Dildiy - (ድልድይ)

Description
ሃሳብ፣ ንባብ፣ ኑረት፣ ሕይወት፣ ፍቅር እና ምናብ!!
_
https://dildiy.net

For feedback:

[email protected]
_

The problem is not to find the answer, it's to face the answer ~ Terence McKenna
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 4 months, 1 week ago

Last updated 4 months ago

ይህ ስለ Manchester United መረጃዎችን የሚያገኙበት የ Telegram ቻናል ነው 🇪🇹
--------------------------------------------------------------
☞︎| ስለ ማንቸስተር ዩናይትድ ትኩስ መረጃዎች
☞| ቀጥታ ስርጭቶች ከየስታድየሞቹ
☞| የዝውውር ዜናዎች
☞| ስለ ማንችስተር ዩናይትድ ታሪኮች

📩 ለማስታወቂያ ስራ DM :- @Marcoabdu

Last updated 3 months ago

2 months ago

ማሳረጊያ

___

[... ነገሩን በደንብ ከተመለከትነው የሰው ልጅ እንኳንና ከሌላ ከራሱም ነፃ አይደለም...]

____

[እንዲያው ግን ነገሩን ወደ መሬት ለማውረድ ያህል...]

🌿 ማድረግ የምትችለውን ሁሉ ማድረግ ነፃነት አይደለም… ከአድራጊነትህ ጋር ኃላፊነት አለ… ተግባርህ የሌሎችን ጉዳት ካስከተለ ከፀፀት አትነፃም… 

🌿 እንዳሻህ መናገር ወይም መፃፍ ነፃነት አይደለም… ቃልህ የአብሮ መኖር ሚዛን ካዛባ አልያም ጎራ ለይቶ ደም ካቃባ ከተጠያቂነት አትድንም… 

🌿 ነፃነት ብቻነትም አይደለም… ኑረት ለሌሎች ባለን አበርክቶት እንጂ በራስ ደሴት ጡዘት ከቴም አትሞላም… 

🌿 ነፃነት እንደልቡ መኖርም አይደለም… እንደ ደንቡ መመላለስ እንጂ…

____

[እህስ…]

🌼 ኦርጅናሌው ነፃነት የልጅነት ንጽሕና ይመስለኛል!! እንደልጅ ልጅነት - እንደ ሕፃን ‘ጅልነት’ የመኖር ድፍረት… የልጅነት ዓለም ከራሱ ከ’ነፃነትም’ ነፃ ያወጣል… ነፃ ነኝ ከሚለው ባዶ እምነትም ጭምር… 

🌼 ልጅነት ነፃነትን ይኖራታል እንጂ አያነፃጽራትም… ነፃ ነኝ አይደለሁም ውዝግብ የሌለበት ኑረት ነው ‘ነፃ ነፃነት’… የሚኖሩት ግን የማያስቡት… ከራስ ውስጥ የሚወልዱት… ፈቅዶ የሚቸርህ አልያም ከፍቶ የሚነሳህ የሌለበት እውነት ነው ነፃነት… 

🌼 ይህን ነፃነት ከሰንሰለት እስርም ሆነ ከግዞት ተከርቸም መሃል ሆነህ ልታጣጥመው ትችላለህ… ከደቋሽ ክንድና አደፍራሽ ሁከት ሳትርቅም ልትኖረው ትችላለህ… 

🌸 ምክንያቱም ‘ነፃ’ ነፃነት ነውና… 🌸

____

ብዙ ፍቅር!! 🌷🌷🌷

____

@bridgethoughts

2 months ago
Dildiy - (ድልድይ)
2 months ago

[ከጥበቃ ነፃ አይደለንም]… 

በአገኘዋለሁ ተስፋ ውስጥ እንደታሰርን አለን… በይመጣል ጥበቃ ውስጥ እንደታበትን አለን… 

ለኑረት አንዳች አበርክቶ የሌለው ሁሉ ቁጭ ብሎ ይጠብቃል… ከሰማይ ይጠብቃል… ከምድር ይጠብቃል… ከወዳጁ ይጠብቃል… ከመንግስት ይጠብቃል… 

ከጥበቃ ነፃ ስላይደለ ግምቱ ፍርሽ ሲሆንበት ይበሳጫል… ከሌሎች የሚጠበቀውን ልክ አበጅቶ “ከአንተ አይጠበቅም” ይላል… 

ደግሞ ወዲህ የሚጠብቀውን የማያውቅም አለ… ሳሙኤል ቤኬት አንድ ጊዜ “Waiting for Godot” የሚል አብሰርድ ድራማ ጽፎ ነበር… በድራማው ውስጥ የሚታዩት ሁለት ገጸባሕሪያት ካሉበት ጭንቅ ያወጣቸው ዘንድ In the middle of nowhere ቆመው የማያውቁትን አንድ ነገር ሲጠብቁ ይታያል… ተጠባቂው ሲመጣ ባይታይም እነርሱ ግን ጥበቃቸውን አያቋርጡም… 

አንደኛው ገጸባሕሪ በመሰላቸት: 

“Nothing happens, nobody comes, nobody goes, it's awful!” ይላል… 

ያም ሆኖ ቀረ ብለው አይንቀሳቀሱም… ምክንያቱም 'ጎዶትን' እየጠበቁ ነው…

ESTRAGON - Let's go. 

VLADIMIR - We can't. 

ESTRAGON - Why not? 

VLADIMIR - We're waiting for Godot. … 

የድራማው ፀሐፊ አንድ ጊዜ በጋዜጠኛ ተጠየቀ፡ “ጎዶት ማን ነው?”… 

ቤኬት መለሰ፡ “እኔም አላውቀውም”

___

@bridgethoughts

2 months ago
Dildiy - (ድልድይ)
2 months ago

[ከቂም ነፃ አይደለንም]… 

ስለት የቆረጠው ጣትህ ደም እስከመች ነው ይፈስ ዘንድ የምትተወው?... ነገር የጓጎጠው ልብህስ ገላ እስከመች ነው ይቆስል ዘንድ ችላ የምትለው?... 

የጣትህ ደም ፍሰት አንተ ችላ ብትለውም በደምህ ውስጥ ያሉት ፕላትሌትስ ከየቦታው ተጠራርተው በሚሰሩት ግድብ /Blood clotting/ ይቋረጣል… የልብህ ቁስል ግን ፈቅደህ በምትሰጠው ይቅርታ እንጂ በሌላ መንገድ አይጠግም… 

ይቅርታ ከሚደረግለት በላይ ለአድራጊው የሚሰጠው ሰላም ትልቅ ነው… ቂመኛ ስትሆን በዳዬ ያልከውን ባየህ አልያም ባሰብክ ቁጥር በደሉ ካደረሰብህ የአንድ ጊዜ ሁነት በላይ ደጋግመህ ትታመማለህ… ይቅር ስትል ግና ከመጀመሪያው ቁስልም ትፈወሳለህ… 

ያልኖርክበትን ዘመን ጠቅሰህ የለውጥን እርሾ ነው የክፋትን ቁርሾ የምታሻትተው?… የትናንትን በደል ቆጥረህ በግመል ሽንት ነው በቀስት አቅጣጫ ጉዞህን የምትቃኘው?… 

ቅድመ አያትህ ለአያትህ ያሻገረውን ክፋት ትተህ ጥበቡን ቀምር፣ አያትህ ለአባትህ የተወውን ጠብመንጃ ጥለህ ሞፈሩን አንሳ፣ ከአባትህ የፍቅር ታሪክ ለልጅህ ጦማር አዘጋጅ… ‘ስታልፍ’ የሚነበበው ታሪክህ እርሱ ብቻ ነውና…

___

@bridgethoughts

2 months ago
Dildiy - (ድልድይ)
2 months ago

[ከትርጉም ነፃ አይደለንም]… 

በኑረት ሃዲድ ላይ እርምጃዎቻችንን የሚወስኑ ትርጉማ ትርጉሞችን የያዘ ኮሮጆ አለን… ለነገሮች የሚኖረን ምላሽ ትርጉማችን ላይ ይንጠለጠላል… በትክክል ከትርጉም እስራት ነፃ አይደለንም… 

ለሕይወት ያለህ ትርጉም ነው - የእልፍ በረከቷን ጓዳ አልያም የንፉግነቷን ጎድጓዳ የሚያሳይህ… ለፍቅር ያለህ ትርጉም ነው - የዓይናማነቱን ድምቀት አልያም የእውርነቱን ጽልመት የሚያቆይህ… ለስራ ያለህ ትርጉም ነው - የወዝህን ሲሳይ አልያም የሌሎችን ፍሬ ብካይ የሚያስመኝህ… ሌላውም ሁሉ እንዲሁ ነው… 

ትርጉም ከሰጠህ በኋላ ሌላ ተዓምር መጠበቅ የለብህም… መዝገቡን ከዘጋህ በኋላ ሌላ ምዕራፍ ሊኖር አይችልም… ትርጉም ያበጀህለት ታስረሃል - ነገርህንም ቋጥረሃል… ከልብ ደስተኛ የሆነ አንድ ሰው ታውቅ እንደሁ ለነገሮች ያለውን አተያይ ጠይቀው… ወይ የትርጉም ሜኑ የለውም - ሁሉን እንዳመጣጡ ተቀብሎ ይኖራል… አልያም በጎ በጎዎቹ ትርጉሞች የኑረቱ አካል ናቸው…

___

@bridgethoughts

2 months ago
Dildiy - (ድልድይ)
2 months ago

[ከነኝታ ነፃ አይደለንም]… 

‘እንዲህ ነኝ’ – ‘እንዲያ ነኝ’ ስትል የምትውለው ከነኝታህ ተጽዕኖ መላቀቅ ባለመቻልህ ነው… ነኝታህ ከመሆንታህ ይበልጥብሃል… የሆንከው ግን ነኝ ከምትለው የማይናጸር ጥልቅ ነው… 

ነኝታህ የመሆንታህን ብርሃን ያደበዝዛል… ነኝታህ ከጎሳህ፣ ከስራህ፣ ከችሎታህ፣ ከሃብትህ፣ ሐይማኖትህ… ወዘተ ይመነጫል… መሆንታህ ግና የአማናዊው ተፈጥሮህ መሰረት ነው… The essence of who you are in the deepest level... አግዮስ፣ ንዑድ፣ ክቡር፣ ጽሩይ… 

ነኝ የምትለውን ሁሉ አውልቀህ ብትጥል ምን የሚቀር ይመስልሃል?… ምንም!... መሆንታው ላይ የቆመ ግና ያልሆነው ስለሌለ ነኝ የሚለው አይኖረውም… የሚያጣው ስለሌለው ባዶነት አይሰማውም…

___

@bridgethoughts

2 months ago
Dildiy - (ድልድይ)
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 4 months, 1 week ago

Last updated 4 months ago

ይህ ስለ Manchester United መረጃዎችን የሚያገኙበት የ Telegram ቻናል ነው 🇪🇹
--------------------------------------------------------------
☞︎| ስለ ማንቸስተር ዩናይትድ ትኩስ መረጃዎች
☞| ቀጥታ ስርጭቶች ከየስታድየሞቹ
☞| የዝውውር ዜናዎች
☞| ስለ ማንችስተር ዩናይትድ ታሪኮች

📩 ለማስታወቂያ ስራ DM :- @Marcoabdu

Last updated 3 months ago