ስለ እኛ...

Description
በዚህ ቻናል
🌹ልቦለዶች
🌹አስተማሪ ታሪኮች ይገኛሉ እና አይጠቅመንም ብላችሁ ውጡ አሏችሁ የገባ አይወጣም ተስማምተናል 🤝🏻🙏 እናም ደሞ 🌹ግጥሞችን
🌹የ ሕይወት ምክሮችን ታገኛላቹ።

ግሮዑፓችንን ለመቀላቀል kefelegachu👇👇👇
https://t.me/TsDi11
Advertising
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated hace 3 semanas, 5 días

Last updated hace 3 semanas

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated hace 1 mes, 1 semana

3 months, 1 week ago
ስለ እኛ...
3 months, 1 week ago
[#Update](?q=%23Update)

#Update

" እዚህ አዲስ አበባ የተከሰተ የመሬት መንቀጥቀጥ የለም፤ ሞገዱ በመሬት ውስጥ ተጉዞ መጥቶ ነው ፤ አዋሽ አካባቢ ነው የተከሰተው በሬክተር ስኬል 4.9 ነው " - ዶክተር ኤልያስ ሌዊ

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጂኦ ፊዚክስና ስፔስ ሳይንስ ዳይሬክተር ዶክተር ኤልያስ ሌዊ ለብሔራዊ ቴሌቪዥን በሰጡት ቃል ምን አሉ ?

" እስካሁን ባለው መረጃ እዚህ የመሬት መንቀጥቀጡ እዚህ አዲስ አባባ የተከሰተ ሳይሆን አዋሽ አካባቢ የተከሰተ ነው።

ግን በመሬት ውስጥ አልፎ እዚህ አዲስ አበባ ውስጥ ልዩ ልዩ ቦታዎች ተሰምቷል።

ይሄን ግልጽ ማድረግ እንፈልጋለን እዚህ አዲስ አበባ የተከሰተ አይደለም። ግን በመሬት ውስጥ ተጉዞ መጥቶ እዚህ ያሉ ህንጻዎችን አንቀጥቅጧል።

በሪክተር ስኬል 4.9 ነው ያገኘነው። ይሄም ከፈንታሌ የሚባል ተራራ አለ ወደ መተሃራ አካባቢ ነው የተከሰተው። እስካሁን ያለው መረጃ ይሄ ነው።

ሰውም ይረጋጋ እዚህ አዲስ አበባ የተከሰተ የመሬት መንቀጥቀጥ ሳይሆን ከሩቅ የተከሰተ የመሬት መንቀጥቀጥ ሞገዱ በመሬት ውስጥ ተጉዞ መጥቶ በተለይ እዚህ ሰሜን እና ሰሜን ምስራቅ ያሉ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች በጣም ተረብሸዋል። ልክ ነው ከዛም ሊሰማ ይችላል።

በሬክተር ስኬል 4.9 ነው ይሄ ነው ያለው መረጃ።

ተጨማሪ መረጃ እንዳገኘን በግልጽ እንነግራለን። " ብለዋል።

ዛሬ ምሽት በአዲስ አበባ በነበረው የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረት ምክንያት በተለይ የጋራ መኖሪያ ቤቶች የሚኖሩ ነዋሪዎች ህንጻቸው ሲንቀጠቀጥ እንደነበር ገልጸውልናል። በዚህ ምክንያት ከቤታቸው ወጥተው መሬት ላይ ወርደው ተሰባስበዋል።

#Ethiopia

@tikvahethiopia

3 months, 1 week ago

#AddisAbaba

በአዲስ አበባ ከተማ አሁን ምሽት ላይ የተለያዩ አካባቢዎች የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቷል ።

በአንዳንድ ቦታዎችም ሕዝብ የሚኖርባቸው
ህንጻዎችን ረዘም ላለ ጊዜ አንቀጥቅጧል።

ይጠብቀን 🙏

Share @ስለ እኛ

3 months, 1 week ago

እኔ እና ወንድሜ 🥀🥀🥀

እኔ እና ወንድሜ የምድርን መህፀን ስንቆፍር
ስንቆፍር ትንሽ ወረድ ብለን ያገኘነው ነገር
ሆዳም ያጠፋዉን ነፃነትን ነበር
እኔ እና ወንድሜ
ነፃነትን አልፈን ስንቆፍር ስንቆፍር ት ንሽ
ወረድ ብለን ያገኘነው ነገር ሰንሰለት
ያሰረዉን የ እውነትን ቃል ነበር
እኔ እና ወንድሜ
ሰንሰለትን በጥሰን እውነትን ወደላይ ይዘነው
ስኖጣ ነፃነት ከሰሌን ፈልገነው ታጣ
እኔ እና ወንድሜ
ያኔ ተስፋ ቆርጠን ይሄው እስከዛሬ እያለቀስን
አለን እየቆፈርን አለን ከለታት በ አንዱ ቀን
ነፃነትን ብናገኘው ብለን 😶

3 months, 1 week ago
"ምን እያሰብክ ነው...."

"ምን እያሰብክ ነው...."

"ለምን እንደማትሄጂ...."

"መልሱን ካገኘህ ብታስኮርጀኝ አልጠላም..."

"ልለምንሽ ሂጂ...."

"ምን እንደሚገርመኝ ታውቃለህ..."

"አላውቅም...."

"ሞኝነትህ...."....ፈጠን ብሎ ወደ እኔ ዞረ...መጥቼ አጠገቡ ከተቀመጥኩ ይሄን ስለው ነው ለመጀመሪያ ጊዜ ያየኝ....

"ምን ማለት ነው...."....አለኝ አይኑን እያጉረጠረጠ....

"ደስታን ለነገ እንደመቅጠር ሞኝነት አለ...?....መለየትን ፈርቶ እንደመለየት ያለ ሞኝነት ካገኘህ እኔ ልቀጣ...ነገ ብቻዬን ልቀር እችላለሁ ብሎ ብቻ መሆንን ከዛሬ እንደመጀመር ቂልነት ከየት ይገኛል...."

የተጉረጠረጠው አይኑ ቦታው ተመልሶ...
"ሳልነግርሽ እንዴት አወቅሽ...."....የሚል ጥያቄ አስከተለ...

"እስቲ እቀፈኝ...."

.....ይሄን ጊዜ ገልመጥ አደረገኝ እና አየር አየሩን ማየት ጀመረ.....

"አየህ አታቅፈኝም....ትፈራለህ....የልብን ሰው ማቀፍ የሚሰጠውን እረፍት ታውቀዋለህ....ስለ ነገ እርግጠኛ ስላልሆንክ ነገ በምን አርፋለሁ ብለህ የዛሬን እረፍት አታርፍም....ከእረፍትህ ጋር ከመጣበቅ ይልቅ ከሸክምህ ጋር መጣበቅን ትመርጣለህ...

አስተውለኃዋል ግን እያንዳንዱ እርምጃህ እኮ የተጠና ነው...እስከዚህ ነው የምሄደው...በዚህ ካለፍኩ ናፍቆት አለ ይቅርብኝ....ከዚህ መልስ ፍቅር አለ....ከዚህ ትንሽ ከሄድኩኝ attachment አለ...እያልክ ነው የምትጓዘው...."

ትንሽ አርፌ ቀጠልኩ....

"ማወቅ ያለብህ ነገር እንደዚህ አይነት ፎርሙላ ህይወትህን ከማክበድ ውጪ የሚፈይደው ነገር እንደሌለ ነው....አለም እንደዚህ አትሰራም....አልታመም መሬት አይንካኝ እየተባለ አንኖርባትም...በቃ መድሀኒት እየፈለግክ ነው የምትኖረው....መድሀኒቱ ደግሞ ምን አልባት ይሄ ነው...ፍቅር..."

"አሁን ምን አድርግ ነው የምትይኝ...."

"...ትንሽ ለቀቅ በል....ትንሽ ብቻ ፍቀድልኝ....ትንሽ ብቻ እቀፈኝ....ትንሽ ብቻ ፍርሀት ቀንስ...ትንሽ ብቻ እመነኝ..."

"በቃ...."....አስተያየቱ የሹፈት ሳይሆን ሌላ እንድቀጥል ግብዣ ይመስላል...ቀጠልኩ...

"አንድ ይቀራል...."

"ምን...."

"ዛሬን በደንብ ኑር....".....ይሄን ጊዜ ከተቀመጠበት በፍጥነት ተነስቶ ቆመ...እንደለመደው ሊሸሽ መስሎኝ የመጨረሻ ንግግሩን ለመስማት ፊቱ ቆምኩኝ...ይሄኔ ታቅፌ እንደማላውቅ አቀፈኝ....

ዳይ ወደ መኖር💃💃💃

Shewit

https://t.me/shewitdorka
https://t.me/shewitdorka
https://t.me/shewitdorka

3 months, 1 week ago

አንደዚህ በቀላሉ አሸወዳለው ብዬ አስቤ አላውቅም ነበር
አነጋገርህ በ ቅመማ ቅመም በ ልዩ ሁኔታ የተቀመመ ስራ እና ወጥመድህን እንዴት ዘርግተህ እንዴት እንደወደኩ አሁን ሳስበው ይገርመኛል
ግን ከዛ ሁሉ ነገር በኋላ አልከስህም አልፈርድብህም
ምክንያቱም በህይወቴ የማልረሳውን ትልቅ ትምህርት አስተምረኸኛል ጠንቃቃም እንደሆን አርገህኛል።
እንዴት ራሴን ማስደሰት እና ጠንካራ ማድረግ እንዳለብኝ ጎድተህ አስተምረህኛል

ትላንት የገጠመን ጉዳት ለ ዛሬ ትምህርት እናድርገው እንጂ እንዳይጠልፈን

3 months, 1 week ago

🥀🥀🥀🥀
ግንኮ ከለታት አንድ ቀን ሁሉም ነገር ማብቂያዉን ያገኛል

ታዲያ ለምን እንዲ እንሆናለን?

3 months, 2 weeks ago

አንድ አንዴ ትታችሁ ማለፍን ልመዱ

አዎ ብዙ ማይታለፉ ሊረሱ የማችሉ ጊዜ አሳልፋችህዋል ዋጋ ከፍላቹዋል ግን ያን ማድረጋችሁ ከጎዳችሁ ተዉት እየተባላችሁ ነው ፈጣሪ ማስጠንቀቂያ እየሰጣችሁ ነው
ምናልባትም ከገፋችሁበት ምን እንደሚከተላችሁ ማን ያውቃል ስለዚህ እለፉ ዝምታን ልመዱ
ወደ ኅዋላ አይታችሁ ንቃቹ ተዉት ለናንተ ያላለውን መመኘትን ተዉ ተራምዳችሁ ስታልፉት ምን ታገኙ ይሆን እሱን ብቻ አስቡ ታሪክ አልፎ ይወራል እንጂ ዛሬ ላይ አይኖርም ያለፈ ታሪካችሁን አውሩት እንጂ አትኑሩት

ስለ እኛ
ስለ ሁላችን
ሼር 🙏🙏🙏

3 months, 2 weeks ago
ስለ እኛ...
3 months, 2 weeks ago

ትዝታ አይጠፋም ምን ጊዜም

የኔዋ ትዝ ይልሻል ያ ጊዜ ምንም ሳናውቅ ስለ ፍቅር ሳይገባን ፍቅርን የኖርን ጊዜ እውነት አይረሳኝም ስታመም ስታስታምሚኝ ስታኮርፊ ሲደብረኝ ስትስቂልኝ ልቤ ቅልጥ እየተሳቀኩ በሌለኝ ብር ትንሽ ስጦታ ስሰጠትሽ ትንሽነቱን ሳታይ በደስታ ስታብጂ ምኔንስ ብረሳ ይፈረድብኛል ፍቅር እኮ ነሽ አንቺ እኔ አይረሳኝም አንቺስ ይረሳሻል ከቤትሽ መጥቼ እንዳላንኩአኩአ ፈርቼ ናፍቆት ልቤን ሲያስጨንቀው ከ ወንድምሽ ጋር ተጣልቼ ስጋ ወንድምሽን ትተሽ ለኔ ያገዝሽ ጊዜ ልብሽ ስስ ነውኮ የኔ እናት ወንድምሽን ወደሽ ደሞም ፍቅሬን ብለሽ
እንደውም አታስታውሺም ናፍቆት አይሎብሽ እናቴን አታለሽ በጉአሮ ቤት ዘለሽ ከክፍሌ የተገኘሽ
ያንቺስ አይወራም ብዙ ነው ስስትሽ ልቤ ሕሴት ታደርግ ዘንድ እወድሃለሁ በይኝ ስሞትልሽ ❤️❤️❤️

ፍቅር ለሆኑና ለፍቅር ለሚኖሩ ሰዎች ይድረስ 🙏🏾እወዳቹሃለው 🥰

We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated hace 3 semanas, 5 días

Last updated hace 3 semanas

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated hace 1 mes, 1 semana