Yared Alayu

Description
@Thanks5r

AMHARA VOICE


ይህ ቻናል ወቅታዊ Amhara ዊ መረጃዎችን የሚያገኙበት ነው!!
══════
@enGroupHelp
@GroupHelp
@esGroupHelp
@ptGroupHelp

One Amhara




📣
Advertising
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 2 months, 1 week ago

Last updated 6 days, 22 hours ago

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ ? @Esat_tv_comment_bot

??ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ??

Last updated 2 months, 3 weeks ago

5 days, 6 hours ago

በአስገዳጅ ብሔራዊ ውትድርና ስም በሚደረግ ጭፍጨፋ እና በኢትዮጵያዊያን ወጣቶች ደም የሚፀና ስልጣን አይኖርም!!!

አፋጎ (AFG)
```````````

የውድቀት አፋፍ ላይ የሚገኘው የብልጽግናው አገዛዝ በአማራ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች በከተሞች የሚገኙ የቀን ሰራተኞችን፣ የትምህርት ገበታ ላይ የተቀመጡ ህጻናትን፣ አስተማሪዎቻቸውንና የመንግስት ሰራተኞችን የፋኖ ደጋፊ ናችሁ በሚል ሰበብ በገፍ እያፈሰ የተሀድሶ ስልጠና በሚል ያዘጋጀውን ማደናገሪያ በመጠቀም አስገድዶ ወደ ማጎሪያ ካምፖች ሲያግዝ የቆያቸውን ወጣቶች ወደ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ተቋማት በማጓጓዝ ላይ ነው።

ከአማራ ክልል እያፈሰ ወደ አልታወቀ ቦታ የሚወስዳቸውን ወጣቶች በርሃብ፣ በበሽታና በድብደባ አለፍ ሲልም ሰበብ እየፈጠረ በመረሸን እንደሚያጠፋቸው የታወቀ ነው። ለዚህም በአማራው ህዝብ ላይ ይፋዊ ጦርነት ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ በጀግናው የአማራ ፋኖ ሃይል በተደመሰሰ ቁጥር በመኖሪያ ቤታቸው፣ በአደባባይ ቦታዎችና በቤተ እምነቶች የሚማሩ የአብነት ተማሪዎችን፣ ህፃናትና አረጋውያንን አማራ በመሆናቸው ብቻ በጅምላ ሲረሽን መክረሙ በቂ ማሳያ ነው። ሰሞነኛው የአብይ አህመድ አፈሳም የጀርመኑ ናዚ በአይሁዳውያን ላይ ሲፈፅመው እንደነበረው የኦሺዊትዝ የእገታ ማዕከል የሚታይ አማራን ወጣት አልባ ህዝብ በማድረግ ለማጥፋት የሚደረግ አፈሳና እመቃ በመሆኑ የተለመደ የውትድርና አፈሳ ነው ብሎ መዘናጋት በራስ ላይ ሞት እንደማወጅ ያለ ነው።

ኢትዮጵያዊያን ወጣቶችን ሁሉ የስልጣን ማስጥበቂያ ዕቃዎች እንደሆኑ አድርጎ የሚቆጥረው ይህ አገዛዝ ይህንን የአፈሳ ተግባሩን እንደ አማራ ክልሉ ሁሉ በተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች ያለምንም ሃፍረት በማናለብኝነት እያከናወነ ይገኛል። ይህ የአገዛዙ ተግባር የሃገሪቱን አምራች ዜጎች በጅምላ በመጨፍጨፍና ወደ ወታደራዊ ካምፕ በማጋዝ እርስ በእርስ በማጫረስ ወጣት አልባ ሃገር ለመፍጠር  አረመኒያዊ ተግባር እየፈፀመ መሆኑን በግልፅ ያሳየበት ነው።

ከኦሮሚያ አካባቢ የሚያፍሳቸውን ወጣቶች በዘረኝነትና በፀረ አማራነት እየቀሰቀሰ "የኦሮሞ መንግስት ነው፤ መንግስታችሁን ከመውደቅ አድኑት" እያለ አገሪቱን ወደ ባሰ የእርስ በርስ ጦርነት ለማስገባት ቆርጦ መነሳቱንና የወጣቶችን አዕምሮ እየበረዘ በማታለል ማሰለፍ ያልቻለው ብልፅግና በግድ እና በሽብር የሃሰት የግድያ ፈጠራዎችን አቀናብሮ ቪዲዮ በማሳየት፣ በካድሬዎቹ በኩል የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን በግድ ሰልፍ በማስወጣት ሽብርና ግርግር በመፍጠር የኦሮሞን ህዝብ ጭምር እረፍት እየነሳ ይገኛል።

ስለሆነም-

  1. ሰሞነኛው አፈሳ አስገዳጅ ብሄራዊ ውትድርና ሳይሆን አማራን በአንድ ላይ ማመቅና ሲስተማቲክ በሆነ መልኩ በተለያዩ ስልቶች ወጣት አልባ ለማድረግ ያለመ መሆኑን ተረድቶ መላው የአማራ ህዝብ የአገዛዙን ህገ ወጥ ድርጊት ተቃውሞ እንዲቆም፣ በተለይ ወጣቱ ጨርቄን ማቄን ሳይል በየአካባቢው በሚገኘው የፋኖ አደረጃጀት ውስጥ በመካተት ራሱንና ህዝቡን ከጥፋት እንዲያድን ጥሪ እናቀርባለን።

  2. የደርግ ዘመን ብሄራዊ ውትድርና ማንኛውም ዕድሜና ጤናው የሚፈቅድለት ዜጋ አገሩን በውትድርና የማገልገል ግዴታ አለበት በሚል በአዋጅ የተደገፈ ነበር። ይሁንና ከመብት አኳያ ያለ ግለሰቦች ይሁንታ የሚፈፀም ትክክል ያልሆነ ተግባር ቢሆንም በይፋ የታወቀና ሌላ የተለየ ሥጋት የሚፈጥር አልነበረም። የደርግ ብሄራዊ ውትድርና ተቀባይነት ስላልነበረው ውጤት ማምጣት አልቻለም። ይልቁንም ውድቀቱን እንዳፋጠነው የቅርብ ታሪካችን ነው።  "በፊት የበቀለውን ጀሮ በኋላ የበቀለው ቀንድ በለጠው" እንዲሉ  የብልፅግናው አገዛዝ ከደርግ ዘመን በከፋ ሁኔታ ወጣቶችን በጅምላ እያፈሱ ወደ ወታደራዊ ካምፖች እያስገባ ነው። ድርጊቱም የኢትዮጵያን ዳር ድንበር ለመጠበቅ ሳይሆን ኢትዮጵያውያንን እርስ በእርስ ለማጫረስ ያለመ በመሆኑ ሁሉም ኢትዮጵያውያን ይህንን የአገዛዙን ሴራ ተረድቶ በጋራ በመቆም ድርጊቱን እንዲያወግዝ ጥሪ እናቀርባለን።

  3. በኦሮሚያና በደቡብ የሀገራችን አካባቢዎች የምትገኘ ኢትዮጵያውያን አፈሳው አብይ አህመድን ስልጣኑን ለማስጠበቅ የሚፈፅመው አረመኒያዊ ተግባር እንጅ ጠንካራ የመከላከያ ኃይል በመፍጠር የኢትዮጵያን ዳር ድንበር ለማስጠበቅ በማሰብ አለመሆኑን ተገንዝባችሁ በአማራ ህዝብ ላይ ለከፈተው ጦርነት ተባባሪ እንዳትሆኑ፣ ልጆቻችሁንም እንዳታስጨርሱ ይልቁንም ከአማራ ህዝብ ጎን እንድትቆሙ ጥሪ እናቀርባለን።

  4. ዓለምአቀፉ ማህበረሰብና የሰብአዊ መብት ድርጅቶች ይህን ይፋ የሆነ ህገ ወጥ ድርጊት እንዲያወግዝና ከህዝባችን ጎን እንዲቆም ጥሪ እናቀርባለን።

ፎቶው:- በዘመቻ መቶ ተራሮች እጅ የሰጡ ምርኮኞችን ለአንድ ዓለም አቀፍ ጋዜጠኛ ስናስጎበኝ የተወሰደ ነው።

አስረስ ማረ ዳምጤ

@yaya192123
@yaya192123
@yaya192123

5 days, 11 hours ago

ሰበር ዜና!

የአማራ ፋኖ በወሎ ተጠናክሮ በቀጠለው የህልዉና ተጋድሎ ወልድያ ዙሪያ ከባድ ተጋድሎ በማድረግ ታላቅ ድል ተጎናፀፈ::

የሰሜን ወሎ ዞን ዋና መቀመጫ ወልድያ ከተማና በዙሪያው በርካታ ተጋድሎዎችን እያደረገና በርካታ ድሎችን እየተጎናፀፈ የሰነበተው በዋርካው ምሬ ወዳጆ የሚመራው የአማራ ፋኖ በወሎ ከትናትና ህዳር 19/2017 ዓ.ም ማለዳ ጀምሮ እስከ ዛሬ ንጋት ለ24 ሰዓት ቀንና ሌሊት ያለማቋረጥ በተደረገው ተጋድሎ 49ኛና 52ኛ ክፍለጦር የአብይ አህመድ ዙፋን ጠባቂ የጠላት ሃይል በርካታ ሙትና ቁስለኛ ሆኖ ይዞታወቹን ለጀግኖቹ አስረክቦ እንደተለመደው  ፈርጥጧል::

በተጋድሎው አሳምነው ክፍለጦር አራት ሻለቆችና ሃውጃኖ ክፍለጦር ሁለት ሻለቆች የዞብል አምባ ክፍለጦር ሁለት ሻለቆችን ተጠባባቂና ደጀን አድርገው የተፋለሙ ሲሆን በጠላት በኩል ሁለት ክፍለጦር አሰልፎ በርካታ ተጋድሎዎች ተደርገዋል::

በፍልሚያዉም የጠላት ሃይል ከፋኖ መካናይዝድ በኩል የሚወነጨፍበትን ሞርተር መቋቋም ያቃተው ሲሆን ወልድያ ስታዲዮምና ማር ማቀነባበሪያው ላይ ያለ ጠላትም የሞርተር ጥቃት ተፈፅሞበት በርካታ ሙትና ቁስለኛ ሆኗል::

ተጋድሎው በበርካታ የወሎ ቤተ-አምሐራ ቀጠናዎች በበርካታ የደፈጣና የመደበኛ ዉጊያ ድሎች ታጅቦ  እየተደረገ ያለ ሲሆን በቅርቡም የወረዳና የዞን ከተሞችን መቆጣጠርን ያለመ ተጋድሎ የሚደረግ ይሆናል:: በእስካሁኑ ተጋድሎዎችም ከራያ አላማጣ ዋጃ እስከ ወልድያና ደሴ የፌደራል መንገድ እየተባለ የሚጠራዉን መስመር ጨምሮ በርካታ የቀጠናው አካባቢዎች በፋኖ ቁጥጥር ስር ያሉና የህዝብ አስተዳደርም የተዘረጋበት ሁኔታ እንዳለ የሚታወቅ ነው::

በቀጣይም የህልዉና ተጋድሎው እስከ ድልና ነፃነት ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ድል ለፋኖ
ድል ለ አማራ ህዝብ
የ አማራ ፋኖ በወሎ
ህዳር 20/2017 ዓ.ም

@yaya192123
@yaya192123
@yaya192123

5 days, 13 hours ago

መረጃ‼️

**በአማራ ክልል በተፈጸሙ የተለያዩ-የድሮን ጥቃቶች ቢያን 450 ሰዎች መገደላቸዉ ተዘገበ

በክልሉ በሁለት አመት ገደማ ዉስጥ በትንሹ ከ 50 በላይ የድሮን ጥቃት ተፈጽሟልም ተብሏል**

የኢትዮጵያ መንግሥት ሠራዊትና በአማራ ክልል የሸመቁት የፋኖ ታጣቂዎች ዉጊያ ከገጠሙ ወዲሕ የመንግሥት ጦር በሰዉ አልባ አዉሮፕላኖች (ድሮን) ባደረሰዉ ተደጋጋሚ ጥቃት በትንሹ 450 ያክል ሰዎች መገደላቸዉ ተዘገበ።

የኢትዮጵያ ፒስ ኦብዘርቫቶሪ የተሰኘዉ ተቋም እንደሚለዉ ከሚያዝያ 2015 እስከ ሕዳር 2017 ባለው ጊዜ ዉስጥ በአማራ ክልል 54 የድሮን እና የአየር ጥቃቶች መፈጸማቸውን መዝግቧል።

ይሁንና “ራቅ ባሉ የሀገሪቷ አካባቢዎች የሚፈፀሙ የድሮን ጥቃቶችን ለመዘገብ ያለው አስቸጋሪ ሁኔታ ሲታይ ይህ አሃዝ ዝቅተኛ ግምት” ሊሆን እንደሚችል ፒስ ኦብዘርቫቶሪ አስታውቋል።

በጥቃቶቹ የፋኖ ታጣቂዎች እና ሰላማዊ ሰዎችን ጨምሮ 449 ሰዎች መገደላቸው ሪፖርት እንደተደረገ በኢትዮጵያ ፒስ ኦብዘርቫቶሪ ተመዝግቧል።

የአማራ ማኅበር በሰሜን አሜሪካ የአድቮኬሲ ዳይሬክተር ሆነ ማንደፍሮ  ደግሞ በአማራ በሚደረገዉ ጦርነት የመንግሥት ሥልት “በከፍተኛ ደረጃ ድሮን መሠረት ያደረገ” በመሆኑ “ንጹኃን ዜጎች ላይ ከፍተኛ ሰብአዊ ጉዳት እየደረሰ ነው” ሲሉ ይናገራሉ።

ጥቃቶቹ ሰዎች የሚሰበሰቡባቸው አደባባዮች፣ የትምህርት፣ የጤና እና የዕምነት ተቋማት ዒላማ ማድረጋቸውን የሚናገሩት አቶ ሆነ “ ከጦርነቱ ጋር ግንኙነት የሌላቸውን ንጹኃኖችን እየጨፈጨፉ ነው።

ይኸ ደግሞ በስሕተት አይደለም” ሲሉ ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል።

ማኅበራቸው ከጥቅምት 5 ቀን 2016 እስከ ሕዳር 14 ቀን 2017 ባለው ጊዜ ውስጥ በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች በተፈጸሙ 125 የድሮን እና የአየር ጥቃቶች 754 ሰዎች መገደላቸውን እና 223 መጎዳታቸውን መዝግቧል። “እኛ የምንመዘግባቸው የድሮን ጥቃቶች በሰላማዊ ሰዎች ላይ ብቻ ዒላማ ያደረጉ ናቸው” የሚሉት አቶ ሆነ “ተዋጊ ኃይሎች ላይ የድሮን ጥቃት ከደረሰ አንመዘግብም” ሲሉ አስረድተዋል።

Via DW

አማራና የአማራ መሬት ያልቻለው ነገር የለም።

@yaya192123
@yaya192123
@yaya192123

1 week, 5 days ago

የአማራ ፋኖ በጎጃም ህዳር 13/2017 ዓ.ም

✍️#የ3ኛ(የጎጃም አገው ምድር ክፍለ ጦር ዛሬም እንደተለመደው የአብይን ጭፍራ ሰራዊት በከበባ ሲያጭድ ሲወቃው ውሏል።ዛሬ ሞት የጠራው የብርሃኑ ጁላ ጦር ከተለያዩ ቦታዎች አሰባስቦ ወደ አይደፈሬዎች መንደር ፋግታ ከተማ ቢመጣም #ዋዝ ላይ ሲለበለብ ውሏል።
በውጊያው

✍️ #፲ አለቃ ኤፍሬም አጥናፉ ብርጌድ (ያፋግታ ለኮማ ወረዳ

✍️ #ቢትወደድ መንገሻ ጀንበሬ ብርጌድ(ዳንግላና አካባቢው)

✍️ #ዘንገና ብርጌድ(ቲሊሊና አካባቢው) በጥምረት የአብይን ገዳይ ቡድን እያጨዱ ሲከምሩት ውለዋል።

✍️ከ120 በላይ ጠላት ሙትና ቁስለኛ ተደርጓል።ጠላትን መልሰው በመጣበት እግሩ ሰደውታል።የፋኖን በትር ያልቻለው የጠላት ኃይል 3 ንጹሃንን ጤፍ እየወቁ በነበረበት ሰዓት በግፍ ረሽኗል።

✍️#የ2ኛ(ተፈራ ዳምጤ)ክፍለ ጦር አካል የሆነው የጎንጅ ቆለላው #ንስር ብርጌድ 3ኛ ሻለቃ ከጎንጅ ከተማ ወጥቶ ወደ ዴጋንሳ ቀበሌ ሲንቀሳቀስ የነበረን ጠላት በደፈጣ ልኩን አግኝቶ የአንድን የፋኖ አመራር ቤት አቃጥሎ ተመልሷል።

#የ5ኛ(የራስ ቢትወደድ መንገሻ አቲከም) ክፍለ ጦር አካል የሆነው ሁሌም ባለድሉ #አረንዛው ዳሞት ብርጌድ ቢተው(ማንኩሳ) ሻለቃ ማንኩሳ ከተማ ላይ የነበረን ጠላት ሙትና ቁስለኛ በማድረግ ከሞት የተረፈው ጠላት እግሬ አውጭኝ ብሎ በመፈርጠጡ ማንኩሳ ከተማን ከጠላት ነፃ ማድረግ ተችሏል።

✍️በሌላ ግንባር ይሄው አረንዛው ዳሞት ብርጌድ ፍኖተ ዳሞት ሻለቃ ከብርሸለቆ፣ከፍኖ ተሰላምና ከማንኩሳ አወጣቶ አሰሳ ላይ የነበረን የጠላት ኃይል #ክሊኒክ(ርግብ) ላይ ጠላትን ረፍርፈው ሙትና ቁስለኛውን አሸክመው መልሰው ሰደውታል።

✍️ ሰሞኑን ወደ የቦቅላ ንዑስ ወረዳ በ4 አቅጣጫ ሂዶ የነበረው ጠላት በጀግኖቹ የ7ኛ ክፍለ ጦር አናብስቶች ተመቶ ሲመለስ የቦቅላ ከተማ ላይ ካሉ ባንኮች ለጥበቃነት ሲያገለግል የነበረን የጦር መሳሪያ ዘርፎ ወጥቷል።

✍️ ከፀደይ ባንክ 3 የጦር መሳሪያ
አቡና ባንክ 2 የጦር መሳሪያ
ከንግድ ባንክ 2 የጦር መሳሪያ እንዲሁም ከየቦቅላ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት 1 የጥበቃ መሳሪያ በድምሩ 8 የተቋማትን መጠበቂያ መሳሪያ ወስደዋል።

✍️ይሄን መሳሪያ ከወሰዱ በኃላ ከፋኖ የማረኩት ለማስመሰል እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ።
አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ፣አዲስ ተስፋ!

ፋኖ ዮሐንስ አለማየሁ
የአማራ ፋኖ በጎጃም ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ምክትል ኃላፊ

@yaya192123
@yaya192123
@yaya192123

1 week, 5 days ago

ወሎ ቤተ-አምሐራ

የአማራ ፋኖ በወሎ በቀጠለው የህልዉና ተጋድሎ ጠላትን በደፈጣ ጥቃት ሙትና ቁስለኛ በማድረግ ማሳቀቅ ረፍት መንሳቱና መፈናፈኛ ማሳጣቱ ብሎም በደፈጣ ተዳክሞ ሲገኝ በመደበኛ ዉጊያ መደምሰስና መማረኩ ተጠናክሮ ቀጥሏል::

ዞብል አምባ ክፍለጦር ካለው ሰራዊት 1ኛ ሻለቃ እና በፋኖ አሻግሬ ሙሉ (ቦምበኛው) የሚመራው የአማራ ፋኖ በወሎ ልዩ ዘመቻ ዛሬ ህዳር 13/2017 ዓ.ም በጋራ በወሰዱት የደፈጣ ጥቃት ታላቅ ድል ተጎናፅፈዋል::

ጥቃቱ ከቆቦ ከተማ በምዕራብ ተኩለሽ መስመር ከ4-5 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የተፈፀመ ሲሆን በደፈጣ ጥቃት የተጀመረው ዉጊያ ወደ መደበኛ አድጎ ጠላት በርካታ ሙትና ቁስለኛዉን ይዞ ወደ ቆቦ ከተማ ፈርጥጧል:: የደፈጣ ጥቃቶቹ ከከተሞች በቅርብ ርቀት ተጠናክረው የቀጠሉ ሲሆን ጠላትም በበርካታ ጥቃቶች ተሰላችቶ ወደ ፋኖ እየኮበለለ ይገኛል::

ራያ ቆቦ ተኩለሽ የገባው ጠላትም መሉ ለሙሉ ከበባ ዉስጥ ገብቶ ረሽንና ተጨማሪ የሰው ሃይል እንዳይደርሰው ሆኖ ያለበት ሁኔታ ነው ያለው ሲል የዞብል አምባ ክፍለጦር ህዝብ ግንኙነት ፋኖ ሃብተማርያም መንበሩ ገልፇል::

በቀጣይም የህልዉና ተጋድሎው እስከ ድልና ነፃነት ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲሉ የዞብል አምባ ክፍለጦር አመራሮች እና የልዩ ዘመቻ አዛዡ ፋኖ አሻግሬ ሙሉ (ቦምበኛው) ገልፀዋል::

ድል ለፋኖ
ድል ለአማራ ህዝብ
የአማራ ፋኖ በወሎ
ህዳር 13/2017 ዓ.ም

@yaya192123
@yaya192123
@yaya192123

1 week, 5 days ago

የተጋድሎ ውሎ መረጃ
የአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ ከሰም ክፍለጦር ተስፈ ብርጌድ ከልጓም የለሹ የብልፅግና ቡድን ጋር ሲፋለም ዋለ።
ህዳር 13/2017 ዓ/ም
ሸዋ አማራ ኢትዮጵያ
አማራን ጨርሼ በኢትዮጵያ ፍርስራሽ ላይ ኦሮሙማን እገነባለሁ የሚለው የወፈፌው አብይ አህመድ አሊ ኦህዴድ መራሹ የብልፅግና ቡድን ዛሬም በሸዋ ጠቅላይ ግዛት በቀድሞ አጠራሩ ተጉለትና በልጋ አውራጃ በረኸት ወረዳ በተለያዩ ቀበሌዎች በታንክ በመቶ ሰባት በሞርተር ዙ23 እና መሰል ከባድ መሳሪያዎች የታገዘ ዉጊያ ከአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ ከሰም ክፍለጦርር ተስፋ ገብረስላሴ ብርጌድ ጋር ሙሉቀን የፈጀ ፍልሚያ ሲካሄድ መዋሉን ማረጋገጥ ተችሏል።

ዛሬ ህዳር 13/2017ዓ/ም ከሌሊቱ 9:00ሰዓት ላይ መነሻውን የበረኸት ወረዳ መቀመጫ ከሆነችው መተህብላ ከተማ አድርጎ መድረሻውን በረኸት ወረዳ ቀበሌ04 የተንቀሳቀሰው የአገዛዙ አራዊት ሰራዊት በጀግኖቹ የአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ ከሰም ክፍለጦር ተስፋ ገብረስላሴ ብርጌድ ድባቅ የተመታ ሲሆን በበርካታ ተሽከርካሪዎች አስክሬኑ ወደ መተህ ብላ ከተማ ሲያመላልስ ውሏል።

በደረሰበት ምት የተበሳጨው ወራሪው የኦህዴድ መራሹ አራዊት ሰራዊት ሀገር ሰላም ብለው በቤታቸው የተቀመጡ ሴቶች አዛውንቶችና መሰል ግለሰቦችን በማገት ተጠምዶ የዋለ ሲሆን ይህ ዜና እስካጠናከርንበት ጊዜ ድረስ ጦርነቱ እንደቀጠለ ነው።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የኦነግ መራሹ የብልፅግና ሰራዊት የአማራን ህዝብ አልወጋም በማለት በየቀኑ ከነ ሙሉ ትጥቁ ፋኖን መቀላቀሉ የቀጠለ ሲሆን ከትናንት ህዳር 12/2017 ዓ/ም እስከዛሬ ህዳር 13/2017ዓ/ም ከደብረብርሃን ከተማ አስተዳደር አፄዘርዓያዕቆብ ከፍለከተማ ጎሸባዶ ቀበሌና ከሌሎች ቦታዎች 10 የሰራዊት አባላት የአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ ነጎድጓድ ክፍለጦርን ከነ ሙሉ ትጥቃቸው ተበላቅለዋል።
"ድላችን በክንዳችን"
የአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ የህዝብ ግንኙነት ክፍል

@yaya192123
@yaya192123
@yaya192123

2 weeks, 4 days ago

:~

ዛሬ ህዳር 7 ቀን 2017 ዓ.ም ጧት 4 ሰዓት ባህር ዳር ኤርፖርት ወታደራዊ ETr156 የሚል
ሄሊኮፍተር ወድቃለች፤ በዚህም በረራ ተቋርጧል!"

በተያያዘ ዜና የኤምሬት ኤሊኮፍተሮች በመላው አማራ ከጧት የጀመረ ቅኝት እያደረጉ ይገኛሉ። ያዉ ሰሞኑን የተጠናከረ የድሮን ጥቅት ሊኖር ስለሚችል ማህበረሰባችን አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ በተገኘው አማራጭ ለማህበረሰቡ መረጃው ይድረስ!

@yaya192123
@yaya192123
@yaya192123

2 weeks, 4 days ago

የአገዛዙ ሰራዊት አማራን የማጥፋት ተልዕኮውን ተሸክሞ የሚዞረው ስብስብ ዛሬ ማለትም 07/ 2017 ዓ.ም ሁለት ሲቪል ግለሰቦችን ከቤት አውጥቶ ረሽኗል። 

ከሌሊቱ ዘጠኝ ሰዓት ላይ ከፍ/ሰላም  ወደ ሐሙሲት(አውንት መንዝ) ለመሔድ የተነሳው የአገዛዙ ሰራዊት መንገድ ላይ(ገራይ ትምህርት ቤት አካባቢ) ባልጠበቀው ሁኔታ በጎጃም አገው ምድር ክፍለ ጦር በአረንዛው ዳሞት ብርጌድ ሲመታ ወደ ኋላ በማፈግፈግ ከ ከተማው ዙሪያ ካሉት ገጠራማ መንደሮች መካከል ገራይ ተብሎ ከሚጠራው  አካባቢ ቤት ለቤት እየዞረ ንጹሀንን ሲረሽን አርፍዷል።
ከአንድ ቤት ሁለት ግለሰቦችን እረሽኗል።

በዚህም አንዲት ሴት ወንድሟንና ባሏን በአንድ ቅጽበት አጥታለች።ባለቤቷን ከቤት አውጥተው ከቤቱ በራፍ ፊትለፊት ሲገድሉት ወንድሟን ደግሞ እዛው እቤት ውስጥ ገድለውት ሒደዋል።

አገዛዙ ለማንም የማይራራ የክፉዎችናስብስብ ስለሆነ ሁሉም ሰው በአገኘው አጋጣሚ አምርሮ ሊታገለው ይገባል።

ድል ለአማራ!

@yaya192123
@yaya192123
@yaya192123

2 weeks, 4 days ago

ሰበር ዜና

ህዳር 7/2017 ዓ/ም ሸዋ አማራ ኢትዮጵያ

የአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ  ታሪካዊቷን አንኮበር ከተማ ለመቆጣጠር ታላቅ ተጋድሎ እያደረገ ይገኛል።
በኢ/ር ደሳለኝ ሲያስብ ሸዋ ዋና መሪነት በፊትአውራሪ ባዩ አለባቸው ዋና ጦር አዛዥነት የሚመራው የአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ ነጎድጓድ ክፍለጦር ጋተውና መብረቁ ብርጌድ የተወሰኑ ሻለቆች ከጣይቱ ብርጌድ ጋር ጥምረት በመፍጠር ከጠዋቱ 2:00 ሰዓት ጀምሮ ታላቅ ተጋድሎ እያደረጉ የሚገኙ ሲሆን የጠላት ሀይልም በአራት አቅጣጫ የተከበበ በሆኑ መውጫና መግቢያ አጥቶ እየቃተተ ይገኛል።
   በሌላ በኩል ከመርሀቤቴ አለም ከተማበነሳት ወደ ጎረንዳዮ ሰርቃ ማርያም ያቀናው የጠላት ሀይል የአይበገሬዎቹን ነናደው ክፍለጦር አባት አባላት አሰላለፍና ወትሮ ዝግጁነት ከተመለከተ በኋላ የተወሰነ ከባድ መሳሪያ ከሰዠርቀት በመወርወር የአካባቢውን ማህበረሰብ በመዝረፍና ንፁሃንን በማፈን ወደመጣበት አለም ከተማ ፈርጥጧል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ መነሻውን እነዋሪ ከተማ  መድረሻውን ታሪካዊቷ ጅሁር ከተማ ያደረገ የጠላት ሀይል ወይራምባና ጫሶ ከማለፋ በፊት በአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ ነጎድጓድ ክፍለጦር መብረቁ ብርጌድ እየተወቃ ይገኛል።
    በሌላ በኩል በትናንትናው ዕለት በአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ ከሰም ክፍለጦር ጀግናው ፊትአውራሪ አስማረ ዳኜ ብርጌድ ተወርዋሪ የፋኖ አባላት ትናንት ህዳር 6/2017 ዓ.ም ሌሊት ጊና አገር ከተማ ሰርገው ገብተው በፈፀሙት የደፈጣ ጥቃት በአሳግርት ወረዳ በሚሊሻ ጠርናፊነት የወረዳውን ህዝብ ሲገድልና ሲያስገድል የነበረው ሀምሳ አለቃ አስናቀ ወንድማገኝ ማን አለብኝ ብሎ እቤቱ እንደተኛ የማያዳግም እርምጃ ተወስዶበት!

"ድላችን በክንዳችን"
የአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ የህዝብ ግንኘነት ክፍል

3 weeks, 4 days ago
የአማራ ፋኖን ትግል እና የእለት ከእለት …

የአማራ ፋኖን ትግል እና የእለት ከእለት የግንባር ውሎ በፍጥነት የሚያደርሳችሁ እውነተኛ የህዝብ ድምፅ የሆነውን ታላቁን ፩ አማራ ቻናል ተቀላቀሉ

አማራ ሆኖ ይህን ቻናል አለመቀላቀል የማይቻል ነው
👇👇👇👇
https://t.me/+Uov0vlHTAwcwMzZk
https://t.me/+Uov0vlHTAwcwMzZk
https://t.me/+Uov0vlHTAwcwMzZk

We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 2 months, 1 week ago

Last updated 6 days, 22 hours ago

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ ? @Esat_tv_comment_bot

??ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ??

Last updated 2 months, 3 weeks ago