Sαlαh ❲Fαith Defender❳ ⚒

Description
ይህ ቻናል ሙስሊም ባልሆኑ አካለት እሥልምና ላይ ለሚነሱ ጥያቄዎች ንፅፅራዊ ምላሾችን የሚሰጥ ነው።
Advertising
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated hace 3 semanas, 5 días

Last updated hace 3 semanas

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated hace 1 mes, 1 semana

1 month, 3 weeks ago

እንግዲህ ዛሬ ማታም በዚህ ርዕስ ይጠብቁን።

1 month, 3 weeks ago

□ ዲያቆኑ "ሳላህ ተሳዳቢ ነው" ይላል፣ እስኪ ይህን ይቃወም እንደሆነ እንየው።

https://vm.tiktok.com/ZGdYBSWSe/

1 month, 3 weeks ago

ዛሬም ማታ ከምሽቱ 3:00 ላይ እንገናኝ።

2 months ago

□ ጥያቄ ለክርስቲያኖች ? ምናልባት ከመለሱ ብዬ ነው።

https://vm.tiktok.com/ZGdFU7nVo/

2 months ago

□ የውይይት ጥሪ ለአክሊል (እስኪ ዲያቆኑ ከመጣ እንየው😉)

https://vm.tiktok.com/ZGdF2FnAv/

2 months ago

በድጋሚ የተፖሰተ😅

https://vm.tiktok.com/ZGdNqEf6E/

5 months, 1 week ago

በቲክቶክ መንደር ከሚታዩት ችግሮች መካከል አንዱ ያለ እውቀት እንዲሁ በስሜታዊነት ውይይት ማድረግ ነው። ለእምነት ጥብቅና መቆም ከቅንነት ቢሆንም ያለ እውቀትና ልምድ ሲሆን ግን ጭፍንተኝነት ነው። በዚህ መንገድ የሚደረጉ ውይይቶች ከሚያመጡት ትርፍ ይልቅ የሚያስከትሉት አሉታዊ ተፅዕኖዎች ስለሚበዙ በተቻለ አቅም እንዲህ የሚያደርጉ ሰዎችን በሞራል እና ጊፍት በማበረታታት ሌላ ጥፋት እንዲያስከትሉ ከማድረግ ይልቅ ቆጣ ብለው መጀመሪያ ስለ ንፅፅር እንዲያጠኑ ቢደረግ የተሻለ ይመስለኛል።

*® Sαlαh Responds ☑️***

5 months, 1 week ago

‟በስቃይ እና መከራዬ የሚያዝንልኝን አምላክ እንጂ በስቃዩ የማዝንለት አምላክ የለኝም።”

*® Sαlαh Responds ☑️***

5 months, 1 week ago

የሰማይ [ጀነት] ቋንቋ ?

ዐረብኛ በጀነት ውስጥ ግልጋሎት ላይ የሚውል ቋንቋ መሆኑን ቁርኣንም ሆነ ተዓማኒነት ያላቸው ሐዲሳት ፈጽሞ አይናገሩም። ይህ ማለት ዐረብኛ በሰማይ የሚገለገሉበት ቋንቋ መሆን አይችልም ማለት ሳይሆን የጀነት ነዋሪዎች የሚጠቀሙበት ቋንቋ መሆኑን የሚናገር ማስረጃ ስላልተገኘ በእርግጠኝነት እርሱ እንደሆነ የሚነገርበት ምንም ፍንጭ የለም። በእርግጥ ይህን ስናነሳ በብዙ የተሰራጫ አንድ ሐዲስ መጠቀሱ አይቀሬ ነው። እስኪ እንመልከተው:-

أحبّوا العربَ لثلاثٍ : لأنّي عَربيّ ، والقرآنُ عربيّ  وكلامُ أهلِ الجنةِ عربي
‟ዐረብን ለሦስት ምክንያቶች እወዳለሁ፣ አንደኛ እኔ ዐረብ ስለሆንኩ፣ ሁለተኛው ቁርኣን በዐረብኛ ስለወረደ፣ ሦስተኛው የጀነት ቋንቋ ዐረብኛ ስለሆነ።” (መጅሙዕ አል-ዘዋዒድ 10/55)

ይህ ሪዋያ ፈጽሞ ከነቢዩ የመጣ ንግግር ሳይሆን በእሳቸው ላይ በሐሰት የተወራ ፈጠራ  (Fabrication) ነው። ጥንታውያኑም ሆነ ዘመናዊያን ሊቃውንት በአጠቃላይ "መውዱዕ" موضوع ያሉት ዘገባ ነው። በእርግጥ ከፊሎቹ የደኢፍ ደረጃም ሰጥተውታል። ለምሳሌ ኢብኑል ጀውዚይ በመውዱዕ ሐዲሳት ስብስቡ ውስጥ አካተውታል [አል-መውዱዓት 2/292]፤ ኢማሙ ዞሀቢይ'ም "ፈጠራ" ነው ብለዋል [ሚዛን አል-ኢዕቲዳል 3/103]፤ አሽ-ሸውካኒይ'ም በተመሳሳይ "መውዱዕ" መሆኑን ገልጸዋል [አል-ፈዋዒድ አል-መጅሙዓህ ገጽ 221]፤ ታላቁ ሙሐዲስ ኢብኑ ሒባንም አንዳች መሰረት ያሌለው መውዱዕ መሆኑን በተደጋጋሚ ገልጸዋል [አል-መጅሩሒን 1/138]፤ ኢብኑ ሐጀር አል-አስቀላኒም በበኩላቸው ፈጽሞ የነቢዩ ንግግር ያልሆነ "መውዱዕ" መሆኑን ተናግረዋል [ሊሳን አል-ሚዛን 2/125]፤ አል-ጀውረቃኒም "መውዱዕ" የሆነ ሪዋያ እንደሆነ ገልጸዋል [ኢብጧል ወ-መናኪር 2/317]፤ ኢብኑል ቀይሰራኒም በተመሳሳይ ፈጠራ/መውዱዕ መሆኑን ጽፈዋል [ተዝኪራህ ገጽ 7]፤ ሸይኽ አልባኒም በሲልሲላቸው እና በደኢፍ አል-ጃሚዕ 173 ቁጥር ላይ «መውዱዕ» እንደሆነ ገልጸዋል።

ሸይኹል ኢስላም (ኢብኑ ተይሚያህ) በትንሳኤ ቀን አላህ ሰዎችን በየትኛው ቋንቋ ነው የሚያናግራቸው ? የጀነት ሰዎች በዐረብኛ ነው የሚግባቡበት ? የገሃነም ሰዎች ደግሞ በፋርስኛ ነው የሚያወሩት የሚባለው ነገር እውነት ነው ወይ ? ተብሎ ተጠየቀ።

الحمد لله رب العالمين لا يُعلم بأي لغة يتكلم الناس يومئذ ، ولا بأي لغة يسمعون خطاب الرب جل وعلا ؛ لأن الله تعالى لم يخبرنا بشيء من ذلك ولا رسوله عليه الصلاة والسلام ، ولم يصح أن الفارسية لغة الجهنميين ، ولا أن العربية لغة أهل النعيم الأبد
እንዲህ ብሎም መለሰ ❝..ለዓለማቱ ጌታ ምስጋና ይገባው፣ በዚያች ቀን ሰዎች የሚግባቡበት ቋንቋ የትኛው እንደሆነ አይታወቅም። የአላህንም ንግግር (ኹጥባ) በምን ቋንቋ እንደሚሰሙ አልተገለፀም። ምክንያቱም አላህም ሆነ መልዕክተኛው በዚያን ጊዜ በየትኛው ቋንቋ እንደምንግባበ አልነገሩንም፣ የገሃነም ሰዎች ቋንቋም ፋርስኛ ነው የሚለው ንግግር በማስረጃ የተረጋገጠ አይደለም። ዐረብኛ የጀነት ቋንቋ መሆኑም በማስረጃ የተደገፈ ንግግር አይደለም።
(?መጁሙዕ አል-ፈታዋ ቅፅ 4፣ ገጽ 299)

ስናጠቃልል:- የጀነትም ሆኑ የጀሀነም ሰዎች የሚግባቡበት፡ አላህም ሲያናግራቸው በየትኛው ቋንቋ እንደሆነ ፈጽሞ የተነገረ (የተገለጸ) ነገር የለም። ዛሬ ላይ ዓለማቀፍ በሆነው እንግሊዝኛ ይሁን ቁርኣን በተወረደበት ዐረብኛ ወይም አዲስ በሚፈጠር ቋንቋ ይሁን ምንም የመጣልን ትክክለኛ ትውፊት የለም። ስለዚህ በግምት የጀነት ቋንቋ ይሄ ነው ብሎ መናገር አግባብ አይደለም።

--------------------------------------------
®Sαlαh Responds ✍️
t.me/mahircomp123

We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated hace 3 semanas, 5 días

Last updated hace 3 semanas

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated hace 1 mes, 1 semana