ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated hace 3 semanas, 5 días
Last updated hace 3 semanas
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot
🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹
Last updated hace 1 mes, 1 semana
ሁሉም የመዳረሻ መንገዱን ይዞ እየሄደ ነው።
ባለመናወጽ ቁሞ የሚጠብቅ ምንም ፍጡር የለም።
በዚህም የፍጡርን አቅምና መጠን እንረዳበታለኝ።
ፍጡር ሁኖ በባሕርዩ ባለማለፍ ጸንቶ መኖር የሚችል ምን ነገር አለ?
እስከ ጊዜው ድረስ ግን በመተካካት ትዕዛዝ እየተውተረተረ ተፈጥሮውን ያስቀጥላል።
መተካካተን በትክክለኛው መንገድ በማስቀጠል ትዕዛዝ ግን የተፈጥሮ እና የተከሥቶ ሀላፊነት አለብን።
ይህ ቀን ይለፍ ዝም በል።
የብዙዎች ምክር ይሄ ቀን ይለፍ ዝም በል።ዝቅ ያለ እና ዝም ያለ ነው ይህንን ቀን የሚያልፈው? ይላሉ።
ቀኑ እስሲያልፍ እድሜ ያልፋል፣ታሪክ ያልፋል፣ወገን ያልፋል፣ኦርቶዶክሳውያን ያልፋሉ፣የክርስትና አሻራዎች ያልፋሉ፣እውነት ራሷ በውሸት ተተክታ እውነት መስላ ታልፋለች፣..እና ማን በመሠከራት እውነት ላይ ነው ነገን መረዳት የምንችለው? ሲባሉ።
እንግዲህ ነገርሁህ ለአንተ ብየ ነው ይላሉ።
ያለ እውነት፣ያለ ክርስትና፣ያለ ታሪክ፣..በምድር ላይ ብዙ ዓመት ኑሮ እንጀራ ለመብላት ሲባል ብቻ ዝም ማለት አይከብድም?
በመቅለስለስ ብቻ በእግዚአብሔር አምሳል የተፈጠርሁ ክህደትና ሃይማኖትን የምለይ ፍትሀዊ ሰው ነኝ ማለት ይቻላል?
"የኢየሱስ ሕይወት ደግሞ በሥጋችን ይገለጥ ዘንድ ሁልጊዜ የኢየሱስን መሞት በሥጋችን ተሸክመን እንዞራለን።የኢየሱስ ሕይወት ደግሞ በሚሞት ሥጋችን ይገለጥ ዘንድ እኛ ሕያዋን የሆንን ከኢየሱስ የተነሣ ዘወትር ለሞት አልፈን እንሰጣለንና።ስለዚህ ሞቱ በእኛ ይሠራል።፪ቆሮ.፬፥፲-፲፪ ያለው ቃል እንዴት ይተረጎማል?
ፍርሀትን በመላበስ፣እውነትን በማድበስበስ፣ፊት በመቀለስ፣ከንፈር በማለስለስ፣አስመሳይነት በመላበስ የክርስትና አረዳድና ሕይወት ይገለጣል?
በምድር ላይ የማይለመድ ነገር ምን አለ?
በክርስትናችን ምክንያት በታወጀብን አንዲት ምድራዊት ሕይወትን የሚነጥቀን ሞት እንኳን ተለምዶ ተራ ልምድ ሆነ።
ከሁሉም በላይ ነውርን፣ ጥፋትን፣ ኃጢአትን፣ ሆዳምነትን፣ ማስመሰልን፣ ሸንጋይነትን፣ ዓለማ ቢስነትን፣ እውነትን መርሳትን፣ ማመቻመችን ... መለማመዳችን ነው የሚያስፈራው።
ያልለመድነው የጥፋት አይነት የት ይገኛል?
መልካሙን ጥንታዋውን ልምዳችንን እየረሳን የማይጠቅመንን ልምድ ከተላበሰነ በጣም ያስፈራል።
የጥፋት ልምድ መልካሙን ሁሉ ሳያጠፋ አይቀርም። ጥፋት ልምድ ከሆነ አጥፊነቱን ማንስ ያውቅበታል?
ፍርሀት ትንሣኤ ሙታንን አለማመን ነው።
ትልቁ ኑፋቄ ፍርሀት ነው።ጴጥሮስ በዕለተ ዓርብ በልቡ አምኖ በአፉ ጌታውን አላውቀውም ብሎ የካደው ስለፈራ ነው።ጴጥሮስ የፈራለታ ከሀዲ ነው።ጴጥሮስ የጨከነለታ ሃይማኖተኛ ነው።እየፈሩ አባት መሆን አይቻልም ከሀዲ መሆን ግን ይቻላል።እየጨከኑ ግን ከክርስቶስ ፍቅር ማን ይለየኛ? በማለት አባት መሆን ይቻላል።የነበረን ያጣነው የሚያስፈልገን የረሳነው ምንድን ነው?
እንደ ይሁዳም በአፍ እያመኑ በተግባር መካድ ሐዋርያ አያደርግም።ሆዴ ይሙላ ደረቴ ይቅላ ብሎ ጌታውን የመሸጥ ተልእኮ ነው እንጂ።እኛን የደረሰብን የቱ ነው?
አሁን አሁን እንደ ክርስቶስ ለምእመናንን ቤዛ ሁኖ ፊት ለፊት እነሆ መንገዱ ብሎ ያለ ፍርሀት በሃይማኖት የሚመራ ሕያው አባት ማግኘት መታደል ነው።
ሕያው አባትነት መስቀላዊ መሪነት ነው።መሪነት ደግሞ ሥልጣን ሲይሆን የሕይወት ለውጥን የሚሻ አስተሳስብ ነው።
የሕይወት መሪነት ደግሞ ሁነትን የመረዳት እና ስለ በጎቹ ቤዛ የመሆን ግብር ነው
ለበግቹ መቅደም ደግሞ አምላካዊ ምግብን ያለሀኬት የማስቀጠል ጴጥሮስነትን የመትከል ተግባር ነው።
ጴጥሮስነትን መትከልም ሙሴነት ነው እየተጎዱ ማብራት እየተቸገሩ መሥራት ያልተለየው ግብር ይህ ነውና።
ፍጹማዊ መሪነት ክርስቶስ ነው፦እየተሰቀሉ ማሳየት።ሳይሰቀሉ ክርስቶስነት ሳይቀበሩ ትንሣኤ የለም።
ፍርሀት የሸበበው ሰውነት ወንጌላዊ ክርስቶሳዊ አይደለም።በክብር ለመነሣት መከራ መቀበል አይገባምን? "ከሰው ይልቅ ለእግዚአብሔር ልንታዘዝ ይገባል።"የሐ ሥራ.ምዕ.፭፥፳፱
ፍርሀት ትንሣኤ ሙታንን አለማመን ኑፋቄ ነው።
ትልቁ ኑፋቄ ፍርሀት ነው።ጴጥሮስ በዕለተ ዓርብ በልቡ አምኖ በአፉ ጌታውን አላውቀውም ብሎ የካደው ስለፈራ ነው።ጴጥሮስ የፈራለታ ከሀዲ ነው።ጴጥሮስ የጨከነለታ ሃይማኖተኛ ነው።እየፈሩ አባት መሆን አይቻልም ከሀዲ መሆን ግን ይቻላል።እየጨከኑ ግን ከክርስቶስ ፍቅር ማን ይለየኛ? ማለት ይቻላል።የነበረን ያጣነው የሚያስፈልገን የረሳነው ምንድን ነው?
እንደ ይሁዳም በአፍ እያመኑ በተግባር መካድ ሐዋርያ አያደርግም።ሆዴ ይሙላ ደረቴ ይቅላ ብሎ ጌታውን የመሸጥ ተልእኮ ነው።እኛን የደረሰብን የቱ ነው?
እንደ ክርስቶስ ለምእመናንን ቤዛ ሁኖ ፊት ለፊት እነሆ መንገዱ ብሎ ያለ ፍርሀት በሃይማኖት የሚመራ ሕያው አባት ማግኘት መታደል ነው።
ሕያው አባትነት መስቀላዊ መሪነት ነው።መሪነት ደግሞ ሥልጣን ሲይሆን የሕይወት ውጥን የሚሻ አስተሳስብ ነው።
የሕይወት መሪነት ደግሞ ሁነትን የመረዳት እና ስለ በጎቹ ቤዛ የመሆን አስተሳስብ ነው
ለበግቹ መቅደም ደግሞ አምላካዊ ምግብን ያለሀኬት የማስቀጠል ጴጥሮስነት የመትከል ተግባር ነው።
ጴጥሮስነትን መትከልም ሙሴነት ነው እየተጎዱ ማብራት እየተቸገሩ መሥራት ያልተለየው ግብር።
መሪነት ክርስቶስ ነው፦እየተሰቀሉ ማሳየት።ሳይሰቀሉ ክርስቶስነት ሳይቀበሩ ትንሣኤ የለም።
ፍርሀት የሸበበው ሰውነት ወንጌላዊ ክርስቶሳዊ አይደለም።በክብር ለመነሣት መከራ መቀበል አይገባምን? "ከሰው ይልቅ ለእግዚአብሔር ልንታዘዝ ይገባል።"የሐ ሥራ.ምዕ.፭፥፳፱
ፍርሀት ትንሣኤ ሙታንን አለማመን ነው።
ትልቁ ኑፋቄ ፍርሀት ነው።ጴጥሮስ በዕለተ ዓርብ በልቡ አምኖ በአፉ ጌታውን አላውቀውም ብሎ የካደው ስለፈራ ነው።ጴጥሮስ የፈራለታ ከሀዲ ነው።ጴጥሮስ የጨከነለታ ሃይማኖተኛ ነው።እየፈሩ አባት መሆን አይቻልም ከሀዲ መሆን ግን ይቻላል።እየጨከኑ ግን ከክርስቶስ ፍቅር ማን ይለየኛ? ማለት ይቻላል።የነበረን ያጣነው የሚያስፈልገን የረሳነው ምንድን ነው?
እንደ ይሁዳም በአፍ እያመኑ በተግባር መካድ ሐዋርያ አያደርግም።ሆዴ ይሙላ ደረቴ ይቅላ ብሎ ጌታውን የመሸጥ ተልእኮ ነው።እኛን የደረሰብን የቱ ነው?
እንደ ክርስቶስ ለምእመናንን ቤዛ ሁኖ ፊት ለፊት እነሆ መንገዱ ብሎ ያለ ፍርሀት በሃይማኖት የሚመራ ሕያው አባት ማግኘት መታደል ነው።
ሕያው አባትነት መስቀላዊ መሪነት ነው።መሪነት ደግሞ ሥልጣን ሲይሆን የሕይወት ውጥን የሚሻ አስተሳስብ ነው።
የሕይወት መሪነት ደግሞ ሁነትን የመረዳት እና ስለ በጎቹ ቤዛ የመሆን አስተሳስብ ነው
ለበግቹ መቅደም ደግሞ አምላካዊ ምግብን ያለሀኬት የማስቀጠል ጴጥሮስነት የመትከል ተግባር ነው።
ጴጥሮስነትን መትከልም ሙሴነት ነው እየተጎዱ ማብራት እየተቸገሩ መሥራት ያልተለየው ግብር።
መሪነት ክርስቶስ ነው፦እየተሰቀሉ ማሳየት።ሳይሰቀሉ ክርስቶስነት ሳይቀበሩ ትንሣኤ የለም።
ፍርሀት የሸበበው ሰውነት ወንጌላዊ ክርስቶሳዊ አይደለም።በክብር ለመነሣት መከራ መቀበል አይገባምን? "ከሰው ይልቅ ለእግዚአብሔር ልንታዘዝ ይገባል።"የሐ ሥራ.ምዕ.፭፥፳፱
አስበው ሊያደነቁሩን ከፈለጉ አስበን እናስተምር።
በማይሆን የወሬ ተስፋ ተሞልተን ነገን ከምንረሳው ልጆች ላይ እየሠራን ብንጠብቅ ይሻላል።
አሁን አማራጭ የሌለው ትምህርት ቤታችን አብነት ነው።ስለሆነም ልጆች ዳግም ከፊደልና ከቁጥር እንዲወለዱ የዕውቀት ማዕከል አድርገን እናስተምር።
ትልቁ ጽድቅ ትውልድን በተረካቢነት መተካት ነው።እኛ ከላይኞች አባቶቻችን የተቀበልነው እንደ ሚገባ ጠብቀን ለሚተካው ትውልድ ካላስረከብነው የጌታውን ወርቅ የቀበረው ሰነፉ አገልጋይ መሆናችን ነው።
እኔ የነገ አደራ አለብኝ የሚል መልካም አሳቢ ሰው ሁሉ ሊጨነቅበት የሚገባው ጉዳይ ቢኖር ነገን ተረክበው አደራቸውን የሚጠብቁ ሕፃናት ናቸው።
ከአብነት ትምህርቱ ጋራ ጎን ለጎን ሳይነጣጠሉ፦
፦የሀገር ታሪክ
፦የጽሑፍ ትምህርት
፦የሀገር ባህልና ወግ
፦የጨዋ ደንብ(ሥነ ሥርዓት)
፦የሥነ ምግባር ትምህርት
፦ትምህርተ ግብርና፦ተግባረ እድ፦አገልግሎት፦ሀገርና ሃይማኖት፦ቅርስ እና የሀገር ሀብት ጥበቃ፦የባለውለታ አባቶች ታሪክ፦ትምህርተ ሰማዕትነት.. የመሳሰሉ ትምህርቶች ቢሰጣቸው ጥሩ ነው።ስለማያቁት እና ስላልተነገራቸው ሀገር ሃይማኖት ተረካቢ ሊሆኑ አይችሉም።ይገባቸዋል የምንለውን በጎ ትምህርት ሁሉ ለልጆቻችን እናስተምር።ማን ያውቃል ወይምኮ በዚሁ መንገድ ትናንት ያጣነውን የአባቶቻችንን ቅዱስ ጥበብ እናገኘው ይሆናል።
ልጅን አለማስተማር ግን የህሊና ወንጀል ነው።
"ትምህርት የማያልቅ ምርት ነው"
ልጅን አለማስተማር ትልቅ የሕይወት ዕዳ ነው።
በሀገራችን በተለያዩ አካባቢዎች ሕፃናት ትምህርት ካቆሙ ዓመታት እየተቆጠሩ ነው።ይሄ ደግሞ ያልተማረ ኋላ ጀርባ ሳያል የሚገዣ ዜጋ እንዲኖር ብሎ ሥርዓቱ የፈጠረው አእምሮን የማቀንጨር ሥርዓታዊ ፕሮጀክት ነው።
ስለሆነም የትምህርት በሮች ከተዘጉብን የማይዘጉ የአብነት በሮችን መክፈት አማራጭ የሌለው መፍትሄ ነው።
የማያነቡ የማይጽፉ ዜጎች እንዳይኖሩ የኔታዎቻችን እንደ ጥንቱ እንደ ጧቱ መፍትሄ ሊሆኑን ይገባል።
ልጅን ወደ የኔታዎች ሰዶ አለማስተማር ደግሞ ወንጀል ሁኖ በማኅበረ ሰቡ ዘንድ መቀስቀስ አለበት።
በእጃቸው ያለውን ትምህርት ቤት ከዘጉብን በእጃችን ያለውን ነባር አማራጭ እንጠቀም።
የትውልድ ጉዳይ ያገባኛል የምትሉ ሁሉ ልጆቻችሁን የጎረቤት ልጆችን መላው ለትምህርት የደረሱ ልጆችን ሴት ወንድ ሳትሉ ወደ አብነት እንዲገቡ አነሣሡ።
የነገ ሀገር፣የነገ ሃይማኖት በተሠሩ አእምሮዎች ውስጥ ትገኛለች።
የዘራነውን የምናጭደው የጨድነውን የምናመርተው ዘሬ ነው።
ያልዘራነው ማጨድ ያላጨድነውን መሰብሰብ ግን ጉም አፋሽነት ዖፍ ነዳሽነት ነው።
ሁሉም አልፎ ዛሬ ታሪክ መሆኑ ላይቀር ነገር መርሳት የለብንም።ነገ ደግሞ አሁን ያሉን ሕፃናት እና የሚተኩት ትውልዶች ናቸው።
የሰው ያለሽ ከማለት በአብነት ትምህርት ቤቶቻችን በኩል የተማረ ሰው እንሥራ።
በምድር ላይ የነገ ተረካቢዎችን ከማፍራት የተሻለ ምንም ትሩፋት የለም።
ነገ ይታያችኋል ወይ???
ያለ ትምህርት ነገ ምንድን ነው?
ነገ የማን ነው?
በደንብ እናስብ በደንብ በቅንነት እንነት እንሥራ።
ትናንት የዛሬ ውጤት ነው።ዛሬ ደግሞ የነገ ምርት ነው።ስለ ነገ መጨነቅ ቅዱስ ሀልዮ ነው።
ሁሉም ሕጻናት ወደ አብነት ይሂዱና ነገን እንሣልባቸው።አለማስተማር ግን የአስተሳስብ ዕዳ መሆን አለበት።
በሁሉም አካባቢዎች አብነት መማር ዕሴት ባህል እስኪሆን እንሥራ።የሰላም ዘመን እስኪመጣ እጃችን ላይ ባለን እንትጋ።
....“በአባ ቢሾይ ገዳም ከአባቶች መነኰሳት ጋር ተገናኘሁ። በዚያም የቦታውን መንፈሳዊነትም ሆነ የእንግዳ ተቀባይነታቸውን ነገር፣ እንዲሁም ዘርፈ ብዙ የሆነውን ተግባራቸውንና ትምህርታቸውን ተመለከትሁ፤ ሆኖም ግን ካየሁት ሁሉ አንዱንም እንኳ እንደሚገባ አድርጌ አሟልቼ ልገልጸው አልችልም። ሆኖም የክርስትና ገዳማዊ ሕይወት በታሪካችን ውስጥ የነበረውን ሚና መዘንጋት ለእያንዳንዱ ዐረብ ታላቅ ኪሳራ የመሆኑ ነገር ላይ ትኩረት ማድረግ እንደሚገባ ማስተዋል ተገቢ መሆኑን ለራሴ ተረድቻለሁ። በእ*ስልምና ሃይማኖት ውስጥ ምንኲስናና ገዳማዊ ሕይወት የሚባል ነገር አለመኖሩን ማሰብ ውስጥን የሚረብሽና የሚያሳዝን ነገር ነው።”
መናንያን በሥራ የሻከሩ እጆች ያሏቸው ብቻ ሳይሆኑ ከርኩሰትና ከነውር ንጹሕ የሆነች ነፍስ ትኖራቸው ዘንድ የሚጋደሉ እውነተኛ ጀግናዎችና ትክክለኛ ፈላስፋዎች ናቸው። ከመብላትና መጠጣት፣ ከማግባትና ከመጋባት ባሻገር ወዳለው ሰማያዊ ሕይወት የሚያመለክቱ አቅጣጫ ጠቋሚዎችና ዐዋጅ ነጋሪዎች ናቸው።
ስለሆነም ሰው ያልደረሰበትን ነገር በመሰላል ወጥቼ ልንቀፍ ማለት ተገቢ አይደለም! ሊታገሡት የሚገባም አይደለም! በዕድሜያቸውም ሆነ በእውቀታቸው ታዳጊ የነበሩት የ1950ዎቹና 60ዎቹ ትውልዶች በኦርቶዶክስ-ጠል መምህራን የተሞሉት ጥላቻ ዛሬ ያፈራውን መራራ ፍሬ እያየን፣ የእነዚያ የመንፈስ ልጆች የሆኑ በዕድሜ እንኳ ባይሆን በአእምሮ ሕፃናት የሆኑ ኦርቶዶክስ-ጠሎች ተገቢ ያልሆኑ ነገሮችን ሲናገሩና ሲጽፉ እያዩ ኦርቶዶክሳውያን ዝም ማለት አይችሉም።
ኦርቶዶክሳውያን፣ ገና ለገና ያሻንን ብንላቸው ለክፉ አይሰጡንም የሚሉ የፈሪዎችና የአጎብዳጆች የብዕር መፈተኛና የአፍ ማሟሻ መሆንን መቀበል ከማይችሉበት የመጨረሻ ደረጃ ላይ ደርሰዋል። ስለዚህ ወደ ላይ አያዳልጣችሁ! የሚታየውን ብቻ ሳይሆን የማይታየውን መፍራትም ብልህነት ነው!
በዲ/ን ያረጋል አበጋዝ
ወደ ላይ አያዳልጣችሁ!
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስን አንድ ጨዋነት የራቀው ሰው ሰደባቸው አሉ። በኋላ ግን ጸጽቶት እግራቸው ላይ ወድቆ “ይማሩኝ፣ አጥፍቻለሁ፣ አድጦኝ ነው” ሲላቸው፣ እርሳቸውም “ታዲያ ወደ ታች ያድጣል እንጂ ወደ ላይ ያድጣል እንዴ?” አሉት ይባላል።
ወደ ላይ የሚያድጣቸውን ብዙ ሰዎች እያየን ነው። ሰሞኑን ዘነበ ወላ የተባለ ግለሰብ፣ ሊነቅፈው ቀርቶ ሊረዳውና ሊያደንቀው እንኳ እጅግ የሚበዛበትን የምናኔ ሕይወት ለመንቀፍ ሲሞክር ሰምተናል (የተነገረው በሕንድኛ ወይም በታይ ቋንቋ አይደለም!)። ይህን የመሰሉ እናውቃለን ከሚሉ አላዋቂዎች ወይም ጭፍን ጥላቻ ካሳወራቸው ሰዎች በኦርቶዶክሳዊነት ላይ በተለያየ መንገድ የሚሰነዘሩ ጥቃቶች እየበዙ መምጣታቸው ጉዳዩን እንደ ቀላል ለማለፍ የማይቻል ያደርገዋል። ዛሬ ካለው የተከማቸ ኦርቶዶክስ-ጠልነት ያደረሱን ከ20ኛው መ/ዓ መጀመሪያ ጀምሮ ኦርቶዶክስ ጠል በነበሩ ግለሰቦችና ቡድኖች ይሰነዘሩ የነበሩ የጥላቻ ንግግሮችና ጽሑፎች መሆናቸውን ልብ ይሏል።
ምናኔያዊ ሕይወት፣ ከትንሣኤ በኋላ የምናገኘውን እንደ መላእክት የመሆንን ሕይወት፣ በዚህ ዐለም ገንዘብ የማድረግ ሕይወት ነው። “በትንሣኤስ እንደ እግዚአብሔር መላእክት በሰማይ ይሆናሉ እንጂ አያገቡም አይጋቡምም” እንዳለ ጌታችን። ማቴ. 22፡30 መላእክት በተፈጥሯቸው እንደማያገቡና እንደማይጋቡ ሁሉ፣ ከትንሣኤ በኋላ ደግሞ ለሰዎችም ማግባትና መጋባት እንደማይኖር ሁሉ፣ መላእክት ዛሬ የሚኖሩትን፣ የሰው ልጆች ደግሞ ከሞት በኋላ የሚያገኙትን ሕይወት መናንያን ገዳማውያን በአሁኑ ሕይወት ይኖሩታል። እንደዚሁም ምናኔያዊ ሕይወት አዳም ከመበደሉ በፊት የነበረው ሕይወት ምን ይመስል እንደ ነበረ በመስታወት የሚያሳይ ነው፣ ጌታችን የሰጠውን ሕይወት በምልዓት የሚያሳይ ነው።
ምናኔያዊ ሕይወት በክርስትና ውስጥ ያለውን እጅግ የገዘፈና ዘርፈ-ብዙ የሆነ ነገረ-ሃይማኖታዊና መንፈሳዊ ፋይዳ ለጊዜው ብናቆየው እንኳ፣ ክርስቲያናዊ ገዳማት ለሰው ልጆች ያበረከቷቸው ኢኮኖሚያዊ፣ እውቀታዊና ታሪካዊ ጠቀሜታዎች እጅግ በጣም ብዙ ናቸው። ጥቂቶቹን እንኳ ብናስታውስ፤ ዩኒቨርሲቲዎችና አዳሪ ት/ቤቶች በዋናነት የተቀዱት ከገዳማት ነው። የከፍተኛ ተቋማት ተማሪዎች ሲመረቁ የሚለብሱት ጋዋንና የሚደፉት ቆብ የገዳማትን ቀሚስና ሞጣህት እንዲሁም ቆብ የሚመስለው በአጋጣሚ አይደለም።
በአውሮፓ የውኃ ኃይልን ለወፍጮና ለቆዳ ሥራ መጠቀምንና ማዕድናትን ማውጣትንና መጠቀምን በስፋት ያስተዋወቁት ገዳማውያን ናቸው። የአውሮፓን የእርሻ መሬት፣ ሥነ ጥበብና እውቀት ከጥፋት በመጠበቅና በማበልጸግ ረገድ ገዳማት የተጫወቱት ሚና ምትክ አልባ ነው። አንዳንድ ገዳማት በየዓመቱ የአበምኔቶች መደበኛ ስብሰባ ስለነበራቸው፣ የደረሱባቸውን አዳዲስ የቴክኖሎጂ እውቀቶችና ልምዶች ይለዋወጡ ስለነበር በዚህ መንገድ ሥልጣኔ በመላው አውሮፓ እንዲስፋፋ የራሳቸውን ታላቅ ሚና ተጫውተዋል።
ከክርስትና በፊት የጉልበት ሥራ መልካም ክብርና ስም አልነበረውም። በግሪኮች ትምህርት መሠረት የጉልበት ሥራ የዝቅተኞቹ ኅብረተሰብ ክፍል (የድሀውና የባሪያዎች) ሥራ ተደርጎ ይወሰድ ነበር። በሮማውያን ዘንድም ለሥራ የነበረው መንፈስ ተመሳሳይ ነበር። ለጉልበት ሥራ በተለይም ለግብርና ከፍ ያለ ቦታና ከበሬታ የሰጡት ገዳማት ናቸው።
ከዚህም ጋር ገዳማት ለድሆች፣ ለስደተኞች፣ ለወላጅ አልባ ልጆች፣ ለሕሙማንና ለችግረኞች መጠጊያዎች በመሆን አገለግልዋል። ለምሳሌ ያህል፣ በ4ኛው መ/ዓ የነበረው ቅዱስ ባስልዮስ የመሠረታቸው ገዳማት ሐኪም ቤቶች፣ የድሆች መመገቢያዎችና የችግረኞች መርጃ ማዕከሎችም ነበሩ። የዘመናዊ ሆስፒታል ጽንሰ-ሐሳብ መሠረቱ ክርስቲያናዊ ገዳማት ናቸው።
እንደዚሁም ገዳማት የሥነ ጽሑፍና የትምህርት ማዕከላት ነበሩ። ታላላቅ ቤተ መጻሕፍት የነበራቸው ብዙ ገዳማት ነበሩ። ብዙ መጻሕፍት ከእኛ እንዲደርሱ ያደረጉት መጻሕፍትን የሚሰበስቡና ባለሙያዎችን መድበው በእጅ የሚያስገለብጡ ገዳማት ናቸው። ብዙዎቹ መጻሕፍትና የታሪክ መዛግብት ከጥፋት ተርፈው ከዛሬ የደረሱት በገዳማት ተደብቀውና ተጠብቀው ስለኖሩ ነው።
ግሪኮች በኦቶማን ቱርክ በተገዙባቸው ወደ 300 የሚደርሱ ዘመናት ውስጥ እምነታቸውን ብቻ ሳይሆን ቋንቋቸውን፣ ባህላቸውንና ሥነ ጽሑፋቸውን ሕያው አድርገው የጠበቁት በገዳማት ዋና ማዕከልነት ነበር። ገዳማቱ ለካህናት ብቻ ሳይሆን በቱርኮች ግዛት ሥር ለነበሩ መላው ግሪካውያን ስውር ት/ቤቶች ነበሩ። በአገራችንና በሌሎች አገራትም ብዙ ተመሳሳይ ታሪኮች አሉ። ነጻነትን ለሚወዱና ባርነትን ለሚጸየፉ ሰዎች ሁሉ እነዚህ ትርጉማቸው ጥልቅ ነው። የቤተ ክርስቲያን ጠላቶች ገዳማትን ትቁር ጥምድ የሚያደርጓቸውም ለዚህ ነው።
መናንያን አባቶችና እናቶች ለሰው ልጅ ሁሉ ምሕረትን ከእግዚአብሔር የሚለምኑ ናቸው። በአስቄጥስ ገዳም ስለ ነበረ አባ ኢሳይያስ ስለ ተባለ አባት በመጽሐፈ ገነት እንዲህ ተብሎ እናገኛለን፡- “በዋዕየ ፀሐይ ላይ ራቁቱን ቁሞ ስለ መላው ዐለም ሲጸልይ ሳለ ከመነኰሳት አንዱ እንዲህ የሚል ድምጽ ሰማ፡- ‘ከእርሱ ጸሎት የተነሣ ለዐለሙ ሁሉ ምሕረት አድርጌያለሁና ሂድና ለአባ ኢሳይያስ ሰውነቱን የሚሸፍንበት ልብስ ስጠው።’”
ገዳማውያን መናንያን ሌላውን የሚዘርፉና የሚያጠፉ ሳይሆኑ ለሰው ልጆች ሁሉ ምሕረትን የሚለምኑ ናቸው፣ ሰውን የሚያሳድዱ ሳይሆኑ የተሰደዱትን የሚቀበሉ ናቸው። እንኳንስ የሰው ልጅ እንስሳትና አራዊት እንኳ አዳኞች ሲያሳድዷቸው ሸሽተው የሚጠጉባቸው ናቸው። የፍርሃትና የአጎብዳጅነት መንፈስ ያይደለ የእውነትና የጥብዓት መንፈስ ያለው ሁሉ ይህን ይረዳል።
ምንም እንኳ ምናኔያዊ ሕይወት ዓላማው በዚህ ዐለም ሀብት መበልጸግ ባይሆንም፣ በኢኮኖሚያዊ አስተዋጽኦ ረገድም ቢሆን ገዳማት በየዘመናቱ የነበራቸው ሚና ቀላል አልነበረም። ለአብነት ያህል በዘመናችን የግብፅን የእንስሳት ተዋጽዖ ምርቶች በከፍተኛ ድርሻ የሚሸፍኑት ኦርቶዶክሳውያን ገዳማት ናቸው። የአስቄጥስ ገዳም ለግብፅ የአየርና የዐፈር ጠባይ ተስማሚ የእህልና የአትክልት ዝርያዎችን በማምረት የአገሪቱን የምግብ አቅርቦት ችግር በመፍታት ረገድ የተጫወተው ሚና ታላቅ ነው።
በተለይም ደግሞ የአስቄጥስ ገዳም መነኰሳት በሳይንሳዊ ምርምር በግብፅ ምድር ለመጀመሪያ ጊዜ ያመረቱት “ፎደር ቢት” (fodder beet) የተሰኘ የስኳር ድንች ዓይነት አዲስ ምርት በእጅጉ ተመስግነውበታል። የአሰቄጥስ ገዳም መነኰሳት በዚህ ረገድ ላበረከቱት አስተዋጽዖ ሙስሊሙ መሪ አንዋር ሳዳት ከታላቅ ምስጋና ጋር ብዙ ሽልማት አበርክቶላቸዋል። ሌሎቹ የግብፅ ገዳማትም ለበረሃው ተስማሚ የሆኑ የዕፅዋትና አዝዕርት ዓይነቶችን በሳይንሳዊ ምርምር በመፈለግ ረገድ ከፍተኛ ሥራ እየሠሩ ናቸው።
ወደ ግብጽ አባ ቢሾይ ገዳም ተጉዞ የነበረ አህመድ ኤል-ጋማል የተባለ የተባበሩት ዐረብ ኤምሬትስ ጋዜጠኛ November 21, 1988 ላይ በወጣ “Khaleeg” በተባለ ጋዜጣ ላይ “A visit to the Depth of the Desert” በሚል ርዕስ እንዲህ ጽፎ ነበር፡-
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated hace 3 semanas, 5 días
Last updated hace 3 semanas
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot
🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹
Last updated hace 1 mes, 1 semana