Unlock a World of Free Content: Books, Music, Videos & More Await!

Geez Media Center

Description
https://t.me/GeezMediaCenter
Advertising
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 5 days, 4 hours ago

Last updated 3 weeks, 1 day ago

በዚህ ቻናል ወቅታዊ፣ታማኝ እና ፈጣን መረጃ ያገኛሉ❗
መረጃ ለማድረስ እና ማስታወቂያ ለማሰራት ከስር ባለው ሊንክ ይጻፉልን👉http://t.me/ayulaw

Last updated 1 month, 3 weeks ago

1 month ago

በቃ!
አሁን ሁለገብ ውድቀት ላይ ነን።
ይህን መካድ በእየእለቱ የሚያርደውን አእምሮ የሚያስታጥቅ አመራር አለ፣ በእየለቱ የሚታረደውን ሕዝብ ከላላና ፍትሕ የሚነፍግ ሥርዓት አለ።
የሚያዋጣው ይህን ተጨባጭ ሰው ክብሩን ጥሎ በእንስሳ ደረጃ የሚኖርባት አገርና በአራዊት ደረጃ ለሰው ደምና መከራ የማይጨነቁ መሪዎች፣ እምነታቸውን ለምቾትና ለድሎት መሣሪያ ያደረጉ የእመነትና የባህል መሪዎች መስራፋታቸውን ተቀብሎ ንስሐ መግባት፣ ጥፋታችንን የሚመጥን መልካምነትን ለመላበስ፣ ክፋትና ርኵሰትን ለመጋደልና ራሳችንን ነፃ በማውጣት የደምን ጎርፍና የመከራም ናዳ ማስቆም ነው።

በዚህ አይነት ሁኔታ ውስጥ ሕሊና ቀረለት፣ ሰብእናው ያልወደቀበት፣ ለሕሊናው የሚገዛ እና የፈሪሐ እግዚብሔር ጠብታ በልቡ ያለ ሁሉ ማንንም ነፃ አውጭና መፍትሔ ሰጭ ሳይጠበቅ የሚከተሉትን ተግባራት በአስቸኳይ መጀመር አለበት፡-
1) ንስሐ መግባት፣ የበደሉትን መካስ፣ የወሰዱትን መመለስ፣ ያሳዘኑትን ይቅርታ መጠየቅ፤
2) በመዋቅር፣ በሥርዓት፣ በክፌ ርእዮትና ትርክት ምክኒያት መከራ ለሚቀበሉት ድምጽ መሆን፤
3) ክፉ ሰዎችን ከቤታችን ጀምረን እንስተካከሉ የምንችለውን ሁሉ ማድረግ፤
4) የንዑስ-ማንነት ፖለቲካ የሚፈጥረው የዘረኝነት ደዌ ወደ ልጆቻችን እንዳይጋባ በመጠንቀቅ ስለ ሰብአዊነት፣ ፍትሓዊነት፣ እውነትና ፍቅር፣ የአገር ጠቃሚና አሰባሳቢ ታሪክ፣ ስል ዘመነኞችን የክፉዎች ፖለቲካን አሁን እያስከተለ ያለው እልቂትና ስስት በግልጽ ማስተማር፤
5) በመራው የተሰደዱትን፣ ያዘኑትን፣ እናትና አባት፣ ባልና ሚሰት አጥተው የተቸገሩትን በአቅም መርዳት፤
6) ለመከራችን ምክኒያት የሆነው በሐሰትና ስሕተት ራሱን ከሰብእና፣ ከዜግነትና ሃይማኖት በላይ ያደረገውን የንዑስ ማንነት ፖለቲካ በሚቻለው መንገድ ሁሉ መቃወም፣ ማጋላጥ፣ ርኵስ የጥፋት መንገድ መሆኑን በንግግርና ባለመተባበር ተግባር ማሳየት፤
7) ከመልካሞች ጋር በመደራጀት ክፉዎችን መከላከል፣ ማሸነፍ፣ መመለስ፣ ሰው ማድረግ፤
8) በየባህላችን፣ እመነቶቻቸን፣ የማኅበረሰብ መዋቅሮቻችን ውስጥ ከመንገድ የወጡ፣ የፖለቲካ አገልጋይ የሆኑ የምቾትና የድሎት ምርኮኞችን ወደ ንሥሐና ወደ የሚመሩትን ሕዝብ እረኝነት ተመልሰው በተግባር እንዲገልጡ ጫና ማድረግ፣ ድጋፍ መንሳት፤
9) አገር ውስጥ ለሚገኙ የክፋት ብድኖች ሁለገብ ድጋፍ መንሳት፤ በተቃራኒው መልካሞችን፣ አውነተኞችን፣ እውነትና ፍትሕን የሚያሳድዱትን አካላት ለይቶ መቃወም፣ ማጋለጥ፣ አሠራራቸውን ለዜጎችና ለውጭ መንግሥታት ሁሉ ማሳጣት፤
10) ቴክኖሎጂን ለተራ ወሬና ጊዜ ማጥፊያ ሳይሆን የሰውን ልጆች ለማዳን መጠቀም።

ይህ ሁሉ የሚቻለው ግን በእግዚአብሔር ላይ ፍጹም እምነት በማኖር፣ ሁሉን ስለ እግዚአብሔር ፍቅር ማድረግ እና ለግል ሥልጣን፣ ለግል ዝና፣ ለግል ጥቅምና ድሎትና ምቾትን ፍለጋ አለመሆኑን ከልቡ ተማክሮ ራሱን ላሳመነ ሰው ነው እንዲሁ ለመሆን ቁርጥ ሕሊና ማድረግ።

1 month ago
Geez Media Center
1 month ago
Geez Media Center
1 month ago
Geez Media Center
1 month ago
"**የእምነት አባቶች ፣የአውደምህረት ሰባኪያን ዛሬ ላይ …

"የእምነት አባቶች ፣የአውደምህረት ሰባኪያን ዛሬ ላይ እስጢፋኖስን የስብከት ርዕስ ለማድረግ አትጨነቁ። እንደ እስጢፋኖስ ድንጋይ የተከመረባቸው የእራሳችሁ ወገኖች አይኗችሁ ላይ ተስለው ተቀምጠዋልና "

እግዚአብሔር ይቅር ይበለን !!!

Kune Demelash kassaye -Arba Minch

1 month ago

ምናልባት አሁን እየተደረገ ባለው ዉጊያ የዐብይ አሕመድ አገዛዝ ተሸንፎ ሃገራችን የሰላም አየር ትተነፍስ ይሆናል።ቤተ ክርስቲያን ግን ውስጧ በተሸሸጉ ጠላቶችዋ እንደ ደማች መቀጠሏ አይቀሬ ነው።ይህ እንዳይሆን መፍትሔው ኦርቶዶክሳዊ ትግል መጀመርና የውስጥ ጠላቶችን መንጥሮ ማስወገድ ነው።ከሲኖዶስ እስከ አጥቢያ ድረስ።

1 month, 1 week ago

ካህኑ አገልጋዩ ቄስ በዐውደ ምህረት ተረሸኑ።😭😭
በደምበጫ ከተማ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን አገልጋይ ቄስ ተረሸኑ። በትናንትናው ዕለት 03/8/2016 ዓ.ም የፋኖ ኢንጂነር ተመስገን ብርጌድ በደምበጫ ነበልባሎች የተለበለበው የብልጽግና ሰራዊት በሽሽት ቤተክርስቲያን ገብቶ ቄሱን በዐውደ ምህረት ረሽኗቸዋል።

በአካባቢው የነበሩት ሌላኛው ሽማግሌ ምዕመን አቶ ድልነሳ ካሳሁም በትናንትናው ዕለት በብልጽግና ሰራዊት የተረሸኑ አባት ናቸው።

የእነዚህን አባቶች ዝርዝር መረጃ ተጨማሪ ይዘን እንመጣለን።

@GeezMediaCenter

1 month, 1 week ago

(የቀጠለ) 👆🏿👆🏿👆🏿
ዛሬ ደግሞ እርስ በእርስ ኦሮሞን ማፋጀት፥ ማሰቃየቱን በየመንደሩ ቀጥሎበታል።

የኦሮሞ ሕዝብና የትግራይ ሕዝብ ራሱን ባሮች ካደረጉት፥ በነፍስም በሥጋ ከገደሉት፥ የሰማዩንም የምድሩንም አገራቸውን ትልቋን ኢትዮጵያና ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያንን፥ ነባሩን የኢትዮጵያ ውብ እስልምና የነጠቁትን "ነፃ አውጭዎች" ነን ባዮቹን ጠላቶቹን በግልጽ መቃወም መጀመርና ራሱን ነፃ ማውጣት አለበት!!

©ፋንታሁን ዋቄ

@GeezMediaCenter

1 month, 1 week ago

በዐብይ አሕመድ አሊ ዘመነ መንግሥት፦

፩   ኦርቶዶክሳዊነት ወንጀል ነው ከዚህ የተነሳ በሃገሪቷ ያሉ ምዕመናን ያለ ማንም ከልካይነት ይገደላሉ፣ሃብት ንብረታቸውን ይቀማሉ፣ቤታቸው ይፈርሳል ፣በግፍ ይሰደደሉ።

፪ ) ኦርቶዶክሳዊው ማኅበረሰብ ሃገር እንዲመራ፣ሥልጣን እንዲይዝ ፣በመንግሥትና በግል መሥርያቤቶች እንዲቀጠር አይፈቀድለት።

፫)ፖለቲካ ፓርቲ እንዲመሠርት፣እንዲታጠቅና ከክፉዎች ራሱን እንዲጠብቅ አይፈቀድለትም።

፬) እርሰበርሱ እንዲጨራረስ የማይረባ አጀንዳ ይሰጠዋል።

፭) ልጅ መዉለድ እንዳይችል ቁጥሩም እንዲቀንስ  ይደረጋል(በክትባት፣በወሊድ መከላከያ)

፮  ከአንድ ክልል ወደ ሌላ ክልል መንቀሳቀስ ነውር ነው።ከተፈቀደልህ ዉጭ መኖር አትችልም።

፯  የጥንታዊቷን የኢትዮጵያ ልዕልናዋን ማውራትም ሆነ ማስተማር የድሮ ሥርዐት ናፋቂ፣ነፍጠኛ፣አሓዳዊ፣ጨፍላቂ ፣አንድ እምነት ባይ፣ደንቆሮ፣ኋላ ቀር፣ጽንፈኛ  የሚል ታርጋ ያስለጥፋል ከዚህም አልፎ ለእሥርና ለሞት ይዳርጋል።በአንጻሩ ደግሞ ስለ" አዲሲቷ ኢትዮጵያ" የሚሰብኩ ይሸለማሉ ፣ሥልጣን ይመጸወትላቸዋል፣የለውጡ ደጋፊዎች  ተብለውም ይሞካሻሉ።

፰ አንድ ሰው ከብሔሩ ዉጭ  ትዳር መመሥረት አይችልም።

፱ ራሱ መንግሥት ከመሠረተልህ እምነት እና ሲኖዶስ ውጭ ሌላ መከተል አይቻልም።

፲ ኦርቶዶክሳዊነትን ማዋረድ እንደ ጀግንነት ይቆጠራል።

ኢዮሳፍጥ ጌታቸው

1 month, 2 weeks ago

ቅድስና አልባ ሲኖዶሶች

ምንደኞች የግል ጥቅማቸውን ለማስጠበቅ ሲሉ  አንድ የሆነውን ሲኖዶስ በሦስት ከፍለውታል።የአምስት ኪሎው ሲኖዶስ፣የህወት ሲኖዶስ እና የኦነግ ሲኖዶስ ናቸው።አሁንም ቢሆን ነገሩ በዚህ የሚያበቃ አይደለም።ገና ብዙ ቅድስና አልባ ሲኖዶሶች ይፈለፈላሉ።የቅብዓት ሲኖዶስ ምሥራቅ ጎጃም አከባቢ እንዳለ ይታወቃል።መንበረ ሐርቤ የሚባል ሲኖዶስ በዋግኽምራ አከባቢ ሊመሠረት እንቅስቃሴ ላይ ነው።የአገው ሕዝብ ሲኖዶስ፣የቅማንት ሕዝብ ሲኖዶስ ፣የአማራ ሲኖዶስ  ፣የሲዳማ ሲኖዶስ፣የደቡብ ሕዝብ ሲኖዶስ፣የጋምቤላ ሲኖዶስ ወዘተ...የሚሉ ሲኖዶሶች እንደሚሙጡ አልጠራጠርም።ይህ  እውን እንዲሆን እነ ዐብይ አሕመድ ሌት ተቀን እየሠሩ ነው።የአምስት ኪሎው ሲኖዶስ እውነትን መጋፈጥ ሲገባው ለዐብይ አሕመድ አሸርጋጅ ሆኖ በእነ አቡነ አብርሃም በኩል "ከመንግሥት ጋር እየተነጋገርን ነው ፣ከመንግሥት ጋር ወርቃማ ውይይት አድርገናል " በሚል ድንዛዜ ዘወትር ሲቃያችንን ያበዛዋል።ተዉ እረፉ የዘር ሹመት ይቅርባችሁ ሲባሉ ልጆቻቸውን ከመስማት ይልቅ ለዐብይ አድልተው ዛሬ የማንወጣ ማጥ ውስጥ ከተቱን።እነርሱማ ማጣፊያው አጥሮአቸው  አንዴ የጠቅላይ ሚኒስትር ቢሮ አንዴ የሰላም ሚኒስትር ቢሮ እያሉ ጸረ ኦርቶዶክሳውያን ባለሥልጣናትን ሲለማመጡ የሚሰማቸው አጥተው  በከንቱ ሲባዝኑ ይዉላሉ። አሁንም ቢሆን አልመሸም ወደ ቅድስናው መንገድ እንመለስ።የሲኖዶስ መሪው መንፈስ ቅዱስ እንጂ ፖለቲከኞች እና ዘረኞች አይደሉም።እንደ አረጋውያን አባቶች እንደ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት አቡነ ቄርሎስ እና አቡነ ሉቃስ እውነቱን እንጋፈጥ።

We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 5 days, 4 hours ago

Last updated 3 weeks, 1 day ago

በዚህ ቻናል ወቅታዊ፣ታማኝ እና ፈጣን መረጃ ያገኛሉ❗
መረጃ ለማድረስ እና ማስታወቂያ ለማሰራት ከስር ባለው ሊንክ ይጻፉልን👉http://t.me/ayulaw

Last updated 1 month, 3 weeks ago