Geez Media Center

Description
https://t.me/GeezMediaCenter
Advertising
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 3 weeks, 1 day ago

Last updated 2 weeks, 3 days ago

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated 1 month ago

8 months, 1 week ago

አምኀ ወሰላምታ ዘሰሙነ ትንሣኤ እስከ በዓለ ኃምሳ!!                           

ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን                          
በዐቢይ ኃይል ወሥልጣን
አሰሮ ለሰይጣን
አግዐዞ ለአዳም
ሰላም 
እምይእዜሰ
ኮነ
ፍሥሐ ወሰላም

እንቋዕ ለብርሃነ ትንሣኤሁ ለእግዚእነ ወአምላክነ ወመድኃኒነ ኢየሱስ ክርስቶስ በጥዒና ወበዳኅና አብጽሐክሙ።

ሰላሞ ወፍቅሮ የሀበነ።

ሠናይ በዓል ይኵን ለነ!!

@GeezMediaCenter

8 months, 1 week ago

ኢየሱስ ፡ ክርስቶስ፡ ጥዑመ፡ ስም 

የጌታ፡ ኢየሱስ፡ ክርስቶስን፡ ስሙን ለሚጠራው  ጣፋጭ ፡ ነው የጌታ ፡ ኢየሱስ፡ ክርስቶስን ሥጋ ውን ፡ ለሚቀበለው ረኀበ ነፍስን የሚያስወግድ  የሕይወት ምግብ ፡ ነው ። የጌታ ኢየሱስ ፡ክርስቶስ፡ ደሙን ፡ ለሚጠጣው ጽምዓ ፡ ነፍስን ፡ የሚያረካ ፡ የሕይወት ፡ መጠጥ ፡ ነው ። አሁንም ፡ እኛን ፡ ለመባረክና፡ ጠላታችንን ፡ ድል ፡ ይነሣልን ፡ ዘንድ ጋሻ ፡ ጦሩን ፡ አሲዞ ፡ ልዩ ፡ መልክተኛውን ወደኛ ፡ ይላክልን። 

ኢየሱስ ፡ ክርስቶስ 

ጌታ፡ ኢየሱስ፡ ክርስቶስ፡ ለሰው ልጅ ፡ ሲል ፡ የቆሰላቸው ቍስሎቹ ሕይወቱን አሳልፎ  የስ ጠበት ፡ ቅዱስ ፡ መስቀሉ ፡ በፊት ለፊቱ፡ ተቀድሞ ፡ የወይን ምንጭ የሚሆን ፡ በጦር  የተወጋው ፡ ጐኑ ፡ ቍርባነ አምልኮ ፡ የሚሆን ሥጋውና ፡ ደሙ ፡ በተዘጋጀበት ቅዱሳን ፡ አርበኞቹ፡ ተሸልመውና፡ ተጊጠው፡ ለግብዣ ፡ በተጠሩ፤ ጊዜ ፡ እኛንም ፡ ወደ ሙሽራው ፡ ሠርግ ፡ቤት፡ በአንድነት፡ ያግባን። 

ለጥብሐ፡ ሥጋከ  እሴስዮ

መድኃኒቴ ፡ ኢየሱስ ፡ ሆይ ፤ የሕይወት ፡ ምግብ፡የሆነ' ሥጋህን እመገበዋለሁ ፤የሕይወት ፡ መጠጥ የሆነ ፡ ደምህንም ፡ እጠጣዋለሁ ። ፈጣሪዬ ፡ ክርስቶስ ፡ ሆይ ፤ በቀራንዮ ፡ ለመሥዋዕት ፡ የቀረ ብክ ፡ ንጹሕ  በግ  ነህና  ውበትህን  አየው ፡ ዘንድ  እመ ኛለሁ። ልመናዬን ፡ በሱራፊ'ጽዋ ሙላው ፡ ማኅየዊ  ወይም አምላካዊ ፡ በሚሆን ፡ መከራህና፡ ሞት ህም ፡ ቍስለ ፡ ነፍሴን ፡ ፈውሰው።

ለጥብሐ ሥጋከ፡ እጸግቦ 

ጌታዬ ፡ ኢየሱስ ሆይ፤ ቅዱስ፡ ሥጋህን፡ በልቼ፡ በልቼ፡ እጠግ በዋለሁ። ክቡር ፡ ደምህንም ፡ ጠጥቼ ጠጥቼ ፡ ከጥሜ ፡ እረካበታለሁ ። ፈጣሪዬ ፡ ክርስቶስ ፡ ሆይ ፤ ጐንህን ፡ በጦር ፡ የተወጋህ፡ የዋህ በግ ፡ እኮን፡ ነህ ። ምናልባት፡ ከማ ርያም ፡ ከሥጋዋ ፡ ሥጋ ፡ ከነፍሷ ፡ ነፍስ ፡ ነሥቶ ፡ ሰው ፡ ሆኖ ፡ አልተወለደም ፡ የሚልህ የቅድስት ፡ ሥላሴ እምነት  የሌለው አይሁዳዊ ፡ ከሐዲ  ቢኖር  እንደተ ራበ ፡ ውሻ  አገር ላገር  ይዙር። ጐዳና ፡ ከጐዳና ይንከራተት። 

አመ ፡ ትመጽእ ለኰንኖ 

ጌታዬ፡ ኢየሱስ፡ ሆይ፤ ከእግሮችህና ፡ ከጐንህ ፡ ከፈሰሰው ፡ ደም ጋር ፡ ለፍርድ ፡ በመጣህ ፡ ጊዜ ነፍሴን ፡ ንዑድ ፡ ክቡር  ለሚሆን እጅህ ፡ አደራ ፡ እሰጣለሁ ። የሰማይና፡ የምድር፡ ንጉሥ፡ ክር ስቶስ ፡ ሆይ ፤ አሁንም ፡ እራስህን በበትር ፡ የተደበደብከው ፡ መደብ ደብና ፡ እንደባሪያ ፡ ለሠላሳ ፡ ብር የተሸጥከው፡ መሸጥ፡ በዚያን ' በቍርጥ፡ ፍርድ ፡ ቀን ፡ ዋስ ጠበቃ ፡ ይሁኑኝ ።

ስብሐት ለከ 

ጌታ፡ ኢየሱስ ሆይ፤ በፍጥረቱ 'ሁሉ፡ አንደበት ፡ ለአንተ፡ ምስ ጋና ፡ ይገባል ። ፈጣሪ ፡ ክርስቶስ  ሆይ ፤ አፍኣዊ ፡ ሥጋን ፡ ውሳጣዊ ዛ ሰውነትን ፡ የምትቀድስ ፡ ለአንተ ምስጋና ፡ ይገባል ። ለተራቆቱት ፡ ልብሳቸው ፡ ለአንተ ፡ ለኢየሱስ ፡ ምስጋና ፡ ይገባል ። የማትሻር የማታልፍ፡ንጉሥ፡ ክርስቶስ፡ ሆይ፤ ለአንተ ፡ ምስጋና ፡ ይገባል ። የቅ ዱስ  አብ  አካላዊ  ቃል  ኢየሱስ ፡ ክርስቶስ ፡ ሆይ ፤ ለአንተ ፡ ክብር ፡ ምስጋና ፡ ይገባል ለዘለዓለሙ ፡ አሜን 

8 months, 2 weeks ago

በግብረ ሕማማት ውስጥ የሚገኙ የውጭ ጥሬ ቃላት ትርጉም፡-

ከመ/ር ሸዋንዳኝ አበራ

በሰሙነ ሕማማት በቤተ ክርስትያን ውስጥ የምንገለገልበት መጽሐፍ ግብረ ሕማማት ይባላል፤ በዚህ መጽሐፍ ውስጥ ከሌሎች ልሳናት ወደ ግእዝም ሆነ ወደ አማርኛ ሳይተረጎሙ የተቀመጡ የዕብራይስጥ፣ የቅብጥ እና የግሪክ ጥሬ ቃላት ስለሚገኙ ትርጉማቸውን እንመልከት፦

፩፦ ኪርያ ላይሶን፥ ቃሉ የግሪክ (ጽርዕ) ሲሆን አጠራሩ (Κίρι Έλισον) «ኪርዬ ኤሌይሶን» ነው፤ ኪርዬ - ማለት እግዚኦ -አቤቱ ማለት ሲሆን ኤሌሶን ማለት ደግሞ ተሣሀለነ - ማረን ማለት ሲሆን በአንድ ላይ «ኪርዬ ኤሌይሶን» እግዚኦ ተሣሀለነ - አቤቱ ማረን ማለት ነው፡፡ ነገር ግን በተለምዶ ኪርያ ላይሶን ማለትን እናዘወትራለን ምንም እንኳን ቃሉ የጽርእ ቢሆንም እኛ እስከ ተጠቀምንበት ድረስ በቃላት ላይ ጥንቃቄ ማድረጉ እጅግ ተገቢ ይሆናል ምክንያቱም ለተባእት የተነገረውን ለእንስት መጠቀሙ የቃላት ግድፈት ብቻ ሳይሆን የዶግማም መፋለስ ያስከትላልና መታረም ይኖርበታል፡፡

በእኛ ዘንድ ልምድ ሆኖ ኪርያላይሶን ነው የምንለው፤ ይህም በድምጾች መሳሳብ ቢሆንም ሌላ ትርጉም የሚያስከትል በመሆኑ ትክክለኛውን ድምጽ መያዝ ይኖርብናል፤ «ኪርያ» ማለት «እግዝእትነ» ማለት ሲሆን ኪርያ ላይሶን ማለት ደግሞ  እግዚእትነ መሐረነ - አቤቱ ማሪን ማለት ነው፤ በዘልማድ ኪርያ ላይሶን የምንለው ኪርዬ ከሚለው የ(ዬ)፤ ኤላይሶን ከሚለው ደግሞ የ(ኤ) ድምፆች በመሳሳባቸው የ(ያ)ን ድምፅ በመተካት እኛው ያመጣነው ድምፅ እንጂ ትክክለኛ ድምፅ ካለመሆኑም በተጨማሪ ትርጉሙም ዶግማ ያፋልሳልና ትክክለኛውን ድምፅ (Κίρι Έλισον) «ኪርዬ ኤሌይሶን» የሚለውን መከተል ግድ ይለናል፡፡

፪፦ ናይናን፥ የቅብጥ (ግብጽ) ቃል ሲሆን ትርጉሙም «መሐረነ» ማረን ማለት ስለሆነ ይህ ቃል ከሌሎች ቃላት ጋር በመሆን ዓረፍተ ነገር ይፈጥራል ወይም ኃይለ ቃል ይሰጣል ይኸውም፦ እብኖዲ ናይናን፥ ታዖስ ናይናን፥ ማስያስ  ናይናን፥ ኢየሱስ ናይናን፥ ክርስቶስ ናይናን፥ አማኑኤል ናይናን፥ ትስቡጣ ናይናን ይባላል፡፡

፫፦ እብኖዲ፥ የቅብጥ (የግብጽ) ቃል ሲሆን ትርጉሙም «አምላክ» ማለት ነው፤ «እብኖዲ ናይናን» ሲልም «ኦ አምላክ መሐረነ» አምላክ ሆይ ማረን ማለት ነው።

፬፦ ታኦስ፥ የግሪክ (ጽርዕ) ቃል ሲሆን ትርጉሙም «ጌታ አምላክ» ማለት ነው፤ «ታኦስ ናይናን» ማለትም ጌታ አምላክ ሆይ ማረን ማለት ነው፡፡

፭፦ ማስያስ፥  መሲሕ ማለት ሲሆን ቃሉ የዕብራይስጥ ነው ትርጉሙም በጽርዕ ክርስቶስ ማለት ነው፤ «ማስያስ ናይናን»  ማለትም «ኦ መሲሕ መሐረነ» መሲህ ሆይ ማረን፥ ክርስቶስ ሆይ ማረን ማለት ነው፡፡

፮፦ ትስቡጣ፥ የግሪክ (ጽርእ) ቃል ሲሆነ «ድስቡጣ - ዴስፓታ» ከሚለው ስርወ ቃል የወጣ ነው፤ ትርጉሙም «ደግ አመላክ ወይም ደግ ገዢ» ማለት ሲሆን ትስቡጣ ናይናን ጌታችን ሆይ ማረን ማለት ነው።

፯፦ ሙኪርያ፥ የቅብጥ (ግብጽ) ቃል ሲሆን «ኦ እግዚኦ» አቤቱ ሆይ ጌታ ሆይ ማለት ሲሆን ሙኪርያ ናይናን ማለት አቤቱ ሆይ ማረን ማለት ነው፡፡

፰፦ ሙአግያ፦ የቅብጥ (ግብጽ) ቃል ሲሆን «ኦ ቅዱስ» ቅዱስ ሆይ ማለት ሲሆን ሙአግያ ናይናን ማለት ቅዱስ ሆይ ማረን ማለት ነው፡፡

፱፦ ሙዳሱጣ፥ የቅብጥ (ግብጽ) ቃል ሲሆን «ከሁሉ በላይ የሆንክ ሆይ» ማለት ሲሆን መዳሱጣ ናይናን ማለት ከሁሉ በላይ የሆንክ ሆይ ማረን ማለት ነው፡፡

፲፦ አምንስቲቲ ሙኪርያ አንቲ ፋሲልያሱ፥ የቅብጥ (ግብጽ) ቃል ሲሆን ጌታ ሆይ በመንግሥትህ አስበን ማለት ነው፡፡

፲፩፦ አምንስቲቲ ሙአግያ አንቲ ፋሲልያሱ፥ የቅብጥ (ግብጽ) ቃል ሲሆን ቅዱስ ሆይ በመንግሥትህ አስበን ማለት ነው፡፡

፲፪፦ አምንስቲቲ ሙዳሱጣ አንቲ ፋሲልይዝሱ፥ የቅብጥ (ግብጽ) ቃል ሲሆን ከሁሉ በላይ የሆንክ ሆይ በመንግሥትህ አስበን ማለት ነው፡፡

እንበለ ደዌ ወሕማም፥ 
እንበለ ጻማ ወድካም፥ ለብርሃነ ትንሣኤሁ ያብጽሐነ፥ ያብጽሕክሙ እግዚአብሔር በፍሥሐ ወበሰላም፡፡  (ያለ ደዌና ያለ ሕመም፥ ያለ ጣርና ያለ ድካም፥  እግዚአብሔር ለብርሃነ ትንሣኤው በደሰታና በሰላም ያድርሰን፤ ያድርሳችሁ፡፡

@GeezMediaCenter

8 months, 3 weeks ago

በቃ!
አሁን ሁለገብ ውድቀት ላይ ነን።
ይህን መካድ በእየእለቱ የሚያርደውን አእምሮ የሚያስታጥቅ አመራር አለ፣ በእየለቱ የሚታረደውን ሕዝብ ከላላና ፍትሕ የሚነፍግ ሥርዓት አለ።
የሚያዋጣው ይህን ተጨባጭ ሰው ክብሩን ጥሎ በእንስሳ ደረጃ የሚኖርባት አገርና በአራዊት ደረጃ ለሰው ደምና መከራ የማይጨነቁ መሪዎች፣ እምነታቸውን ለምቾትና ለድሎት መሣሪያ ያደረጉ የእመነትና የባህል መሪዎች መስራፋታቸውን ተቀብሎ ንስሐ መግባት፣ ጥፋታችንን የሚመጥን መልካምነትን ለመላበስ፣ ክፋትና ርኵሰትን ለመጋደልና ራሳችንን ነፃ በማውጣት የደምን ጎርፍና የመከራም ናዳ ማስቆም ነው።

በዚህ አይነት ሁኔታ ውስጥ ሕሊና ቀረለት፣ ሰብእናው ያልወደቀበት፣ ለሕሊናው የሚገዛ እና የፈሪሐ እግዚብሔር ጠብታ በልቡ ያለ ሁሉ ማንንም ነፃ አውጭና መፍትሔ ሰጭ ሳይጠበቅ የሚከተሉትን ተግባራት በአስቸኳይ መጀመር አለበት፡-
1) ንስሐ መግባት፣ የበደሉትን መካስ፣ የወሰዱትን መመለስ፣ ያሳዘኑትን ይቅርታ መጠየቅ፤
2) በመዋቅር፣ በሥርዓት፣ በክፌ ርእዮትና ትርክት ምክኒያት መከራ ለሚቀበሉት ድምጽ መሆን፤
3) ክፉ ሰዎችን ከቤታችን ጀምረን እንስተካከሉ የምንችለውን ሁሉ ማድረግ፤
4) የንዑስ-ማንነት ፖለቲካ የሚፈጥረው የዘረኝነት ደዌ ወደ ልጆቻችን እንዳይጋባ በመጠንቀቅ ስለ ሰብአዊነት፣ ፍትሓዊነት፣ እውነትና ፍቅር፣ የአገር ጠቃሚና አሰባሳቢ ታሪክ፣ ስል ዘመነኞችን የክፉዎች ፖለቲካን አሁን እያስከተለ ያለው እልቂትና ስስት በግልጽ ማስተማር፤
5) በመራው የተሰደዱትን፣ ያዘኑትን፣ እናትና አባት፣ ባልና ሚሰት አጥተው የተቸገሩትን በአቅም መርዳት፤
6) ለመከራችን ምክኒያት የሆነው በሐሰትና ስሕተት ራሱን ከሰብእና፣ ከዜግነትና ሃይማኖት በላይ ያደረገውን የንዑስ ማንነት ፖለቲካ በሚቻለው መንገድ ሁሉ መቃወም፣ ማጋላጥ፣ ርኵስ የጥፋት መንገድ መሆኑን በንግግርና ባለመተባበር ተግባር ማሳየት፤
7) ከመልካሞች ጋር በመደራጀት ክፉዎችን መከላከል፣ ማሸነፍ፣ መመለስ፣ ሰው ማድረግ፤
8) በየባህላችን፣ እመነቶቻቸን፣ የማኅበረሰብ መዋቅሮቻችን ውስጥ ከመንገድ የወጡ፣ የፖለቲካ አገልጋይ የሆኑ የምቾትና የድሎት ምርኮኞችን ወደ ንሥሐና ወደ የሚመሩትን ሕዝብ እረኝነት ተመልሰው በተግባር እንዲገልጡ ጫና ማድረግ፣ ድጋፍ መንሳት፤
9) አገር ውስጥ ለሚገኙ የክፋት ብድኖች ሁለገብ ድጋፍ መንሳት፤ በተቃራኒው መልካሞችን፣ አውነተኞችን፣ እውነትና ፍትሕን የሚያሳድዱትን አካላት ለይቶ መቃወም፣ ማጋለጥ፣ አሠራራቸውን ለዜጎችና ለውጭ መንግሥታት ሁሉ ማሳጣት፤
10) ቴክኖሎጂን ለተራ ወሬና ጊዜ ማጥፊያ ሳይሆን የሰውን ልጆች ለማዳን መጠቀም።

ይህ ሁሉ የሚቻለው ግን በእግዚአብሔር ላይ ፍጹም እምነት በማኖር፣ ሁሉን ስለ እግዚአብሔር ፍቅር ማድረግ እና ለግል ሥልጣን፣ ለግል ዝና፣ ለግል ጥቅምና ድሎትና ምቾትን ፍለጋ አለመሆኑን ከልቡ ተማክሮ ራሱን ላሳመነ ሰው ነው እንዲሁ ለመሆን ቁርጥ ሕሊና ማድረግ።

We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 3 weeks, 1 day ago

Last updated 2 weeks, 3 days ago

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated 1 month ago