Dive into the Ultimate Free Library: Your One-Stop Hub for Entertainment!

ኢትዮ ኘላስ + Ethio Plus

Description
በኢትዮጵያ እና ከኢትዮጵያ ባሻገር ያሉ መረጃዎች እና ሃሳብ የሚቀርብበት ቻናል ነው።

አለምአቀፋዊ እይታ እና ግንዛቤን በመረጃ እናሳድግ!

#Diplomacy #International #Politics #Science #Culture #Sport #Art
Advertising
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 2 days, 4 hours ago

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated 2 weeks, 5 days ago

Last updated 2 weeks, 5 days ago

7 months, 3 weeks ago
ሁለቱ የማራቶን ባለክበረወሰኖች

ሁለቱ የማራቶን ባለክበረወሰኖች

Eliud Kipchoge 🇰🇪 2:01.09 Men's WR
Tigist Assefa 🇪🇹 2:11.51 Women's WR

Are women closing the gap?

#Ethiopia #berlinmarathon

7 months, 3 weeks ago

በዚህ ቀጣና የታላላቅ ኢኮኖሚ አንቀሳቃሽ የሆኑት ቻይና፣ አሜሪካ፣ ፈረንሣይ፣ ሩሲያ፣ ጃፓን፣ ቱርክና መሰል አገሮች የሚያደርጉት ፉክክርም የኢትዮጵያን ጥቅም የሚነካ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ የኢትዮጵያን ጥቅም ያማከለ ወዳጅነትና ትብብር መፍጠር ያስፈልጋል ሲሉም አሳስበዋል፡፡

በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የታላቁ ህዳሴ ግድብ ተደራዳሪ ዲፕሎማትና የቀጣናው ጉዳይ ተንታኝ ዘሪሁን አበበ፣ በቀይ ባህር ቀጣና ኢትዮጵያን በማግለል የሚመሠረት ማንኛውም ዓይነት ትብብር ውጤታማም እንደማይሆንና ፍሬም እንደማያፈራ ተናግረዋል፡፡ ይሁን እንጂ በዚህ ቀጣና የሚደረጉ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ወይም የደኅንነት ፉክክሮችን ኢትዮጵያ ወደ መልካም አጋጣሚ በመቀየር ተጠቃሚ መሆን ትችላለች ብለዋል፡፡

የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታ ማዦር ሹም አማካሪ ሌተና ጄኔራል ዓለምሸት ደግፌ በመድረኩ ባደረጉት ንግግር፣ የመካከለኛው ምሥራቅ አገሮች ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በቀይ ባህር ቀጣና እያሳዩት ያለው ፍላጎት የኢኮኖሚ፣ የዲፕሎማሲና የፖለቲካ ስትራቴጂካዊ ጠቀሜታዎችን ለማጋበስ ነው ብለዋል፡፡

በመሆኑም በዚህ አሳሳቢ በሆነው ቀጣና መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችም ጠንካራ ትብብር በማድረግ አፋጣኝ ምላሽ ሊሰጡበት እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡ አገሮቹም ለዚህ አመቺ የሆነ አዲስ የፖሊሲ አማራጭ መተግበር እንደሚያስፈልጋቸው አሳስበዋል፡፡

በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የመካከለኛው ምሥራቅ ፓስፊክና እስያ ጉዳዮች ዳይሬክተር ገበየሁ ጋንጋ (አምባሳደር) በበኩላቸው፣ እ.ኤ.አ. ከ2020 ወዲህ በቀይ ባህር አካባቢ በርካታ የዓለም አገሮች የርዕዮተ ዓለምና የኢኮኖሚ ፍላጎታቸውን ለማሳካት በከፍተኛ ሁኔታ ሲማትሩ ይታያሉ ብለዋል፡፡ በዚህ ፉክክር ምክንያት ቀጣናው የደኅንነት ሥጋት ውስጥ መግባቱን ገልጸዋል፡፡

በተጨማሪም ቀጣናው የሚመሠረቱ አዳዲስ አገሮች መብዛትና አገሮቹም በሚፈለግባቸው መጠን እንደ አገር ጠንክሮ መቆም አለመቻል፣ ለዓለም አቀፍ የሽብርተኛ ተቋማት ምቹ ምኅዳር እየሆኑ ነው ብለዋል፡፡ በመሆኑም ለዚህ የፖለቲካ ምስቅልቅል ሁሉን አቀፍና አካታች የጋራ ዕቅድና ትልም በማውጣት፣ ችግሩን በዘላቂነት የመፍቻ መንገድ ማበጀት ተገቢ ነው ሲሉ አክለዋል፡፡ የቀጣናው አገሮች የትብብር ፎረም መመሥረት ከቻሉ ከውጭ ኃይሎች የሚመጣን ያልተገባ የፖለቲካ ፉክክር የመቀነስ አቅም እንደሚኖር አስረድተዋል፡፡

የአፍሪካ ቀንድ አገሮች በትብብር መሥራት ባለመቻላቸው ከመካከለኛው ምሥራቅም ሆነ ከምዕራባውያን አገሮች ወደ ቀጣናው መጥተው መፎካከራቸው ምክንያቱ፣ የቀጣናው አገሮች መተኛት ነው የሚሉት ደግሞ አብደታ (ዶ/ር) ናቸው፡፡ የቀጣናውን አገሮች መተኛት በምሳሌነት ሲያብራሩ፣ ‹‹ለአብነት በሱዳን በተፈጠረው ቀውስ አገሮች ቁጭ ብለው የተነጋገሩበት ስለመሆኑ እጠራጠራለሁ፤›› ብለዋል፡፡ ራቅ ካሉ አገሮች መጥተው በጉዳዩ ላይ ተዋናይ መሆናቸውንም አስታውሰዋል፡፡ በጦርነቱ ውስጥ ያሉት የጦር ጄኔራሎች ብቻ ሳይሆኑ ስለጦርነቱ ባህሪና ስለውጭ አገሮች ጣልቃ ገብነት ግልጽ የሆነ ምክክር ያስፈልጋል ያሉት አብደታ (ዶ/ር)፣ በቀጣናው አገሮች መካከል ያለው ትልቁ ችግር እንደሚባለው በግልጽ አለመተዋወቃቸውና መነጋገር አለመቻለቸው ነው ሲሉ አብራርተዋል

7 months, 3 weeks ago

📍በቀይ ባህር ፖለቲካ ላይ የመከረው የመጀመሪያ ጉባዔ
~~~~~~~~
በሪፓርተር ጋዜጣ
ሰሞኑን በአዲስ አበባ ለመጀመርያ ጊዜ በቀይ ባህር ቀጣና የፀጥታ እንቅስቃሴ ላይ በመከረው ጉባዔ፣ ኢትዮጵያ የወደብ ጥያቄዋን በዲፕሎማቲክ አማራጮችና በትብብር ማዕቀፎች ላይ ትኩረት እንድታደርግ ጥሪ ቀረበ፡፡

የውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት ከመከላከያ ዋር ኮሌጅ ጋር በመተባበር መስከረም 10 ቀን 2016 ዓ.ም.፣ ‹‹የቀይ ባህር የደኅንነት ሁኔታ ቀጣናዊ ምክክርና ትብብር መልከዓ ፖለቲካዊ መጠላለፍ በበዛበት ዓለም ወቅት›› በሚል ርዕስ ባዘጋጁት ጉባዔ፣ መቀመጫቸውን በአዲስ አበባ ካደረጉ የተመረጡ የውጭ ዲፕሎማቶች፣ ተወካዮች፣ የዘርፉ ተዋናዮች የመንግሥት ተቋማት ተወካዮች፣ የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮችና ሌሎች ተጋባዦች በተገኙበት ውይይት ተካሂዷል፡፡

ውይይቱ በኢትዮጵያ የወደብ ባለቤትነትና በቀጣናው ያለው የኃያላን አገሮች ፉክክር ላይ ያነጣጠረ ሲሆን፣ በመድረኩ ሁሉም የቀይ ባህር ቀጣና አገሮች ዲፕሎማቶች ተሳታፊ ነበሩ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) በቅርቡ ከባለሀብቶችና ከሚዲያ ኃላፊዎች ጋር በተለያዩ መድረኮች አደረጉት በተባለው ንግግር፣ አትዮጵያ በተለያዩ አማራጮች የወደብ ባለቤት ትሆናለች ብለው መናገራቸውን የሚያመላክቱ መረጃዎች በስፋት ሲሠራጩ ነበር፡፡

በአዲስ አበባ ለመጀመርያ ጊዜ በቀይ ባህር ፖለቲካ ላይ ባተኮረው መድረክ በዋናነት ከተንፀባረቁ ጉዳዮች አንዱ የኢትዮጵያ ወደብ የማግኘት ጉዳይ ሲሆን፣ በዚህ አጀንዳ ላይ ወደብ የመጠቀም መብት ወይስ የወደብ ባሌበት የመሆን፣ ወደብን በኃይል የመውሰድ ወይስ በዲፕሎማቲክ መንገድ የማሸነፍ የሚሉ ሐሳቦች ተንሸራሽረዋል፡፡

በውይይቱ ከመቶ ሚሊዮን በላይ ሕዝብ ያላትን አገር ወደብ አልባ ማድረግና በቀይ ባህር ቀጣና ላይ በሚከናወኑ ማናቸውም እንቅስቃሴዎች ማግለልን በዝምታ ማለፍ ለመጪው ትውልድ ፈተና ጥሎ መሄድ ነው ያሉት፣ የቀድሞው የዳያስፖራ ማኅበር ፕሬዚዳንትና የዓለም አቀፍ ዳያስፖራ ማኅበር የቦርድ አባል አቶ እንድሪስ መሐመድ ናቸው፡፡

‹‹ከዚህ በፊት የነበረው የእኔ ትውልድ አገሪቱን ወደብ አልባ ያደረጋትን ስህተት ማናቸውም አማራጮች በመጠቀም መፍትሔ ሊያመጣ የሚችል ሥራ መሥራት ይገባል፤›› ብለዋል፡፡ ወደብ የማግኘት ጉዳይ አማራጭ የሌለው በመሆኑ በሰጥቶ በመቀበል፣ ከዚያም ካለፈ የኃይል አማራጮችን የመጨረሻ መንገድ ማድረግ እንደሚያስፈልግ አቶ እንድሪስ አስረድተዋል፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ መሳፍንት ተፈራ፣ ከቀይ ባህር ፖለቲካ ኢትዮጵያን አግልሎ መቆየት የማይቻል በመሆኑ ማናቸውም ቀይ ባህርን የተመለከቱ ጉዳዮች ላይ ኢትዮጵያ የራሷ የሆነ ሚና ልትጫወት ግድ ይላታል ብለዋል፡፡

ከ120 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ ያላት አገር በፀጥታ፣ በንግድና ኢንቨስትመንት፣ በደኅንነት ወይም በሌላ ጉዳይ እያደገ ከሚመጣው ፍላጎት ጋር ከቀይ ባህር ውጭ መንቀሳቀስ የማይቻላት በመሆኑ፣ በዚህ ቀጣና በማንኛውም ኢትዮጵያን ተሳታፊ ሊያደርግ የሚችል ጉዳይ ላይ ተሳታፊ መሆኗን ማረጋገጥ እንደሚገባት አብራርተዋል፡፡

በቀይ ባህር ቀጣና የደኅንነትና የፖለቲካ እንቅስቃሴ ላይ ባተኮረው መድረክ ምክትል ዳይሬክተሩ እንደገለጹት፣ ቀይ ባህርን የሚመለከቱ ጉዳዮች ላይ እንደ አንድ ጥናት ተቋም መከናወን ያለባቸው አስፈላጊ የመፍትሔ አማራጮች በገለልተኝነት ተዘጋጅተው በየጊዜው ለውይይት ይቀርባሉ ብለዋል፡፡

በዲፕሎማሲው ዘርፍ ለረዥም ዓመታት ያገለገሉትና በቀጣናው ጉዳይ ላይ ዕውቀት ያካበቱት ግሩም ዓባይ (አምባሳደር) እንደሚሉት፣ ኢትዮጵያ የባህር ወደብ ያስፈልጋታል የሚለው ጉዳይ በአመዛኙ በብዙዎች ዘንድ ተቀባይነት ያለው ዕሳቤ ነው ሲሉ አስረድተዋል፡፡

ይሁን እንጂ ኢትዮጵያ ወደብ ባለቤት ትሆናለች የሚለውና ወደብ የመጠቀም መብት ይኖራታል የሚለው ጉዳይ ተለያይቶ መታየት እንዳለበት አሳስበዋል፡፡ ይህ ማለት አንድ አገር የሌላን አገር ድንበር አልፎ መሀል ላይ የወሰን ንብረት ባለቤት ነኝ ብሎ መናገር የማይቻል በመሆኑ ነው ብለዋል፡፡

የወደብ ባለቤትነት የሚባለው ንግግር ጥንቃቄ የሚያሻው መሆኑን ያስረዱት ግሩም (አምባሳደር)፣ ባለቤትነት የሚለው ጉዳይ የማያስኬድ ነው ብለዋል፡፡ በቀጣይ የወደብ ተቃሚነትን ላይ ለመነጋገር ሲታሰብ የወደብ ባለቤትነትንና የመጠቀም መብትን ዕሳቤ ግምት ውስጥ ማስገባት እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል፡፡ ለዚህ ማስረጃ ያቀረቡት ምክንያት ደግሞ፣ የማንንም ድንበር በኃይል እወስዳለሁ ብሎ መነሳት የማይቻልና ዓለም አቀፍ ሕግንም የሚጥስ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

‹‹ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ባለወደብ እንሁን በሚል የተለያዩ ሐሳቦች ሲነሱ ይደመጣል፣ ነገር ግን ይህ በፍላጎት ብቻ የሚሳካ ነገር ባለመሆኑ ምክንያታዊ በመሆንና አካባቢን በማጥናት በዚያ ማዕቀፍ ውስጥ ሊሠሩ የሚችሉ አማራጮችን በሰላማዊ መንገድ መፈለግ ያሻል፤›› ብለዋል፡፡ ይሁን እንጂ የኢትዮጵያ የተረጋገጠ የባህር ወደብ ማግኘት ኢትዮጵያውያን ብቻ ሳይሆን፣ ትልልቅ አገሮች ጭምር ለኢትዮጵያ የወደቡን አስፈላጊነት በብዙዎች ዘንድ እምነት የተጣለበት ነው ብለዋል፡፡

በአጠቃላይ ኢትዮጵያ የጂኦግራፊ አቀማመጧን በመውሰድ የቀይ ባህር ኃይል ነች ለሚለው ጥያቄ የባህር ዳርቻ ስለሌላት አይመለከታትም ማለት ይቻል ይሆናል፡፡ ይሁን እንጂ ከቀይ ባህር በ48 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኝና እያደገች ያለች ትልቅ አገር በመሆኗ፣ በአፍሪካ በዲፕሎማሲውም ሆነ በፖለቲካው ተፅዕኖ እየፈጠረች ያለች፣ ከመካከለኛው ምሥራቅ አገሮችም ጋር ጠንካራ ግንኙነት ያላት ስለሆነች የባህር ጠረፍ የላትም በሚል ከቀይ ባህር እንዳትጠቀም ማድረግ የማይሆን ጉዳይ ነው፤ ሲሉ አክለዋል፡፡

ቀይ ባህር ለኢትዮጵያ ትልቅ ሚና አለው ያሉት ግሩም (አምባሳደር)፣ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ እያደገ በመጣ ቁጥር የተረጋገጠና ዋስትና ያለው የባህር በር ያስፈልጋታል ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያ ወደብ ማግኘት አለባት የሚለው ጉዳይ በምን መልኩ ይመለስ የሚለው ጉዳይ ግን ምክክርና ውይይት ያስፈልገዋል ያሉት ሌላኛው ተሳታፊ የምክክር፣ ጥናትና ትብብር ማዕከል የተሰኘ ተቋም ዋና ዳይሬክተር አብደታ ድሪብሳ (ዶ/ር) ናቸው፡፡

የወደብን ጉዳይ የሚመለከቱ ዓለም አቀፍ ሕጎች የሚያመላክቱትን አማራጭ ማየት ያስፈልጋል ብለው፣ ነገር ግን በዲፕሎማሲው ማሳመን ሳይቻል በኃይል ለመሄድ ሲሞከር ከሚጠቁት አገሮች ጀርባ ሌሎች ደጋፊ አገሮችና ዓለም አቀፍ ሕግ በመኖሩ፣ በሌላ አገር መሬት ላይ ጦርነት ከፍቶ የትም አይደረሰም በማለት ተናግረዋል፡፡ በሰጥቶ መቀበል መርህ አማራጭ ወይም ከቀጣናው አገሮች በአንዱ ለኢትዮጵያ የወደብ ጥያቄ መፍትሔ ሊያመጣ የሚችል አዲስ መሪ ሲተካ መሆኑን አመላክተዋል፡፡

በውይይቱ ወቅት በስፋት የተነሳው ሌላኛው ጉዳይ የቀጣናው የደኅንነት ሥጋትን የተመለከተ ነበር፡፡ ይህን በተመለከተ ግሩም (አምባሳደር) እንዳብራሩት፣ በቀጣናው በርካታ ሽኩቻዎችና ፉክክሮች ስላሉ በርካታ ዓይኖች እያማተሩ ናቸው፡፡ የቀይ ባህር ቀጣና አገሮች ከምንጊዜውም በላይ ትብብር ካልመሠረቱ በሜዳቸው የተመልካች እንጂ የተጫዋችነት ሚና አይኖራቸውም ብለዋል፡፡

በአፍሪካ ቀንድ ውስጥ በሚገኙ አገሮች የፖለቲካ ሽግግር መኖሩን፣ የመካከለኛው ምሥራቅ አገሮች የደኅንነትና የዲፕሎማሲ ፍላጎት ማደጉንና እነዚህ አገሮች ባላቸው ሀብት ወደቦችን እየገዙ እንደሆነ አስረድተዋል፡፡

8 months ago
ኢትዮ ኘላስ + Ethio Plus
8 months ago
ኢትዮ ኘላስ + Ethio Plus
8 months ago
***📍*** የአማርኛ ቋንቋ በሞስኮ ትምህርት ቤቶች …

📍 የአማርኛ ቋንቋ በሞስኮ ትምህርት ቤቶች መሰጠት ተጀመረ
~~~~~~~~~~~~~~~
የሩሲያው ዜና አግልግሎት ስፑቲኒክ እንደዘገበው አማርኛን ጨምሮ የአፍሪካ ቋንቋዎችን በሩሲያ ትምህርት ቤቶች መሰጠት ተጀምሯል።

የቋንቋዎቹ ትምህርት መጀመር በሩሲያ እና በአፍሪካ ሀገራት መካከል የሚኖረውን ኢኮኖሚያዊ፣ ዲፕሎማሲያዊና በባሕላዊ መስኮች የነበሩ ትስስሮችን ይበለጥ ለማሳድግ ሚናው የጎላ መሆኑን የትምህርት ቤቶች ርዕሰ መምህራን ተናግረዋል።

አማርኛ ቋንቋን በሁለተኛ ቋንቋነት መማር የጀመሩ ተማሪዎች ለስፑቲኒክ እንደተናገሩት፣ ቋንቋውን ከማወቅ ባሻገር ወደ ኢትዮጵያ መጥተው የህዝቡን ባህልና አኗኗር የማወቅ ጉጉት አሳድሮባቸዋል።

ሩሲያ በሞስኮ ትምህርት ቤቶች ከመስከረም ጀምሮ አማርኛ ቋንቋ ማስተማር እንደምትጀምር ባለፈው ዓመት ማስታወቋ ይታወሳል።

8 months ago
***🇪🇹*** New World Record

🇪🇹 New World Record
ጉዳፍ ፀጋዬ የአለም ክብረወሰን ሰበረች

አትሌት ጉዳፍ በዩጂን ዳይመንድ ሊግ የ5ሺ ሜትር ርቀት ክብረወሰንን ሰብራለች

8 months, 1 week ago

📍 ከተማ እየገነባ ያለው የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን፤ ቀለም እየቀቡ ኪራይ ከመሰብሰብ ሪል ስቴትን ወደ መገዳደር ያመራ ተቋም፤

በአስቻለው እውነቱ

ዛሬ ጸሐይ ስለሞቀው ሀቅ እነግራችኋለሁ፡፡ ወደ 2016 በስኬት ከሚጓዙ የሀገራችን መንግስታዊ ተቋማት የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን አንዱ ነው፡፡ ይህ ተቋም ለዓመታት የደርግ አዋጅ ያጎረሰውን አፉ ላይ ይዞ ያንን እያመነዠገ ከሚኖርበት ድንዛዜ ወጥቷል፡፡

በተለይም አሁን ተቋሙን እየመሩ ያሉት ዋና ሥራ አስፈጻሚው አቶ ረሻድ ከማል ልታይ ልታይ ያለማለት ድምጻቸውን አጥፍተው የሚመሩትን መስሪያ ቤት ሌላ ተአምር ውስጥ አስገብተውታል፡፡ ሚዲያዎች ወደ እሳቸው ሄዱ እንጂ ወደ ሚዲያ አልመጡም ነበር፡፡ የተቋሙ ስራ አፍጦ መነጋገሪያ ሲሆን አሁን መገናኛ ብዙሃንም ስለ ፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ማውራት ጀምረዋል፡፡

ያ አከራይቶ ኪራይ እየሰበሰበ እጁ ላይ ቤት የሚወድቅበት ተቋም አሁን አዲስ አበባ ዓይን ውስጥ የሚገቡ ህንጻዎችን በአጭር ጊዜ እውን አድርጓል፡፡ በርካታ ቤቶችን ሰርቷል፡፡ ነባር ቤቶችን በዘመናዊ መልክ ለመያዝ ጥረቶች እያደረገ ነው፡፡

ኮርፖሬሽኑ በኮንስትራክሽን ዘርፉ የሚስተዋለውን የግብዓት አቅርቦት እጥረትን የሚያቀሉ የኮንክሪት ውህድ እና ብሎኬት ማምረቻ ማሽን ተከላ ለማከናወን የግንባታ ፕሮጀክት ሥራ መጀመሩ ተበስሯል፡፡ በቀን ከ60 ሺህ በላይ ብሎኬቶችን የሚያመርተው ይህ ፕሮጀክት ለኮርፕሬሽኑ በዓመት ከ4 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ ያስገኛል፡፡

የኮርፖሬሽኑ ስኬት ሪፖርት አይደለም፡፡ መካኒሳ፣ አዋሬ፣ ተዘንዓ፣ ቀበና፣ ሱማሌ ተራ በመሳሰሉት አካባቢዎችመሬት ላይ የቆሙ ሕንጻዎች ትናንት ያልነበሩ ዛሬ የሚታዩ ናቸው፡፡ በ2010 ዓ.ም. 300 ሚሊዮን ብር ገቢ የነበረው ተቋም 2015 ዓ.ም. ላይ ከ2.7 ቢሊዮን ብር በላይ ደርሷል የሚለው ዜና ቁጥር ብቻ ተብሎ የሚታለፍም አይመስለኝም፡፡

ተቋም እዚህ እዚያም ግሩም ግንባታዎችን እያነጸ ቤት ገንብቶ ከተማ እያነጸ እንደሆነ እንደ ገርጂ ያሉ ሳይቶች ማሳያ ናቸው፡፡ እናም በእኔም እምነት ያለ ግርግር ትልቅ ስራ ሰርቶ ዓመቱን በስኬት ያጠናቀቀ ተቋም ብባል የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን እላለሁ፡፡

ቀለም ከመቀባት እና ቧንቧ ከመጠገን ውጪ እዚህ ግባ የማይባል ስኬት ሳያስመዘግብ እጅና እግሩ ታስሮ የኖረውን ይሄንን ተቋም ከድንዛዜ በማውጣት አሁን ሪል ስቴት የሚገዳደር ሆኗል፡፡

የተቋሙ ሥራ አስፈጻሚ የሚመሩት የልዑካን ቡድን ሰሞኑን በሀገረ እንግሊዝ ለንደን የስራ ጉብኝት አድርጎ ነበር፤ በእንግሊዝ አገር ከሚኖሩ ኢትዮጵያን እና ትውልደ ኢትዮጵያን ጋር በዳያስፖራ የመኖሪያ ቤት ፕሮግራም ላይ ተወያይቷል፡፡ ለዲያስፖራው የሚሆኑ ጥራት ያላቸውን ቤቶች ገንብቶ ለማቅረብ ወጥኗል፡፡ ልዩ የሚያደርገው ግን የፕሮጀክት ፍጥነቱ ከጥራት ጋር ሳይነጣጠል በአጭር ጊዜ የሚሳካ መሆኑ ነው፡፡

እንደ እኔ ደግሜ እላለሁ ይህንን ያሳለፍነውን ዓመት በስኬት ተሻገርነው ማለት ከሚችሉ ጥቂት የመንግስት ተቋማት አንዱ ይሄ መስሪያ ቤት ነው፡፡ በዚህ ፍጥነት እና ስኬት ከቀጠለ በቀጣዮቹ አስርና አስራ አምስት አመታት በእርግጠኝነት ተአምር ሰርቶ እንደ አህጉር ምሳሌ የሚሆን ተቋም ይሆናል፡፡

8 months, 1 week ago
ኢትዮ ኘላስ + Ethio Plus
8 months, 1 week ago
ኢትዮ ኘላስ + Ethio Plus
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 2 days, 4 hours ago

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated 2 weeks, 5 days ago

Last updated 2 weeks, 5 days ago