ትምህርት በቤቴ®

Description
A channel created for sharing

🔺study tips,
🔺short notes,
🔺tutorials,
🔺educational news,
🔺life tips and some motivational quotes ...


Buy ads: https://telega.io/c/temhert_bebete
📩 For comment- @Tmhert_bebete_info_bot
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 2 months ago

Last updated 1 month, 4 weeks ago

ይህ ስለ Manchester United መረጃዎችን የሚያገኙበት የ Telegram ቻናል ነው 🇪🇹
--------------------------------------------------------------
☞︎| ስለ ማንቸስተር ዩናይትድ ትኩስ መረጃዎች
☞| ቀጥታ ስርጭቶች ከየስታድየሞቹ
☞| የዝውውር ዜናዎች
☞| ስለ ማንችስተር ዩናይትድ ታሪኮች

📩 ለማስታወቂያ ስራ DM :- @Marcoabdu

Last updated 3 weeks, 3 days ago

2 weeks, 3 days ago

#EXITEXAM #note

ትምህርት ሚኒስቴር የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ ተግባራዊ ማድረግ ከጀመራቸው ስራዎች አንዱ የሆነ የተመራቂ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና ከጥር 26 ቀን 2017 ዓ/ም ጀምሮ ይሰጣል።

⚡️በፈተና ወቅት ከተፈታኝ ተማሪዎች ምን ይጠበቃል ?

👉🏾 ተፈታኞች ወደ መፈተኛ ክፍል ሲመጡ ማንኛውም አይነት ስልክ፣ ስማርት ሰዓት ፣ ታብሌት ፣ ላፕቶፕና ... ወዘተ ተመሳሳይ ኤክትሮኒክ ቁሳቁስ መያዝ በፍፁም የተከለከለ ነው።  (ይዞ የተገኘ ፈተናው /ውጤቱ ተሰርዞበት በቀጣይ ጊዜ እንዲቀመጥ ይደርጋል)

👉🏾 ፈተና ከመጀመሩ ከ30 ደቂቃ በፊት መፈተኛ ክፍል መገኘት አለባቸው ይህም ማለት ከጥዋቱ 2፡00 በፊት ፤ ከሰዓት ደግሞ ከ8፡00 በፊት ተፈታኞች መገኘት አለባቸው።

👉🏾 ተፈታኞች ለፈተና ሲመጡ ID መያዝ ያለባቸው ሲሆን User Name እና Password lower-case and upper-case ፊደላትን ለይተው በጥንቃቄ መያዝ አለባቸው።

👉🏾 ተፈታኞች ፈተና ከተጀመረ በኃላ ከ30 ደቂቃ በፊት ከፈተናው ክፍል መውጣት የለባቸውም።

👉🏾 ተፈታኞች ፤ ፈተናውን የሚያስፈትኑ መምህራን በሚያሳዩት ቦታ ብቻ መቀመጥ አለባቸው።

👉🏾 ሁሉም ተፈታኝ እንዲቀመጥ የተመደበበት የራሱ ኮምፒውተር ላይ ብቻ ተቀምጦ መክፈትና መጠቀም አለበት።

👉🏾 በፈተና ክፍል ውስጥ መነጋገር እና ከቦታ ቦታ መዘዋወር በፍፁም የተከለከለ ነው። እንዲሁም ማንኛውም ተፈታኝ ከጎኑ ያለውን ተማሪ ኮምፒውተር በፍፁም ማየት የለበትም።

👉🏾 ምንም ዓይነት ወረቀት ወደ መፈተኛ ክፍል ይዞ መምጣት አይቻልም።

👉🏾 ተፈታኞች በምንም ሁኔታ መኮርጅም ሆነ ማስኮርጅ ተግባር ላይ ቢሳተፉ እርምጃ ይወሰድባቸዋል።

👉🏾 ሁሉም ተፈታኞሽ ለፈታኝ መምህራንና ለአስተባባሪዎች  መታዘዝ ያለባቸው ሲሆን የፈተናው ደንብ እና ስርዓት ተገዢ መሆን ይጠበቅባቸዋል።

👉🏾 በድጋሚ ተፈታኞች የፈተና መግቢያ ትኬት (Exit Exam Entry Ticket) መያዝ ይጠበቅባቸዋል።

NB.  ሁሉም ተፈታኞች ወደ መፈኛ ክፍል ተፈትሸው እንዲገቡ የሚደረግ ሲሆን ማንኛውም ተፈታኝ ከፀጥታ ኃይሉ ጋር በፍተሻ ወቅት ይሁን ሥርዓት ለማስያዝ በሚደረግ እንቅስቃሴ እንቅፋት ሆኖ ከተገኘ ከመፈተኛ አከባቢ እንዲገለል ተደርጎ በቀጣዩ የመውጫ ፈተና መስጫ ወቅት እንዲቀመጥ ይፈቀድለታል።

⚡️ከፈታኝ መምህራን የሚጠበቅ

👉🏾 የተፈታኝ ተማሪዎችን ID በአግባቡ በማረጋገጥ ወደ ክፍል እንዲገቡ ማደረግ ይጠበቅባቸዋል።

👉🏾 ተፈታኝ ተማሪዎችን በሥም ዝርዝራቸው መሠረት ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል።

👉🏾 ፈታኝ መምራህን የተማሪዎችን አቴንዳንሰ ይወስዳሉ ፤ ተማሪዎችን ፊርማ ያስፈርማሉ።

👉🏾 በፈተና ክፍል ውስጥ ደምጽ እንዳይሰማ፣ ተማሪዎች ከቦታ ቦታ እንዳይዘዋወሩ ተገቢውን ቁጥጥር ማድረግ አለባቸው።

👉🏾 የፈተናው አጠቃለይ ሂደት በትኩረት መከታተል አለባቸው።

👉🏾 በህመም ምክንያት ተማሪዎች ከክፍል መውጣት ቢፈልጉ ከሱፐርቨዘር ጋር በመነጋገር አስፈላጊውን እርዳታ ያደርጋሉ።

👉🏾 ተማሪዎች በጎናቸው ያለውን ሌላ ኮምፒውተር እንዳይመለከቱ መቆጣጠር አለባቸው።

👉🏾 ተማሪዎች ፈተናው ከተጀመረ ከ30 ደቂቃ በፊት እንዳይወጡ መቆጣጠር ይጠበቅባቸዋል።

👉🏾 ሲኮርጂ ወይንም ሲያስኮርጅ የተገኘ ተማሪ ከመፈተኛ ክፍል እንዲወጣ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል።

👉🏾 ፈተናው ከጀመረ 15 ደቂቃ በኃላ የሚመጣ ተማሪ እንዲገባ ማድረግ የላባቸውም።

👉🏾 የፈተና አፈጻጸም ሪፖርት ለሱፐርቨዘር ማቅረብ

🌺 መልካም ፈተና 🌺

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የትምህርት በቤቴ ቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ!
https://t.me/temhert_bebete
https://t.me/temhert_bebete

2 weeks, 5 days ago

የኦሮሚያ ክልል የ2017ዓም 1ኛ ሴሚስተር ሞዴል ፈተና

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የትምህርት በቤቴ ቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ!
https://t.me/temhert_bebete
https://t.me/temhert_bebete

2 weeks, 6 days ago

#ExitExam

176 ሺሕ ተማሪዎች የመውጫ ፈተናን ለመውሰድ መመዝገባቸው ተገለጸ

👉ፈተናው ከጥር 26 እስከ 30 ድረስ ይሰጣል

ጥር 23/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በ2017 ዓ.ም አጋማሽ ላይ የሚሰጠውን የቅድመ ምረቃ ፕሮግራሞች የመውጫ ፈተና ለመውሰድ 176 ሺሕ ተማሪዎች መመዝገባቸውን ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል።

ፈተናውን በድጋሚ የሚወስዱትን ጨምሮ በጠቅላላው 176 ሺሕ ተማሪዎች የመውጫ ፈተናውን ይወስዳሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ በትምህርት ሚኒስቴር የአካዳሚክ ጉዳዬች መሪ ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ኤባ ሚጀና #ለአሐዱ ገልጸዋል።

በዚህም መሰረት በኢትዮጵያ የሚገኙ በሁሉም የኒቨርሲቲዎች ፈተናው የሚሰጥ ሲሆን፤ ተጠሪነቱ ለትምህርት ሚኒስቴር ያልሆነው የመከላከያ ዩኒቨርሲቲ ጭምር በዚህ ፕሮግራም ተካታች መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

የግል ኮሌጆችን በሚመለከት አሐዱ ላቀረበላቸው ጥያቄ ትምህርት ሚኒስቴር የግል ኮሌጆች ላይ ገብቶ ለመፈተን የሚያስችል መዋቅር እንደሌለው በማንሳት፤ ነገር ግን ተማሪዎች በአቅራቢያቸው በሚገኝ የመንግስት ተቋም በኩል መፈተን እንደሚችሉ ገልፀዋል።

የፈተና ቀኑ በተለያዩ ምክንያቶች ዘግይተው ትምህርት የጀመሩትን ዩኒቨርሲቲዎች ታሳቢ ያደረገና በቂ ዝግጅት ማድረጋቸው ከተረጋገጠ በኋላ መወሰኑን ተናግረዋል።

ፈተናውን ለመስጠት ታቅዶ የነበረው ጥር 14 እና 15 የነበረ ቢሆንም፤ ሁሉም ዩኒቨርስቲዎች እኩል ትምህርት ባለመጀመራቸው ወደ ጥር 26 ቀን 2017 ዓ.ም. እንዲሸጋገር መደረጉን ገልጸዋል፡፡

በዚህ የፈተና ፕሮግራም ተንቀሻቃሽ ስልክና የወረቀት ፅሁፍ ይዞ መገኘት ፈፅሞ #የተከለከለ መሆኑን የገለጹት የአካዳሚክ ጉዳዮች መሪ ሥራ አስፈፃሚው፤ "ተፈታኞች መታወቂያ መያዝና ከፈተና ፕሮግራሙ 30 ደቂቃ ቀድሞ ቦታው ላይ መድረስ ይጠበቅባቸዋል" ብለዋል፡፡ የወጣው ፈተናም ከተማሩት በመሆኑ ሳይጨነቁ በተረጋጋ መንፈስ መስራት እንደሚገባቸው አሳስበዋል።

የዘንድሮው የዩኒቨርስቲዎች የመውጫ ፈተና ከዚህ በፊት ይሰጥ እንደነበረው ሙሉ ለሙሉ በኦንላይን የሚካሄድ ሲሆን፤ ከጥር 26 እስከ 30 ከሰኞ እስከ አርብ ባሉት አምስት ተከታታይ ቀናት እንደሚሰጥ አስታውቀዋል።

የተማሪዎች ፈተና እንደተጠናቀቀ ቅዳሜ ማለትም የካቲት 1 ቀን የመምህራንን ስልጠና ሲወስዱ የነበሩ መምህራን ፈተና ይወስዳሉ ተብሎ ይጠበቃል።

[ዘገባው የአሃዱ ሬድዮ ጣቢያ ነው]

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የትምህርት በቤቴ ቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ!
https://t.me/temhert_bebete
https://t.me/temhert_bebete

3 months ago
“**Many of life’s failures are people …

Many of life’s failures are people who did not realize how close there were to success when they gave up.”Thomas A. Edison
More ⬇️
? @daily_inspiree ?

3 months ago
8ተኛው ዙር ያጋሩ ይሸለሙ ተጀመረ!

8ተኛው ዙር ያጋሩ ይሸለሙ ተጀመረ!
ቴሌግራም ቻናላችንን ለወዳጅዎ ያጋሩ: ይሸለሙ!

የግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ይፋዊ የቴሌግራም ቻናል

  1. በመጀመሪያ ቀጣዩን የቦት ሊንክ ይጫኑ፡- https://t.me/global_bank_referral_bot?start=433177540
  2. START የሚለውን ይጫኑ፣
    3. JOIN CHANNEL የሚለውን ይጫኑ፣
  3. ወደ መጀመሪያው ቦት ይመለሱ፣
  4. CONTINUE የሚለውን ሲጫኑ የመጋበዣ ሊንክዎን ያገኛሉ፣
  5. መልዕክቱን ቢያንስ ለ30 እና ከዚያ በላይ ወዳጅ ዘመድዎ ሼር ሲያደርጉ ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ በየሳምንቱ ላፕቶፕ ፣ ስልኮችን እና ልዩ ልዩ ሽልማቶችን ያበረክታል፡፡

ሽልማቱ ዘወትር ቅዳሜ ለተሸላሚዎች ይደርሳል፡፡

ደንብና ሁኔታዎች ተፈፃሚ ናቸው፡፡

ለተጨማሪ መረጃ በነፃ የጥሪ ማዕከል ቁጥራችን ☎️ 8118 ☎️ ይደውሉ፡፡

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ
ለጋራ ስኬታችን

3 months, 1 week ago

ራስ ገዝ የሚሆኑ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሚተመነው ክፍያ ማህበረሰቡ ላይ ጫናን በማይፈጥር መልኩ ሊሆን እንደሚገባው ተጠቆመ

በኢትዮጵያ በቅርቡ ዩኒቨርሲቲዎች ራስ ገዝ እንዲሆኑ መወሰኑን ተከትሎ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቀዳሚውን የራስ ገዝነት ደረጃ በመያዝ በዘንድሮ ዓመት የመማር ማስተማሩን ስራ መጀመሩ ይታወቃል፡፡ በዚህም መሰረት ለትምህርት መርሃ ግብሮቹ ያወጣውን ገንዘብ ይፋ ማድረጉ ይታወሳል፡፡

ሃሳባቸውን ለመናኸሪያ ሬዲዮ የሰጡ የትምህርት እና የህግ ባለሙያዎች ምንም እንኳን ተቋሙ ራሱን በራሱ ቢያስተዳድርም ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍል ያማከለ አሰራር ሊኖረው እንደሚገባ ገልፀዋል፡፡

መነሻውን ከሌሎች ሀገራት ያደረገው ይህ የራስ ገዝነት አካሄድ ብዙ ውዝግቦች የነበሩበት መሆኑን የገለፁት የትምህርት ባለሙያው ዶ/ር መክብብ ጣሰው ነገር ግን ከሃይማኖቱም ሆነ ከፖለቲካ ጫና በመላቀቅ ጥራት ያለው ትምህርት ለመስጠት ያስችላል ብለዋል፡፡

ከዚህም ባለፈ አቅም የሌላቸውን ተማሪዎች ከዩኒቨርሲቲው ባሻገር ድርጅቶች እና ባላሃብቶች እንደሚደግፉ በመግለፅ በኢትዮጵያም ዩኒቨርሲቲዎች ራስገዝ መሆናቸው የሚበረታታ መሆኑን ይጠቅሳሉ፡፡ ነገር ግን በክፍያው  ከሌሎች ሀገራት ያለውን ተሞክሮ መውሰድ ካልተቻለ በትምህርት ስርዓቱ ላይ ተፅዕኖ እንደሚያሳድር ይገልጻሉ፡፡

ይህንኑ ሀሳብ የሚጋሩት የህግ ባለሙያው አቶ ጥጋቡ ደሳለኝ ትምህርት ማህበራዊ አገልግሎት ከሚባሉት ውስጥ እንደመሆኑ ለማህበረሰቡ በተመጣጣኝ መንገድ ሊቀርብ ይገባል ባይ ናቸው፡፡ ትምህርት ፍትሃዊ በሆነ መንገድ ሊቀርብ ይገባል ያሉት አቶ ጥጋቡ   አግላይ እንዳይሆኑ በህግ ማዕቀፍም ሊኖራቸው እንደሚገባ ይጠቁማሉ፡፡

አቅም ለሌላቸው ተማሪዎች ትምህርት በነፃ በመንግስት በኩል ሊቀርብ የሚገባ መሰረታዊ ጉዳይ ነው ሲሉ ሃሳባቸውን የገለፁልን ደግሞ የህግ ባለሙያው አቶ አይናለም ጌታሁን ናቸው፡፡ 

በዩኒቨርሲቲ ደረጃም ወጪ መጋራት(ኮስት ሼሪንግ) የማስተማር አግባብ እንዳለ በመጥቀስ አሁን ላይ በራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲው የተቀመጠው የገንዘብ ተመን ምናልባትም ከሚያወጣቸው ወጪዎች ጋር ተያይዞ ሊሆን ይችላል የሚል ግምታቸውን ያስቀምጣሉ፡፡ ነገር ግን ማንም ሰው እስኪቸገር ድረስ የማስከፈል ሂደት ካለ እና ሌሎችም ነገ ላይ ራስ ገዝ ሲሆኑ በዚሁ የሚቀጥሉ ከሆነ  ትምህርቱ ወደ ንግድነት የሚቀየር ይሆናል ሲሉ ያላቸውን ስጋት አቶ አይናለም ያስቀምጣሉ፡፡

ትምህርትን በጥራት ማድረስ በሚል ብቻ ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍል ያላማከሉ እርምጃዎች እንዳይወሰዱ በመንግስት በኩል ቁጥጥር ሊደረግባቸው እንደሚገባ ተመላክቷል፡፡ (መናኸሪያ ሬዲዮ)

ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ
?*?*???????**

@temhert_bebete
@temhert_bebete

3 months, 1 week ago
[#MoH](?q=%23MoH)

#MoH

የ2024 ትምህርት ዘመን የብሔራዊ የህክምና ስፔሻሊቲ ስልጠና (ERMP) አመልካቾች ምዝገባ ከህዳር 3-17/2017 ዓ.ም እንደሚከናወን ጤና ሚኒስቴር አሳውቋል፡፡

ለበለጠ መረጃ፦
https://www.moh.gov.et/en/ermp-announcements

@temhert_bebete

3 months, 1 week ago
***❇️*** In Africa Together ***❇️***

❇️ In Africa Together ❇️
አለም አቀፍ ዩኒቨርስቲዎች ተጋባዥ በሆኑበት በአይነቱ ልዩ የሆነ ኢቨንት በ አዲስ አበባ እና በክልል ከተሞች አዘጋጅቶ እንደነበር እና ከብዙ ሺ በላይ ተማሪዎች የዚህ እድል ተሳታፊዎች እንደነበሩ ይታወቃል ።
?እርሶስ በተለያየ አጋጣሚ ይህ እድል አምልጦታል አያስቡ ኢን አፋሪካ ቱጌዘር ይህ እድል ላመለጣቸው ተማሪዎች በድጋሚ የእድሉ ተሳታፊ
የምትሆኑበትን እድል አዘጋጅቶላችዋል።

ይምጡና ?? ከአሜሪካ፣ ?? ከካናዳ፣ ?? ከጀርመን፣ ?? ከፈረንሳይ፣ ?? ከስፔን፣ እና ?? ከዱባይ ዩኒቨርሲቲዎች የመጡ ተወካዮችን በኦንላይን ያግኙ።

? በሀይስኩል
? በዲግሪ
? በማስተር

እኛጋር ሲመጡ ምን ያስፈልጎታል:
- ፓስፖርት / የልደት ሰርተፍኬት
- ትራንስክሪፕት

የዝግጅቱ ቦታ:
? Addis Ababa, Harmony hotel - ህዳር 6& 7

?️ ያለምንም ቅድመክፋያ !
ይፋጠኑ ያለን ቦታ ውስን ነው!

✍️ የመመዘገቢያ ገጽ:
[Registration Link](https://forms.gle/m6w7WF8x7uivDsYz7

3 months, 1 week ago
[#EthiopianAviationUniversity](?q=%23EthiopianAviationUniversity)

#EthiopianAviationUniversity

የኢትዮጵያ አቪዬሽን ዩኒቨርሲቲ ለ200 ጋቦናውያን ልዩ የአቪዬሽን ስልጠና የሚወስዱ ተማሪዎችን ተቀብሏል።

በተለያዩ የአቪዬሽን ዘርፎች ትምህርታቸውን ለሚከታተሉት ተማሪዎቹ በኢትዮጵያ አየር መንገድ እና በኢትዮጵያ አቪዬሽን ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ አመራሮች አቀባበል ተደርጓል።

@temhert_bebete

3 months, 2 weeks ago

የምስራች አሁን online ላላችሁ ብቻ ጥያቄ ና መልስ ልንጀምር ነው

1⃣ ለወጣ 500 ብር ካርድ
2⃣ ለወጣ  250 ብር ካርድ
3⃣ ለወጣ  100 ብር ካርድ

? ዝግጁ ከሆናችሁ ጀምር የሚለውን ይጫኑ

We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 2 months ago

Last updated 1 month, 4 weeks ago

ይህ ስለ Manchester United መረጃዎችን የሚያገኙበት የ Telegram ቻናል ነው 🇪🇹
--------------------------------------------------------------
☞︎| ስለ ማንቸስተር ዩናይትድ ትኩስ መረጃዎች
☞| ቀጥታ ስርጭቶች ከየስታድየሞቹ
☞| የዝውውር ዜናዎች
☞| ስለ ማንችስተር ዩናይትድ ታሪኮች

📩 ለማስታወቂያ ስራ DM :- @Marcoabdu

Last updated 3 weeks, 3 days ago