ዳሩል ኢሕሳን

Description
? አሰላሙ ዐለይኩም

ስለ ቻናላችን ያሎትን ሀሳብና አስተያየት በ @HaidayaBot ይላኩልን! እናመሰግናለን!

አላማዬ የቁርኣን እና የሐዲሥን ግዝፈት ታላቅነት እና ውበት አጉልቶ ማሳየት ነው።

@HaiderKhedir

? ይህን የYouTube ቻነል ሰብስክራብ በማድረግ ጠቃሚ ኢስላማዊ ትምህርቶችን ይቋደሱ!

https://m.youtube.com/user/haiderrkedirtv
Advertising
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 3 недели назад

Last updated 2 недели, 2 дня назад

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated 1 месяц назад

6 months, 3 weeks ago
***⛔******?*** ማስጠንቀቂያ ለእናቶች እና አባቶች!

? ማስጠንቀቂያ ለእናቶች እና አባቶች!

ቤቶችን ያፈረሱ፤ የሀብትና ንብረት እንዲሁም የልጆችን በረከት የሰለቡ ቃላት፡-

"አላህ አያሳካልህ!"
አለመግባባቶች እና ፍቺዎች ጨመሩ!!

" አላህ ያንሳህ!"
በሽታ ተስፋፋ ድንገተኛ ሞት ጨመረ!!

"አላህ ይርገምህ!"
ሃይማኖታዊና ዓለማዊ ሁኔታችን ተበላሸ!!

"አላህ ያዋርድህ!"
ቅሌትና ፌዝ እንደ አሸን በዛ!!

የቤታችን ምሰሶ በእርግማን እና ስድብ ላይ የቆመ ከሆነ

ልጆቻችን ስኬት ርቋቸው የውድቀት ምሳሌ ቢሆኑ... ወይም ለወላጆች ታዛዥ አልሆን ብለው ቢያምፁ ... አልያም ቤቶቻችን ውስጥ ፍቅር እና መተዛዘን የውኃ ሽታ ሆኖ ቢቀር ፈፅሞ ሊደንቀን አይገባም!

ምክንያቱም ቤተሰቡ በትክክለኛ የጥፋት ጀልባ ላይ ተሳፍሯልና!!

የአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋለ፦

"በራሳችሁ ላይ (በመጥፎ) ዱዓእ አታድርጉ፤ በልጆቻችሁም ላይ ዱዓእ አታድርጉ፤ በገንዘባችሁም ላይ ዱዓእ አታድርጉ፤ ምናልባትም ያደረጋችሁት ዱዓእ አላህ ለጥያቄዎች ሁሉ ምላሽ ከሚሰጥበት ጊዜ ጋር ተገጣጥሞ የለመናችሁትን ሊሰጣችሁ ይችላልና።"

ሙስሊም በቁጥር (3009) ዘግበውታል።

ምርጥ ወላጅ I #ለወላጆች I
ምርጥ እናት I #ለእናቶች I
ምርጥ አባት I #ለአባቶች I

? https://t.me/HidayaTerbiya ?

6 months, 4 weeks ago

? የዐረፋ ቀን ዱዓ

ከዐብደላህ ብን ዐምር ብን አል’ዐስ እንደተወራው የአላህ መልእክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል፦

وعن عبد الله بن عمرو بن العاص رضي الله عنهما أن النبي صلى الله عليه وسلم قال

((خَيْرُ الدُّعَاءِ دُعَاءُ يَوْمِ عَرَفَةَ ، وَخَيْرُ مَا قُلْتُ أَنَا وَالنَّبِيُّونَ مِنْ قَبْلِي : لَا إِلَهَ إِلَّا اللَّهُ وَحْدَهُ لَا شَرِيكَ لَهُ لَهُ الْمُلْكُ وَلَهُ الْحَمْدُ وَهُوَ عَلَى كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ))

رواه الترمذي ( 3585 ) وحسَّنه الألباني في " صحيح الترغيب " ( 1536 ) .

{ ከዱዓዎች ሁሉ በላጩ የዐረፋ እለት ዱዓእ ነው:: እኔም ሆንኩ ከኔ በስተፊት የነበሩ ነብያት ከተናገሩት መካከል በላጩ ቃል :- ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም ፣ እርሱም ብቸኛና አጋር የሌለው ነው  ንግስናም ምስጋናም ለእረሱ ነው እርሱም በሁሉም ነገር ላይ ቻይ ነው የሚለው ቃል ነው:: }

(ቲርሚዚይ (3585) ዘግበውታል ፤ ኢማሙ አልባኒ ሰሒሕ አት’ተርጊብ (1536) ላይ ሐዲሡን ሐሰን ብለውታል።)

? https://t.me/HidayaTerbiya ?

Telegram

Hidaya Terbiya II ሂዳያ ተርቢያ

Hidaya Terbiya ሂዳያ ተርቢያ የመልካም ትውልድ ማፍርያ! @HidayaTerbiya

***?*** የዐረፋ ቀን ዱዓ
7 months, 1 week ago

? አስርቱ የዙልሒጃ ወርቃማ ቀናት

? በሂዳያ ተርቢያ

? ዙልሒጃ 01/12/1445

? #HidayaPublication

⭐️ https://t.me/HidayaTerbiya ⭐️

2 years, 5 months ago
***?***አስደሳች ዜና ለዒልም ፈላጊዎች!

?አስደሳች ዜና ለዒልም ፈላጊዎች!

በኡስታዝ ሱለይማን ዐብደላህ የሚሰጡ ቋሚ ትምህርቶችን በቴሌግራን Live ይከታተሉ።

የሚሰጡ ትምህርቶች፦

? የቁርኣን ተፍሲር

ዘወትር ረቡዕ ከ4:30 እስከ ዙሁር

? አል’ዐርበዑነ ፊ–ል’አሕካም

ቅዳሜ ከዐስር ሰላት በኋላ እስከ 12:00

? ቻናሉን በማስተዋወቅ የኸይር ተቋዳሽ ይሁኑ!

?@ustazsuleyman

2 years, 5 months ago

? የሂዳያ ስንቅ በነሲሓ ?

ወቅቱ ክረምትና የረፍት ጊዜ እንደመሆኑ መጠን

? ወላጆች ልጆቼ ጊዜያቸውን በምን ያሳልፉ ይሆን? የዲን ትምህርት የት ላስተምራቸው? ብለው የሚጨነቁበት ነው።

? ልጆችም በፊናቸው የትና በምን እንደሚያሳልፉ የሚብሰለሰሉበት ወቅት ነው!

እነሆ! ይህን ጭንቀታችሁን የምታቃልሉበት መፍትሄ ይዘን ከተፍ ብለናል!

ክረምቱን የዲን ዕውቀት ስንቅ የምትሰነቁበት ልዩ ገፀ በረከት!

? የሂዳያ ስንቅ በነሲሓ!

በአካል ሄደው መማር ለማይችሉ ዕድሜያቸው ከ8 -13 ላሉ ታዳጊዎች የተዘጋጀ አዲስ መጽሐፍ አዲስ የክረምት ኮርሰ በነሲሓ ቲቪ!

? ይህ ኮርስ ለታዳጊዎች እንዲሆን ታስቦ ቀለ ባለና ልዩ በሆነ መልኩ የተዘጋጀ ሲሆን፤ ለኮርሱ መስጫ አጋዥ መጽሐፍም ተሰናድቷል።

መጽሐፉ በውስጡ የዐቂዳ፣ ፊቅህ፣ ሲራ እና አደብ ትምህርቶችን ከመመዘኛ ጥያቄዎችን ጋር አካቶ ይዟል።

የመጽሐፉ ማብራሪያ ፕሮግራም በነሲሓ ቴሌቪዥን ይቀርባል።

? መጽሐፉን፦

ቤተል ነሲሓ ቲቪ ቢሮ እና

በኢብኑ መስዑድ ኢስላሚክ ሴንተር ቅርንጫፍ ጣቢያዎች ማግኘት ትችላላችሁ!

ለበለጠ መረጃ ስልክ፦
09 30 484284

አዘጋጅ፦ ሂዳያ ተርቢያ ከነሲሓ ቲቪ ጋር በመተባበር!

ምርጥ ትውልድ I #ክረምት #ኮርስ I

I #ሂዳያ #Hidaya #ተርቢያ #Terbiya I

? https://t.me/HidayaTerbiya ?

Telegram

Hidaya Terbiya II ሂዳያ ተርቢያ

Hidaya Terbiya ሂዳያ ተርቢያ የመልካም ትውልድ ማፍርያ! @HidayaTerbiya

***?*** የሂዳያ ስንቅ በነሲሓ ***?***
2 years, 6 months ago

የዐረፋ ቀን ዱዓ

ከዐብደላህ ብን ዐምር ብን አል’ዐስ እንደተወራው የአላህ መልእክተኛ እንዲህ ብለዋል፦

وعن عبد الله بن عمرو بن العاص رضي الله عنهما أن النبي صلى الله عليه وسلم قال

((خَيْرُ الدُّعَاءِ دُعَاءُ يَوْمِ عَرَفَةَ ، وَخَيْرُ مَا قُلْتُ أَنَا وَالنَّبِيُّونَ مِنْ قَبْلِي : لَا إِلَهَ إِلَّا اللَّهُ وَحْدَهُ لَا شَرِيكَ لَهُ لَهُ الْمُلْكُ وَلَهُ الْحَمْدُ وَهُوَ عَلَى كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ))

رواه الترمذي ( 3585 ) وحسَّنه الألباني في " صحيح الترغيب " ( 1536 ) .

{ ከዱዓዎች ሁሉ በላጩ የዐረፋ እለት ዱዓእ ነው:: እኔም ሆንኩ ከኔ በስተፊት የነበሩ ነብያት ከተናገሩት መካከል በላጩ ቃል :- ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም ፣ እርሱም ብቸኛና አጋር የሌለው ነው  ንግስናም ምስጋናም ለእረሱ ነው እርሱም በሁሉም ነገር ላይ ቻይ ነው የሚለው ቃል ነው:: }

(ቲርሚዚይ (3585) ዘግበውታል ፤ ኢማሙ አልባኒ ሰሒሕ አት’ተርጊብ (1536) ላይ ሐዲሡን ሐሰን ብለውታል።)

የዚህ ዱዓ አጭር እና ጥቅል ማብራሪያ!

«لَا إِلَهَ إِلَّا اللَّه»ُ

“ላ ኢላሃ ኢለላህ” (ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም) ይህ የመጀመሪያው የዱዓ ክፍል “ከሊመቱ ተውሒድ” የተውሒድ ቃል በመባል ይታወቃል:: ይህ ቃል በሁለት መሰረታዊ ማእዘናት የቆመ ሲሆን:: ነፍይ {ማራቅ/ውድቅ ማድረግ} እና ኢሥባት {ማጽደቅ} ይባላሉ:: በዚህም ይህ የተውሒድ ቃል መጀመሪያው ነፍይ መጨረሻው ደግሞ ኢሥባት ይሆናል::

“ላ ኢላህ”(አምላክ የለም) የሚለው ቃል ሙሉ ለሙሉ ከአላህ ውጪ ከሚመለኩ አካላት በጠቅላላ አምልኮን ውድቅ ሲያደርግና ሲያርቅ::

“ኢለላህ” (ከአላህ በስተቀር) የሚለው ደግሞ የአምልኮ  ተግባራትን በጠቅላላ ከነዓይነቶቻቸው ለአላህ ብቻ ያጸድቃል::

“ላ ኢላሃ ኢለላህ” ስንል ከአላህ በስተቀር ማንንም ምንንም አናመልክም ፣ ከአላህ በስተቀር ማንንም አንለምንም ፣ ከአላህ በስተቀር ለማንም አናርድም [በስሙ አንሰዋም {ለቀብርና ለጅን ለመሳሰሉት}] ፣ ከአላህ በስተቀር አምልኮን ለሌላ ለማንንም  ቅንጣት ታክል አሳልፈን አንሰጥም እያልን ነው::

﴿قُلۡ إِنَّ صَلَاتِي وَنُسُكِي وَمَحۡيَايَ وَمَمَاتِي لِلَّهِ رَبِّ ٱلۡعَٰلَمِينَ﴾ [الأنعام: 162]

‘’ስግደቴ፣ መገዛቴም፣ ሕይወቴም፣ ሞቴም ለዓለማት ጌታ ለአላህ ነው» በል፡፡’’ {አል አንዓም: 162 }

ይህ ነው ትክክለኛ  የተውሒድ ቃል የሆነችው “ላ ኢላሃ ኢለላህ” ትርጓሜ:: ነፍይ እና ኢሥባት በማቆራኘት እንጂ አላህን በብቸኝነት ተመላኪ ማድረግ አይቻልም:: እነዚህ ሁለት ማዕዘናት “ላ ኢላሃ ኢለላህ” ጸንታ እንድትቆም የሚያደርጉ ናቸው::

« وَحْدَهُ لَا شَرِيكَ لَهُ »

“ወሕደሁ ላ ሸሪከ ለሁ” (ብቸኛና አጋር የሌለው ነው) የሚለው ሁለተኛው የዱዓው ክፍል ደግሞ  የ “ላ ኢላሃ ኢለላህ”ን ትርጉምና ማዕዘናቱን የሚያጠናክር ነው::

“ወሕደሁ” (ብቸኛ ነው) የሚለው ኢሥባትን የሚያጠናክር ሲሆን ።

“ላ ሸሪከ ለሁ” (ተጋሪ የለውም) የሚለው ደግሞ ነፍይን ያጠናክራል::

በጥቅሉ ደግሞ “ወሕደሁ ላ ሸሪከ ለሁ” የሚለው “ላ ኢላሃ ኢለላህ” የምታመላክተውን ተውሒድ ያጠናክራል:: ተውሒድ ያለውን ታላቅ ደረጃና አንገብጋቢነትና ልዕቅናውን ያስገነዝባል::   

«لَهُ الْمُلْكُ وَلَهُ الْحَمْدُ وَهُوَ عَلَى كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ»

“ለሁል ሙልኩ ወለሁል ሐምዱ ወሁወ ዐላ ኩሊ ሸይኢን ቀዲር”

(ንግስናም ምስጋናም ለእረሱ ነው እርሱም በሁሉም ነገር ላይ ቻይ ነው።) 

የሚለው የዱዓው ክፍል ደግሞ  የተውሒድነ ማስረጃና መረጃዎቹን የሚጠቁም ነው::

አሸናፊና የበላይ የሆነው አላህ ከእርሱ ውጪ እውነተኛ አምላክ የለም ፣ ከእርሱ ውጪ በእውነት የሚመለክ እንደሌለ ያጠናክራል::

ንግስና ለእርሱ ነው ፣ በንግስናው ደግሞ ተጋሪ የለውም:: ምስጋናም በጠቅላላ ጥራት ለተገባው አላህ ነው:: ምክንያቱም አላህ በሁሉም ነገር ላይ ቻይ ነውና:: በሰማይም ይሁን በምድር አንዳችም የሚያቅተው ነገር የለም::

በመሆኑም ይህችን ታላቅ ቃል እጅግ የላቀችና በላጭ የሆነች ቃል መሆኗን ልንረዳ  ይገባል::

ይህን ጥያቄ ለጠየቀው ሰው አላህ መልካም ምንዳውን ይክፈለው አላህ በመልካም ይመንዳው።

የዕውቀት ባለቤቶች እንደሚሉት የምናደርጋቸውን ዱዓዎችና ዚክሮች ይህም ይሁን ሌሎች በአግባቡ የሚጠቅሙንና በእኛ ላይም መልካም ተጽዕኖ ማሳደር የሚችሉት ትርጉማቸውን እየተገነዘብን የሚያመላክቷቸውን ቁም ነገሮች እየተረዳንና እያስተነተንን የምናደርጋቸው ሲሆን ነው::

ያለበለዚያ  እንዲሁ በዘፈቀደ የምናነበንባቸው ከሆነ የምንለውን ሳናውቀውና ፣ የሚያመላክቱትን ቁም ነገር ሳንረዳ የምንል ከሆነ በእኛ ላይ የሚያሳድረው ተጽዕኖ እጅግ አናሳና ደካማ ይሆናል::

ለዚህም ነው አብዛኛዎቹ ሰዎች ይህንን ዱዓ እያደረጉ፦

“ላ ኢላሃ ኢለላህ ወሕደሁ ላ ሸሪከ ለሁ ለሁል ሙልኩ ወለሁል ሐምዱ ወሁወ ዐላ ኩሊ ሸይኢን ቀዲር”

ነገር ግን የሚሉትን በአግባቡ ስለማያውቁትና ስለማይገነዘቡት ይህንን ዱዓ አድርገው ብዙም ሳይቆዩ እጃቸውን አንስተው ከአላህ ውጪ ያለ አካል በማይችለው ነገር ላይ  “እከሌ ሆይ!  ድረስልኝ ከጭንቅ አውጣኝ” ሲሉ የሚደመጠው::

በአላህ እጠበቃለሁ! ከአላህ ውጪ ያለን አካል እጁን አንስቶ  ከለመነ “ላ ኢላሃ ኢለላህ” ያለው የታል ??? የታለ ተውሒዱ???

﴿وَمَنۡ أَضَلُّ مِمَّن يَدۡعُواْ مِن دُونِ ٱللَّهِ مَن لَّا يَسۡتَجِيبُ لَهُۥٓ إِلَىٰ يَوۡمِ ٱلۡقِيَٰمَةِ وَهُمۡ عَن دُعَآئِهِمۡ غَٰفِلُونَ﴾ [الأحقاف: 5] 

“እስከ ትንሣኤ ቀን ድረስም ለእርሱ የማይመልስለትን ከአላህ  ሌላ ከሚጠራ ሰው ይበልጥ የተሳሳተ  ማነው? እነርሱም  ከጥሪያቸው  ዘንጊዎች  ናቸው፡፡”

{አል አህቃፍ :5 }

ስለዚህም ይህንንም ይሁን ሌሎች ዱዓዎችና ዚክሮችብ ስናደርግ ትርጉሙን በትክክል መገንዘብ ፣ የሚያመላክቱትን ቁም ነገር ማስተዋልና ማስተንተን አንገብጋቢ ጉዳይ ነው:: ይህን ማድረግ ስንችል በራሳችን ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ እና  ላቅ ያለ ጥቅምን ማግኘት እንችላለን::

ምንጭ ፦ (ሸይኽ ዐብዱረዛቅ አል በድር (አላህ ይጠብቃቸው) “ፈዳኢሉ የውም ዐረፋ” በሚል ርዕስ በዙልሒጃ 8 / 12 / 1436 ባደረጉት ሙሐደራ ላይ ከትምህርቱ በኋላ ይህን ዱዓ እንዲያብራሩላቸው ከታዳሚ ለቀረበላቸው ጥያቄ ከሰጡት ምላሽ ለፅሁፍ በሚያመች መልኩ የተረጎምኩት ነው::)

{ሐይደር ኸድር}

[ሰኞ (የውሙ ዐረፋ)
ዙልሒጃ 9 / ነከ 12 / 1439
August 20 / 8 / 2018
ነሀሴ 14 /12 /2010]

? https://t.me/SabahTube
۩••۩┈┈┈•⊰۩?۩⊱•┈┈┈۩••۩

ጠቃማዊ መልዕክቶች እንዲደርስዎ…

? Join Me

? ሼር ማድረግ እንዳይረሱ!

?Telegram:
? https://t.me/haiderkhedir

? YouTube: https://youtu.be/zYoslq8zj6Qክነከ

2 years, 10 months ago
***?*** ሂዳያ በነሲሓ የታዳጊዎች የረመዳን ኮርስ! …

? ሂዳያ በነሲሓ የታዳጊዎች የረመዳን ኮርስ! ?

ለበለጠ መረጃ ስልክ፦
0930484284

ሂዳያ ተርቢያ ከነሲሓ ቲቪ ጋር በመተባበር

ምርጥ ትውልድ I #ረመዳን #ኮርስ I

I #ሂዳያ #Hidaya #ተርቢያ #Terbiya I

? https://t.me/HidayaTerbiya ?

2 years, 10 months ago

? ልጆችዎን የሚያስደስቱበትና ውስጣቸውን የሚገነቡበት ድንቅ ቃላት!

? እወድሃለሁ I እውድሻለሁ
? አምንሃለሁ I አምንሻለሁ
?አንተ/ቺ በጣም ውድ የአላህ ስጦታ ነህ/ሽ
? አስተያየትህን/ሽን አከብራለሁ
? አንተ/ቺ ድንቅ ልጅ ነህ/ሽ
? አንተን/ቺን ማዳመጥ ደስ ይለኛል
? ና/ነይ ላቅፍህ/ሽ
? ምን ማድረግ ትወዳለህ/ጃለሽ?
? በውጤትህ/ሽ ረክቻለሁ
? ድካምህ/ሽ እረዳለሁ
? ስላየሁህ/ሽ ደስ ብሎኛል

ምርጥ ወላጅ I #ለወላጆች I

I #ሂዳያ #Hidaya #ተርቢያ #Terbiya I

? https://t.me/HidayaTerbiya ?

Telegram

Hidaya Terbiya II ሂዳያ ተርቢያ

Hidaya Terbiya ሂዳያ ተርቢያ የመልካም ትውልድ ማፍርያ! @HidayaTerbiya

***?*** ልጆችዎን የሚያስደስቱበትና ውስጣቸውን የሚገነቡበት ድንቅ ቃላት!
2 years, 10 months ago

ሲሞቱ ብቻ አንውደዳቸው!
ለዓሊሞች ትኩረት እንስጣቸው

ሰዎችን ዓለሊሞችን እውነት ከወደድናቸው …

ሲሞቱ እንባ ከማፍሰስ ዛሬ እንባቸውን እናብስላቸው ፤ ሀዘን ቤት ከመመላለስ በሕይወት እያሉ ደጋግመን እንጠይቃቸው፤
ችግራቸውን እንካፈላቸው ፤
እናፅናናቸው ፣ እናበርታቸው ፤

ለቀብራቸው እንደምንጎርፈው ዛሬ ከጎናቸው ሆነን አለኝታነታችን እናሳያቸው!

የእውነት ከወደድናቸው ዛሬ አለሁላችሁ እንበላቸው! ሲሞቱ ብቻ አንውደዳቸው!

የመልዕክቱ ዓላማ ሰዎች ከሞቱ በኋላ የሚደረጉ መልካም ሥራዎችን ለማሳናስ ሳይሆን ቅድሚያ ማድረግ የምንችላቸውን ጠቃሚ ተግባራትን ማስታወስ ነው።

https://t.me/AYAMedia

Telegram

AYA Media II አያ ሚዲያ

AYA Media II አያ ሚዲያ ትላንትን ማያ – ነገን ማደሽያ ስለ ቻናላችን ያሎትን ሀሳብና አስተያየት በ @Haicrosoft ይላኩልን! እናመሰግናለን! ★ አነቃቂ መልዕክቶች ★ ማህበራዊ ጉዳዮች ★ ጠቃሚ መረጃዎች የሚቀርቡበት ቻናል! #አያ\_ሚዲያ https://m.youtube.com/user/haiderrkedirtv

ሲሞቱ ብቻ አንውደዳቸው!
2 years, 11 months ago

ተግባራዊ ትምህርት…

ውድ አባት ሆይ! ለልጅህ ምርጥ አባትና መልካም አርዓያ መሆን ከፈለግክ፤ ለልጅህ ይህን አድርግ ይህንን አታድርግ የሚሉ ትዕዛዛትን ብቻ ከማስተላለፍ ይልቅ በተግባራዊ ምሳሌ ለማስረዳት ሞክር።

ለምሳሌ የመተባበርን ጥቅም ልታስተምረው ከፈለግክ በቤት ውስጥ አንዳንድ ስራዎችን አንተ መስራት ጀምርና ልጅህ እንዲረዳህ ጠይቀው። ባለቤትህ እገዛህን ፈልጋ ትብብር ስትጠይቅህ ቀና ምላሽ በመስጠት እድሜ ልኩን የማይረሳውን ትምህርት ስጠው።

ምርጥ አባት I #ለአባቶች I

I #ሂዳያ #Hidaya #ተርቢያ #Terbiya I

? https://t.me/HidayaTerbiya ?

Telegram

Hidaya Terbiya II ሂዳያ ተርቢያ

Hidaya Terbiya ሂዳያ ተርቢያ የመልካም ትውልድ ማፍርያ! @HidayaTerbiya

ተግባራዊ ትምህርት…
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 3 недели назад

Last updated 2 недели, 2 дня назад

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated 1 месяц назад