ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated 2 weeks, 5 days ago
Last updated 2 weeks ago
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot
🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹
Last updated 1 month ago
ዶናልድ ትራምፕ ለቢሊየነሩ ኤለን መስክ ሹመት ሰጡ
ተመራጩ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ቢሊየነሩን ኤለን መስክ አዲስ ባቋቋሙት የመንግስት መስሪያ ቤቶች አፈጻጸም ዲፓርትመንት (ዲኦጂኢ) መሪ አድርገው ሾመዋቸዋል።
አዲስ የተመሰረተው ይህ ተቋም ከመንግስት መዋቅር ውጪ ሲሆን ተግባሩም በዋናነት የመንግሰት መስሪያ ቤቶችን አፈጻጸም መፈተሽና መዋቅራዊ ማስተካከያ ምክረ ሃሳብ ማቅረብ መሆኑ ተገልጿል።
የባዮ ቴክኖሎጂ ስራ ፈጠራ ባለሙያ ቪቪክ ራማስዋሚ አዲስ የተቋቋመውን መስሪያ ቤት ከኤለን መስክ ጋር በጋራ እንደሚመሩት አናዶሉ ዘግቧል።
ሹመቱን አስመልክቶ ዶናልድ ትራምፕ “ሁለቱ ሰዎች በኔ አስተዳደር ዘመን የተንዛዛ የመንግስት ቢሮክራሲን የማፈራረስ፣ የበዛ ቁጥጥርን እና ለብክነት የሚያጋልጡ ወጭዎችን መቀነስ እንዲሁም የፌደራል ኤጀንሲዎችን እንደገና በማሻሻል መንገድ ይከፍታሉ” ብለዋል።
ትራምፕ አዲሱን ተቋም የዚህ ዘመን “የማንሃታን ፕሮጀክት” በማለት አሜሪካ አቶሚክ ቦንብ ለመስራት ከተጠቀመችበት የፕሮጀክት ስም ጋር አነጻፅረውታል።
አማካሪው ተቋም በፌደራል መስሪያ ቤቶች የአፈጻጸም ድክመቶችን በመፍታት እና ፈጠራ የታከለበት የመንግስታዊ አሰራርን በማስተዋወቅ ጥረቱ ከነጩ ቤተ መንግስትና ከከበጀትና አስተዳደር ቢሮ ጋር በትብብር ይሰራል ተብሏል።
ኤለን መስክ አዲሱ መስሪያ ቤት በመንግስት አሰራር ስርዓትና በገንዘብ ብክነት ውስጥ በተሳተፉ በርካታ ሰዎች ዘንድ አስደንጋጭ መልዕክት ያስተላልፋል ብለዋል።
ይህ አዲሱ ተቋም አሜሪካ ለዓመታዊ ወጭዋ ከመደበችው 6 ነጥብ 5 ትሪሊዮን ዶላር ላይ የሚባክነውንና በሙስና የሚጭበረበረውን ሀብት እንደሚያስቆመው ትራምፕ ተናግረዋል።
ተቋሙ ተልዕኮውን አሜሪካ የተመሰረተችበትን 250ኛ የልደት በዓሏን በምታከብርበት በፈረንጆቹ ሐምሌ 4/2026 እንደሚያበቃም ተጠቅሷል።
‘’መንግስት በሚወጡ የትምህርት ፖሊሲዎች ዙርያ ግብዓቶችን እንዳቀርብ ይጠይቀኝና፤ ያቀረብኳቸው ግብዓቶች ግን በቅጡ ሳያያቸው ውድቅ ያደርጋቸዋል’’ ሲል የኢትዮጵያ የግል ከፍተኛ የትምህርት እና የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ማህበር ተናገረ፡፡
ማህበሩ በተለያዩ ጊዜያት በትምህርት ሚኒስቴር እና በትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን በኩል በሚወጡ ፖሊሲዎችና መመሪያዎች ላይ ያለውን አተያይ እና የመፍትሄ ሀሳቦች ጥናት አድርጎ እንደሚያቀርብ ተናግሯል፡፡
‘’ነገር ግን እነዚህን በመንግስት ተጠይቆም ሆነ በራሱ ተነሳሽነት የሚያቀርባቸው ግብዓቶችና የመፍትሄ ሀሳቦች በአግባቡ እንኳ ታይተው አያውቁም’’ ሲል ማህበሩ ዓመታዊ ጉባኤውን ባካሄደበት ወቅት ሲናገር ሰምተናል፡፡
የማህበሩ ፕሬዚደንት አረጋ ይረዳው(ዶ/ር) በተለያዩ ጊዜያት በሚወጡ የትምህርት ፖሊሲዎች ዙሪያ ዘርፉን አይተን እና ጥናት አድርገን ለፓርላማ አቅርበን፤ ፓርላማውም ከተቀበለን በኋላ ምንም ታሳቢ ሳያደርጋቸው ወደ ጎን ትቷቸዋል ብለዋል፡፡
‘’የምናቀርባቸው ግብዓቶች ታሳቢም ሆነ ተግባራዊ የማይደረጉ ከሆነ የኛ ድካም ትርፉ ምንድነው?’’ ሲሉም ጠይቀዋል፡፡
በተጨማሪም በትምህርት ሚኒስቴር እና በትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን በኩል ተናቦ የመስራት ክፍተት እንደሚያዩም አስረድረዋል፡፡
በማህበሩ የቀረበው ቅሬታን በተመለከተ ሸገር ራዲዮ በህዝብ ተወካዎች ምክር ቤት የሰው ሀብት፣ ስራ ስምሪት፣ ድልድል እና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባል የሆኑት ታደሰ በዛ (ዶ/ር)ን ጠይቋል፡፡
ዶ/ር ታደሰ ‘’መንግስት ከዚህ በፊት ትኩረት ያደርግ የነበረው በራሱ የሚተዳደሩት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ላይ ነበረ፤ አሁን ግን የግሉንም በማካተት አዲስ ማዕቀፍ ተዘጋጅቶ የክትትልና የቁጥጥር ስራ እየተሰራ ነው’’ ብለዋል፡፡
የግል የከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ለሀገር የሚያበረክቱት አስተዋጽኦ ትልቅ ነው፤ መንግስትም ይህንንይረዳል ብለዋል የቋሚ ኮሚቴው አባል፡፡
በሚወጡ የትምህርት ፖሊሲዎችና መመሪያዎች የግሎቹ ታሳቢ እንደሚደረጉ አስረድተዋል፡፡
Sheger Fm
መንግሥት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያቀረበው አዲሱ የባንክ ሥራ አዋጅ፣ በባንክ ሥራ ላይ ለመሠማራት የሚፈልጉ ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ከአገር ውስጥ ወይም ከውጭ አገር ኢንቨስተርነት አንዱን ብቻ እንዲመርጡ እንደሚያስገድድ ተገልጧል።
ኢትዮጵያ ውስጥ አክሲዮን የገዙ ትውልደ ኢትዮጵያዊ የኾኑ የውጭ አገር ዜጎች ግን እንደ አገር ውስጥ ኢንቨስተር የመቆጠር መብት እንዳላቸው ረቂቅ አዋጁ መደንገጉን ኢትዮጵያ ኢንሳይደር ዘግቧል። እንደ ውጭ ዜጋ መቆጠር የሚፈልጉ ትውልደ ኢትዮጵያዊያን፣ ለውጭ ዜጎች የተደነገጉ ድንጋጌዎች ተፈጻሚ ይኾኑባቸዋል ተብሏል።
ረቂቅ አዋጁ የውጭ ዜጎች ባንድ ባንክ ውስጥ መያዝ የሚችሉትን የአክስዮን መጠን፣ ከባንኩ የተፈረመ ካፒታል ውስጥ ከ49 በመቶ እንዳይበልጥ ገደብ እንደጣሉ ዘገባው ጠቅሷል።
ሰበር .. ቤተመንግሥት የተደበቀው 400 ኪ/ግ ወርቅ ሚስጥር 😲 | ነገስታቶችን ያስወቀሰዉ ጉዳይ | እዉነታዉ ምን... https://youtube.com/watch?v=auBVBrJWu_g&si=eA85_REy6galxjCP
በኢኳቶሪያል ጊኒ ከታዋቂ ሴቶች ጋር ሲፈፅም የነበረውን ወሲብ፤ በቪዲዮ ካሴቶች ያከማቸው ባለስልጣን
የኢኳቶሪያል ጊኒ የፋይናንስ ምርመራ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ባልታሳር ኢንጎንጋ ከታዋቂ ሴቶች እና የባለስልጣናት ዘመዶች ጋር ከቢሮ እና በተለያዩ ቦታዎች ወሲብ ሲፈፅም የሚያሳዩ ቪዲዎች አከማችቶ ተገኝቷል።
ቪዲዮው የሀገሪቱን ፕሬዝዳንት እህት ጨምሮ የታዋቂ ሰዎችን የወሲብ ህይወት የሚያሳይ ነው የተባለ ሲሆን ከ400 በላይ የወሲብ ካሴቶችን በባለስልጣኑ ቢሮ እና መኖሪያ ተገኝቷል ተብሏል።
ድርጊቱ የተጋለጠው የ54 አመቱ ኢንጎንጋ በተጠረጠረበት የማጭበርበር ወንጀሎች ላይ ተመስርቶ በተደረገ ፍተሻ ነው።
በዚህም ባለስልጣኑ በቤቱ እና በቢሮው ውስጥ ወሲባዊ ግንኙነቶችን በቢሮው እና በተለያዩ ቦታዎች ሲፈፅም የሚያሳዩ ቪዲዮዎች በማህበራዊ ትስስር ገጾች ተሰራጭተዋል።
በቪዲዮ ቅጂው ከታዩት ውስጥ የፕሬዝዳንት ቴዎዶሮ ኦቢያንግ ንጉማ ምባሶጎ እህት፤ የከፍተኛ ባለስልጣናት የትዳር አጋሮች ጨምሮ የቅርብ የቤተሰብ አባላት እና ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ዘመዶች እንደሚገኙ አፍሪካ ኒውስ ዘግቧል።
ሮይተርስ በበኩሉ በቪዲዎቹ ላይ የሚታዩትን ባለስልጣናት እና ትክክልኝነት ማረጋገጥ እንዳልቻለ ገልጿል።
የቪዲዮ ቅጂዎቹ በማህበራዊ ትስስር ገጾች ከወጡ በኃላ ከፍተኛ የህዝብ ቁጣ በመቀስቀስ የብዙሃን መገናኛዎችን ቀልብ ስቧል።
የአገሪቱ ምክትል ፕሬዝደንት ቴዎዶሮ ኦቢያንግ ማንጉ ማንኛውም ሰራተኛ በስራ ቦታ የወሲብ ድርጊት ሲፈጽም ከተገኙ “የሥነ ምግባር ደንቡን በመጣስ” እንደሚታገድ ገልፀዋል።
እኚህን መሰል ድርጊቶች ለመከላከልም የክትትል ካሜራዎችን በፍርድ ቤት እና በሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች እንዲገጠሙ አዘዋል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአፍሪካ በአይነቱ የመጀመሪያው ነው የተባለውን ኤይርባስ A350-1000 የተሰኘውን አዲስ አውሮፕላን ተረክቧል፡፡
አየር መንገዱ በፈረንሳይ ቱሉስ በተከናወነው ስነስርዓት ከአውሮፕላን አምራቹ ኤርባስ ኩባንያ የተረከበውን የመጀመሪያውን አውሮፕላን ዛሬ በአዲስ አበባ ቦሌ ዓለማቀፍ አየር ፣ማረፊያ አስተዋውቋል፡፡
አቪየሽን ሳንስ ፊሮንተርስ ከኤርባስ ጋር በመሆን ለኢትዮጵያ አየርመንገዶች ፋውንዴሽን የተበረከተውን በ100 ሺህ ዩሮ የሚገመት የህክምና ቁሳቁስ ተሸክሞ በአየርመንገዱ ባለስልጣናት ከሰዓቱን አዲስ አበባ የደረሰው አውሮፕላኑ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት እና ዲፕሎማቶች በተገኙበት በደማቅ ስነስርዓት አቀባበል ተደርጎለታል፡፡
በአውሮፕላኑ አቀባበል ስነስርዓት ወቅት ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈጻሚ መስፍን ጣሰው ዛሬ አየር መንገዱ የተቀበለው ኤይርባስ A350-1000 አውሮፕላን አየር መንገዱ ካዘዘው አራት አውሮፕላኖች አንዱ ነው፡፡
በኢትዮጵያ እየተከሰተ ያለው የመሬት መንቀጥቀጥ ለ10 ሺህ ገደማ ሰዎች የእሳተ ገሞራ ፍንዳታ ስጋት እንደሆነ ተጠቆመ
'Gelology Hub' በሚል የሚታወቀው እሳተ ገሞራዎችን እና የመሬት እንቅስቃሴዎችን በተመለከተ ትንታኔ የሚያቀርበው ድርጅት እንዳለው በአለም ዙርያ ትኩረት የተነፈገው ይህ አደገኛ ክስተት የእሳተ ገሞራ ፍንዳታን ሊያስከትል የመቻል እድሉ ከፍተኛ ነው።
በኢትዮጵያ እየተካሄዱ ያሉ ግጭቶች እና ጦርነቶች ይህ ተፈጥሮአዊ አደገኛ ክስተት ብዙ ትኩረት እንዳያገኝ አድርጎታል የሚለው Geology Hub ይህን መረጃ ለህዝብ ማድረስ የፈለገው የሰው ህይወት ለማትረፍ ነው ብሏል።
ከመስከረም ወር ጀምሮ ከፍተኛ የሆነ የቀለጠ አለት ክምችት እየታየ መሆኑን ገልጾ እስካሁን ከአደጋው አካባቢ 700 ገደማ ሰዎች እንዲነሱ መደረጉን ገልጿል።
በዚህ አደገኛ ስፍራ የሚገኙ 10 ሺህ ገደማ ሰዎች በአስቸኳይ ከስፍራው እንዲነሱ መደረግ እንዳለባቸው የሚገልፀው Gelology Hub ይህን ጉዳይ በዋሽንግተን ዲሲ ለሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ እና ለአሜሪካው የጂኦሎጂካል ሰርቬይ ማሳወቁን ጨምሮ ጠቅሷል።
21 ኪ/ሜ ርዝመት ያለው ይህ የእሳተ ገሞራ ግፊት በመካከለኛ ኢትዮጵያ አዋሽ አካባቢ እንቅስቃሴው እንደቀጠለ የታወቀ ሲሆን ከዚህ ጋር ተያይዞ ከዚህ በፊት በአካባቢው ያልነበሩ አዳዲስ ሙቅ ውሀዎች መፍለቅ መጀመራቸውም ታውቋል።
ለአራተኛ ግዜ በአዋሽ ፈንታሌ እስከ 4 ነጥብ 7 ሬክተር ስኬል የተመዘገበ የተለያየ ደረጃ ያለው የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱን ሠመራ ዩኒቨርሲቲ አስታውቆ ነበር።
መሠረት ሚዲያ
የ 3 ወር ደመወዛቸዉ ያልተከፈላቸዉ እና ቁጥራቸዉ ከ 1 ሺህ በላይ የሚልቁ የፐርፐዝ ብላክ ሰራተኞች ለከፍተኛ ችግር መጋለጣቸውን ተናገሩ
አጠቃላይ ቁጥራቸው ከ 1 ሺህ በላይ የሚልቁ የፐርፐዝ ብላክ ኢትዮጵያ ሰራተኞች ከነሐሴ ወር ጀምሮ መከፍል የነበረበት ደመወዝ እንዳልተከፈላቸዉ በመግለፅ በዚህም ምክንያት በድርጅቱ ሰራተኞች ላይ የኑሮ ጫናዉ በእጅጉን እየበረታ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
እነዚሁ ሰራተኞች እንደሚሉት ከሆነ ምንም እንኳን የተቋሙ አመራሮች በተጠረጠሩበት ጉዳይ ክሳቸው በፍርድቤት እየታየ ቢሆንም "የእኛ የደመወዝ ጥያቄ ግን ችላ ተብሏል" ሲሉ ነዉ ቅሬታቸዉን ለካፒታል ያቀረቡት ።
ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈቀዱ የድርጅቱ ሰራተኞች እንዳሉት " ከዚህ ቀደም ወሩ በተጠናቀቀ በ 30 ወይም በማግስቱ ይደርሳቸዉ የነበረዉ ደመወዝ አሁን ግን የኩባንያው የበላይ አመራሮች ሰርተዋል በተባለው ጥፋት ተጠያቂ መሆን ሲገባቸዉ ሰራተኛው ግን ለችግር መጋለጥ የለበትም" ይላሉ።
ሰራተኛው ምንም በማያዉቀዉ ጉዳይ እየተንገላታ ይገኛል የሚሉት እነዚሁ የካፒታል ምንጮች ደርሷል ካሉት ችግሮች መካከል :- ደመወዙን ተማምኖ ልጆቻቸውን የግል ትምህርት ቤት ያስገቡ የተቋሙ ሰራተኞች ክፍያ መፈፀም አቅቷቸዋል ፣ የቤት ኪራይ መክፈል ያቃታቸው ሰራተኞች ወደ ቤተሰቦቻቸው ጋር እንዲሄዱ እና በብድር ኑሯቸዉን እንዲገፉ የተገደዱ ሰራተኞች ይገኙበታል።
ቀጣይ እጣፈንታቸዉ ያሳሰባቸው እነዚሁ ሰራተኞች በዚህ ጉዳይ የሚመለከተው የመንግስት አካል ጋር ቀርበዉ ጉዳያቸው እንዲታይላቸው ሙከራ ቢደረግም ምላሽ አለማግኘታቸው እና ተቋሙ አሁን ላይ ምንም አይነት ገንዘብ ማንቀሳቀስ እንዳይችል በመደረጉ ስራዎች እንዲቋረጡ መደረጉ ነዉ የሚናገሩት ።
በዚህ ምክንያት የሰራተኞቹ ጉዳይ በፍርድቤት ሊታይ እንደሚገባ እና ቀጣይ ተስፋ ሰጪ ነገር ማሰብ እንዳይችሉ እያደረጋቸው እንደሚገኝ ነዉ የተናገሩት ።
የኑሮ ዉድነትን ታሪክ አደርጋለሁ በሚል ከ 4 ዓመታት በፊት የግብርና ኢንዱስትሪውን የተቀላቀለው ፐርፐዝ ብላክ ቀድቀ ከተሰማራበት ዘርፍ በተጨማሪ በሪል እስቴት ግንባታ ጨምሮ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን ቀርፆ እየሰራ እንደሚገኝ አስታዉቆ ነበር።
ይሁን እንጂ በአክሲዮንነት የተቋቋመው ድርጅቱ ጀምሬያለሁ ያላቸዉን ፕሮጀክቶች ከመፈፀም ይልቅ በተግባር የታየ ለዉጥ ባለመኖሩ በተደጋጋሚ ቅሬታ ሲቀርብበት እንደነበር ይታወሳል ።
ከሰሞኑ ደግሞ የፍትሕ ሚኒስቴር የሙስና ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዐቃቤ ሕግ የፐርTዝ ብላክ ኢቲኤች ትሬዲንግ አ.ማ የቦርድ አባልና ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍስሐ እሽቱን (ዶ/ር) ጨምሮ በ10 ግለሰቦች ክስ እንደመሰረተባቸዉ ይታወቃል ። Capital
ምክር ቤቱ ክቡር የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ በተገኙበት 6ኛ ዙር 4ኛ ዓመት 3ኛ መደበኛ ስብሰባውን ይካሂዳል፡፡
በዕለቱ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ክቡር አምባሳደር ታዬ አፅቀስላሴ መስከረም 27 ቀን 2017ዓ.ም ለሕዝብ ተወካዮች እና ለፌዴሬሽን ምክር ቤቶች የጋራ ስብሰባ ያደረጉትን የመክፈቻ ንግግር አስመልክቶ፤ ከምክር ቤቱ አባላት በሚቀርቡ ጥያቄዎች ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር) ምላሽና ማብራሪያ ይሰጣሉ፡፡
ይህን ተከትሎም ምክር ቤቱ የመንግስትን አቋም በማዳመጥ የድጋፍ ሞሽኑን ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
Hopr
ብሊንከን የሃማስ መሪ ከተገደሉ በኋላ ታጋቾቹን ለማስለቀቅ "እውነተኛ ዕድል ይኖራል" አሉ!
የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን፣ እስራኤል የሃማሱን መሪ ያህያ ሲንዋርን መግደሏ አሁንም ጋዛ ውስጥ በታጣቂው ቡድን እጅ ያሉትን ቀሪዎቹን ታጋቾች የሚያስለቅቅ ስምምነት ላይ ለመድረስ እውነተኛ እድል ማምጣቱን ተናገሩ።ብሊንክን ይህን የተናገሩት፣ ዛሬ ረቡዕ ከቴል አቪቭ ወደ ሳኡዲ አረብያ ከመብረራቸው በፊት ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ነው።
"እስራኤል ሃማስ ላይ በምታካሂደው ጦርነት ወታደራዊ ዓቅሙን ማዳከም ጨምሮ ብዙ ስኬት አግኝታለች" ያሉት ብሊንከን "የቀረው ታጋቾቹን ማስለቀቅ እና ጦርነቱን ማጠናቀቅ ነው" ብለዋል።ጦርነቱ ሃማስን ከጋዛ በሚያስወጣ እና የእስራኤል ወታደሮችም እዚያ እንዳይቆዩ በሚያደርግ መንገድ መጠናቀቅ እንዳለበትም ብሊንክን አሳስበዋል።
ከጦርነቱ በኋላ ለጋዛ የሚኖረው እቅድ አስተዳደር፣ ደህንነት፣ መልሶ ግንባታ፣ እንዲሁም ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ፍልስጤማውያንን ለመርዳት ማድረግ የሚችለውን ጨምሮ በሚቀጥሉት ቀናት ከአረብ አገሮች ጋራ የሚወያዩበት ርዕስ እንደሚሆን ብሊንከን ተናግረዋል፡፡ብሊንከን ነገ ሐሙስ ወደካታር ይሄዱ እና አርብ በለንደን ከአረብ ሀገራት አቻዎቻቸው ጋራ እንደሚገናኙ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።
ብሊንከን እና የመከላከያ ሚኒስትሩ ሎይድ ኦስተን እስራኤል ወደጋዛ የሚገባውንን የሰብአዊ ርዳታ መጠን እንድትጨምር፣ አለዚያ የአሜሪካን ወታደራዊ ርዳታ እንደምታጣ የሚያስጠነቅቅ ደብዳቤ ከላኩ አንድ ሳምንት በኋላ ሁኔታዎች መሻሻል ቢያሳዩም ብዙ እንደሚቀረውና ቀጣይነት እንደሚያስፈልገው የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ትላንት ረቡዕ በሰጡት መግለጫቸው ተናግረዋል፡፡
አምና የሰጡትን ተመሳሳይ ማስጠንቀቂያ ተከትሎ እስራኤል ወዲያውኑ የሰብአዊ ርዳታ አቅርቦቱ መጠን እንዲጨምር ብታደርግም እንዳልቀጠለ ብሊንከን አውስተዋል። አዲሱ ማስጠንቀቂያ "ባዶ ማስፈራሪያ" ይሆን እንደሆን የተጠየቁት የውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ " በሕጉ መሠረት ለመሥራት ቁርጠኛ ነኝ" ብለዋል፡፡
ብሊንከን ከአንድ ዓመት በፊት ከተቀሰቀሰው የእስራኤል እና የሃማስ ጦርነት ወዲህ ባደረጉት 11ኛ ጉብኘታቸው ከእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ እና ሌሎች ባለሥልጣናት ጋራ ትላንት ማክሰኞ ተገናኝተው ተወያይተዋል።የሃማሱ መሪ ሲንዋርን ግድያ ተከትሎ ዩናትይትድ ስቴትስ ወደ አካባቢው ተመልሳ የተኩስ አቁም ጥረቱን እንድትገፋበት መልካም አጋጣሚ የተከፈተላት መሆኑ ተመልክቷል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ የእስራኤል ኅይሎች ዛሬ ረቡዕ የሊባኖስ ደቡባዊ የወደብ ከተማ ታይር ላይ የአየር ጥቃት አካሂደዋል፡፡ ጥቃቱን ያደረሱት ነዋሪዎች ከተማዋን ለቅቀው እንዲወጡ ትዕዛዝ ከሰጡ ከሰዓታት በኋላ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡ ሌሊቱን ቤይሩት ውስጥ ያሉ ከሄዝቦላህ ጋር ግንኙነት ያላቸውን አካባቢዎች ደብድበናል ስትል እስራኤል አስታውቃለች፡፡ዛሬ ረቡዕ ቤይሩትን የጎበኙት የጀርመን የውጭ ጉዳይ ሚንስትር አናሌና ቤርቦክ ለሊባኖሱ ጦርነት ዲፕሎማሲያዊ መፍትሄ እንዲፈለግ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
Via VoA
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated 2 weeks, 5 days ago
Last updated 2 weeks ago
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot
🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹
Last updated 1 month ago