Hamza media

Description
የዕውቀት ምንጭ

ዲኖትን ይማሩ።
አጫጭር ታሪኮች
ሀዲሶች。。。


https://youtube.com/channel/UCMyjU57ElAACkRt16RChdWA

For cross & promotion @abunehyan1
Advertising
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 3 недели назад

Last updated 2 недели, 2 дня назад

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated 1 месяц назад

1 month ago

አዲስ እይታ👀

ዛሬ ከመግሪብ ሰላት በሗላ ወንድማችን ኡስታዝ አብዱልአዚዝ የተወሰነ ሙዛከራ(ማስታወሻ) አድርጎልን ነበር አና በዚች 10ደቂቃ ማትሞላ የሙዛከራ ጊዜ ውስጥ ግን ሁሌ ማለት በሚያስችል መልኩ ከምንቀራውቸና በጣም አጫጭር ከሆኑ ሱራዎች መካከል የምትመደበዋን ሱረቱ ነስርን በተመለከተ አይቼው የማላውቀውን አስገራሚ እይታ አሳይቶኛል።እሱንም ለናንተ ላካፍላቹ አሰብኩ።ታላቁ ጌታ የመካ መከፈትን አስመልክቶ ለነብያችን ብስራትን ሲያበስር እንዲህ አላቸው

إِذَا جَاءَ نَصْرُ اللَّهِ وَالْفَتْحُ

የአላህ እርዳታና (መካን) መክፈት በመጣ ጊዜ፤

وَرَأَيْتَ النَّاسَ يَدْخُلُونَ فِي دِينِ اللَّهِ أَفْوَاجًا

ሰዎችንም ጭፍሮች እየኾኑ፤ በአላህ ሃይማኖት ውስጥ ሲገቡ ባየህ ጊዜ፤

ታድያ ይህ ከሆነ እና አላህ ይህንን ኒዕማ ካፈሰስልህ የሚል ትረጉም ባለው መልኩ ደግሞ ቀጣዮ አያ ላይ ፍላጎቱን እንዲህ ሲል አሰፈረ

فَسَبِّحْ بِحَمْدِ رَبِّكَ وَاسْتَغْفِرْهُ ۚ إِنَّهُ كَانَ تَوَّابًا

ጌታህን ከማመስገን ጋር አጥራው፡፡ ምሕረትንም ለምነው፡፡ እርሱ ጸጸትን በጣም ተቀባይ ነውና፡፡

ይህ የተለያዮ ኡለማዎች የተለያየ ተፍሲር ማዕና እንደሰጡት አውቃለው አዲስም አደለም የዛሬውን እይታ ግን ወላሂ አይቼም ሰምቼም አላቅም

ታውቃላችሁ ይህንን አያ ሳነበው ትዝ ሚለኝ የነብያችን ሞት መቃረብ መለየት የመካ መከፈት ብቻ ብዙ ታሪኮች ከነብያችን ጋር የተያያዘ ነበር።ዛሬ ግን አዲሱ እይታ እኛስ አንገባም ወይ ሚለው ነው።

ትላንት ከነበርንበት ችግር ያወጣን የአላህ ነስር አደለምን?የዱንያን በርስ አልከፈተልንም?ኒዕማን አልሰጠንም?ከትላንት ማያልፍ ከሚመስል ዳገት ማያልቅ ከሚመስል ቁልቁለት ያወጣን አላህ አይደለምን ለኛስ ነስሩን ፈትሁን አልሰጠንም?የጠየቅነውን ዱዓ አልሰማንም?……ይህ ሁላ ነስር እና ፈትህ ካልሆነ ታድያ ምንድነው ታድያ ወዳጆቼ

فَسَبِّحْ بِحَمْدِ رَبِّكَ وَاسْتَغْفِرْهُ ۚ إِنَّهُ كَانَ تَوَّابًا

ጌታህን ከማመስገን ጋር አጥራው፡፡ ምሕረትንም ለምነው፡፡ እርሱ ጸጸትን በጣም ተቀባይ ነውና፡፡

ተወዳጆች ጌታችንን ለሰጠን ነስር እና ፈትህ ከምስጋና ጋር እናጥራው ምህረትንም እንለምነው በርግጥ ጌታችን መሀሪና አዛኝ ነውና🥰

©ከኡስታዝ አብዱልአዚዝ ሙሀደራ የተቀነጨበ

አቡ ዙበይር{ሀምዛ}🙌

1 month ago
1 month ago

😍ሁሉንም ሀጃ አዳማጭም ሰጪ 🤲
🤗ማንም የለም አል ረህማን ውጪ ❤️
ኢምሀል ዱዐ ናፋቂ ቀልብ 1በዱኣቹ አላህ ያግራው በሉኝ🤗🤗

4 months ago

«መውሊድ» ከእስልምና አይደለም !!!

... ኢስማኤል ወርቁ...

https://t.me/amr_nahy1

4 months ago

ይቻላልም አይቻልምም ምትሉ ከማስረጃ ጋር የአላህ ዲን እንጂ ስሜት ቦታ የለውም

4 months ago

መውሊድ????

6 months, 3 weeks ago

ድንቅ ተግፃሳፅ ... ለእህቶቼ ይድረስልኝ ።

ፋጢማ ረዲአላሁ አንሃ አንድ ቀን ቁጭ ብላ እያለቀሰች  ሳለ ምን ሆነሽ ነው ለምን ታለቅሽያለሽ ? ብላ አንደኛዋ ጠየቀቻት !
እሷን ግን ያስለቀሳት የአዱኒያ ጉዳይ አልነበረም !!
መልሷ እንዲህ የሚል ነበር…… እያስለቀሰኝ ያለው  የሞትኩኝ እለት ጀናዛዬ ታጥቦ ተገንዞ ሲሰገድብኝ
ወንድ ፊት ነው ያኔ የምሆነው እና ወንዶች ሲሰግዱብኝ ከከፈኑ ውስጥ የሰውነቴ ቅርፅ ስለሚታይ ሊኖር የሚችለው ነገር አሁኑኑ ሳስበው ዘግንኖኝ ነው  አፍሬ ነው አለች ።

ሱበሃነላህ የምታለቅሰው ለዚህ ነበር

➟ የሰው ልጅ ሲሞት ስራው ይቋረጣል ሆኖም ሳለ ምንም አቅም በሌላት ጊዜ ለሚከሰተው ነገር ለተለመደው ነገር ቁጭ ብላ ታለቅሳለች  ዛሬ ግን  ያለውን ፈርቅ  እዩት !! ወላሂ ያሳዝናል የድሮዋ ፋጢማ እና የዛሬዋ ፋጢማ ልዩነቱን እስኪ እዩት !!
ያቺ ፋጢማ  ረዲአላሁ አንሃ በ5 ጨርቅ ተጠቅልላ ያውም ለምክንያት ለሰላት ሊሰገድባት  ያውም ጀናዛ ሬሳ ነው ምንም የሚታይ ወንድ አይቶት ለሚከሰተው ነገር ትጨነቅ ነበር ከሞተች ቦኋላ  አላህ አይጠይቃትም። 

እህቴ ዛሬ የእግርሽ ጥፍር ለምን ወጣ ? የፀጉርሽ ጫፍ ለምን ታየ ? ከሰውነትሽ ሽታ ወንድ ጋር ለምን ሄዳ ብሎ ወሏሂ አሏህ ይጠይቅሻል።
ረሱል ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ተናግረዋል  የትኛዋም ሴት ሽቶ ተቀብታ ከወንዶች አጠገብ አታልፍም  ወንዶች የእሷ ሽታ አይሸታቸውም  እሷ ዝሙተኛ ናት ዝሙተኛ ናት  ዝሙተኛ ናት ብለዋል ‼️

እያንዳንዱ ድርጊት ከረህማን ጋር ፣ ከአላህ ጋር ፣ ከማሊከል  ሙልክ ጋር የሚያጋጭ መሆኑን እያወቀች አንዴም ቁጭ ብላ አታለቅስም !  ለማልቀስም አታስብም ! እንደውም ስትመከር ሁሉ የምትሰጠው ምላሽ ሌላ ነው ። አላህ አላከረረም ፤ አላህ አላጠበቀም፤ እንደ ድሮ እንኑር ወይ ? የሚል የሚያሳዝን መልስ ትሰጣለች።

የምትገላለጭው እህቴ ሆይ ፦
ያለችሽ ሰዓት አሁኑኑ ነውና ወደ ጌታሽ ተመለሺ ።  ነገ ከነገ ወዲያ ሀገር ስገባ ፣ ባል ሳገባ ፣ የመሳሰሉትን  ምክንያቶችን  አታቅርቢ ። መለከል መውት በየትኛው ሰዓት ሩዕሽን እንደሚወስዳት ምን አሳወቀሽ ያ ኡክቲ

6 months, 3 weeks ago

የትኛውም የምግብ ራዳር ይጣሳል..እያባበልን የምንበላበት ጊዜ አብቅቷል!

6 months, 3 weeks ago

ዛሬ፣ ነገና ከነገ በኋላ እነዚህ ቀናቶች የመብላት፣ የመጠጣት፣ አላህን የማውሳት ቀናቶች ናቸውና አትፁሙ።]

7 months ago

ከሰለፎች መካከል የዐረፋህ ቀን ሲደርስ ዱዓእ አደርግበታለሁ ብለው ወሳኝ ጉዳያቸውን ቋጥረው የሚይዙ ነበሩ። አላህ ካደረሰን ይህ ድንቅ ቀን የፊታችን ቅዳሜ ነው። በተለይ ከሰዓት በኋላ በተለይም ከዐስር በኋላ ሁሉንም ጉዳያችንን ትተን ከወዲሁ ጊዚያችንን በማመቻቸት ወሳኝ ጉዳዮቻችንን ይዘን ለአላህ «ያ ረብ!» ለማለት እንዘጋጅ።

ከአላህ ውጭ ለማንም የማንነግራቸው፣ ብንነግራቸውም ሰዎች በአግባቡ የማይረዱን፣ ውስጣችንን የሚያብሰለስሉን ስንትና ስንት የታፈኑ እምቅ ስሜቶችና ጭንቀቶች አሉብን አይደል! በተለይ ደግሞ ሙእሚን ዱንያን እንደምንም ቢያልፋትም አኺራው ወሳኝ ነውና ሁሉንም ጉዳያችንን ለርሱ ለማመልከት እንዘጋጅ። አላህ ያግራልን።

We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 3 недели назад

Last updated 2 недели, 2 дня назад

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated 1 месяц назад