Save Amhara Fano💪✊💪🌍 🛰🦅💚💛❤️

Description
መረጃ እና አስተያየት
ለመስጠት በዚህ አድርሱን
👇👇 
@SaveAmharafanoam

የተቀደሰን ነገር በእግሩ ለሚረግጥ ፥
ተመልሶም ያጎረሰውን እጅ ለሚናከስ
ርኩስ መጫወቻ የማይሆን የነቃ ማህበረሰብ
እስክንፈጥር ድረስ ብዕራችን አይነጥፍም።
Advertising
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated hace 3 semanas, 5 días

Last updated hace 3 semanas

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated hace 1 mes, 1 semana

1 month, 2 weeks ago
Save Amhara Fano💪✊💪🌍 🛰🦅💚💛❤️
1 month, 2 weeks ago
Save Amhara Fano💪✊💪🌍 🛰🦅💚💛❤️
1 month, 2 weeks ago

#አማራ ለአማራነቱ ነው እየታገለ ያለው በሚለው ሀሳብ ዙሪያ ጥርጣሬም፣ክስም ሆነ ወይም ያ ለምን ሆነ ብሎ ሊጠይቅ የሚችል አካል ቢኖር አማራን ለምን በአማራነትህ ትታገላለህ የሚለውን ጥርጣሬ፣ከስም ሆነ ሌላ ነገር ይዞ አማራን ከመጠየቁ በፊት አማራ ወደዚያ መንገድ ለገፉት በደሎችና መከራዎች በሙሉ ጠያቂው ራሱ ህያው ምስክር ነበር።

#ችግሩ ለአማራ መከራና በደል ግዴለሽነት ይሁን ወይም መታበይ ግልፅ የሆነ ነገር የሌለ በሚመስልበት መንገድ አማራ ለአማራነቴ እየታገልኩ ነው የሚል የትግል መርህ ይዞ የተጥቅ ትግል እያደረገ ባለበት በዚህ ወቅት ከብዙው በጥቂቱ መናኛ ጣያቄዎች ወይም ጥርጣሬዎች ውስጥ ኢትዮጵያዊነትስ በሚል የሚቀርበው ጥያቄ አንዱ ነው።

I say ~ What about Ethiopian-ism?

#ዛሬ አማራ የህልውና አደጋ ለወደቀበት አማራነቴ እየታገልኩ ነው ብሎ የወደቀበትን አደጋ አንድ ሁለት ብሎ ዘርዝሮ አቅርቦ ግልፅ ያደረገ ቢሆንም ያንን የህልውና አደጋ ጥያቄ ከመመለስ ይልቅ አማራ መልስ ላላገኘለት ጥያቄ የትጥቅ ትግል ላይ ባለበት ወቅት የአማራ ህዝብን ትግል ለማንቋሸሽ ወይም ጭቃ ለመቀባት ተገቢ ያልሆነ ~ counter questioning argument ~ በተለይ What about Ethiopian-ism የሚል ወንጋራ ሀሳብ ሲቀርብ እስኪ እናንተን ኢትዮጵያዊ አማራን ሌላ ሊያደርገው የሚያስችለው ~ if they have ~ a million reason ~ ወዲህ በሉ ብትላቸው ሊጠቅሱት ከሚችሉት ነገር ውስጥ አማራ በአንዱም አንሶ የሚገኝበት አንዳች ጉዳይ አይኖርም።

#ችግሩ ይሄን አስረግጦ መናገርም በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ለአማራ ሲሆን ሀጥያት የመሆኑ ጉዳይ ነው።

#ፋኖዎች ሆይ: –
የህልውና ትግላችን ወደ ህልውና ትግል እንድንገባ በገፉን ሰዎች ጥያቄም ሆነ ሙግት ~ justify ~ አይሆንምና ለጉንጭ አልፋ ክርክር ጊዜ ሳትሰጡ ወይማ ለማስረዳት ሳትደክሙ ወደፊት ብቻ ነው።

1 month, 3 weeks ago

#የኛም የአማራ ህዝብ ነገር ተመሳሳይ ነው። ወያኔ በጫካ ዘመን በአማራ ህዝብ ላይ የነበራቸው ጥላቻ 1983 ስልጣን ላይ ወተው የፖለቲካ ስልጣን እስከሚጨብጡ ድረስ ምንም ነገር አልፈጠረም ነበር። ስልጣን ላይ ሲወጡ ~ prejudice +power = Racism ( በኛ ሀገር ~ ethnic racism) የሰጣቸውን ሀይል ሀይል ጨምረውበት በ27 የስልጣን ዘመናቸው የፈፀሙት በደል፣በባለፈው ጦርነት ወደ አማራ ክልል ባደረጉት ወረራ ህዝባችን ላይ የፈፀሙት ሰይጣናዊ እብደትና አሁን በዚህ ሰሞን በአብይ አህመድ የሚመራው የማእከላዊ መንግስት አይዞህ ባይነትና ድጋፍ ቀጣይ ወረራ ለመፈፀም ያላቸውን ፍላጎት አካቶ ስልጣን ከመያዝና ስልጣን ከያዘ አካል ጋ በመመሳጠር የተፈፀመ ዘረኝነት ሆኖ ተመዘገበ። የኦነግም ያም ነው።ኦነጎች ድሮ ስልጣን በጨበጠው ወያኔ ተመርተው ፣ዛሬ እነሱን የሚስል የሀገሪቱን ስልጣን በመጨበጠ ሰው ስር ተደብቀው~ with political impunity and with total delibrate directtives የ prejudice + power ሰይጣናዊ ግብር በህዝባችን ላይ እየፈፀሙበት ለመሆኑ ሁሉም ምስከር ነው። ይሄን ግፍ ለማስቆም አማራው ሲሰባሰብ as if we have prejudice + power እጃችን ላይ እንዳለና የአማራው ህዝብ ራሱን ለማዳን መሰባሰቡ የፈጠረው ቀውስ ያለ ይመስል በራሳቸው ልክ በመለካት አማራውን በአማራነቱ መቆሙን ፅንፈኛ ብሄርተኛ በሚል የተያዘው ፍረጃ ከሞራልም ሆነ ከምንም አንፃር በፍፁም ውሀ የማያነሳ ክስ መሆኑን ለማሳየት ከብዙ ታሪኮች ውስጥ ከላይ በዶር ኻሊድ የቀረበው ትንታኔ የኛን ሀገር የፖለቲካ እብደት ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ ሀቅ ነው።

ወጋችንን ስንቀጥል:–

#በዚያው ቃለ ምልልስ ላይ ከተመልካች ከቀረቡ ጥያቄዎች ውስጥ ጥቁሮች የከለር ፖለቲካ ላይ ብቻ ትኩረታችሁን ከምታደርጉ ለሁሉም ህዝቦች total liberalization በአሁን ሰአት ባረጋገጠችው አሜሪካ ውስጥ እኩልነትን፣ነፃነትና ፍትህን ለማስፈን ለምን አትሰሩም? የጥቁሮች መብት፣የጥቁሮች ምናምን እያላችሁ ዘር ላይ ከተቸከላችሁ reverse racism ን እናንተስ እየጫወታችሁ አይደለም ወይ የሚል ጥያቄ ነበር የቀረበላቸው?
ተመሳሳዩ ጥያቄ በሀገራችንም ፖለቲካ ውስጥ የተለመደ ነው። የብሄር ፖለቲካን መጫወት ወያኔና ኦነግ ወይም ሌሎች የተወቀሱበትን ነገር መድገም ወይም በነሱ የጥላቻ መንገድ መጓዝ አይሆንም ወይ የሚል ጥያቄ በኛም ወገኖች ዘንድ ሲነሳ ይታያል። ይህ ጥያቄ ልክ ሊሆን ይችል የነበረው የብሄር ፖለቲካን እጠየፋለሁ ለሚል ቡድን የብሄር የፖለቲካ ድርጅቶችን በአቅምም ሆነ በመዋቅር challenge ሊያደርግ የሚያስችል የፖለቲካ መታገያ ሜዳና ይሄን የሚያበረታታ የመንግስት ፍላጎትና ቁርጠኝነት ሲኖር ነበር። በኛ ሀገር ወያኔዎችም ሆኑ ኦነጎች ወይም ሌሎች ያሉበትን የብሄር ፖለቲካ አልደግፍም ሆነ ወይም በነሱ መንገድ አልጓዝም ብትል የሚገጥምህ ተከራካሪ የሌለህ ምንም አይነት political leverage የሌለህ አቅመ ቢስ መሆን ነው። ለዚህ የኛ የአማራ ህዝብ የደረሰበት መከራና የዜግነት ፖለቲካ እናራምዳለን የሚሉ ነገር ግን እስከ አሁን ድረስ ምንም አይነት የፖለቲካ ተፅእኖ መፍጠር ያልቻሉት የነ ዶር ብርሀኑ ነጋና፣የነ ልደቱ አያሌው፣የነ ታማኝ በየነ ያለፉት የ34 አመት የፖለቲካና የአክቲቪዝም የህይወት ጉዟቸው ምስክር ነው።

Dr .ካሊድ መሀመድ ሲመልሱ:–

"If a slave master whipping the slave and blood is running down the slave's back and the slit incidentally whether the term cracker comes from the cracker of the man who has the crack of the whip on the slave's back. But if the slave takes the slave master's whip from him and starts whipping the slave master with his whip? that is not reverse racism and that Is not reverse discrimination. That is the slave getting out from the yoke of bondage and oppression." በሚል ነበር የመለሱት።

#የአማራ ህዝብ በወያኔ ለ 27 አመት እና በብልፅግና ላለፉት አምሰረት አመትና አሁንም የቀጠለውን መከራ ለመመከትና ለመከላከል በወያኔና በኦነግ በራሳቸው የብሄር የፖለቲካ ስሌት አማራ ብሄርተኛ ሆኖ መነሳቱ ህልውናውን ለማስጠበቅ ብሎም "trying to get out of bondage and oppression " ካልሆነ በስተቀር በምንም አይነት መለኪያ reverse ብሄርተኝነት ሊሆን እንደማይችል ከወያኔዎች፣ከኦነጎች ወይም ከመሀል ሰፋሪዎች ጪኸት ይልቅ ከላይ ካለው ታሪካዊ ንግግር መማር አለብን።

Footnote

Hearken unto me, my people:–
የማንም ጩኸትና ዘለፋ ሳይረብሸን በአማራነት ብቻ በአንድነት ከመታገል ውጭ አማራጭ የሚሆን መንገድ የለም።

1 month, 3 weeks ago

#በስማ በለው ( hearsays) የሚወቀሰው የአማራ ብሄርተኝነት!

(Prejudices + power = Racism)
(ጭፍን ጥላቻ + ስልጣን = ዘረኝነት)
=========================
#የአማራ ህዝብ በዘርና በቋንቋ በተሸነሸነ ሀገር ውስጥ የዘርና ቋንቋ ፖለቲካ ትሩፋቶች ከሚያስገኙት ጥቅም ይልቅ የሚፈጥሩት ችግር የበለጠ ነውና በዚህ ከረጢት ውስጥ ተሰፍቼ ከመኖር ይልቅ ሀገራዊ ራእይ ባለው የዜግነት ፖለቲካ ውስጥ ተሳትፎየን ማድረግ እመርጣለሁ ባለበት ጊዜ ውስጥ በታሪክ የመዛግብት ገፅ በተመሰከረና መሬት ላይ በእውኑ አለም ተፈፀም ባየነው ግፍና መከራ ልክ የተረፈው ነገር የዘርና ቋንቋ ፖለቲካ ከሚያስገኙት ትሩፋቶች ተጋሪ መሆንን ሳይሆን በዘርና ቋንቋ የተሸነሸነው ፖለቲካ ጥቅም ያስገኘላቸው አካላት ለብቻው ተለይቶ እንዲጠቃ የሚያደርግ ፖለቲካን ነበር የመሰረቱት። ከዚያም ህዝባችን በጊዜ ቀመር ውስጥ በሚቀያየሩ መንግስታት ልክ ሊፈታ የማይችል መከራ እንደወደቀበት ተረድቶ ለዚያ የሚመጥን የአቋም ሽግሽግ ሲያደርግ በዘርና ቋንቋ በተሰፋው የዘር ፖለቲካ ውስጥ የአንደኛነት ዜግነትና የብሄር ፖለቲካ መልካም ፍሬዎችን ተቋድሰው ፣ጊዜ በሰጣቸው ስልጣን የሀምሳ አምት ወልጋዳ ትርክት ፍሬ የሆነውን የበቀል በትራቸውን በአማራ ህዝብ ላይ ባሳረፉ የብሄር ፖለቲከኞች ጫማ ልክ አማራን በመለካት አማራ ለህለውናው የሚያደርገውን ትግል ማራከስ የጠላቶቻችን ዋነኛ አጀንዳ ከሆነ ቆየት ብሏል።

#በዚህ ዙሪያ ~ historical contextual relevance and resemblance ~ ያለውን አስረጁ ታሪክ ከአማራ ህዝብ መከራ ጋ በማጣቀስ በሚከተለው መንገድ ለማየት ሞክረናል።

Dr. Khalid Muhammed በጥቁር አሜሪካውያኔን የእኩልነት ትግል ውስጥ በ 1980 እና 1990 ዎቹ በ black panther እና ከዚያም በ Nation of Islam ከፍተኛ አስተዋፅኦ በማድረግ እስከ መሪነት የደረሰ ትልቅ አስተዋፅኦ ያደረጉ ሰው ነበሩ። እንደ እኤአ አቆጣጠር በ1994 በአሜሪካ ዝነኛ የቴሌቪዥን Host ከነበረው ሚስተር Phil Donahue show ጋር በነጮች ዘረኝነትና በጥቁሮች የነፃነት ትግል ዙሪያ ከተለያዩ ክፍል የተሰባሰቡ ሰዎች በተገኙበት መድረክ ትልቅ ቃለ ምልልስ አድርገው ነበር። ጥቁር አሜሪካውያን በጥቁርነታቸው የሚደርስባቸውን ዘረኝነትና የፖለቲካ በደል ለመታገል የተሰባሰቡት በዘር መለያቸው በጥቁርነታቸው ነበር። ጥቁርነትን ይሰብካሉ። በጥቁርነታቸው የደረሰባቸውን በደል ዘርዝረው ህዝባቸውን ያስተምራሉ። ጥቁሮች በጥቁርነታቸው እንዲሰባሰቡና በጥቁርነታቸው ቆመው እንዲታገሉ ያነቃሉ፣ ይመክራሉ፣ ህዝባቸውንም ያስተምራሉ። ይህ በሌሎችዘንድ አልተወደደም።

እናም በ Phil Donahue በሚዘጋጀው Phil Donahue show ላይ አንዱ የሚከተለውን ጥያቄ ጠየቀ።

"Are we going to preach hate, or Are we gonna have a race war? Where are we going, or what would you like to do or promote? Where do you think we should go? " የሚል ነበር ጥያቄው።

እሳቸውም ሲመልሱ ይሄን ነበር ያሉት:–

"We are told by the honorable minister Luis Farrakhan to show courtesy, respect, and kindness. To be polite to all people as long as they are courteous and respectful, kind and polite to us. But we must look at the fact that we don't teach hatred. Everywhere we go as black people we face hatred. Look at it, look at it. Angels food in white people is a white cake, devil food in cake is you said black, you wear white clothes at weddings and black at funerals. Blackball, blackmail. Our won babies according to behavioral scientists, our baby girls, when confronted with choosing between a black doll and a white doll, there has been so much damage done, they chose the white doll and say the black doll is ugly. So, Racism is everywhere and it is institutionalized. We (blacks) can't be racist. Because racism is prejudice power. Nothing I say up here or anywhere in the world will impact any white fox audience on your job, in politics, in economics, in housing, in society. We don't have the power to do that. So we can't be racist. Do you know what I am saying? " በማለት ነበር ማብራሪያቸውን የጨረሱት።

#ይሄን ጉፋይ በቀጥታ ወደኛ ሀገር ስናመጣው አማራ ላይ የተሰራው ethnic discrimination ነው። አማራ በብሄሩ ከሌላው ተለይቶ በማንነቱ፣በዘሩ በቋንቋው፣ በአለባበሱ፣ በባህሉ፣በሀይማኖቱ፣ በርስት፣በቦታው እና በአጠቃላይ በአማራ በሆነ ነገር ላይ የተፈፀመ ፍፁም ወንጀል የሆነ ነገር ነበር የተሰራበት። እና አማራ ታግሶ፣ታግሶ ሁሉንም አይነት መከራ ተሽክሞ፣ተሽክሞ ሌላው ቢቀር የተለወጠ መንግስትና ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር ተደረገ በተባለበት ሀገር ውስጥ የማይለወጥና በጥላቻ የታወረ ማእከላዊ መንግስትም ሆነ ሌሎች የፖለቲካ ተዋንያን ባሉበት ሀገር ውስጥ አማራ ጥቁር አሜሪካውያን በጥቁርነታቸው ቆመው መታገል እንደጀመሩት ሁሉ ከእንግዲህ በቃኝ ብሎ በአማራነቱ መሰባሰብ ሲጀምር የጥቁር አሜሪካውያን መሰባሰብና በጥቁርነታቸው መቆም ያስፈራቸው አካላት "የዘር ጦርነት ልትጀምሩ ነው ? ፣ ጥቁር ጥቁር እያላችሁ ጥላቻን እየሰባካችሁ ነው? ወይስ ምንድን ነው ብለው ማሸማቀቅ እንደሞከሩት የኛም ሀገር ፖለቲካ አማራው አማራ ነኝ ብሎ መቆም ሲጀምር ተመሳሰሰዩን ነገር ለመፈለፀም የተሞከረበት አጋጣሚ ብዙ ሆኖ አይተነዋል።እያያነውም ነው።
ዶር ካሊድ መሀመድ ግን ዘረኝነት ማለት ~ prejudice +power ማለት ነው ይላሉ። እና እኛ ጥቁሮች መድረክ ላይ በመውጣት ለህዝባችን የምናደርገው ማንቃት ወይም በክርክሮች ተሳትፈን የምንናገረው በሙሉ ህዝባችንን ከማንቃት ባለፈ ሌሎች በስራቸው፣ በኢኮኖሚያቸው፣ በቤቶች ፕሮጀክት (የኛ ሀገር ኮንዶሚኒየም) ሆነ በሌሎች ነገራችሁ ላይ የሚያመጣው ተፅእኖ የለም ይላሉ። ምክኒያቱም ስልጣን (የፖለቲካ ስልጣን) እጃችን ላይ የለም። የፖለቲካ ስልጣን እጃችን ላይ ከሌለ ለጥቁር ህዝቦች የምናደርገው ትግልና ተጋድሎ በፍፁም ዘረኝነት ሊሆን አይችልም ነበር ያሉት።

1 month, 3 weeks ago

There was and still is something very wrong with Ethiopian politics.

ኢትዬጵያ አንድነቷ ተጠብቆ፣የባህር በሯ ተከብሮ ይኖር ዘንድ ~ ተብሎ በተነገረ የጦርነት ታሪክ ውስጥ :–
መሪው ~ መንግስቱ ሀይለማርያም

መሪነቱን የወሰደው ~ ከ ጄኔራል አማን አምዶም
ከ ተፈሪ በንቲ
ከ ደበላ ዲንሳ
ወደ ዚምባቡዌ ሲሰደድ የተካው ~ ጄኔራል ተስፋዬ ገ/ኪዳን ገለቱ
ሆኖ

ጦርነቱ ሲጠናቀቅ ~ የሀገር አንድነቱ ጉዳይ፣የባህር በሩ ጉዳይ ተረስቶ:– ያሸነፉት አማራን እንደሆነ ሲደሰኮር
ጦርነቱ የአማራ የነበረ ይመስል በጦርነቱ ለደረሰው ጥፋት ይቅርታ ለመጠየቅ ኤርትራ ሄደው አማራን አሲዘው ይቅርታ ሲጠይቁ

ወያኔዎች ከአማራዎቹ ኢህዴን ጋ ሆነው መንግስቱ ሀይለማርያም ይመራው የነበረውን የኢትዬጵያን መንግስት በጦርነት አሸነፍን ባሉ ማግስት ~ አማራን አሽንፈን እንደ ሲጋራ አጭሰን ጥለነዋል ሲሉ

There was something very wrong with Ethiopian politics.

ወያኔዎች 27 አመታት ሀገር እያስተዳደሩም ~ አማራን ሲወቅሱ ኖረው ከስልጣን ገለል ብለው ከአብይ አህመድ ጋ በገጠሙት ጦርነት አሁንም አማራን እየወቀሱ ያሉበትና ወቀሳ ያላቆሙበት ሁበት ~ There still something very wrong with Ethiopian politics ~ ተብሎ ሊታሰብ ከሚችለውም በላይ የሆነ ነገር ነው።

አብይ አህመድ ፣ለማ መገርሳና ሽመልስ አብዲሳ ከአማራዎቹ እነ ገዱ አንዳርጋቸውና ደመቀ መኮንን ጋ ሆነው በአማራ ማስተኛዋ ክኒን ኦሮማራ ድራማ ወያኔን ገለል ባደረጉ ማግስት አቦ ሸመልስ አብዲሳ በአዲስ አበባ በመስቀል አደባባይ ነፍጠኛን የሰበረን ቦታ ሰብረነዋል ሲል ስልጣን የተረከበው ከአማራ እጅ እንጂ ከወያኔ ከዚያ አለፍ ሲልም በጦርነት ሜዳ ግዳይ ጥሎ እንደሚፎክር የጦር ሜዳ ጀግና ይመስል የነበረበት ንግግር ~ There was and still something very wrong with Ethiopian politics ~ ለማለት የሚያስገደድ ሁነት ነበረው።

ትናንት ወያኔ ዛሬ እነ አብይ አህመድ እጃቸው ላይ ያለው ስልጣን ትናንት የአማራ ገዢ መደብ ናቸው ብለው ሲወቅሷቸው የነበሩ መሪዎች ይዘውት የነበረው አይነት ~ with a little bit of modernity and money ~ ስልጣን ነው።
Maybe they can'tt fitinto it ~ የአማራ ስም ከአፋቸው በፍፁም ሊጠፋ ያልቻለበት ጉዳይ ~ There still something very wrong with Ethiopian politics ~ የሚያስብል ጉዳይ ነው። አሁንም!!!

አማራን በክልልህ በአማራነቱ መርጠህ ደሙን አፍስሰህ ፣በጅምላ ጨፍጭፈህ፣ ያለ ፍታትና ሶላተል ጀናዛ በጊሪደር በጀምላ መቃብር ቀብረህ፣ንብረቱን ዘርፈህና አቃጥለህ መግደል ያልቻልከውን አፈናቅለህ፣ የማንነተ መለያ የመታወቂያ ካርዱን አይተህ በአማራነቱ ወደ አዲስ አበባ አትገባም ብለህ ክልክለህ ይሄም አልበቃ ብሎ በቀየውና በርስቱ የሀገር ድንበር እንዲጠብቅ የተቋቋመውን ተቋም አማራን እንዲወር ጦር አዝምተህ ፣ታንክ፣የጦር ጄትና ድሮን አሰማርተህ በአማራ ላይ መከራ ማዝነባቸው ሳያንስ ፋኖዎች ኦሮሚያ ክልል ገብተው ሰው አረዱ ስትል ~ There must be in essence something very,very, very wrong with Ethiopian politics.

2 months ago

ጀግኖቹ አንድ ሄሊኮፕተር መትተው 🚁 ጥለዋል 💪💪💪

2 months ago

ዶ/ር ወንዶሰን አሰፋ

ዛሬ በፍርድ ቤት ያደረገው ታሪካዊ ንግግር

ከዚህ በመቀጠል በተከሰስኩበት ክስ የእምነት ክህደት ቃሌን እሰጣለሁ።
በቀዳሚነት የተከሰስኩት ጉዳይ የአማራ ህዝብ እኩል ከሌሎች ብሄሮችና ህዝቦች ጋር የአገር ባለቤት ሆኖ እያለ አገር ተወስዶበታል ብሎ ተናግሯል የሚል ነዉ።ክሴ ይሄን የሚል በመሆኑ አሁን ለፍርድ የቀረበዉ የአማራ ህዝብ የህልዉና ትግል ነዉ ማለት ነዉ።

የአማራ ህዝብ ላለፉት ሰላሳ አራት አመታት ፀረ አማራ ሀይሎች ተደራጅተው እና ተቀናጅተው ስልታዊ እና መንግስታዊ ጥቃት እያደረሱበት ያሉ ህዝብ ነዉ።
የአማራ ህዝብ የአገር ባለቤትነቱንበግልፅ በአደባባይ የተነጠቀዉ በ1983 ዓ.ም አማራ ጠል ሀይሎች የመንግስት ስልጣንን ተቆጣጥረዉ ባደረጉት የ ሰኔ 1983ቱ የቻርተሩ ጉባኤ ነበር።

ጉባኤው ያለምንም የአማራ ህዝብ ዉክልና የተካሄደ መሆኑን የስርአቱ ቁንጮ መለስ ዜናዊ በአደባባይ የመሰከረው ሀቅ ነዉ።በዚህ የቻርተር ጉባኤ የተመሰረተው የሽግግር መንግስት ባደረገው የክልል አከላለል ዉስጥ ምንም አይነት የአማራ ህዝብ ዉክልና ያልነበረው ሲሆን በዚህ የሽግግር መንግስት ዘመን የተዘጋጀው ህገመንግስትም የአማራን ህዝብ በማዉገዝ ተጀምሮ በማዉገዝ ያለቀ መሆኑን የቻርተሩ ጉባኤ ቃለጉባኤዎች ፣ የሽግግር ም/ቤቱ ቃለጉባኤዎች፣ የህገመንግስት ጉባኤ ቃለጉባኤዎች ዘላለማዊ ምስክር በመሆኑ ያስረዳሉ ።

በዘመኑ ትህነግ/ኢህአዴግ በአማራ ህዝብ ላይ የፈፀሙት አድሏዊ ድርጊቶች ፣መፈናቀሎች፣ የንብረት ዉድመት፣ የዘር ፍጅትእና አገር አልባነት ልለፈዉና የዛ ስርአት ቀጥተኛ ወራሽ የሆነውን የብልፅግና ፓርቲ እና መንግስት በአማራ ህዝብ ላይ የፈፀመዉን እና እየፈጸመ ያለዉን በደል ልግለፅ።

የብልግና መንግስት በአማራ ህዝብ ተጋድሎ ወደ ስልጣን የመጣ ቢሆነም ህገመንግስታዊ ማሻሻያን ጨምሮ ፀረ አማራ የሆኑትን የመንግስት ፖሊሲዎች አስተካክላለሁ ብሎ ቃል ገብቶ የነበረ ቢሆንም በተግባር ግን አማራ ጠል መሆኑን ያስመሰከረዉ ጊዜ ሳይወስድ ነበር።

የብልፅግና መንግስት ከ ትህነግ ኢህአዴግ የወረሰውን የፌደራል እና የክልል ህገመንግስቶች ,ፖሊሲዎች እና መመሪያዎች ይዞ ቀጥሏል።ከ 50 በላይ በአማራ ህዝብ ላይ የዘር ፍጅት እንዲፈፀም ፀረ አማራነትን የሚቀሰቅሱ መፃህፍት አሳትሟል ።በምርምር መፅሄቶች ስም አማራ ጠልነትን ሰብኳል።በመንግስትነቱ በሚያስተዳድራቸው በኦሮምያ ቱሪዝም ቢሮ፣ በኦሮምያ ፕሬዝዳንት ፅ/ቤት፣ በኢትዮጽያ ፕሬስ ድርጅቱ ስር በሚታተሙ መፅሄትና ጋዜጦቹ በአማራ ህዝብ ላይ ለአመታት የቆየ የጥላቻ ዘመቻ አካሂዷል ።ከከፍተኛ እስከ ዝቅተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ፀረ አማረ ንግግሮች እና ትንኮሳዎች ተደርገዋል።

በተጨማሪም የብልፅግና መንግስት የአማራ ህዝብ የፖለቲካ ዉክልና እንዳይኖረው በማድረግ ዛሬ በአስር ሚሊዮኖች የሚቆጠረው ከአማራ ክልል ዉጭ የሚኖረው የአማራ ህዝብ ምንም አይነት የፖለቲካ ዉክልና የለዉም ።

ከመንግሥት የስራ ሀላፊነት ጠርጎ በማዉጣት አድሎአዊ አሰራርን በማስፈን በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎች በማፈናቀል ፣ በቢሊዮኖች የሚገመት የአማራን ህዝብ ሀብትና ንብረት በማውደም እንዲሁም ዘግናኝ የሆነ እንኳን ሊያዩት ሊሰሙት እንኳ የሚከብድ የዘር ፍጅት እንዲፈፀም አድርጓል ። ይህ የዘር ፍጅትበመላው ኢትዮጵያ በሶማሌ ፣ በኦሮሚያ ፣ በትግራይ ፣ በሲዳማ ፣ በቀድሞ የደቡብ ክልል ፣ በጋምቤላ እና በቤኒሻንጉል ክልሎች የተፈፀመ ነው ።
ለዚህም በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ የአይን ምስክሮች በተጨማሪ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ፣ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ጉባኤ ፣ በኢትዮጵያ የሰብአዊ መብቶች ላይ የሚሰሩ ጥምረት እንዲሁም አለም አቀፍ የሆኑት የተባበሩት መንግስታት ሰብአዊ መብት ኮሚሽን እና የሂውማን ራይትዎችን ዘገባዎች በማየት መረዳት ይቻላል ።

ጉዳዩን ሊከታተል ይችላል ተብሎ ይታሰብ የነበረው የብልፅግናው የአማራ ክልል መንግሥት ደግሞ እንኳን የአማራን ህዝብ ሊታደግ የገዛ ስልጣኑን የማያውቅ ፣ የፖለቲካ ነፃነቱን አሳልፎ የሰጠ እንዲሁም ከውሳኔ ሰጪነት ወደ ፈፃሚነት የወረደ ነው ። (ከክልሉ ውጪ ያሉ አማራዎች እንታገላቸዋለን እንጂ አንታገልላቸውም)ከማለት የደረሰ ሎሌ ነዉ።

በተደጋጋሚ ባጋጠሙ ጉዳዮችም ተፈትኖ የወደቀ ለምሳሌ በአማራ ልዩ ሃይል መፍረስ ፣ በፕሪቶሪያ ድርድር ፣ በሱዳን ወረራ ፣ በአጣዬ እና ሸዋሮቢት ፍጅት የአማራን ህዝብ መብት ማስከበር ያልቻለ ለተፈናቃይ ዱላ ለዘር ፈጂዎች ግን ካባ የሚሸልም ስብስብ ነው ።

የፌደራል መንግሥቱ ደግሞ ያለምንም እፍረት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፣የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነሩ ፣ አቃቢ ህጉ ፣ መርማሪው ፣ ደህንነቱ ፣ የፍርድ ቤት አስተዳደር በአጠቃላይ የአንድ ብሔር/ሀይማኖት አባላት በመሆን ህግን የማጥቂያ መሣሪያ በማድረግ የአማርን ሕዝብ ልጆች ያጠቃል ።

የአማራ ሕዝብ ከላይ በጠቀስኳቸው ምክንያት የሀገር ባለቤትነቱ የተወሰደበት ፣ ሀገሩን የተቀማ በመሆኑ ፣ ድርጊቱም ሥርአታዊና መንግሥታዊ ለመሆኑ የሚመሠክሩ በርካታ ማስረጃዎች ያሉ በመሆኑ የአማራ ህዝብ ከዚህ የህልውና አደጋ ለመውጣት መንቃት ፣ መደራጀትና እራስን ከጥቃቶች መከላከል ይገባዋል የሚል የፀና አቋም ያለኝ በመሆኑ ይሄንን ዘረኛ እና ነውረኛ አንባገነን ሥርዓት ለመጣል ትግል እንደሚያስፈልግ እምነቴ ነው ።

በጭብጦቹም ላይ

  • የሸዋ ፋኖን በማደራጀት በኩል የራሴን አስተዋፅኦ አድርጊያለሁ
    የአማራ ፋኖን ወደ አንድነት ለማምጣት ሲባል የተመሠረተው አመቻች ኮሚቴ ሰብሳቢ ሆኜ ሠርቻለሁ
    የአማራ ፋኖ ምክርቤት እንዲመሠረት የራሴን አስተዋፅኦ አድርጊያለሁ

አገሪቱ በተቀበለቻቸው ዓለምአቀፍ የሰብአዊ መብት ድንጋጌዎችና የብልፅግና መንግሥት እመራበታለሁ በሚለው ህገመንግስት በሰፈሩት ሰብአዊና እና ዲሞክራሲያዊ መብቶቹን መሰረት በማድረግ የህዝቤን ግፍ እና በደል ለማስቆም በህቡዕ ሳይሆን በአደባባይ ታግያለሁ።

*የሰራሁት በሙሉ በግልጽ በአደባባይ የተፈፀመ እንጂ ምንም አይነት ህቡዕ ድርጅት አቋቁሜ አልሰራሁ።

*በህቡዕ አደረጃጀት ተፈፀሙ የሚሉትን ተግባራት አላዉቅም።አልፈፀምኩም

የኢትዮጵያ ህዝብ የአማራን ህዝብ በደል በደንብ ይገነዘባል ብዬ አምናለሁ የኢትዮጵያ ህዝብ "የአማራ ህዝብ እንባ በዋንጫ"ቢሰጣቸዉ የማይጎፈንናቸዉን የብልፅግና ስርአት ቁንጮዎች በቃችሁ ሊላቸዉ ይገባል።

በተጨማሪም የአማራ ህዝብ የህልዉና ትግል ለነፃነት ለእኩልነትና ለፍትህ የሚደረግ ትግል እንጅ ጠላቶቻችን እንደሚያወሩት ሌላዉን ለመጨፍለቅ የሚደረግ ባለመሆኑ የኢትዮጵያ ህዝብ የአማራን ህዝብ የህልውና ትግል ደግፎ እንዲቆም እጠይቃለሁ።

አለማቀፉ ማህበረሰብም የአማራ ህዝብ እየተፈፀመበት ያለዉን የዘር ፍጅትና መፈናቀል ቸል በማለቱ በጣም እያዘንኩ ለአምባገነኑ መንግስት ጅምላ ጨራሽ ድሮዎኖች እና ተተኳሾችን የሚያቀብሉ አገራት ታሪክና እና እግዚአብሔር ፍርዱን ይሰጣችኋል እላለሁ።

አመሰግናለሁ ።
ኅዳር 5/2017 ዓ.ም

ዶ/ር ወንዶሰን አሰፋ

2 months ago
Save Amhara Fano💪✊💪🌍 🛰🦅💚💛❤️
2 months, 1 week ago

ኮሎኔሉ ተሸኘ!!

ሰሜን ምስራቅ እዝ ሁለተኛ ኮር ምክትል አዛዥ ኮሎኔል ጣዕመ በጀግኖቹ ተጋድሎ ተደመሰሰ!💪💪💪

We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated hace 3 semanas, 5 días

Last updated hace 3 semanas

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated hace 1 mes, 1 semana