ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated hace 3 semanas, 5 días
Last updated hace 3 semanas
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot
🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹
Last updated hace 1 mes, 1 semana
የጃፓን መኪና አምራቾች ቻይናን መቋቋም አልቻሉም
-----
👉 ኒሳን፣ ሆንዳ እና ሚትስቢሺ
የቻይና አምራቾችን ለመገዳደር ሊዋሃዱ ነው !
በአለም የመኪና ምርት እና ገበያ ክስተት የሆኑትን የቻይና አምራቾች ነባሮቹ ስመ ጥር የጃፓን ኩባንያዎች መቋቋም ተስኗቸዋል።
የመኪና ኢንዱስትሪው ከነዳጅ ወደ ኤሌክትሪክ እያደረገ ባለው ሽግግር እነ ቢዋይዲን መፎካከር ተስኗቸው ገበያቸው እየቀነሰ የመጡት ኒሳን ፣ ሆንዳ እና ሚትስቢሺ ጥምረት ፈጥረው ለመዋሃድ ወስነዋል።
ሶስቱ እውቅ የጃፓን ኩባንያዎች በተናጠል የሚያደርጉት ጉዞ አሁን ባለው የአለም ገበያ ተፎካካሪ እንዳይሆኑ አድርጓቸዋል።
ከጊዜ ወደ ጊዜ በአለም የመኪና ገበያ ውስጥ ያላቸው ድርሻ እየቀነሰ መምጣቱን ተከትሎ መፍትሄ ሲያፈላልጉ ቆይተው በመጨረሻው ውህደት መፍጠር ብቸኛው አማራጫቸው ሆኗል።
በዚህም መሰረት ከመጪው አዲስ አመት ጀምሮ ኒሳን እና ሆንዳ ተዋህደው የገበያ አቅማቸውን ለማሳደግ ስምምነት ያደረጉ ሲሆን በሶስተኛነት ሚትስቢሺን የውህደታቸው አካል ለማድረግ ስምምነት ላይ ደርሰዋል።
ይህ ጥምረት የአለማችን ሶስተኛ የመኪና ሻጭ ኩባንያ ያደርጋቸዋል ተብሏል።
የሶሰቱ ኩባንያዎች ስራ አስፈፃሚዎች በጋራ በሰጡት መግለጫ የመኪና ኢንደስትሪው ወደ ኤሌክትሪክ እያደረገ ባለው ሽግግር በቂ ስራ ባለመስራታቸው ስፍራቸውን አስጠብቀው መጓዝ እንዳቃታቸው ገልፀዋል።
ቶዮታ በዚህ ረገድ ቀደም ብሎ በኤሌክትሪክ እና ሃይብሪድ ምርቶች ውስጥ በከፊል መግባት መቻሉ እንደሶስቱ የጃፓን አምራቾች ተጎጂ አልሆነም።
አምራቾቹ በቀጣይ ሰኔ የውህደት ሂደቱን አጠናቀው ገበያውን ይቀላቀላሉ ።
በመኪና ምርት ይህነው የሚባል የገበያ ድርሻ ያልነበራቸው የቻይና የኤሌክትሪክ መኪና አምራቾች ካለፉት አራት አመታት ወዲህ ተፅዕኗቸው አይሏል።
ኢ+
መሰረት ደፋር ምክትል ኘሬዝደንት ሆነች
-------__
ዛሬ ስብሰባ ያደረገው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አዲሱ ስራ አስፈፃሚ ተ/ምክትል እና ምክትል ኘሬዝደንቶችን መርጧል።
ኢ/ር ጌቱ ገረመው ተቀዳሚ ምክትል መሰረት ደፋር ደግሞ ምክትል ኘሬዝደንት ሆነው ተመርጠዋል።
ስራውን በይፋ የጀመረው አዲሱ አመራር ብሄራዊ ስፓርታችንን ከተጋረጡበት ችግሮች የማዳን ትልቅ ሃገራዊ የቤት ስራ ይጠብቀዋል።
አትሌቲክሳችን ከቢሮ ሽኩቻ እና አተካራ ተላቆ ወርቃማው ዘመን እንዲመለስ እንመኛለን ! እንሻለን !!
.....ወደ ስራ ......
ኢ+
ፑቲን ዛሬ በአመታዊ ጋዜጣዊ መግለጫቸው ምን አሉ?
----
ቭላድሚር ፑቲን የፈረንጆች አዲስ አመት መጠናቀቅን አስመልክቶ አመታዊ ጋዜጣዊ መግለጫ ዛሬ ሰጥተዋል።
ኘሬዝደንቱ በቃለ መጠይቃቸው በርካታ ጉዳዮችን የደሳሱ ሲሆን ዋና ዋናዎቹ የሚከተሉት ናቸው ፦
🇷🇺 አስመልክቶ
ሩሲያ ዛሬም የተረጋጋች እና ጠንካራ ሃገር ናት። ምንም እንዃን በርካታ የደህንነት ስጋት በውጭ ሃይሎች ቢደቀንብንም እድገታችን አልተገታም። ኢኮኖሚያችን የዋጋ ግሽፈት ቢፈትነውም መልካም በሚባል ደረጃ ላይ ይገኛል ።
🇺🇸 አስመልክቶ
ከአዲሱ የአሜሪካ ኘሬዝደንት ዶናልድ ትራምኘ ጋር በመንኛውም ሰአት ተገናኝቼ ለመነጋገር ዝግጁ ነኝ ፥ለአራት አመታት ምንም አይነት ግንኙነት ያልነበረን በመሆኑ ከተገናኘን ብዙ የምናወራባቸው ጉዳዮች አሉን።
🇺🇦 አስመልክቶ
በዩክሬን ጦርነት ዋና ግባችን የኔቶን መስፋፋት መግታት ነው የነበረው ይህን አሳክተናል። ሰራዊታችን ከዩክሬን ጋር እያደረገ በሚገኘው ውጊያ የበላይነቱን አረጋግጦ ቀጥሏል።
እንደሁልጊዜውም እኛ ለሰላማዊ ውይይት ዝግጁ ነን ። በተቃራኒው የዩክሬን ሃይሎች ለድርድር ቀናኢ አይደሉም ፥
🇸🇾 አስመልከቶ
የአሳድ መንግስት መውደቅን የሩስያ ሽንፈት አድርገው የሚወስዱ የተሳሳቱ ናቸው። እኛ ከአስር አመት በፊት በሶሪያ ሰራዊት ያሰማራነው አሸባሪዎች ቁጥጥር ስር ሃገሪቱ እንዳትወድቅ ነው ። አሁን ያለው ለውጥ ከዚህ ፍላጎታችን ውጭ የሆነ አይደለም።
ሶሪያን ከተቆጣጠሩ ወታደራዊ ቡድኖች ጋር መልካም ግንኙነት አለን። ሩሲያ ከግዛቷ ውጭ በሶሪያ ያላት ብቸኛ የጦር ሰፈሯ ተጠብቆ እንዲቀጥል መግባባት ፈጥረናል።
በሶሪያ የተፈጠረው ለውጥ ከየትኛውም ሃገር በላይ ተጠቃሚ እያደረገ ያለው እስራኤልን ነው። የወቅቱን ሁኔታ በመጠቀም የሶሪያ መሬቶችን መልሳ እየያዘች ነው።
በመድረኩ በእነዚህ ቋንቋዎች ተጠቅመን በየስብሰባው ካልተሟገትን መብታችን ካላስከበርን በቋንቋ ክፍተት ወደ ኋላ ከተንሸራተትን አገርም ይሰደባል፣ይናቃል…በተለይ አሁን የምንመርጠው ፕሬዚዳንት ለሀገር ቤት ብቻ አይደለም...መራጮች ማሰብ ያለባቸው አለም አቀፍንም ነው...ይሄ ግን በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ልብ የተባለ አይመስልም...ከዚህ ይልቅ ኃይሌ ወደ ፌዴሬሽኑ እንዳይመጣ ምን ማሰሪያ እናብጅለት በሚለው የተጠመደ ነው የሚመስለው...ቋንቋን በተመለከተ መስፈርቱ ላይ እንደ አንድ ግዴታ መቀመጥም ነበረበት…
🎤ሀትሪክ፡- ...ይሄንን አለም አቀፉ ተሞክሮህን ወይም ሃሳብህን በተመለከተ ከሚዲያ ይልቅ ለፌዴሬሽኑ ለማካፈል ምን ያደረከው ጥረት አለ…?...
📌ኃይሌ፡- … (እንደ መሳቅ እያለ)… አይ አንተ ለወቀሳ ትቸኩላለህ እንጂ ምክሬን ለመለገስ ሞክሬያለሁ...እኔ ወደ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አመራርነት አልመጣም፤ ከእኔ ይልቅ እንደ ሀገር የሚጠቅሙ መስፈርቶች ላይ በተለይ አለም አቀፉ አትሌቴክስ ተቋማት ላይ የስራ ቋንቋ በሆኑት እንግሊዘኛና ፈረንሣይኛ ቋንቋ ላይ ትኩረት አድርጋችሁ ስሩ...አለም አቀፉ መድረክ ታዛቢ ሆነን መመለስ ይበቃል ብዬ ለፌዴሬሽኑ የጽ/ቤት ኃላፊ ለአቶ ዮሐንስ እንግዳ ነግሬዋለሁ...አሁን ወደ ስልጣን የምናመጣው ሰው ከሁለቱ ቋንቋዎች ከቻለ ሁለቱንም ካልሆነም አንዱን አውቆ ቢመጣ አለም አቀፉ መድረክ ላይ ታዛቢ ሳይሆን ተሟጋች ይኖረናል...በቀረው ጊዜ መራጩም ተመራጩም ያስብበት ነው የምለው…አንዳንዴ እኮ ከአለም አቀፉ አትሌቲክስ ለፌዴሬሽኑ በጽ/ቤት በኩል ከሚላከው ደብዳቤ ውጪ ለፕሬዚዳንት ተብሎ በግል ኢሜል የሚላኩ Top Secret (ጥብቅ ምስጢራዊ) የሆኑ ደብዳቤዎች ይመጣሉ...ለምሣሌ ከዶፒንግ ፣ከሀገር ጥቅም አኳያ ትልቅ ፋይዳ ያላቸው ምስጢራዊ መልዕክቶች ይመጣሉና ወደዚህ ቦታ የሚመጣ ሰው በቋንቋ በኩል የመጠቀ ሰው ያስፈልጋል...የቋንቋ ክፍተት እንደ ሀገር ብዙ ነገር እንዳያሳጣን ማስታወስ ያስፈልጋል...፡፡
🎤ሀትሪክ፡- ...ከዘንድሮው ምርጫ ምን ትጠብቃለህ…?...ከሚሠማው አንፃር ፍትሃዊና ተዓማኒነት ያለው ምርጫ ይሆናል ብለህስ ታስባለህ…?...
📌ኃይሌ፡- …አሁን የማያቸውና የምስማቸው ነገሮች በጣም ያስፈሩኛል...ምርጫው የአትሌቲክስ ነው አይደለም...?...ብዬ እንድጠይቅም እያደረገኝ ነው...ከዚህ በፊት በነበሩት ምርጫዎች ያልታዩ ነገሮች ማየቴ፣ ለውክልና የማየው ግብግብና ጥሎ ማለፍ፣ እንዲሁም ለመራጮች ገንዘብ ተመድቧል የሚል ነገር መስማቴ ምርጫውን በስጋትና ፍርሃት ስሜት ውስጥ ሆኜ እንድጠብቀው አድርጎኛል...አሁን ምርጫው የቀረው በጣም አጭር ቀናቶች ናቸው፤በእነዚህ ጊዜያቶች ምርጫው ሁሉንም ወገን የሚያስደስት ፍትሃዊ ምርጫ እንዲሆን ፌዴሬሽኑ ብዙ መስራት አለበት ብዬ አስባለሁ...ምርጫው ከውዝግብ ፀድቶ አትሌቲክሱን በአለም አቀፉ ደረጃ ከፍ ያደረገ አመራር እንዲመጣም ምኞቴ ነው…
🎤ሀትሪክ፡- ...አንዳንድ ወገኖች አንተ የምትሰጣቸውን አስተያየቶች በማድመጥ ኃይሌ ወደ ምርጫው ባለመምጣቱ የሚታየው ጉድፍ ጉድፉን ብቻ ነቀሶ የሚያወጣው ብለው ለሚያሙህ መልስ አለህ…?...
📌ኃይሌ፡- … አሁን ብዙ ውዝግብና ትንቅንቅ የሚታይበትን ቦታ ገብቼ አይቼዋለሁ፣ አውቀዋለሁ፤ለመምጣት ብፈልግ መምጫው መንገድም አይጠፋም ግን እኔ እንደመልመጣ አስረግጬ ተናግሬያለሁ… ስለራስህ አታወራም እንጂ ብመጣም እኮ እንደ ሀገር እጠቅም፣እንደ ሀገር ኩራት እሆን ይሆናል እንጂ የምጎዳ አይመስለኝም…ጥሩ ሽመል መምቺያ ብቻ ሳይሆን መመኪያም ይሆናል ነው የሚባለው አደል...ቢያንስ ቢያንስ ኩራት እሆን ይሆናል እንጂ አላሳፍርም....እንደዚህ ከሚባል ይልቅ ኃይሌ እንዴት ነው የሚመጣው?ምን አድርገን አሳምነን እናምጣው ነበር መባል ያለበት...ግን ያው ታውቀው የለ… (ብሎ ለተወሰኑ ደቂቃዎች ፀጥ ካለ በኋላ) ግን እኔ በግል አቋሜን ተናግሪያለሁ...መቼም አልመጣም ብዬ… በስፖርት አይደል እዚህ የደረስኩት ፣ ድየርጅት ባለቤትም የሆንኩት... ስፖርት ያውም አትሌቲክሱ አሳድጎ፣ ለዚህ አድርሶኝ ሊያጠፉት የሚሞክሩ ነገሮች ሳይ ዝም ለማለት አቅም ያንሰኛል፣ ለዚህ ነው ወጥቼ የምለፍልፈው እንጂ ወደዛ የመመለሱን ነገር አስቤውም አላውቅም…
🎤ሀትሪክ፡- ...ምርጫው ፍትሃዊና ዴሞክራሲያዊ እንዲሆን የስፖርቱ የበላይና የመንግስት አካል የሆነው የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ምን አይነት ሚና መጫወት አለበት ትላለህ በቀረው ጊዜ…?...
📌ኃይሌ፡- …ምን አለ ተናግረህ ባታናግረኝ ... (ኮስተር እንደማለት ብሎ)…ባህልና ስፖርት ሚኒስቴር በቅርብ ኖሮ ስፖርቱን የሚከታተልና ውሣኔ የሚሰጥ አካል ቢሆን ኖሮ የሕግ ያለህ ብለን መቼ ወደ መደበኛ ፍርድ ቤት እንሄድ ነበር? የሚሟገቱልንን ጠብቆች በግላችን ቀጥረን፣ገንዘብ አውጥተን እየተከራከርን ያለነው እኮ ድጋፍ ባለማግኘታችን ነው…ባህልና ስፖርት ሚኒስቴር እንኳን ሊያግዘን ቀርቶ እኛ እኮ አላገዘንም፣ፍትህ አልሰጠንም ብለን አንደኛ የከሰስነውም እሱን ነው...አሁን አትሌቴክሱ ላይ ያለው ግብግብና ስፖርት ስፖርት የማይሸቱ ነገሮችን ባህልና ስፖርት ሚኒስቴር አያውቃቸውም ብለህ ነው? ያውቃል...አሁንም ዳር ቁጭ ብሎ ማየት ስፖርቱን ይጎዳው ይሆናል እንጂ አይጠቅምም...ስለዚህ ምንድነው ነገሩ? ብሎ ሊጠይቅ፣አቅጣጫ ሊያስቀምጥ ይገባል (ያነጋገርነው ማክሰኞ ዕለት ነው) ብዙም የተለየ ነገር ባልጠብቅም የዳር ተመልካች ከመሆን የዘለለ እንቅስቃሴ ሲደረግ ማየት ያስፈልጋል...
🎤ሀትሪክ፡-ጨረስኩ በጣም አመሠግናለሁ...
📌ኃይሌ፡- ...(የእጅ ሠዓቱን እየተመለከተ)...ኡ ስብሠባ ነበረኝ አስረፈድክብኝ...በል ቻው...!...(እየተጣደፈ ወጣ)...
🎤ሀትሪክ፡-እሺ ቻው መልካም ጊዜ...!!!
ከሃትሪክ ጋዜጣ ጋር ያደረገውንቃለ ምልልስ በከፊል እንካችሁ
🎤ሀትሪክ ፡- ... የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን እጩዎችን ለመላክ መመዘኛ ብሎ በተራ ቁጥር 5 ላይ ከዚህ በፊት “ፕሬዚዳንትና ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል ሆኖ በገዛ ፍቅዱ ከአባልነት እንዲነሳ የጠየቀ” ብለው ያስቀመጡትን አንዳንድ ወገኖች ኃይሌን እስከ እነ አያቱ የጠራ፣ኃይሌ ላይ ያነጣጠረ መስፈርት ነው ብለው ጉዳዩን ከአንተ ጋር ያያዙት አሉ…በዚህ ላይ የአንተ እይታ ምንድነው…?...
📌ኃይሌ፡- …(በጣም እየሳቀ) ኃይሌን ከእነ አያቱ ነው የጠራው አሉህ...?...(አሁንም ሳቅ)...አልተሳሳታችሁም በላቸው... (በድጋሚ በጣም እየሳቀ)…እውነት ለመናገር የመስፈርቱ ቁጥር 5 ለእኔ የተዘጋጀ እንደሆነ በግልፅ ይናገራል… የማይገባኝ ነገር እኔ እኮ ምርጫ ውስጥ እንደማልገባ በግልፅ ተናግሬያለሁ፤በዚህ ደረጃ ሰዎች ለምን እንደተጨነቁም አልገባኝም...ተራ ቁጥር 5 እንደዛ ብለው ከሚፅፉ ኃይሌ ገ/ስላሴ ብለው ቢፅፉ እኮ ይቀላቸው ነበር..እውነት ለመናገር ይሄን ለሚመሩት ሰዎች ክብር ነበረኝ...ይሄንን ካየሁ በኋላ ግን በጣም አዝኛለሁ...ገና ለገና ኃይሌ እጩ ይሆናል ተብሎ ከዚህ በፊት ተደርጎ በማያውቅ ሁኔታ "ፕሬዚዳንት ወይም ስራ አስፈፃሚ ሆኖ በራሱ ጊዜ ሪዛይን ያደረገ "ተብሎ መስፈረት ይወጣል? የእውነት ከልብ ያሳዝናል...ሲሆን ሲሆን እንደዚህ አይነት መስፈርት በእኔ ልክ አዘጋጅቶ ለመግፋት ከማሰብ ወደቦታው መጥቼ እንድሰራ ቢደረግ እኔ አይደለሁም አትሌቲክሱም ይጠቀማል..እንደውም ስለራስህ ብዙ አወራህ አትበለኝና አንድ ነገር ትዝ አለኝ…
🎤ሀትሪክ፡- ...(ድንገት አቋረጥኩትና)…?...
📌ኃይሌ፡- …(በጣም እየሳቀ)… “ጥሩ ሽመል ቢያንስ መመከቺያ ይሆናል” የሚል አንድ አባባልን አስታውሳለሁ...እኔ ወደ አትሌቲክሱ በመምጣቴ እንደ ሽመሉ መመከቻ ብቻ ሣይሆን መመኪያ ልሆን እችላለሁ እንጂ በየትኛውም መንገድ አሌቲክሱን አልጎዳም...እውነታው ይሄ ሆኖ ሰዎች ኃይሌ ገ/ስላሴ ብለው መጥራት እስኪቀራቸው ድረስ እንደዚህ አይነት መስፈርት በማውጣታቸው አዝኛለሁ...ይሄን ባደረጉት ሰዎች በጣም አፍሬያለሁ... ከሁሉም በላይ ደግሞ እኔ በዚህ ነገር ቅር እንደተሰኘሁ ልክ አይደለም ብዬ መቃወሜን እንኳን ሰምተው ይቅርታ አለመጠየቃቸውና ዝምታን መምረጣቸው ከልቤ እንዳዝንባቸው አድርጎኛል...ቢያንስ ተሳስተናል ብለው ይቅርታ ሊጠይቁኝ ይገባ ነበር ግን አላደረጉትም...ምክንያቱም ከአፈርኩ አይመልሰኝ የሚል አባባል አለ አይደል? ልክ እንደዛ ነው የሆኑት…
🎤ሀትሪክ፡- ...የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ሌላ የሰራው አነጋጋሪ ነገር ለ12 የክልል ፌዴሬሽንና ለ2 የከተማ አስተዳደሮች መራጭ ሆነው የሚመጡትን አካላት ስልክ ቁጥራችሁን ላኩ ብሎ የላከው ደብዳቤ ጉዳይ ነው…?...
📌ኃይሌ፡- …(ድንገት አቋረጠኝና)… እንዴት...?...እንዴት...?ፌዴሬሽኑ የመራጮቹን ስልክ ቁጥር ላኩልኝ አለ እያልክ ነው …?... (እንደመገረም እያለ)... ካደረኩት በእውነት በጣም ያሳፍራል…?...
🎤ሀትሪክ፡- ...(እኔም በተራዬ ድንገት አቋረጥኩትና)…ካደረጉት ሳይሆን በትክክል ተደርጓል ፌዴሬሽኑ በቀን 24/03/2ዐ17 ዓ.ም በጽ/ቤት ኃላፊው በአቶ ዮሐንስ እንግዳ ስም ተፈርሞ ለሁሉም ፌዴሬሽኖች የተላከው ደብዳቤ “በጉባኤው ላይ የሚገኙ አባላትን ከእነ ስልክ ቁጥራችሁ በደብዳቤ በፌዴሬሽኑ ኢ-ሜይል እንድታሳውቁን" ይላል...አሁንስ ጥያቄዬ ግልፅ ሆነልህ…?...
📌ኃይሌ፡- …እኔ ይሄንን ነገር ገና ከአንተ መስማቴ ነው...አንተ በገለፅከው መልኩ ተብሎ ከሆነ በጣም ያሳፍራል... መራጩን ወይም በድምፅ የሚሳተፉ የጉባኤ አባላትን ስልክ ቁጥር ላክልን ተብሎ ከሆነ እደግመዋለሁ በጣም ያሳፍራል ግን አያደርጉትም ብዬ የምከራከረው አንዳንድ ድርጊቶች ይሆናሉ ብዬ ስለማልቀበላቸው ነው… ካደረጉት ግን በጣም ልክ አይደለም… ድምፅ ሰጪዎች እኮ ድምፅ የሚሰጡት በምስጢር ነው... በምስጢር ድምፅ የሚሰጡ ሰዎች እኮ ሲጀመር መታወቅ የለባቸውም፤ፌዴሬሽኑ ግን የመራጮቹን ስልክ ላኩልኝ ብሎ ያውም በደብዳቤ እስከመጠየቅ ከደረሠ በጣም አስቸጋሪ ነው...
በመራጮች ዘንድም ትልቅ ጥርጣሬንና ስጋትን ይፈጥራል…"ምን አስበው ነው...?..."...የሚሉ ሰዎች እንዲበዙ ያደርጋል... ይሄ በፍጥነት መታረም አለበት…ግን እኔ ከስልክ ቁጥሩ በፊት የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ማድረግ ያለበት ግንዛቤ ማስጨበጡ ላይ ነው… ተፎካካሪዎች አሉ አይደል? ስለ እነሱ መራጩም ህዝብም ግንዛቤ እንዲኖረው የማደረግ ስራን ነው አስቀድሞ መስራት ያለበት...ማን ምን ይዞ እንዲሚመጣ፣ ማን የተለየ አዲስ ነገር ይዞ መጥቷል? የሚለውን አውቆ እንዲመርጥ ግንዛቤ ማስጨበጫ ስራን ነው መስራት ያለበት፤ ሌላው ደግሞ እኔ ላይ መስፈርት ከማውጣት ይልቅ በተለይ በተለይ መታለፍ የሌለበት እጩ መምረጫ መስፈርቱ ላይ ነው…
🎤ሀትሪክ፡- ...ማለት አልገባኝም… (ኮስተር ብዬ)…?...
📌ኃይሌ፡- …(እንደ መሳቅ እያለ)…በደንብ እንዲገባህ እኮ ልነግርህ ነው…(አሁንም ሳቅ)… ለፕሬዚዳንትነት እጩዎች ስንመርጥ ለሀገር ውስጥ ብቻ አይደለም…በተለይ … በተለይ ..ፕሬዚዳንቱን ስንመርጥ ለሀገር ውስጥ አይደለም... አብዛኛውን ለአለም አትሌቲክስ (IAAF) ለአፍሪካ፣ IOC እና ለሌሎችም ኢንተርናሽናል የአትሌቲክስ ተቋማት ድምፅ የሚሆነን ሰው ወይም ፕሬዚዳንትነት ነው መምረጥ ያለብን... አለም አቀፉ መድረክ ላይ ድምፅ ይሆነናል፣ ይሟገትልናል ብለን ነው መምረጥ ያለብን... በየአመቱ በተለይ የአለም ሻምፒዮና ውድድር በሚዘጋጅበት ጊዜ ስብሰባ ይኖራል…ቶኪዮ ላይ 2025 የአለም አትሊቲክስ ሻምፒዮና ይካሄዳል ይህን ተከትሎ ጉባኤዎች ይኖራሉ...
እንደው ለምሣሌ ያህል ለቴሌቭዥን መብትና ለሌሎችም ጥቅሞቻቸው ብድግ ይሉና ማራቶን ከቀኑ ሰባት ሰዓት ይጀመራል ይሉናል...በዚን ጊዜ በቦታው አቅም ያለው ተከራካሪ ፕሬዚዳንት ካለህ እጁን አውጥቶ "በፍፁም መደረግ የለበትም፤እኔ በዚህ ሰዓት ልጆቼን ለውድድር አሳልፌ ለመስጠት አቸገራለሁ"...ብሎ የሚከራከርልን ሰው ነው መምጣት ያለበት፤የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽንም እከሌ የተባለው እጩ ከሀገር ውስጥ አልፎ ለኢንተርናሽናሉም ብቁ ነው ብሎ የእጩዎችን ማንነት የማሳወቅ ስራ መስራት ነበረበት…አሁን ምርጫው ከአንድ ሳምንት ያነሠ ጊዜነው የቀረው...በዚህ ጊዜ ውስጥ ይሄንን ስራ መስራት ይጠበቅበታል.. ከዚህ ውጩ እኔ የምወርድ ከሆነ የሚቀጥለው አመራርም የራሱ ጉዳይ ተብሎ መኬድ የለበትም…
🎤ሀትሪክ፡- ...አንዳንድ ወገኖች ፌዴሬሽኑ የእጩ መስፈርቱ ላይ አለም አቀፉ ቋንቋዎች የሚባሉትን እንግሊዛኛና ፈረንሣይኛ ወይም ከሁለት አንዱን አቀላጥፎ መናገር የሚችል የሚል መካተት ነበረበት ብለው ሃሣብ የሚያቀርቡም ነበሩና የአንተም ሃሣብ ከዚህ ጋር ተመሳሰለብኝ... በዚህ ላይ የአንተ ምልክታ ምንድነው...?...
📌ኃይሌ፡- …ትክክል ነው መሆንም ነበረበት... ከሀገር አሻግረው ልብ ያሉ ሰዎች የሰጡት አስተያየት እንደሆነ ነው የሚሰማኝ…ምክንያቱም እዛ ሄደህ ስብሰባ ስትቀመጥ ከሁለቱ በአንድ ቋንቋ ማለትም እንግሊዝኛ አሊያም ፈረንሣይኛን ነው የምትጠቀመው … ኦሮሚኛ፣አማርኛ ወይም ትግርኛ ቋንቋ እዛ አይጠብቅህም...እነዚህን ነገሮች በደንብ አስረግጠን ማየት አለብን...
ዶናልድ ትራምኘ የአመቱ ተፅዕኖ ፈጣሪ ተብለው በታይም መፅሄት ተመረጡ
----------
መፅሄቱ ሁሌም በየዓመቱ እንደሚያደርገው ዛሬ የ2024 የላቀ ተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰብን በፊት ገፁ ይዞ በመውጣት ይፋ አድርጓል።
የዘንድሮ ተመራጭ ቀጣዩ የአሜሪካ ኘሬዝደንት ዶናልድ ትራምኘ ሆነዋል።
ትራምኘ በፓለቲካ ህይወታቸው ዳግም በመነሳት በአሜሪካ ታሪክ አዲስ ታሪክ መፃፍ ችለዋል ብሏል መፅሄቱ።
እንደ መፅሄቱ ከወራት በፊት በአያሌ የወንጀል ክሶች ከነበሩበት ፈተና በመውጣት በፓለቲካ ህይወት ዳግም ተወልደዋል።
ቀንደኛ ተቃዋሚያቸው በነበረው ታይም መፅሄት የአመቱ ተፅዕኖ ፈጣሪ ተብለው ትራምኘ መመረጣቸው ባላንጣዎቻቸውን ሁሉ እጅ የማሰጠታቸው ሌላው ማረጋገጫ ሆኗል።
በሶማሌላንድ ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር ተደረገ
ከሳምንታት በፊት በተደረገው ምርጫ የተሸነፉት ሙሳ ቢሂ የኘሬዝደንትነት ስላጣኑን በምርጫው አሸናፊ ለሆኑት ዶ/ር አብዱራሂም ዛሬ አስረክበዋል።
የስልጣን ርክክቡ እጅግ በደመቀ ስነስርዓት ቀሃርጌሳ ተከናውኗል።
ለድምፃዊ ማህሙድ አህመድ 118ሺ ዶላር ተበረከተ
--------
ለአንጋፋው አርቲስት ማህሙድ አህመድ በቨርጂኒያ፣ ስፕሪንግፊልድ በተካሄደው የምስጋና ምሽት የተገኘው ገቢ ዛሬ የዝግጅቱ ስፖንሰሮች፣ አርቲስቶች፣ አጋር ድርጅቶችና ግለሰቦች በተገኙበት ለጋሽ ማህሙድ ተበርክቷል። በዚህም መሰረት በምስጋና ምሽቱ ከቲኬት ሽያጭና ከዝግጅት ስፖንሰሮች የገኘው $105,300 (አንድ መቶ አምስት ሺህ ሶስት መቶ የአሜሪካን ዶላር) አርቲስቱ ገቢ ተደርጓል።
ጋሽ ማህሙድ ሳይቸግረው፣ የተረጋጋና የሰከነ ህይወትን ይመራ ዘንድ ይሄው ከአሜሪካ የተሰበሰበው ገንዘብ የተቀመጠለት ልክ እንደ ጡረታ ክፍያ በየወሩ እየወሰደ እንዲጠቀምበት በሚያስችል የትረስት ፈንድ አካውንት ነው።
ከዚህ በተጨማሪ የዝግጅቱ ብቸኛ የሚድያ አጋር የሆነው ኢቢኤስ ቴሌቪዥን ዝግጅቱን ቀርጾ ለማስተላለፍ እና ከማስታወቅያ የተገኘውን ብር 1,623,525 (አንድ ሚሊየን፣ ስድስት መቶ ሃያ ሶስት ሺህ አምስት መቶ ሃያ አምስት የኢትዮጵያ ብር) ለጋሽ ማህሙድ ገቢ ተደርጓል።
ባጠቃላይ የተገኘው ገቢ በአሁኑ ምንዛሬ ወደ 15.5 ሚሊየን የኢትዮጵያ ብር ነው።
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated hace 3 semanas, 5 días
Last updated hace 3 semanas
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot
🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹
Last updated hace 1 mes, 1 semana