ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated 2 months, 1 week ago
Last updated 6 days, 22 hours ago
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ ? @Esat_tv_comment_bot
??ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ??
Last updated 2 months, 3 weeks ago
"የታክስ ደረሰኝ አጠቃቀም እና አስተዳደር መመሪያ /ማሻሻያ/ ቁጥር 188/2017" ምን አዲስ ነገር ይዟል?
አዲሱ መመሪያ ከህዳር 3 ቀን 2017 ዓም ጀምሮ በፍትህ ሚኒስቴር ተመዝግቦ እና ጸድቆ ተግባራዊ መሆን ጀምሯል።
- በመመሪያው መሰረት እያንዳንዱ የደረሰኝ ቅጠል ሲታተም ልዩ መለያ ኮድ (unique QR code) እንዲኖረው የሚያዝ ሲሆን ተካቶ ካልታተም ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
- ማንኛውም አታሚ ደረሰኝ ሲያትም በታክስ ባለስልጣኑ የተዘጋጀውን ልዩ መለያ ኮድ (unique QR code) በመውሰድ በእያንዳንዱ የደረሰኝ ቅጠል ላይ አካቶ ሊያትም የሚገባው ሲሆን፤ ሲያትም የልዩ መለያ ኮዱ ወርድና ቁመት ቢያንስ 2 ሴንቲ ሜትር ሆኖ በደረሰኙ የቀኝ ራስጌ ላይ መታተም እንዳለበት ያዛል፡፡
- ማተሚያ ቤቱ ምንም አይነት ስህተት ወይም ልዩነት ሳይኖር ደረሰኞችን ልዩ መለያ ኮድ (unique QR code) በማካተት ለማተም በማንዋል ደረሰኝ QR- code (Manual Receipt QR-code Web Portal) የተጋራውን ዳታ በትክክል ተቀብሎ የመተግበር ግዴታ እንዳለበት አስቀምጧል።
- ማተሚያ ቤቱ በማንዋል ደረሰኝ QR-code አስተዳደር ፖርታል (Manual Receipt QR-code Web Portal) በኩል ዳታ ሲጋራ ተገቢነት ያላቸውን ሁሉንም የዳታ ጥበቃ ደንቦችና መመሪያዎችን የማክበር ግዴታ አለበት ይላል፡፡
- ማንኛውም ማተሚያ ቤት ልዩ መለያ ኮድ ያለው ማንዋል ደረሰኝ ሲያትም በወረቀቱ ላይ ሊሰርግ የሚችል ኢንክ ጀት (Ink jet) የሚባል ቀለም የመጠቀም ግዴታ አለበት፡፡
- ማንኛውም ማተሚያ ቤት እንዲታተም የተፈቀደውን እና የታተመውን ደረሰኝ በተመለከተ በተዘጋጀው ሲስተም በወቅቱ ሪፖርት የመላክ ኃላፊነት እንዳለበት አስቀምጧል፡፡
- ማንኛውም ማተሚያ ቤት በታክስ ከፋዩ ደረሰኝ እንዲያትም ሲጠየቅ፤ በታክስ ባለስልጣኑ ለታክስ ከፋዩ የተሰጠ የደረሰኝ ህትመት ፈቃድ ደብዳቤ ሳይቀበል ደረሰኝ ማተም የለበትም፡፡
- በዚህ መመሪያ መሰረት የደረሰኝ ህትመት አገልግሎት የሚሰጥ ማተሚያ ቤት ከሚኒስቴሩ ጋር የቅንጅት አሰራር ስምምነት የማድረግ ኃላፊነት አለበት፡፡
በአዲሱ መመሪያ የመሸጋገሪያ ድንጋጌ መሰረትም:-
ማንኛውም ታክስ ከፋይ ይህ የማሻሻያ መመሪያ ተፈጻሚ ከመሆኑ በፊት አሳትሞ ያልተጠቀመባቸው ደረሰኞች መጠቀም የሚችለው የማሻሻያ መመሪያው ተፈጻሚ ከሆነበት ቀን ጀምሮ ባለው ለሶስት ወር ጊዜ ብቻ እንደሆነ አስቀምጧል፡፡
ላኪዎች ከነገ ህዳር 5/2017 ዓም ጀምሮ ካመነጩት የውጭ ምንዛሪ 50 በመቶውን በመሸጥ ቀሪውን ላልተወሰነ ጊዜ በአካውንታቸው ማስቀመጥ ይችላሉ - ብሔራዊ ባንክ
ኅዳር 4/2017 (አዲስ ዋልታ) ላኪዎች ያመነጩትን የውጭ ምንዛሪ 50 በመቶ ወዲያውኑ በመሸጥ ቀሪውን 50 በመቶ ላልተወሰነ ጊዜ ኢትዮጵያ ውስጥ ባለ አካውንታቸው ማስቀመጥ የሚችሉበት አሠራር ከነገ ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚደረግ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አስታወቀ፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ማሞ ምኅረቱ እንዳሉት ላኪዎች ካመነጩት የውጭ ምንዛሪ 50 በመቶውን ለባንኮች ወዲያውኑ በመሸጥ ቀሪውንም በአንድ ወር ውስጥ መሸጥ ይገደዱ ነበር።
በወቅቱ አሠራሩ በጊዜያዊነት ተግባራዊ ሲደረግ የተረጋጋ የውጭ ምንዛሪ ፍሰት እንዲኖር ከመፈለግ እንደነበርም አስታወሰዋል።
ከነገ ጀምሮ ግን ላኪዎች ያመነጩትን የውጭ ምንዛሪ 50 በመቶ ወዲያውኑ በመሸጥ ቀሪውን 50 በመቶ ላልተወሰነ ጊዜ በአካውንታቸው ማስቀመጥ ይችላሉ ብለዋል፡፡
ይህም ማለት ያመነጩትን የውጭ ምንዛሪ በአንድ ወር ውስጥ እንዲሸጡ አይገደዱም ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
የንግድ ፖሊሲዎች ተደጋግመው መውጣታቸው እና መቀያየራቸው ለስራ አስጊ እየሆነብን ነው ሲሉ ነጋዴዎች ቅሬታቸውን አሰሙ
ሰኞ ህዳር 02 ቀን 2017 (አዲስ ማለዳ) በኢትዮጵያ የንግድ ፖሊሲዎች ተደጋግሞ መውጣት የንግድ ዘርፉን ስጋት ውስጥ እየጣለው ነው ሲሉ በአስመጪና ላኪ የስራ ዘርፍ ላይ የተሰማሩ ነጋዴዎች ቅሬታቸውን አሰምተዋል፡፡
በቅርቡ ክልከላ የተጣለበት የፍራንኮ ቫሉታ መመሪያ እንኳን ብዙ ነጋዴዎችን እና ባለሀብቶችን ችግር ውስጥ እያስገባ ስለመሆኑ የዘርፉ ባለሙያዎች ደጋግመው ሲገልጹ ይደመጣል፡፡
እንደነዚህ ያሉት ማሻሻያዎች ኢኮኖሚውን ለማረጋጋት ዓላማ ቢኖራቸውም ፣ ድንገተኛ ትግበራቸው እና በአጭር ጊዜ ውስጥ መቀልበሳቸው ብዙውን ጊዜ የንግድ ሥራዎችን በአግባቡ እንዳይካሄዱ እየዳረገ ነው ሲሉም ነው ቅሬታቸውን ለአዲስ ማለዳ ያሰሙት ።
ስማቸውን መጥቀስ ያልፈለጉ አንድ በቡና ንግድ ላይ የተሰማሩ ነጋዴ እንዳሉት በተደጋጋሚ የፖሊሲ ለውጦችን በኢኮኖሚው ላይ መተግበራቸው ለንግድ ድርጅቶች ቀጣይ እርምጃ ከፍተኛ ጥርጣሬን እየፈጠረ ነው ብለዋል።
“ኢኮኖሚው ከመንግስት የፖሊሲ መረጋጋትን ይፈልጋል ምክንያቱም ብዙ የኢንቨስትመንት ውሳኔዎች መወሰን ሚቻለው ያኔ ነው” ያሉት ቅሬታ አቅራቢው ፖሊሲዎች ከመተግበራቸው በፊት በደንብ ሊጠኑ እንደሚገባ አስምረው መንግስትም ከሚመለከታቸው የዘርፉ አካላት ጋር እንዲወያይ ጠይቀዋል፡
የምጣኔ ሃብት ባለሙያው አጥላው ዓለሙ (ዶ/ር) በበኩላቸው የሚቀያየሩት ፖሊሲዎች የንግድ ባለቤቶች ረጅም ለማቀድ እንዳይችሉና ጥርጣሬ እንዲፈጥርባቸው እንደሚያደርጋቸው ጠቁመዋል፡፡
አክለውም ድርጅቶች በፖሊሲዎች ላይ ሊደረጉ የሚችሉ ለውጦችን በመገመት አሳሳቢ ጉዳዮቻቸውን እና ስራዎቻቸውን በረጅም እቅድ ላይ ከማተኮር ይልቅ በአጭር ጊዜ እቅድና የንግድ እንስቃሴ እንዲገደቡ ያደርጋቸዋል ብለዋል፡፡
በኢትዮጵያ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ በመጣው የኢኮኖሚ ሁኔታ፣ የቢዝነስ ተቋማት ፈጣን የፖሊሲ ሽግሽግ የሚያስከትለውን መዘዝ ለመዳሰስ ፈታኝ እየሆነባቸው እንደሆነ ተደጋግሞ ይነሳል።
ምንጭ አዲስ ማለዳ
የድምፅ ቅጂውን እነሆ!
ያለፈው ሳምንት ቅዳሜ ነሐሴ 04/2016 ምሽት 2:45 ጀምሮ በስለ ስራ! ቴሌግራም ቻናል ወቅታዊ ስለሆነው የሀገራችን ማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ በአቶ ሙከሚል በድሩ አቅራቢነት ውይይት ማድረጋችን ይታወቃል።
አዲሱ በገበያ ላይ የተመሰረተ የውጭ ምንዛሬ ተመን ስርዓት ወይም (Floating exchange rate) ምንነት ተብራርቷል። በተጨባጭ ሀገራችን ላይ ስላለው አሉታዊና አዎንታዊ ጎኖች በአቅራቢው እይታ ተቃኝቷል።
ከመድረክ አወያዩና ከታዳሚያን ለተነሱ ጥያቄዎች አቶ ሙከሚል በድሩ ምላሽ ሰጥተዋል። ከሀገው ውጭ ሆነው በተጣበበ ጊዜያቸው ፕሮግራሙን ላቀረቡልን አቶ ሙከሚል በድሩ በግሩፑ አባላት ስም እያመሰገንን የድምፅ ቅጂውን በቴሌግራም ገፃችንን እንዳያያዝን ለመግለፅ እንወዳለን።
ስለ ስራ! የሁላችን ከሁላችን!
ውይይታችን ተጠናቋል!
አምስተኛ ምዕራፍ አንደኛ መሰናዶ ፕሮግራማችን ተጠናቋል።
ሀገራችን በአሁን ሰአት እየተገበረች ያለውን የኢኮኖሚ ማሻሻያ ለማህበረሰባችን ይዞት የሚመጣው እድል ወይስ ስጋት ነው? በሚል ርዕስ በአቶ ሙከሚል በድሩ አማካኝነት አስተማሪ ፕሮግራም ተደርጓል።
አቅራቢያችን በተጣበበ ሁኔታ ጊዜያቸውን ሰጥተው ሰፊ ማብራሪያ ስለሰጡን እያመሰገንን የድምፅ ቅጂውን በዚሁ የቴሌግራም ገፅ የምናያይዝ ይሆናል።
We just reached 60,000 members in the group! Thank you all for helping make this community strong.
አብራችሁን ስለዘለቃችሁ እናመሰግናለን !❤
ከግሩፑ አላማ ውጭ ፖስት እንዲደረግላቸው መወትወት፣በቀናነት ምላሽ ከመስጠት ይልቅ ሹፈት፣ለማጭበርበር መሞከር፣የሰዎችን ችግር መጠቀሚያ ማድረግ አንዳንድ አባላቶቻችን ላይ የሚታዩ ችግሮች ናቸው ይታረሙ !
የግሩፑን አላማ የምታከብሩ ስህተት ስታዩ የምትጠቁሙን የምታማክሩን እንወዳችኋለን !አሁንም አብረን እንዝለቅ !
ስለስራ የሁላችን !
እንዴት ከረማችሁ ? ወዳጆቻችን !
ግሩፓችንን በተሻለ ይዘትና ተሳትፎ ለማስቀጠል የተቻለንን ጥረት እያደረግን ነው?
ሆኖም አልፎ አልፎ በፌስቡክ ግሩፕ እናንተንም ቅር የሚያሰኙ ፖስቶች፣ኮሜንቶች እያየን ነው።
በተለይ ከተቀመጡት መስፈርቶች ውጪ አንዳንዶቹ እንኳን ልናስተናግዳቸው ልናነበባቸው የሚከብዱ ባህልንም ሀይማኖትንም ያላከበሩ ተደጋጋሚ ጥያቄዎች ይደርሱናል አላሳለፋችሁልንም የሚል ወቀሳም ያቀርባሉ።
እንዲህ አይነት ስራ ላይ ቅሬታ የሚጠበቅ ቢሆንም ግሩፑ የተሻለ ሆኖ እንዲጓዝ የእናንተንም ድጋፍ ይፈልጋልና እንደሁልጊዜው ሁሉ አብራችሁን እንድትሆኑ እንጠይቃለን !
ክፍተት ያላችሁትን ጠቁሙን እናርማለን።
ስራ በእውቀት እንዲሰራ እንተጋለን !
ስለስራ ለሁላችን !
የስለ ስራ! ማህበራዊ ድረ-ገፅ አማራጮችን በመቀላቀልና ለሌሎች በማጋራት ተደራሽነቱን ያስፉ!
? FB - Group https://www.facebook.com/groups/1153093882014917/?ref=share&mibextid=NSMWBT
? FB - Page
https://www.facebook.com/profile.php?id=61552032783167&mibextid=ZbWKwL
? Youtube - https://www.youtube.com/@SilSira-zs5rw
? Tiktok - tiktok.com/@sile.sira
? WhatsApp
https://whatsapp.com/channel/0029Va5Ch0O9WtBw5eGcdZ3H
? Telegram
https://t.me/selesera
ስለ ትብብራችሁ እናመሰግናለን!
Log in or sign up to view
See posts, photos and more on Facebook.
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated 2 months, 1 week ago
Last updated 6 days, 22 hours ago
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ ? @Esat_tv_comment_bot
??ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ??
Last updated 2 months, 3 weeks ago