ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated 4 months, 1 week ago
Last updated 4 months ago
ይህ ስለ Manchester United መረጃዎችን የሚያገኙበት የ Telegram ቻናል ነው 🇪🇹
--------------------------------------------------------------
☞︎| ስለ ማንቸስተር ዩናይትድ ትኩስ መረጃዎች
☞| ቀጥታ ስርጭቶች ከየስታድየሞቹ
☞| የዝውውር ዜናዎች
☞| ስለ ማንችስተር ዩናይትድ ታሪኮች
📩 ለማስታወቂያ ስራ DM :- @Marcoabdu
Last updated 3 months ago
በደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ አስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ በውጭ ገምጋሚዎች አማካኝት ለ5 ቀናት ሲካሄድ የቆየው የእውቅና አሰጣጥ አውደ ጥናት የካቲት 14/2017 ዓ.ም ተጠናቀቀ፡፡ በማጠቃለያ ፕሮግራሙ ላይ ለህክምና፣ ለአንስቴዥያ፣ ለነርሲንግና ለሚድዋይፈሪ ትምህርት ክፍሎች በውጭ ገምጋሚዎቹ የተሰጣቸው ግብረመልስ ቀርቦ ውይይት ተካሂዶበታል፡፡
በውይይት መድረኩ የደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ አካዳሚክ ምክትል ፕሬዚዳንት ጌትነት አሸናፊ (ዶ/ር)፣ የአስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶ/ር ቴዎድሮስ ክፍለዮሐንስ፣ ዶ/ር ኤርሚያስ እንደውነት የህክምና አገልግሎት ትምህርትና ጥራት ኮርፖሬት ዳይሬክተር፣ የካምፓሱ መምህራን፣ ሀኪሞች፣ የተለያዩ የአካዳሚክና አስተዳደር ስራ አስፈፃሚዎችና ቡድን መሪዎች እንዲሁም ከዋናው ግቢ የተጋበዙ መምህራን ተሳታፊዎች ሆነዋል፡፡
ዶ/ር ኤርሚያስ እንደውነት የአስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ የህክምና አገልግሎት ትምህርትና ጥራት ኮርፖሬት ዳይሬክተር እንዳሉት የእውቅና ጉዳይ በተቻለ መጠን የየእለት ስራችን እየሆነ ሲሆን ተከታታይነትና ቀጣይነት ያለው ባህል እስከሚሆን ድረስ ጠንከረን ልንሰራ ይገባል ብለዋል፡፡
የማጠቃለያ መድረኩን የመሩት ዶ/ር ቴዎድሮስ ክፍለዮሐንስ የአስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ ዋና ስራ አስፈጻሚ ለውጭ ገምጋሚዎቹ ላቅ ያለ ምስጋና አቅርበው መድረኩ ብዙ ልምዶችን ያገኘንበት፣ ክፍተቶቻችንን ያየንበት፣ የላቀ ትምህርት የወሰድንበት በመሆኑ የተሰጡ አስተያየቶችን፣ ድክመቶችንና ክፍተቶችን ሙሉ በሙሉ የምንወስድና የምንቀበል ይሆናል ብለዋል፡፡አክለውም እነዚህ የተሰጡ አስተያየቶችና የታዩ ክፍተቶች ተካተውና ተስተካክለው በቀጣይ ሳምንት ተጨማሪ ውይይቶች የሚካሄድና ሰነዶቹ የሚዳብሩበት ሁኔታ ይፈጠራል በማለት ምላሽ ሰጥተዋል፡፡
የደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ አካዳሚክ ምክትል ፕሬዚዳንት ጌትነት አሸናፊ (ዶ/ር) በበኩላቸው ዩኒቨርሲቲው ካሉት 36 ፕሮግራሞች 23ቱን በሀገር አቀፍ ደረጃ እውቅና እንዲያገኙ እየሰሩ መሆኑን ገልጸው አስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ የጀመራቸውን 4 ፕሮግራሞች በዚህ ዓመት አጠናቆ እውቅና እንደሚያገኝ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል፡፡ይህ በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚሰጠው እውቅና ጥሩ ጅማሮ በመሆኑ ወደ አለማቀፍ እውቅና ለመሄድም የሚረዳ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ከዚህ በፊት የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች እውቅና አይሰጣቸውም ነበር፤አሁን ግን እውቅና ማግኘት ግዴታ ስለሆነ በተመረጥንባቸው ፕሮግራሞች ስራችንን ጠንክረን በመስራት ሀገር አቀፍ ደረጃ አውቅና ማሰጠት ይኖርብናል ብለዋል፡፡
በመጨረሻም በዚህ አውደ ጥናት ላይ የውጭ ገመጋሚዎች በመሆን ለተሳተፉት ከትምህርትና ስልጠና ባለስልጣንና ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ለመጡ ባለሙያዎች የምስክር ወረቀት ተሰጥቷል፡፡
መብራት ከጠፋ 3 ቀን
አስራት ወልደየስ ጤና ካምፓስ የሚማሩ ተማሪዎች መብራት ጠፍቶብናል። ጄኔሬተር እስከ ምሽት 4 ሰዓት ብቻ ነው የሚሰራው። ያለብንን የጥናት ስፋት መሸፈን አልቻልንም በማለት ቅሬታቸውን እያቀረቡ ይገኛሉ።
መፍትሔ መስጠት የሚችል አካል አለሁ ይበላቸው።
የሴቶች ዶርም ድልድል
የወንዶች ዶረርሚተሪ ድልድል
መረጃውን ሼር አድርጉ
ውድ የአ/ወ/ጤ/ሳ/ካ/ተማሪዎች
#የመግቢያ ቀንን በተመለከተ ከብዙ ተማሪዎች ጥያቄ እየደረሰን ነው።
ከ ካምፓሳችን ምንም አይነት የተወሰነ የመግቢያ ቀን ስለሌለ መረጃው እንደደረሰን በዚሁ ቻናላችን ይፋ የምናደርግ ይሆናል።
እስከዛው በትዕግስት እንድትጠብቁ ስንል በትህትና እንጠይቃለን።
ተ/ህብረት
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated 4 months, 1 week ago
Last updated 4 months ago
ይህ ስለ Manchester United መረጃዎችን የሚያገኙበት የ Telegram ቻናል ነው 🇪🇹
--------------------------------------------------------------
☞︎| ስለ ማንቸስተር ዩናይትድ ትኩስ መረጃዎች
☞| ቀጥታ ስርጭቶች ከየስታድየሞቹ
☞| የዝውውር ዜናዎች
☞| ስለ ማንችስተር ዩናይትድ ታሪኮች
📩 ለማስታወቂያ ስራ DM :- @Marcoabdu
Last updated 3 months ago