ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated hace 3 semanas, 5 días
Last updated hace 3 semanas
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot
🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹
Last updated hace 1 mes, 1 semana
የፍቅር ቀጠሮ
ጠበቅኩሽ እኔማ እዚያው ሥፍራ ቆሜ
በአክሱም ቁመና በላሊበላ ዕድሜ
እግሮቼን ተክዬ ቀኔን አስረዝሜ
በሔድሽበት መንገድ ልቤ እንደነጎደ
ስንት ነገር መጣ ስንት ነገር ሄደ
ስንት ጊዜስ ነጋ ስንቴ ጎህ ቀደደ
ስንቴ ዝናብ ጣለ ስንት ጊዜ አባራ
ትመጫለሽ ብዬ በቆምኩበት ሥፍራ
ስንቴ አድማሱን ማተርኩ ስንትና ስንት ዓመት
አንገቴን አስግጌ በራስ ዳሽን ቁመት
በአክሱም ቁመና በላሊበላ ዕድሜ
በቀጠርሽኝ ሥፍራ ስጠብቅሽ ቆሜ
ስንት ሳቅ አለፈ ስንትና ስንት ዕንባ
ስንቴስ ክረምት ሆነ ስንቴ ፀደይ ጠባ
ስንቱ ተገናኘ ስንቱ ሰው ተጋባ
ሽል ስንቴ ልጅ ሆነ ስንትስ ጊዜ አረጀ
ስንት ኮት ጨረሰ ስንት እንጀራ ፈጀ
ስንት ዓይነት ሞት አየሁ ስንት ዓይነት ፍፃሜ
በአክሱም ቁመና በላሊበላ ዕድሜ
በቆምኩበት ሥፍራ ስጠብቅሽ ቆሜ?
ስንት ውበት አለፈ ስንት ውበት ነጎደ
ስንት ትውልድ መጣ ስንት ትውልድ ሄደ
ስንት ዕውነት ከፍ አለ ስንት ዕውነት ወረደ
ስንት ዓለም ተሻረ ስንት ዓለም ነገሠ
ስንት ሀገር ተሰራ ስንት አገር ፈረሠ
ስንት ሺህ ዓመት ሸኘሁ ስንት ሺህ ተቀበልኩ
እዚያች ሥፍራ ቆሜ አንችን እየጠበቅኩ
እግሬን አስረዝሜ ቆየሁ ቆየሁና
በላሊበላ ዕድሜ በአክሱም ቁመና
ሳትመጪ ወደኔ ሳላገኝሽ ገና
ብዙ ነገር መጥቶ ብዙ ነገር ያልፋል
የራስ ዳሽን ራስ አንገቱን ይደፋል
አክሱምም ተንዶ እንደጨው ይረግፋል
ላሊበላም ወርዶ ቁልቁል ይነጠፋል
ሰማይና ምድርም ያልፋሉ ታያለሽ
እኔ ግን እዛው ነኝ አንች እስክትመለሽ…
✍️✍️ታገል ሰይፉ
"ህልሜን አላቀልጥም"
ወታደርም ቢባል
ያው በቀቀናም ነው፣
ፍርሃት አለ ውስጡ፣
አሸናፊም ብትል
ይፈራል ነገውን
ፍርሃት አለው ነውጡ፣
ንጉሠ ነገሥትም
ፍርሃት አለ ቆጡ፣
አንበሳ ደቦሉም
ፍርሃት አለ ውስጡ፣
ማንኛውም ብትል
ጠልፎ የሚጥል ሰው
ፍርሃት አለ ውስጡ፣
"ብተወውስ" ብሎ
ይፈራል ታንቲራ፤
እኔ ግን የምልህ
ህልምህን አትፍራ፣
ድፈረው፣ ድፈረው
ወንጀለኛ አይልህም ፍርድ ቤቱ ደፍሮ
አቃቤ ህግ አይከስ፣
እንዲያውም ይፈራል-ይፈራል ወጥሮ
ህልምህን የምተው...
ወመኔ 'ሚዘራው
ገንዘብ ስላጣህ ነው?
ተስፋ ስላጣህ ነው?
ያዘው ግፋ ብሎ
ተስፋን የሚመግብ
ቤተሰብ ነው ያጣህ?
ወይስ ነው ከጀርባህ
ኦና ሆኖ ታየህ?
እኔ ግን የምልህ
እኔ የምመክርህ፣
እንዳትመለስ ነው
ከተስፋ ከእድልህ
እኔ የሚታየኝ
እኔ እንደሚሰማኝ፣
ችግርም ብትፈጥር
በራስህ ላይ ወጥር
ለውጥ አምጣ
ለውጥ አምጣ
ቀን አውጣ
ቀን አውጣ
ችግርና ፍዳህ የመኖርህ ትርጉም
ላብ ነህ ለዚህ ምድር
ወዝ ነህ ለዚህ ዓለም፡፡
ወዝና ጊዜየን በቁሜ ብቀማም
እንደ አሸን ተራግፈው
ጓደኞቼን ባጣም
ወደሁዋላ ስዞር
አንድም ሰው ባይመጣም
ተስፋዬን አልሸጥም
ህልሜን አላቀልጥም፡፡
✍️✍️ ይስማዕከ ወርቁ
ሞት አያምም
እኖር ብዬ ብታረድም
ለመኖር ስል ብሰደድም
እኖር ብዬ ብዋረድም
ዘጠኜ ሞቴን ብሞተው…
አንዴ እንደመኖር አይከብድም!
መኖር ከመምት አይልቅም
ሞት እንደሕይወት አይጨንቅም፡፡
የሞተ ‹‹እሞታለሁ›› ሲል…
በጭራሽ አያውቅም ፈርቶ፡፡
ያልኖረ አያውቅም ሞቶ።
መኖር እንጂ የሚያስፈራኝ
መኖር እንጂ የሚያስገፋኝ
መኖር እንጂ የገደለኝ
መኖር እንጂ የበደለኝ
ሞት አያምም ካቆሰለኝ
ምት አያምም ከገደለኝ!
✍️✍️ በላይ በቀለ ወያ
ፈተሽ እንጋባ
የሰርጌ ቀን መሃላ፣ ሃጥያት ገለመሌ
ኩነኔ ነው ይሄ፣ አመልህ አመሌ
ጡር አለው ምናምን፣ እንዲያ አትበይኝ
ይልቅ ከወደድሽኝ፣ ፈተሽ ተከተይኝ።
"
ደሞ መሃላ ላልሽው
ሳትፈሪ መልሽው
በውነት' ለማገልገል'፣ ለአንዲት አላማ
ምሎ ተገዝቶ፣ በሃገር ፓርላማ
የአምስት መቶ ሰው፣ ማላ ተርከፍክፎ
ሃገር ከተሸጠ፣ ከተሰጠ ታልፎ
ስለ መሃላ ፈርተሽ፣ ለምን መክሰራችን
ሃገር በሸጠ ፊት፣ ፅድቅ ነው ስራችን
ሁሉም በየዘርፉ፣ በመሃላ ከታጨ
ኩነኔ ደርሶበት፣ ፂም እንኳን ካላጨ
የዚህ ሁሉ ምዑር፣ መሃላ ከጠፋ
የምን ኩነኔ ነው፣ ነይ ፈተሽ እንጥፋ።
✍️✍️እንግዳዬሁ ዘሪቱ
#From our subscribers
ስርቆሽ
አልመለስ ያለ ትውልድ
አዳኝ መርከቧን ንቆ
በጥፋት ውሃ ሰጠመ
በዝሙት ሃጥያት ወድቆ
ኀላም ውሃው እንደጠፈፈ
ምድርን 'ሀ' ብሎ ሲያቀና
ኖህ በኩራት እንደቆመ
ፍጥረቱን ሰበሰበና
በቅደም ተከተላቸው
በጥምረት እንዳሳፈረ
ከመርከቡ ሊያወርዳቸው
አንድ በአንድ እየቆጠረ
አጋር የሌለው ፍጥረት
መጀመሪያ ያልነበረ
አንድ እንስሳ ትርፍ ቀረ
ለካስ የዝሙት መንፈስ
ከአህያ ጋር ተሳፍሮ
ሚስቱን እየደበቀ
ከፈረስ ፍቅር ጀምሮ
ከማይሆን ተኝቶ ኖሮ
ከመርከቡ እንደወረደ
መሃን በቅሎን ወለደ!
እንግዲህ ከኖህ ጀምሮ
ዘመን ዘመንን አያደሰ
የጥፋት ውሃም የለ
ዝሙትም እዚህ ደረሰ፡፡
✍️✍️ ሜሮን ጌትነት
ተማሪ ነህ ?
ነግሬሽ ነበረ
ውበት ደም ግባትሽ ፣ ሁሉን ያስደምማል
ከንፈርሽ አየር ነው ፣ በሁሉም ይሳማል
ነግሬሽ ነበረ፡፡
ሰማይ ሚያህል ጭንሽ ፣ ከጭንቅላት ያንሳል
ምን ተራራ ቢያህል...
ጡትሽ አቅመ ቢስ ነው ፣ ሲነኩት ይፈርሳል፡፡
ነግሬሽ ነበረ
ክብረ ቢስ ህይወቶች ፣ ጣፍጠው አይቀጥሉም
የወለዱ ሁሉ ፣ እናቶች አይደሉም፡፡
ነግሬሽ ነበረ
የናትነት ስሟ ፣
ከክብሯ ነው እንጂ ፣ከልጇ እንዳልመጣ
ወልዳም ምንም ነች ፣ ሴት ክብሯን ስታጣ፡፡
ነግሬሽ ነበረ
አትስደበኝ እያልሽ ፣ የነገርኩሽ ሁሉ
ልክ ነሽ አንዳንዴ
እውነቶች ውሸት ፊት ፣ ስድብ ይመስላሉ፡፡
✍️✍️በላይ በቀለ ወያ@loret_tsegaye
@loret_tsegaye
ዓለምና ጊዜ
አንዱ ሥፍራ ሲለቅ አንዱ እየተተካ፤
ሁሉም ርስቴ ነች እያለ ሲመካ፤
ሞኝነት አድሮብን ሳናስበው እኛ፤
ዓለም ሰፈር ሆና ህዝቡ መንገደኛ፤
ትውልድ ፈሳሽ ውሃ, መሬቷም ጅረት፤
መሆኑን ዘንግቶ ይህ ሁሉ ፍጥረት፤
ስትመለከቱት በሰልፍ ተጉዞ . . .
ሁሉም በየተራው ያልፋል ተያይዞ።
✍️✍️ከበደ ማካኤል
ትናንትና ማታ
ላሟሟሽ ሲገባኝ፣እንዳሞሌ አጥቤሽ
በመጨረስ ፋንታ
ለነገ ቆጥቤሽ
አስተርፌሽ ለሰው
የጸጸት ሱናሚ ፤ዓለሜን አመሰው፡፡
ምነው ቢቻል ኖሮ
ፈገግታሽን ቋጥሮ
ሙዳይ ውስጥ መደበቅ
ጃንደረባ ቀጥሮ
ጭንሽን ማስጠበቅ
ክፍት ልቤን ይዤ፤ ዝግ ደጅሽን ጠናሁ
በሰበብ ወድጄሽ ፤ያለሰበብ ቀናሁ፡፡
ፍቅር በተባለ፤ ግራ- ገቢ ነገር
ከጨመተው አገር
ከሰከነው ቀየ
መናፍቅ ይመስል፤ ባዋጅ ተነጥየ
እንደካፖርቴ ቁልፍ፤ ልቤን የትም ጥየ
የትም ስከተልሽ
የትም ሆኖ እድልሽ፤
ሁሉ ያንች ወዳጅ
ሁሉ ባላንጣየ
መፈቀር ሆኖ ጣሽ፤ መቅናት ሆኖ ጣየ
ላንቺ ብስል ፍሬ፤ ለኔ ገለባ ግርድ
ላንቺ እቅፍ አበባ፤ ለኔ እቅፍ ሙሉ ብርድ
ማነው የበየነው ፣ይህን ግፈኛ ፍርድ፡፡
✍️✍️በእውቀቱ ስዩም
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated hace 3 semanas, 5 días
Last updated hace 3 semanas
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot
🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹
Last updated hace 1 mes, 1 semana