Why Pay for Entertainment? Access Thousands of Free Downloads Now!

ትምህርት በቤቴ®

Description
A channel created for sharing

🔺study tips,
🔺short notes,
🔺tutorials,
🔺educational news,
🔺life tips and some motivational quotes ...


Buy ads: https://telega.io/c/AAAAAFAvYe4hmoy1ouXbBA
📩 For comment- @Tmhert_bebete_info_bot
Advertising
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated hace 1 día, 17 horas

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated hace 5 días, 6 horas

Last updated hace 5 días, 19 horas

4 дня, 4 часа назад
ትምህርት በቤቴ®
4 дня, 4 часа назад
ዲላ ዩኒቨርሲቲ በጌዴኦ ዞን ለሚገኙና ዘንድሮ …

ዲላ ዩኒቨርሲቲ በጌዴኦ ዞን ለሚገኙና ዘንድሮ የመልቀቂያ ፈተና ለሚወስዱ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የማጠናከሪያ ትምህርት መስጠት ጀመረ፡፡

ዩኒቨርሲቲው በበጎ ፍቃደኛ መምህራን በመታገዝ በተለያዩ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለሚገኙ ተማሪዎች የማጠናከሪያ ትምህርት ለመስጠት የማስጀመሪያ መርሐግብር አከናውኗል፡፡

በጉዲኦ ዞን ከሚገኙ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መካከል አምስት ትምህርት ቤቶች ላለፉት ሦስት ዓመታት አንድም ተማሪ ወደ ዩኒቨርሲቲ አለማሳለፋቸውን የዲላ ዩኒቨርሲቲ የትምህርት እና ስነ-ባህሪ ተቋም ያደረገው ጥናት ያሳያል፡፡

በመሆኑም የማጠናከሪያ ትምህርቱ በጌዴኦ ዞን የሚታየውን ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገቡ ተማሪዎች ቁጥር ማነስን ለማሻሻል ትልቅ ፋይዳ ይኖረዋል ተብሏል፡፡

የማጠናከሪያ ትምህርቱ ለአንድ ወር ከአንድ ሳምንት የሚቆይ ሲሆን፤ በተመረጡት ትምህርት ቤቶች አርብ፣ ቅዳሜ እና እሁድ የሚሰጥ መሆኑ ተገልጿል።

❤️ @temhert_bebete

4 дня, 9 часов назад
[***🔥*****ExitExamAI.et**](http://%F0%9F%94%A5ExitExamAI.et/)***🔥***

🔥ExitExamAI.et🔥

ሰኔ 14/2016 ለሚጀመረው የመውጫ ፈተና አርቴፊሻል ኢንተለጀንስን መጠቀም ለተሻለ ውጤት! ካለው የፍላጎት መጠን የተነሳ ለ April 23, ተይዞ የነበረው ይፋዊ የማስጀመርያ ቀንና ፈተናው የሚጀመርበትን ግዜ ከግምት ውስጥ በማስገባት ወደ May 01, 2024 (ሚያዝያ 23፣ 2016) የተዛወረ መሆኑን እንገልጻለን። ቀድመው በመመዝገብ ቦታዎን ይያዙ!

ለፈተናው ትዘጋጁ ዘንድ ChatGPTን4.0 በመሳሰሉ AI ሞዴሎችን በመጠቀም የተዘጋጀዉ ExitExamAI.et ለቅድመ ምዝገባ ክፍት መሆኑን ስንገልጽ በደስታ ነው!

የተለያዩ ኢንተርናሽናል ሞዴሎች በ AI የተደገፉ የጥናት ማቴሪያሎች፣ አጠቃላይ የጥያቄ ባንኮችንና የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና መሰናዶዎን ወደ ለከፍተኛ ደረጃ ለማድረስ ይረዳል።

ከታች ያለው ድህረ ገጽ በመጠቀም “join” የሚለውን በመጫን ቀድመው ይመዝገቡ!

ድህረ ገጽ፡ https://exitexamai.et

🚀 ExitExamAI.et will be officially launched on May 01, 2024!🚀

We're thrilled to announce that ExitExamAI.et has officially launched and is open for waitlist registrations! Considering the official exam date, we moved the released date from April 23, 2024 to May 01, 2024.

The AI models offers AI-driven study materials, question banks, international exams, previous models and question along with engaging daily challenges.

Visit: https://exitexamai.et/

Tg: @ExitExamAI

1 неделя, 5 дней назад

የተሻለ ውጤት የሚያመጡ  ተማሪዎች የአጠናን ልምዳቸው ምን ይመስላል**

📢 12 ወሳኝ ነጥቦች

📖1 ጥናት ከመጀመራቸው በፊት ለምን ዓላማ እንደሚያጠኑ ቀድመው ዓላማ ያስቀምጣሉ።
ይህ ማለት ምን ለማወቅ እንደሚያጠኑ ቀድመው ያቅዳሉ።

📖 2 መፅኃፍ ገልጠው ጥናት ከመጀመራቸው በፊት ስለሚያጠኑት ርዕሰ ጉዳይ የራሳቸውን ግምት ያስቀምጣሉ። መፅሀፍ ገልጠው ጥናት ከጀመሩ በኃላ የነበራቸውን ግምት እያጠናከሩ...የተሳሳተው
ን እያስተካከሉ ይጓዛሉ።

📖3 ሲያጠኑ ያገኙትን አንኳር ነጥብ አጠር አድርገው ማስታወሻቸው ላይ ያሰፍራሉ።

📖4 አንብበው ለ መረዳት ያስቸገራቸውን ነጥብ /ሀሳብ/ ደጋግመው ያነባሉ....

📖 5 ጥናት ከ መጀመራቸው በፊት ማጥናት ስለ ፈለጉት ርእሰ ጉዳይ ጥያቄዎች ይፋጥራሉ። መፅኃፍ ገልጠው ጥናት ከጀመሩ በሃላ ለጥያቄዎቻቸው መልስ ይፈልጋሉ እንጂ ሁሉም ነገር በ ማንበብ ጊዜያቼውን አያጠፉም።

📖6 ሲያነቡ ያገኙትን አዲስ ሀሳብ ወይም መረጃ ከ አሁን በፊት ከሚያወቁት ጋር አብሮ ሊሄድ የሚችል መሆኑን እና አለመሆኑን ይመረምራሉ::

📖7 በ አንድ ጊዜ ብዙ ነገር ለ ማጥናት አይሞክሩም፡፡ በ አንድ ጊዜ ብዙ ነገር ለ ማጥናት መሞከር ትርፉ ድካም መሆኑን ተረድተውታል፡፡

📖8 ሁልጊዜም ቢሆን ለትምህርት ጉዳዮች የሚጠቀሙበት የተለየ ጊዜ አላቸው፡፡

📖9 ያሰቡትን ነገር ተግባራዊ ለማድረግ ቁርጠኝነት አላቸው...አያፈገፍጉም፣ አያቅማሙም፡፡

📖10 ሲያጠኑ የሚከብዳቸውን ክፍል ቅድሚያ ሰጥተው ያነባሉ፡፡

📖11 ተባብሮ በመስራት ያምናሉ፡፡ ያግዛሉ፣ ይጠይቃሉ፡፡

📖12 እራሳቸው ይገመግማሉ፡፡ ደካማ ጎናቸዉ በፍጥነት ያስተካክላሉ፡፡**

❤️ @temhert_bebete
❤️ @temhert_bebete

1 неделя, 6 дней назад
1 неделя, 6 дней назад
2 недели, 4 дня назад
ትምህርት በቤቴ®
2 недели, 4 дня назад
ትምህርት በቤቴ®
2 недели, 4 дня назад
ትምህርት በቤቴ®
3 недели, 5 дней назад

የክብር ዶክትሬት ዲግሪ አሰጣጥ

"ግልጽ የሆነ መመርያ እስከሚወጣ ድረስ የክብር ዶክትሬት እንዳይሰጥ ተከልክሏል።"
- የትምህርት ሚኒስትሩ

የተበታተነ አሠራርን ለመቅረፍ ግልጽ የሆነ መመርያ እስኪወጣ ድረስ ዩኒቨርሲቲዎች የክብር ዶክትሬት የሚባል ነገር መስጠት እንዲያቆሙ እንደተነገራቸው የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ገለፁ፡፡

ሚኒስትሩ ይህንን የተናገሩት ‹‹የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ "የዶክትሬት ዲግሪና የክብር ዶክትሬት ዲግሪ ሽልማት በኢትዮጵያ" በሚል ጭብት ላይ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በተካሔደ ምሁራዊ ውይይት ወቅት ነው።

በኢትዮጵያ የክብር ዶክትሬት ሲሰጥ በተበታተነ ሁኔታ በመሆኑ ዩኒቨርሲቲዎች መስጠት እንዲያቆሙ ውሳኔ መተላለፉን ሚኒስትሩ አስረድተዋል፡፡

ትምህርት ሚኒስቴር የክብር ዶክትሬት ዲግሪ አሰጣጥን በተመለከተ መመርያ እያዘጋጀ መሆኑንና መመርያውንም በዚህ ዓመት አጠናቆ ለመጨረስ ሒደት ላይ እንደሆነ ሚኒስትሩ አክለዋል፡፡

በኢትዮጵያ እስካሁን 79 ሰዎች የክብር ዶክትሬት ዲግሪ እንደተሰጣቸው አስረድተው ከነዚህም 68 በመቶ የሚሆነው ለክልል ሰዎች የተሰጠ እንደሆነ ገልጸዋል።

በመድረኩ የመነሻ ጽሑፍ ያቀረቡት ፕ/ር ማስረሻ ፈጠነ በበኩላቸው በዓለም አቀፍ ደረጃ ዩኒቨርሲቲዎች የክብር ዶክትሬት ዲግሪ ሲሰጥ አካዳሚያዊ ያልሆነ ዕውቅናን በመንተራስ እንደሆነና ተሸላሚዎችም ካላቸው ክህሎት፣ ስብዕና እንዲሁም ያበረከቱት አስተዋጽኦ ጋር በተያያዘ መሆኑን ጠቁመዋል።

በዓለም አቀፍ ደረጃ ዩኒቨርሲቲዎች የክብር ዶክትሬት ዲግሪ አሰጣጥን የተመለከተ መመርያ እንዳላቸው አንስተዋል።

በኢትዮጵያ በአሁኑ ጊዜ በርካታ ሰዎችን እያሳሰበ የመጣው ጉዳይ ዩኒቨርሲቲዎች የራሳቸው ሰው የሚሉትን ብቻ በመምረጥ የክብር ዶክትሬት እየሰጡ መሆኑ ነው ብለዋል፡፡

የክብር ዶክትሬት ዲግሪን ከዩኒቨርሲቲዎች የሚያገኙ ሰዎች ጭምር እንደመጠሪያ እንደሚጠቀሙበትና ይኼም በጣም የተሳሳተ ነገር እንደሆነ ገልጸው፣ በርካታ የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎችም ይኼንን ድርጊት እንደሚፈጽሙ አስታውሰዋል፡፡

ዩኒቨርሲቲዎች የክብር ዶክትሬት ዲግሪ የሰጧቸው ሰዎች ያልተገባ ድርጊት ከፈፀሙ፣ የክብር ዶክትሬት ዲግሪውን መንጠቅ እንደሚችሉ ጠቁመዋል፡፡ #ሪፖርተር

❤️ @temhert_bebete

We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated hace 1 día, 17 horas

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated hace 5 días, 6 horas

Last updated hace 5 días, 19 horas