚጥም ምግብም ሰጥቶሃል፤ ተመስገን አትልም?"

"ከዚህ በኋላ ስራ ለመሄድ ትነሳለህ። ሌላ በረከት! ስራ ለመሄድ ሳይሆን ስራ ፍለጋ ለመሄድ ልትወጣ ትችል ነበራ። በረከቶችህን አንድ በአንድ ቁጠር ማለቂያ የለውም። ያለህ ከሌለህ ይበልጣልና ተመስገን በል!"

✍️ ጋሽ ስብሐት ገብረእግዚአብሔር

?መልካም ቀን፤ ቸር ያውለን፤ ቸር ያሰማን?

@kezimkezia

9 months, 4 weeks ago

?ሰላም ለእናንተ ይሁን፤ እንዴት ናችሁ?

የኦቶማን ንጉስ አህመድ ወደ ጦርነት ከመሄዱ በፊት ሚስቱን (ቆንጆዋን ንግሥት) በአንድ ክፍል ውስጥ ቆልፎባት ቁልፉን ለቅርብ ጓደኛው ሙሳ ሰጠው እና "በአራት ቀን ውስጥ ካልተመለስኩ ክፍሉን ክፈት እና ሚስቴን አግባት”ብሎት ፈረሱ ላይ ወጥቶ ወደ ጦር ሜዳ ሄደ።

ከግማሽ ሰዓት በኋላ ንጉሱ ከኋላው አቧራማ ንፋስ እንዳለ አየ። ቆም ብሎ ሲቃኝ ጓደኛው ወደ እሱ በፍጥነት እየሮጠ ሲመጣ ተመለከተ።

"ምነዉ ምን ሆንክ?" ብሎ ንጉሱ ጠየቀ።

በጣም ከመሮጡ የተነሳ ትንፋሹ እየተቆራረጠ ጓደኛው ሙሳ “የተሳሳተ ቁልፍ ነው የሰጠኸኝ” ሲል መለሰ።

ምንድን??? ብሎ አይቶት በድንጋጤ እና በመገረም አየዉ።

ቁልፎቹን ለመሞከር ለ4 ቀናት ይቅርና ለ1ሰአት እንኳን አልጠበቀም።

✍️ አንዳንዴ ጠላትን ስንፈራና ስንሰጋ ገዳያችን እዛ ከጉያችን የጓደኛነትን የወዳጅነትን ጭንብል ለብሱ እናገኘዋለን።

እናም "ጠርጥር እንዳትመነጠር" ነው ጨዋታው።

?መልካም ቀን፤ ቸር ያውለን?

@kezimkezia

1 year, 4 months ago
***?***ሰላም ለእናንተ ይሁን እንዴት ናችሁ***?***

?ሰላም ለእናንተ ይሁን እንዴት ናችሁ?

በዓለም ታዋቂዋ የፋሽን ዲዛይነር እና ደራሲ "ክሪስዳ ሮድሪጌዝ" በካንሰር ህመም ተሰቃይታ ከመሞቷ በፊት ይህን ጽሁፍ ጽፋ ነበር...

  1. በአለማችን ውዱ ብራንድ መኪና ጋራዥ ውስጥ አለኝ፤ አሁን ግን በዊልቸር ነው የምጓዘው።

  2. ቤቴ በሁሉም ዓይነት ብራንድ ልብሶች ፣ ጫማዎች እና ውድ እቃዎች የተሞላ ነው። ነገር ግን ሰውነቴ በሆስፒታሉ በተዘጋጀ ትንሽ አንሶላ ተጠቅልሏል።

  3. በባንኬ ውስጥ በቂ ገንዘብ አለ፤ አሁን ግን ከዚህ ገንዘብ ምንም ጥቅም እያገኘሁ አይደለም።

  4. ቤቴ እንደ ቤተ መንግስት ነው ግን በሆስፒታል ውስጥ ባለ አልጋ ላይ ተኝቻለሁ።

  5. ከአንድ ባለ አምስት ኮከብ ሆቴል ወደ ሌላ ባለ አምስት ኮከብ ሆቴል መሄድ እችላለሁ።

አሁን ግን በሆስፒታል ውስጥ ከላቦራቶሪ ወደ ላብራቶሪ እየተዘዋወርኩ ነው።

  1. በመቶዎች ለሚቆጠሩ ሰዎች ፈርሜያለሁ፤ አሁን ግን የዶክተሩ ማስታወሻ ነው የኔ አውቶግራፍ።

  2. ፀጉሬን ለማስጌጥ ሰባት የውበት ባለሙያዎች ነበሩኝ፤ ዛሬ በራሴ ላይ ፀጉር የሚባል ነገር የለም።

  3. በግል ጀት ወደፈለግኩበት ቦታ መብረር እችል ነበር፤ አሁን ግን ወደ ሆስፒታል በረንዳ ለመድረስ የሁለት ሰዎች እርዳታ እፈልጋለሁ።

  4. ብዙ ምግብ ቢኖርም፥ የእኔ አመጋገብ ግን በቀን ሁለት ክኒን እና ማታ ደግሞ ጥቂት ጨዋማ ውሃ ነው።

ይህ ቤት ፣ ይህ መኪና ፣ ይህ ጀት ፣ ይህ የቤት ዕቃ ፣ ብዙ የባንክ አካውንቶች እንዲሁም ታዋቂነት ምንም አልጠቀሙኝም። ከእነዚህ ውስጥ ምንም እፎይታ ሊሰጠኝ አልቻለም።

እውነተኛ ህይወት፥ ብዙ ሰዎችን ማጽናናት እና ፊታቸው ላይ ፈገግታ እንዲሰፍን ማደረግ ማስቻል ነው።

"ከሞት በስተቀር ምንም እውነታ የለም!!"

?መልካም ምሽት! የነገ ሰው ይበለን?

@kezimkezia

2 years, 1 month ago
2 years, 5 months ago

?ሰላም ለእናንተ ይሁን እንዴት አደራችሁ?

"በመታነጽ ላይ ሳለህ የቦዘንክ ቢመስላቸው አትደነቅ!"

ድሮ እኛ ሃይ ስኩል ስንማር 'ከመማር ይልቅ ፋብሪካ መሥራት ይሻላል' ብለው ትምህርት አቋርጠው ሥራ የገቡ ጓደኞቻችን ነበሩ።

እነዚህ ጓደኞቻችን ወድያው በወሩ ደመወዝ አገኙ፤ ልብስ ቀየሩ። ሲቆዩ ቤት ተከራዩ፤ አልጋና ፍራሽ ፣ ቁምሳጥን ፣ ወንበርና ጠረጴዛ ገዙ። ጓደኛ ያዙ፤ ኬክ ጋበዙ። ኋላም አንዳንዶቹ አግብተው ሌሎቹም በውጭ ወለዱ።

ያኔ ዩኒቨርሲቲ ከገባሁ በኋላ አንዱ ወዳጄ አገኘኝና "አሁንም እየተማርክ ነው?" አለኝ። አዎ! ነበር መልሴ። "አይደክምህም? አይሰለችህም?" አለኝ። "አሁን እኮ ልጨርስ ነው" አልኩና ተለየሁት።

ከዓመት በኋላ እኔ የመጀመሪያ ዲግሪዬን ይዤ ሥራ ስጀምር የወዳጄ ደመወዝ የእኔን ሩብ ያህል ነበር። ከብዙ ዓመታት በኋላ አንድ ምሽት ላይ ወዳጄን አገኘሁት። "ከየት ነው?" ስለው "ከትምህርት" አለኝ። የማታ ትምህርት ጀምሮ ነበር። በቀን "አይሰለችህም?" ያለኝን እሱ በማታ መትጋት ጀምሮበት ኖሯል። "ህምምም..." ብዬ "ምን ያህል ጊዜ ይፈጃል?" ስለው እኔ ቀን የተማርሁትን እጥፍ ጊዜ ጠራልኝ።

አንዳንዱ እንዲህ ነው። መጀመሪያ ሳይታየው ኋላ ከረፈደ እጥፍ ዋጋ ሊከፍል ይገደዳል። ስኬት ቀድሞ በመራ አይደለም። ከእውቀት ሥራን ባስቀደመም አይደለም። ሥራ በዕውቀት ካልሆነ ልፋት ነው።

6ተኛ ፎቅ ላይ በፓምፕ እየተገፋ ኮንክሪት ሲሞላ አይተሃል? ያ በእውቀት የሚሠራ ነው። ያለእውቀት የሚሠራው ግን በባሬላ እያጋዘ ይደክማል።

ትጋት እና ልፋት ይለያያሉ። ትጋት የእውቀት ሥራ፤ ልፋት ደግሞ ተቃራኒው ነው። ትጋ እንጂ አትልፋ!

በልፋት የትም አትደርስም። ይልቅ ጭንቅላትህን አጎልምስ።

?አየህ አንተ ስትታነጽ ፣ ስትተጋ ማንም ልብ አይልህም። ያንተ ራስን ማነጽ አርቀው ለማያስቡት ቦዘኔነት ነው። ሲያዩህ መሬት አትቆፍርም ፣ እንጨት አትልግም ፣ ምስማር አትመታም ፣ ልብስ አትሰፋም ፣ ዳቦ አትጋግርም ፣ መርፌ አትወጋም። ለእነርሱ አንተ እየቦዘንክ ነው።

መጨረሻ ተሳክቶልህ ፣ በኑሮ ከፍ ብለህ ሲያዩህ ግን "እድለኛ ነህ" ይሉሃል። እውነት ነው እድል ማለት ስትተጋ ሳትታይ የተሻለ ውጤት ማስመዝገብ መቻል ነው።

ስንዴዋ አፈር ውስጥ ገብታ ስትበሰብስ ውጤቱን ለሚያውቀው ለገበሬው እንጂ ለሌላው ብክነት ነው። ሌሎች ውጤቱን የሚያዩት ስንዴዋ ስታፈራ ነው።

ዘሩን የሚያናንቁ በፍሬው ቢደነቁ አትገረም።

አንተ ግን ለሌሎች ታይታ ሳይሆን በገባህ መንገድ አቅጣጫህን መርጠህ ትጋ!

አንድ ቀን ውጤቱን ሲያዩ "እድለኛ ነህ" ይሉሃል።

ጌታቸው ከበደ

ከእዚሁ ከቴሌግራም መንደር የተወሰደ!

?መልካም ቀን፤ ቸር ያሰማን፤ ቸር ያውለን?

@Kezimkezia

2 years, 5 months ago

?ሰላም ለእናንተ ይሁን እንዴት አደራችሁ?

"ጉንዳኖች ውሀ ሲሻገሩ አይተህ ታውቅ? ከሆነ በውሃው ላይ ተያይዘው ተያይዘው ይቆማሉ። ጉንዳኖቹ ተያይዘው በወንዝ ላይ በሚሰሩት መንገድ ሌሎች ብዙ ጉንዳኖች ይሻገራሉ፤ ተያይዘዉ ይሻገራሉ። ተደጋግፈው አስፈሪውን ወንዝ ይሻገሩታል። ባይያያዙና ባይደጋገፉ ግን አይቻላቸውም። አንዲት ጠብታ ዝናብ ለአንድ ጉንዳን ውቅያኖስ ብትሆንም ብዙ ጉንዳኖች አንድ ላይ ከተያያዙ ግን ውቅያኖስ መሻገር ይችላሉ።" ✍️ዴርቶጋዳ

ፍቅር የበጎ ነገሮች መክፈቻ ነው፡፡ በፍቅር ያልተዘጋ ሴራ የለም፡፡ በፍቅር ያላበቃለት ጦርነት የለም፡፡ በፍቅር አደብ ያልገዛ ጦረኛ የለም፡፡ ፍቅር የነገሮች መጠቅለያ ፣ የበጎ ነገሮች መሠረት ነው፡፡ የሠው ልጅ ጭንቅላቱን በፍቅር ከሞላ ክፉ ሃሳቦችና ተልካሻ ሴራዎች ወደእሱ ድርሽ አይሉም፡፡ በፍቅር የተሞላ ጭንቅላት ትርፉ በፍቅር መኖር ነው፡፡

"ጦርነት በሕይወትና በቁስ ላይ ከሚያስከትለው ጥፋት የበለጠ የሚያስጠላ ነገር በዚህ ዓለም ያለ አይመስለኝም። የሰው ልጅ በመካከሉ የሚፈጠሩትን ልዩነቶች በውይይትና በሠላም የሚፈታበት ቀን መች ይመጣ ይሆን? ያ ቀን ናፈቀኝ።" ✍️በዓሉ ግርማ

?መልካም ቀን፤ ቸር ያሰማን፤ ቸር ያውለን?

@Kezimkezia

2 years, 5 months ago

?ሰላም ለእናንተ ይሁን እንዴት አረፈዳጅሁ?

"የምትጓዝበት መንገድ ወደ ጥሩ አሊያም ወደ መጥፎ የሚመራው አንተን እንጂ ተመልካችህን አይደለም።

የምትለብሠው ልብስ የሚያሞቀውም ሆነ የሚያበርደው አንተኑ እንጂ የሚያይህን አይደለም።

የምትበላው ምግብ የሚጣፍጠው ወይም የሚመረው አንተን እንጂ ሌላውን አይደለም።

እናም አንድን ነገር ለታይታ ማድረግ ሞኞች የፈለሠፉት የመከበር ሙከራ መሆኑን ተረድተህ በቀጥተኛው መንገድ ለመጓዝ ሞክር።"

Bruce Lee

?መልካም ቀን፤ ቸር ያሰማን፤ ቸር ያውለን?

@Kezimkezia

2 years, 5 months ago

?ሰላም ለእናንተ ይሁን እንዴት አመሻችሁ?

ሰውን ከክፋት ፣ ከስስት ፣ ከዕብሪት ፣ ከትዕቢት ጋር የሚያፋቅረው የመጀመሪያው ምክንያት "ዝንጋዔ ሞት" ነው። ሞትን ያህል ዕዳ መቃብርን ያህል እንግዳ መዘንጋት ሰው በሀብቱ ና በጉልበቱ እንዲመካ ይገፋፋዋል፤ ማን አህሎኝነት ይወርሰዋል።

ይህንን ከመሰረቱ የተረዱ ጥንታዊ ሮማውያን ለገዥዎቻቸው አንድ አዛውንት ይመድቡ ነበር።

ገዥው ማለዳ ተነስቶ ቁርስ ሲጎርስ ያ አዛውንት ድንገት ዘው ብሎ በመግባት አንዲት ቃል ተናግሮ ይወጣል:-
'
'
'

"ትሞታለህ!"

ሮማዊ ጀኔራል ከድል መልስ በሰረገላ ሆኖ ወደ ከተማው ሲመለስ ህዝቡ ዘንባባ ይዞ በክብር ይቀበለዋል። ምርኮውንም እያግተለተለ ሲያልፍ በዚህ ደስታ መካከል ያ አዛውንት ከጄኔራሉ ጀርባ መጥቶ:- " ትሞታለህ!" ብሎት ያልፋል።

ሞትን ማሰብ የመታበይ መድኅን ነው የመታበይ ብቻ ሳይሆን የማግበስበስ ፍቱን መድሃኒት ነውና።

ዓለማየሁ ገላጋይ
?መለያየት ሞት ነው

?መልካም አዳር የነገ ሰው ይበለን?

@kezimkezia

2 years, 5 months ago

?ሰላም ለእናንተ ይሁን እንዴት አደራችሁ?

በቀናችን ውስጥ የሚገጥሙንን ማናቸውም የሕይወት ሁኔታዎች ወደድንም ጠላንም ማስቀረት አንችልም፡፡ አንዳንድ ቀኖች በጣም ደስተኛ ያረጉናል፤ አንዳንዶቹ ደግሞ ይበልጥ ፈታኝ ይሆኑብናል።

የተፈጠረውን ማንኛውንም ነገር መቀበል እና ከሁኔታው ጋር እርቅ መፈጠር ግን ብልሀት ነው፡፡ በዚህ ታላቅ የሕይወት ሚስጥር ለመቆየት ከትላንት ጭንቀቶች መላቀቅ አለብን፤ ትኩረታችንን ወደ አሁን መልሰን ማደረግ ምንችለውን ማስተዋል ይገባናል፤ በነበር እና በይሆናል መጨነቅ ችግራችንን አንድ እርምጃ አይፈታልንም፡።

እራስህን ለሚመጣው አዲስ እድል ክፈት፤ በዚህ ውድ ጊዜ እራስህን ሁን፤ ትናንት ቀድሞውኑ አልፏልና ያለፈውን ተወው። በእያንዳንዱ አዲስ ቀን ድንቅ ነገር እንደሚፈጠር አስተውል። በቀንህ የሚገጥምህን ምንም ነገር ለመቀበል ዝግጁ ሁን።

ሕይወትን አስደሳች እና ቀላል አርጎ መኖር ይቻላል። ግን የተሸከመከውን የሀሳብ ክብደት ለመተው ፈቃደኛ መሆን ይጠበቅብሀል፤ የሕይወት እውነተኛ ክስተት አሁን ነው። አሁን ባለህ ጊዜ ሰላም ፍጠር፤ ዛሬን እንደዛሬ በአዲስ ለመመልከት ትናንትህን መልቀቅ ይኖርብሀል።

ቀንህን የደስታህ ምንጭ አድርጋት።
አንተ አሁን ላይ ሙሉ ሰው ነህ፤ አንቺም ነሽ፤ ዘና በል፤ ዘና በይ።

?መልካም ቀን፤ ቸር ያሰማን፤ ቸር ያውለን?

@kezimkezia

2 years, 6 months ago
***?***ሰላም ለእናንተ ይሁን እንዴት አመሻችሁ***?***

?ሰላም ለእናንተ ይሁን እንዴት አመሻችሁ?

?መልካም አዳር፤ የነገ ሰው ይበለን?

@Kezimkezia

We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 2 months, 1 week ago

Last updated 6 days, 22 hours ago

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ ? @Esat_tv_comment_bot

??ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ??

Last updated 2 months, 3 weeks ago