Elias's Views - የኤልያስ እይታዎች

Description
እውነት ሀሰት አንልም...We just breath through every situation! የተፃፈ ሁሉ እውነት አይደለም፤ እኛ የምንፅፈው ደግሞ እውነትም ሀሰትም ሳንል የተፈጥሮ ዑደቱን እንደጠበቀ ተፈጥሮን ብቻ ነው። ከተፈጥሮ በላይ ማን ዳኛ አለ?? አላማችንም ጥያቄ መፍጠር ነው!
ተፃፈ:-
በ EllaB & Sheko

@gtmna ..join us!!
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 2 months, 3 weeks ago

Last updated 2 months, 2 weeks ago

ይህ ስለ Manchester United መረጃዎችን የሚያገኙበት የ Telegram ቻናል ነው 🇪🇹
--------------------------------------------------------------
☞︎| ስለ ማንቸስተር ዩናይትድ ትኩስ መረጃዎች
☞| ቀጥታ ስርጭቶች ከየስታድየሞቹ
☞| የዝውውር ዜናዎች
☞| ስለ ማንችስተር ዩናይትድ ታሪኮች

📩 ለማስታወቂያ ስራ DM :- @Marcoabdu

Last updated 1 month, 2 weeks ago

1 month ago

የህፃን ልብ...ያድለን🙏

ሰላም ባባዬ! አልኩት። በአንድ ትንሽዬ ባር ውስጥ የሚጫወትን ህፃን።

"Hi, My name is Makbel" አለኝ ለመስማት በሚቸግር የአነጋገር ዘዬ። እኔም አማርኛ መስማት እንጂ መናገር እንደሚከብደው ተረዳሁኝና ፈገግ እያልኩለት ከትልቅ ሰውና ከልጅ የቱ ጋር ብትሆን ደስ ይልሃል አልኩት?

ምንም ሳያቅማማ "ከሴት ጋር አለኝ"😘 መልሱ ግርምት ስለፈጠረብኝ ለምን አልኩት? "እህቴን ሳያት ደስ ስለምትለኝ" አለ በሚያምር አይኑ እያዬኝ።

Second mother ever.....Sisters🙏**

@gtmna

1 month ago

...የኔ ዘመን የህይወት ቅኝት!

Part - 2

አዳጊ ዘሮችህ - ቦታ እንዲኖራቸው
የገረጀፉትን - ቆርጠህ አንሳላቸው!

ይህ ደግሞ የኔ የመኖር ህግ ነው። በህይወት ሁሉም ውብ ነው። ግን ማርጀት አለው። እንደነበረ የሚቀጥል የለም። ለዛም ነው ህይወት መልኳን የምትቀያይረው፤ ለተርጓሚም ለኗሪም ቅኔ የምትሆነው።

ሃሳብም፣ ቁስም፣ ሰውም ያረጃል። በቀናነት ማርጀት የማታን ጀምበር ግባት እንደማየት ሃሴትን ያላብሳል።

መልካም ተሁኖ ሲኖርማ የውስጣችንን እየሱስ፣ አላህ፣ መላዕክትና ነቢያትን በላያችን ላይ እንዲንፀባረቁ ያደርጋል። እነዚህ ፃድቃንን ለማግኘት ደግሞ ያረጁ ነገሮቻችንን መቁረጥ የጠቢብ ምግባር ነው። የኔ ጠቢብ ከአረጁ ነገሮችህ ጋር ብዙም አትለጣጠፍ! የመሞቻ ቀንህን እንዳያሳጥሩብህ።

ሌላው የኔ ዘመን የህይወት ቅኝት ደግሞ "በሌሎች ላይ የምታየው ነገር እራስህን ነው" ስለዚህ ማዬት የማትፈልገውን አንተ/እራስህን ቆርጠህ ጣለው። ሰላም ይሰጥሃል። ግን Be Kind when u have the power to do everything. Be brave to say 'bye' and open for 'hi'. That's all about decision. ህይወት የወላዋዮች አይደለችም። ለሚወላውሉት ፍሬዋ የትም ነው። መድረሻው አይታወቅም። በርግጥ ስለመድረሻ ማሰብ ብዙም ሊቅ አያስብልም። መንገዱን ነው መምረጥ✍️

"Unexamined life is not worthy to be lived" ይላል ሶቅራጥስ። ግን መለኪያው ምን ይሆን? Yeah, መለኪያው መኖር ነው። እንደ አፈጣጠራችን፤ ጌታችንን በመምሰል። ጌታ ማነው የሚል አይጠፋም? ቢሆንም መኖር ደስ ይላል።

ለጊዜው ጨርሰናል!

@gtmna

1 month ago

የኔ ዘመን የህይወት ቅኝት!

Part -1

በዚች በኖርኳት አመታት ውስጥ ስንት አጃኢብ የሚያስብሉ ነገሮችን አየሁኝ፣ ሰማሁኝ አለፍ ሲልም አደረኩኝ🤔

ከቅዱስ እስከ እርኩስ ... ከእርኩስ እሰከ ቅዱስ! ሁሉም ግን መኖር ተብሎ ይጠራል። No science defined life as it is. ሁሉም የሚቀባጥረው የእለት ስሜቱን ነው። ህይወት ደግሞ የእነዚያ የቀን ተቀን ልቅምቃሚ ግብዓቶች ልትሆን ትችላለች። Life might be the feeling that wakening up from stupidity or falling into that shit. ወይም ደግሞ ይሄ ነው ብለን የማንገልፀው ህፀፅ አልባ የራስ ሃሴት።

ለምን ለህይወት ትርጉም አይሰጠውም? ቄሱ ከእየሱስ አንፃር ይተርጉማታል። ፓስተሩ ደግሞ ያንኑ ሃቅ ለራሱ እንዲመቸው አድርጎ በውብ ቋንቋ ይተርክልናል። "ያለ እየሱስ ህይወት የለም"... ሼኪውም በልኩ ይሰፋና "ዲን"ን ያስተምረናል። የኔ ቡድሃም "በሰው ቦታ እስካልቆምክ ድረስ ስለማይገባህ አትፍረድ" እያለ ህይወትን ያበራልናል። ....ቡድሃ ይሙት ሃሳቡን እወድለታለሁ።

እና ህይወት እውነት ናት?🤔 አይደለችም! እና ህይወት ሀሰት ናት?🤔 አይደለችም።

እኔ እየኖርኩ ያለሁት በእነዚህ ሁለት የእውነት እና የሀሰት ክዳን ውስጥ ነው። በእነዚህ ሁለት መዓዘናት ውስጥ ደግሞ ጓደኞቼ አሉ። ይህንን undefined life principleን እንድንረዳው የሚያደርጉኝ። በቃ ህይወት ማለት በእኔና በጓደኞቼ መካከል ስትገኝ ውብ ፅጌሬዳ ነች። We have been discovering abundant beauty. We call it Joyyyyyyyy. In the middle, we have been experiencing some suffering. We call it the tuned teacher.

ስለዚህ ህይወት ... ደስ የምትለው ስትገለጥ ነው። ለነገሩ ብዙ ነገር ሲገለጥ ያሳፍራል። ይሄንን የፈጠረው ግን የድብቁ ማንነታችን ከፈን ነው። እንደ ማህበረሰብ የፈጠርነው ሌላ የህይወት ትረካ። ስለዚህ እውቀት...እውነትን ይፈጥራል። ህይወት ደግሞ እውቀትን ትፈጥራለች። መኖር ደስ ይላል። እሱ ነው ህይወት። "አለመኖር"ን ማወቅ እንጂ መኖር አይቻልም። ስለዚህ ለሞት አልጓጓም። ህይወት አይደለማ። ክርስቶስን መሆን ብችል ግን I would try it ግን ለፍቅር! ህይወትን ይማሯታል እንጂ አይኮርጇትም። የተኮረጀ ህይወት ሀሰት ነው። ሀሰት ደግሞ ከአለመኖር አይተናነስም።

"ሁሉም ሰው ሌላ ሰው ነው" የሚል ነገር አንብቢያለሁ። ሁሉም ሰው ሌላ ከሆነ ደግሞ ....  no theory can't define life though life is rose in throne of garden. ህይወት ማለት መልስ መፈልገም ሊሆን ይችላል። በባሏ ላይ አስር ወንዶችን የቀመሰችን ሴት...ለምን ሴሰኛ ሆንሽ ቢሏት?.... መልሷ ሊሆን የሚችለው...."ውበትን ፍለጋ ነው"...ውበት ደግሞ ህይወት።

ይቀጥላል ......

@gtmna

3 months, 2 weeks ago

ማርያምን ነው የምልህ
በማርያም ነው የምቀና
አምላክ ወልዳ በሱው ታምና
ዝቅ ብላ በኖረችው የሴት መልካም
የሴት ቀና።

@gtmna

3 months, 3 weeks ago
3 months, 3 weeks ago

በርሃ ላይ እንዳለ ቀዝቃዛ መጠጥ፣ ብርድ መሃል እንደተገኘ ጋቢ፣ ድብርት መሃል እንደመጣ ሎተሪ መጨረሻ የወጣን መስሎን አንደኛ ነህ እንደተባልን አይነት መውደድ ነው ልቤ ላይ የተንጋለለው ።

ተንጋለሽ ሳይሽ ሰዓሊ መሆን አምሮኝ ያውቃል፣ ሳቅሽን ለመሳል፣ ክርፊያሽን ለመሳል፣ተንጋለሽ እንዳለሽ መንጋለልሽን ስዬ መኝታ ቤቴ ለመስቀል።

የዳዊት መለሰን ዘፈን "ቁንጅና ራሱ" ነሽን ዝፈንላት ዝፈንላት  ብሎኝ ያዉቃል። ለዛ ነው የዘፈንኩልሽ በቀደም።

ግጠምላት  ግጠምላት ብሎኝ  ያውቃል። ለዛ ነው "የፍቅር ሰላምታ" ፍቅረማርቆስ ደስታን ያነበብኩልሽ።

ተንጋለሽ ሳይሽ ተሸከማት ተሸከማት ሁሌ ነው የሚለኝ  ውፍረትሽን ሳስበው ለስፓይናል ኮርዴ አዝንለታለሁ ለሷስ  አልጋ ቁራኛ ብሆን ምን ትጠቀማለች ብዬ እተዋለሁ ።

አቅምን ማወቅ ታላቅ ችሎታ ነው እንዲሉ አበው ?

ግን እወድሻለሁ ❤️

@gtmna
@gtmna

We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 2 months, 3 weeks ago

Last updated 2 months, 2 weeks ago

ይህ ስለ Manchester United መረጃዎችን የሚያገኙበት የ Telegram ቻናል ነው 🇪🇹
--------------------------------------------------------------
☞︎| ስለ ማንቸስተር ዩናይትድ ትኩስ መረጃዎች
☞| ቀጥታ ስርጭቶች ከየስታድየሞቹ
☞| የዝውውር ዜናዎች
☞| ስለ ማንችስተር ዩናይትድ ታሪኮች

📩 ለማስታወቂያ ስራ DM :- @Marcoabdu

Last updated 1 month, 2 weeks ago