kehulum lehulum bufe ከሁሉም ለሁሉም ቡፌ

Description
ትረካዎች፣ስሜትን ሰቅዘው የሚይዙ ልብ ወለዶች፣ጣፋጭና መሳጭ ታሪኮች፣ድንቃድንቅ ወሬዎች፣አስገራሚ እውነታዎች፣ታሪካዊ ሁነቶች፣ፍልስፍናዎች፣ከታዋቂ ሰዎች ጋር የተደረጉ ቃለ ምልልሶች፣ሳቅን የሚያጭሩ የኮሜዲ ስራዎች፣በተለያዩ ደራሲያን የተጻፉ የግጥም ስራዎች፣የዜማ፣የግጥም፣የኮሜዲ ባለተሰጦዎች ተወዳድረው የሚሸለሙበት ፕሮግራሞች የሚቀርቡበት። ሊንኩን ለማግኘት @lehulumbufe
የሚለውን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ
Advertising
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated hace 3 semanas, 5 días

Last updated hace 3 semanas

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated hace 1 mes, 1 semana

2 months, 2 weeks ago

#challenge #እንቀላቀል! አሪፍ ድምጽና ድንቅ ቅንብር ከድንቅ ዜማና ግጥም ጋር! በአጠቃላይ የተሳካለት ጥሩ ዓሬንጅ መንት ያለው ዓሪፍ  ዋው የሚያስብል  !  ሙዚቃ በቅርቡ ይለቀቃል! ታዲያ የዚህ ሙዚቃ ባለቤት ማነው ካላችሁ! እሸቱ እሳቱ ነዋ ዕንላችኋለን! እነኾ ሙሉ ትራኩ ዕስኪለቀቅ ድረስ; ቅምሻውን  እንካችሁ ብሏል! ታድያ እናንተም; ይህንን ወጣት ምርጥ ጀማሪ ሙዚቀኛ  ሙዚቃው ለብዙ ሰው እንዲደርስለት #ሼር በማድረግ  እንዲሁም የቲክቶክ አካውንቱን #ላይክ #ፎሎው በማድረግ እንድትተባበሩት ስንል በአክብሮት እንጠይቃለን! #link!

!https://vm.tiktok.com/ZMhCRNBft/

2 months, 2 weeks ago

#ወዳጄ_ሆይ_አዲስ_ቀንህን_ተቀበል!

ነግቷል፣ ወፎች ዝማሪያቸውን አሰምተዋል፣ ጸሐይ ከማደሪያዋ ተነስታ አንተ ወዳለህበት እየመጣች ነው።

ዛሬ አዲስ ቀንህ ነውና!

ዛሬ ወደ ሕልምህ አንድ እርምጃ የቀረብክበት፣ ከትናንት ስህተትህ ተምረህ የጎለበትክበት፣ እድሜህ ብቻ ሳይሆን ልምድና እወቅትህ ያደገበት

አዲስ ቀንህ ነው!

ተነስ፦

-እንኳን ደህና መጣህ ብለህ
-ቆራጥ መንፈስን ተላብሰህ
- በምስጋና ተሞልተህ

ተቀበለው!!
ቻናላችንን ለመቀላቀል! https://t.me/lehulumbufe የሚለውን ሊንክ ይጠቀሙ።
ሃሳብ አስተያየታችሁን ደግሞ! @lehulum_1bot ላይ አድርሱን።
ሼር ማድረጉ እንዳይረሳ!!!

2 months, 2 weeks ago

ይህን ያውቁ ኖሯል? **❖ ላሞች የላብ እጢ ያላቸው አፍንጫቸው ውስጥ ብቻ በመሆኑ የሚያልባቸው በዚሁ የሰውነት ክፍላቸው ነው፡፡

❖ ላም የሕንድ ቅዱስ እንስሳ ናት፡፡

❖ አንዲት ላም በቀን 180 ሊትር ምራቅ ታመነ ጫለች።

❖ ላም ደረጃን መውጣት እንጂ መውረድ አትችልም፡፡

  • አንዲት ላም በሕይወት ዘመንዋ እስከ 200.000 ጠርሙስ ወተት ትሰጣለች።**

የእስስት ምላስ የሰውነቷን ሁለት እጥፍ ይረዝማል፡፡ እስስት ሁለቱን አይኖቿን በአንድ ጊዜ በተለያየ አቅጣጫ ላይ ማሳረፍ ትችላለች። ለምሣሌ አንዱን ግራ አንዱን ቀኝ፣ አንዱን ላይ አንዱን ታች፤ አንዱን ግራ ጥግ አንዱን ቀኝ ጥግ ላይ ማሳረፍ ትችላለች፡፡ እስስት ሙሉ ለሙሉ አይኗ ቢጠፋም የቆዳዋ ቀለም የአካባቢውን የቀለም አይነት ተመስሎ መቀያየር ይችላል፡፡ ስለዚህ እስስቶች የአካባቢያቸውን ቀለም የሚያነቡት በአይናቸው ብቻ ሳይሆን በቆዳቸውም ጭምር ነው።ቻናላችንን ለመቀላቀል https://t.me/lehulumbufe በሚለው ሊንክ በኩል ገብተው ጆይን ይበሉ!
ለሀሳብ አስተያየት ደግሞ @lehulum_1bot የሚለውን ይጠቀሙ!

ሼር ማድረጉም እንዳይረሳ!!,

2 months, 3 weeks ago

ህይወት መሰናዶ።
ክፍል 24.
የመጨረሻ ክፍል።

ቻናላችንን ለመቀላቀል! https://t.me/lehulumbufe የሚለውን ሊንክ ይጠቀሙ።
ሃሳብ አስተያየታችሁን ደግሞ! @lehulum_1bot ላይ አድርሱን።
ሼር ማድረጉ እንዳይረሳ!!

2 months, 3 weeks ago

ቻናላችንን ለመቀላቀል! https://t.me/lehulumbufe የሚለውን ሊንክ ይጠቀሙ።
ሃሳብ አስተያየታችሁን ደግሞ! @lehulum_1bot ላይ አድርሱን።
ሼር ማድረጉ እንዳይረሳ!!

2 months, 3 weeks ago

የተወደዳችሁ የከሁሉም ለሁሉም ቻነላችን ቤተሰቦች፣ ላለፉት አያሌ ቀናት ያለ አንዳች መዛነፍ ከምሽቱ 3፣00 ሰዐት በኋላ ሲቀርብላችሁ የነበረው የታላቋ ደራሲት አጋታ ክሪስቲ ስራ የሆነው "ስውሯ ገዳይ" የተሰኘው መሳጭና ልብ አንጠልጣይ ልበወለድ ትረካ እነሆ ወደ መገባደጃው ደረሰ! እናም ከወዲሁ በትረካው ላይ ያላችሁን ስሜትና አስተያየት በግልጽነት ብትሰጡን ለቀጣይ ሂደቶች ይጠቅመናልና፣ የሚሰማችሁን ሁሉ በተመቻችሁ መንገድ፣ ቢቻል ደግሞ ሁሌም ከትረካችን ጋር አያይዘን በምናስቀምጥላችሁ የቦት አድራሻችን፣ ማለትም፣ @lehulum_1bot በኩል አስተያየቶቻችሁን፣ ምልከታችሁንና ስሜታችሁን ብታሳውቁን ደስ ይለናል። ለምትሰጡን አስተያየትም ከወዲሁ ልባዊ ምስጋናችንን ልናቀርብላችሁ እንወዳለን! አላማችን ሁሌም እየተዝናናን መማማር ነው!
ከሁሉም ለሁሉም የሁላችን የደስታና የነጻነት ጓዳ!

2 months, 4 weeks ago

ቻናላችንን ለመቀላቀል! https://t.me/lehulumbufe የሚለውን ሊንክ ይጠቀሙ።
ሃሳብ አስተያየታችሁን ደግሞ! @lehulum_1bot ላይ አድርሱን።
ሼር ማድረጉ እንዳይረሳ!!

2 months, 4 weeks ago
***🧔‍♀******🧔‍♀******🧔‍♀******🧔‍♀******🧔‍♀***! ***😱******😱******😱***! ስውሯ ገዳይ!

🧔‍♀🧔‍♀🧔‍♀🧔‍♀🧔‍♀! 😱😱😱! ስውሯ ገዳይ!
አጋታ ክርስቲ!
በከሁሉም ለሁሉም ቡፌ ቻነል ተዘጋጅቶ የቀረበ! @lehulumbufe!ክፍል 49! ዓርባ ዘጠኝ!

አንዱ የህንድ ልጅ ብቻ ቀረ። ከዚያስ መጨረሻው እንዴት ነበር? ለማስታወስ ሞከረች። በሯ ላይ ደረሰችና ከፍታ ገባች። ክፍሏ ውስጥ ጣሪያ ላይ የተንጠላጠለው ሜንጦ ትዝ አላት። ቀና ብላ ስታየው ገመድ ተንጠልጥሎበታል። ከገመዱ ስር ደግሞ አንድ ወንበር ነበር። ወንበሩን ከኋላ ወደ ጎን ትገፋዋለች። ሁጎ የሚፈልገው ያንን ነበር።
ወዲያውኑ የግጥሙ የመጨረሻ ስንኝ ትዝ አላት!
የተረፈውም ልጅ ራሱን አነቀ!
ትንሹ የቻይና አሻንጉሊት ከእጇ ላይ አምልጧት እርሷም ወደ ፊት ተንደረደረች! ቀዝቃዛው እጅ፣ የሴሪል እጅ አንገቷን ነካት!
“ወደ ድንጋዩ ዋኝ ፡ ሰሪል!”
ቀስ ብላ ወንበሩ ላይ ቆመች! የተንጠለጠለውን ገመድ አስተካክላ አንገቷ ላይ አስገባችው! ሁጎ ቁጭ ብሎ እያያት ነበር! ወዲያውኑም ወንበሩን በእግሯ ወርውራ ጣለችው!
የስኮትላንድ ያርድ ፖሊስ ምክትል ኮሚሽነር የሆኑት ሰር ቶማስ ሌጌ በቁጣ እና ባለማመን ነበር የሚናገሩት!
“ሁሉም ነገር የማይታመን ነው!” መርማሪ ሜይን በትህትና ነበር የሚመልስላቸው። “አዎን ጌታዬ ፡ የማይታመን ነው!” “አስር ሰው ደሴቱ ላይ ሞቷል እያልክ ነው? ምንም ስሜት አልሰጠኝም!” አሉ ሰር ቶማስ። “አስሩም ሞተዋል ጌታዬ!” “የሆነ ሰው ገድሏቸዋል! ካልሆነማ እንዴት አስሩም?” “ችግሩ እንዴት እንደሆነ አለማወቃችን ነው ጌታዬ!”
“ለመሆኑ የዶ/ሩ ምርመራ ምን ያሳያል?” “ምንም አያሳይም። ዋርግሬቭ እና ሎምባርድ በጥይት ሲገደሉ ወ/ሮ ኤሚሊ እና ማሪስተን ደግሞ በሳይናይድ መርዝ ሞተዋል። ወ/ሮ ሮጀርስን ከመጠን ያለፈ የእንቅልፍ ኪኒን የገደላቸው ሲሆን፣ ባለቤታቸው ሮጀርስ ደግሞ በመጥረቢያ ተፈልጦ ሞቷል። ብሎርም አናቱን ተፈንክቶ የሞተ ሲሆን፣ ዶ/ር አርምስትሮንግ ደግሞ ውሃ ውስጥ ተዘፍቆ ሞቷል። ወ/ሪት ቬራ ታንቃ ሞታለች።” በማለት መርማሪው ለረዳት ኮሚሽነሩ ገለፀላቸው።
“የሚገርም ነው! ለመሆኑ ከስቲክልሃቨን መንደር ነዋሪዎችስ ምንም አላገኘህም? መቼም የሆነ ነገር ሳያዩ አይቀርም።” “ነዋሪዎቹ ምስኪን አሳ አጥማጆች ናቸው ጌታዬ። የሰሙት ነገር ቢኖር ደሴቷን ኦውን የተባለ ቱጃር እንደገዛት ብቻ ነው።”
“ለመሆኑ የደሴቱን ሽያጭ እና ድግሱን ያመቻቸው ሰው ማን ነበር?” “አይዛክ ሞሪስ የተባለ ሰው ነው ጌታዬ።” መርማሪ ሜይን መለሰላቸው። “ስለ ሞሪስ የሚታወቅ ነገር አለ?” “ከሶስት አመት በፊት ከቤኒቶ ጋር በመተባበር የማጭበርበር ወንጀል ላይ የተሳተፈ ቢሆንም ማረጋገጫ ግን አልተገኘበትም። በዚያ ላይ በአደንዛዥ እፅ ዝውውር የሚጠረጠር ነበር። ነገር ግን ለዚህም ማረጋገጫ የለንም።”
“ለምን ስለ ደሴቱ አትጠይቁትም?”
“አንችልም! ጌታዬ፡፡ ሞሪስ ሞቷል።
“የደሴቷን ሽያጭ እንዴት ነበር ያስፈፀመው?” “ግዢውን የፈፀመው ራሱ ሲሆን ስሙን ላልጠቀሰው ሶስተኛ ወገን ነበር በውክልና የተዋዋለው።” “የሂሳብ አያያዙ ላይስ የሆነ ፍንጭ የለም?” መርማሪ ሜይን ፈገግ ብሎ፣ “ጌታዬ ሞሪስ ስህተት የሚሰራ ሰው አይደለም! ከቤኒቶ ጋር በተያያዘ ከፍተኛ የሂሳብ ምርመራ አድርገንበት ምንም አላገኘንም።” በማለት አረጋገጠላቸው። በመቀጠልም፣ “ሞሪስ ነበር ስቲክልሃቭን በማምራት የደሴቷ ባለቤት አቶ ኦውን ራሱ መሆኑን የተናገረው።” ለነዋሪዎቹ ደሴቱ ላይ ለአንድ ሳምንት የሚዘልቅ ድግስ እና የመዝናኛ ውድድር እንደሚደረግ ተናግሮ ነበር።” “ነዋሪዎቹ ምንም አልጠረጠሩም ታዲያ?” ረዳት ኮሚሽነሩ ተገርመው ጠየቁት። መርማሪው ፈገግ በማለት ነበር የመለሰላቸው። ጌታዬ፣ የህንድ ደሴት ከኦውን በፊት የወጣቱ ኤልመር ሮብሰን ንብረት ነበረች። ወጣቱ በርካታ ድግስ እና ጨዋታ በማድረጉ ነበር በመንደሩ ነዋሪ የሚታወቀው። ስለዚህ በደሴቷ ላይ ምንም ቢደረግ የመንደሩ ነዋሪዎች ጨዋታ ነው የሚመስላቸው።” 
ረዳት ኮሚሽነሩ በተሰጣቸው ማብራሪያ አልረኩም ነበር። መርማሪ ሜይንም ገለፃውን ቀጠለ። “ፍሬድ ናርኮት የተባለ ሰው ነበር ሟቾቹን ወደ ደሴቷ ያደረሳቸው። ከቀድሞ የወጣቱ ኤልመር ሮብሰን እንግዶች የተለዩ እንደነበሩ ተናግሯል።” “ለመሆኑ መቼ ነበር ወደ ደሴቷ የነብስ አድን የሄደው?” በማለት ረዳት ኮሚሽነሩ ጠየቁ።
ቻናላችንን ለመቀላቀል https://t.me/lehulumbufe በሚለው ሊንክ በኩል ገብተው ጆይን ይበሉ!
ለሀሳብ አስተያየት ደግሞ @lehulum_1bot የሚለውን ይጠቀሙ!
ሼር ማድረጉም እንዳይረሳ!!

2 months, 4 weeks ago
ሰው በራሡ ሲፈርድ,

ሰው በራሡ ሲፈርድ,
የጌታን ደግነት የእግዚኄር መልክ ምስል,

የፍጡር ሹም ስልጣን የዕጁን ጥበብ ኀምሳል,

ሠው ኆኖ መፈጠር መበደል ይመሥል,

በሠው ልክ ቀለም ሠው ላለመኆን ሲል,

ማርፈጅያ ሸለቆ መሸሸግያ ገደል,

የፍሪአትን ዋሻ ጥጉን ሲያደላድል,

ባላወቀ ምላስ ባልተገራ ፊደል,

ሠውን ከሰወኛ ነጥሎ ለመጣል,

ሠው መኆን እዳነው ብሎ ይተርታል..
ተጻፈ በኅብረቃል ኅብሩ!
ቻናላችንን ለመቀላቀል https://t.me/lehulumbufe በሚለው ሊንክ በኩል ገብተው ጆይን ይበሉ!
ለሀሳብ አስተያየት ደግሞ @lehulum_1bot የሚለውን ይጠቀሙ!

ሼር ማድረጉም እንዳይረሳ!! kehulum lehulum bufe ከሁሉም
ለሁሉም ቡፌ

3 months ago
**𝐦𝐞𝐧𝐞𝐭𝐬'𝐢𝐫𝐢 iS BACK !** *****😎***** **[ …

𝐦𝐞𝐧𝐞𝐭𝐬'𝐢𝐫𝐢 iS BACK ! *😎* [ 𝐌𝐞𝐧𝐞𝐭𝐬'𝐢𝐫𝐢 𝐩𝐫𝐨𝐦𝐨𝐭𝐢𝐨𝐧]

መመዝገብ የምትፈልጉ ማሟላት ያለባቹ መስፈርት .....!** ግዴታ ከ 1K በላይ መሆን አለበት ቻናላቹ !**ከ 1K በታች አትምጡ 🙏*😛* ይሄንን ያሟላ በ @menetser21 በኩል ያናግረኝ!**

We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated hace 3 semanas, 5 días

Last updated hace 3 semanas

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated hace 1 mes, 1 semana