ABRET PRO

Description
የአብሬት እንዲሁም የቃዲሪይ ሲልሲላ መንዙማዎችን ፣ ከአካቢሮች የሰማናቸውን ቀሰሶች ፣ እንዲሁም ከመሻኢኾቻችን ኪታቦች አንዳንድ ጠቃሚ ነገሮችን የምንማማርበት አጠቃላይ የሀድራ ስራዎችን የምንዘክርበት ቻናል ነው
@Abretpro
Advertising
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated hace 3 semanas, 5 días

Last updated hace 3 semanas

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated hace 1 mes, 1 semana

3 months ago

ግዜ ይበራራል... መጨረሻ ያለው ነገር ብዙም ግዜ ቢሆን መጥቶ ይደርሳል... መጀመሪያ ያለው ነገር አውሰጥ አለው... አውሠጥ(መሀል) ያለው ነገር መጨረሻ አለው... መጨረሻ ያለው ነገር ሁሉ መጨረሻው ቶሎ መጥቶ ይደርሳል::

መላይካ ብዙ ዘመን የሚኖሩ አሉ... በብዙ ሚሊየን አመት የሚቆጠር አመት የሚኖሩ አሉ... ቢቆዩም መጨረሻቸው ያው ሞ^ት ነዉ::

ሰው ሀሳቡ ምኞቱ ብዙ ነው... ይመጣል የተባለው ዘመን የሚመጣ አይመስለውም... ልጅ የሆነ እንደሆነ አድጌ ፂም አበቅላለው ብሎ አይልም... ደርሼ ሽማግሌ እሆናለሁ ብሎ አይልም... ሁሉም ግን ወዲያውኑ መጥተው ይደርሳሉ::

ከሰው ብዙ የኖረው 1000 አመት ነው:: አንድ ሁለት ሰዎች ከዛ የጨመሩ አሉ እንጂ... ሺ አመት የቆየውም ጨርሶ ሄዷል... ሰው የሆነ እንደሆነ እንደ እንጨት ቆሞ የሚኖር ነገር የለም:: እድሜው ትንሽ ነው... የሰራበት ከሆነ ብዙ ነው እንጂ ካልሰራበት እድሜው ትንሽ ነው... ዛሬም የሞተ ሰው በነብዩሏህ አደም(አ.ሰ) ግዜ ከሞተ ሰው ጋር ሄዶ ይቀላቀላል...

✍🏻ከሸምሰ ዲነል አብሬትይ ሠይዲ አባራሙዝ(ቀ.ሢ) ወአዝ የተወሰደ

3 months, 2 weeks ago

✍🏻ክትበ ስንብት በኸውላን ሰይድ
ክፍል-3

8ቀን እለተ እሮብ ወርሃ ነሃሴ 2016 ከቀኑ 11ሰአት ሼሆቹ እቺን አለም ትተው ተሻገሩ...
(በሰፈር 10 1446 እንደ ሂጅራ አቆጣጠር)
ትላልቆቹን ያለፉበትን ቀን ዘግቦ ያስቀመጠ፣ ያስተላለፈ፣ ለሌሎች የተናገረ ያለፉት የሼሁ ሙሀባ በእሱ ላይ ግዴታ ይሆንለታል ፦ ጀማሉ ዲን አል አንይ ኪታብ የተወሰደ...
እናም ሼሆቹ የሄዱበትን ቀን ፃፉት፣ አስተላልፉት፣ ተናገሩት ውዴታቸውን ታሸንፉበታላቹ...

ወንድሜ ረስተከው ከነበር ሞ^ት እውነት ነው... ቀብርም እውነት ነው... ሞቶ መነሳትም እውነት ነው... አላህ(ሱ.ወ) ፊትም በእርሱና በሰራከው መሀከል አንዳችም ሂጃብ ሳይኖር መቆሙ እውነት ነው...
የሰው ልጅ ወንጀልን ምንም አልሰራሁም ብሎ ይምላል አሉ... በሰራው ላይ መስካሪው አላህ(ሱ.ወ) እንደሆነ የረሳው ይመስላል...

ጌትዋና(የአብሬቱ ሁለተኛ ኸሊፋ ሸህ ሰይዲ ባኡ ሳሊስ) አባታቸውን ለመዘየር በእናንገራ ተገኝተዋል...

በወክቱ የአብሬት ግምጃ ቤት አስተዳደር የነበረውን አህመድ ጉርባን አስጠሩት...
"ለበይክ ጌየትዋና!!" መለሰ...

ጌትዋና ከቀናት በፊት በአፍጥር በኩል በበቅሎዋቸው ተጭነው ሲያልፉ አንድ ገበሬ የሰፈር አማራ ሰፈር የሚባለው ቦታ ላይ የዘራውን ጤፍ አይተው ቦታው ቢዘራበት የሚሰጥ መሆኑ ስለተረዱ ከመሬቱ ቆርሶ እንዲሸጥላቸው አስማምተውት አፍጥር ሰፈር አካባቢ መሬት ገዝተውት ነበር...
"ለአንድ ለጠና ጉዳይ ፈልገንክ ነበር..." ጌትዋና ቀጠሉ "ከአብሬት በታች ከአፍጥር ገብያ አቅራቢያ በምትገኝ መንደር የሰፈር አማራዎች በሰፈሩበት ሰፈር የተባለ ቦታ ላይ አንድ መሬት ገዝቻለሁ... እና ይህንን መሬት አንተ አንድ የምትተማመንበትን ሰው ጨምረህ ጤፍ እንድትዘራበት ትእዛዝ ልንሰጥህ ነው..." ጌትዋና ተናግረው እንደጨረሱ በሀያ የተደፋውን አንገቱ ቀና ሳያደርግ አህመድ ጉርባ "አይ ጌየትዋና ከሰው፣ ከሙሪድ አርቃቹ አትጣሉኝ..." ንግግሩ ከጌትዋና የመራቁን ብሶት አሳስቦት እንጂ የድፍረት አይደለም...

ጌትዋና የአህመድ ጉርባ ጭንቀት ስለገባቸው ቅር ሳይሰኙ የማባበል ያህል "ከቀናት በፊት በኢሻራዬ ሱራዲቀተል ጀላል ላይ አንዲት የተለየች ከዚህ ቀደም አስተውያት የማላውቃትን ኑር አየሁ... የዚህችን ኑር ምንነት ለአንድ የአላህ አገልጋይ ጠየኩት እሱም 'ይህች ኑር ከአለመል አርዋህ አላህ(ሱ.ወ) ሊፈጥር ያወረዳት ሩህ ናት...' ብሎ መለሰልኝ ኑሩዋ ስለገነነብን ስሯን አስተዋልነው(ጌትዋና አንድ ከነሱ ውጪ ያልተሰጠች ስጦታቸው የአንቢያ ሆነ የአውሊያ አልያም የአህለ ሲር ደረጃን ጠንቅቀው ቦታውን ያውቁታል) ... እናም ከሌላ ሊፈጥረው የነበር ቢሆንም ይህ ሩህ ከኛ እንዲያደርገው ሀድረተላህ ተመላልሰን አላህም(ሱ.ወ) እሺ ብሎናል..." ጌትዋና አህመድ ጉርባን ተመለከቱት አሁንም አንገቱን ደፍቶዋል "እና የኛ ችግር የአንተ ችግር አይደል... ይህ ያልኩህ ልጅ በሀገራችን በሰፊው የሚበላውን ቆጮ ማይበላ ነው... ታዲያ አህመድ የኛ እንግዳ የአንተ እንግዳ አይደለም በወጉ አትቀበለውም..." ጌትዋና ንግግራቸውን እንደጨረሱ አህመድ ጉርባ ጉልበታቸውን ስሞ ወደ አብሬት በመሄድ አንድ በጉብዝናው የሚያምንበትን ጎልማሳ ይዞ ወደተባለው ቦታ ወረደ...

እቦታው ላይም ለራሱ ማደሪያ እልፍኝ፣ ለእህልም ማከማቻ የሚሆን ጎተራ በሰዎች ረዳትነት አቁሞ ግንቦት ላይ ገምሶ፣ በሀምሌ ዘርቶ እና አረሶ፣ በመስከረም አርሞ፣ በህዳር አጭዶ፣ በጥር ወቀቶ አመረተ በመቀጠልም እንደወጉ ጎተራ አስገብቶ ከመረ... ባበጀው መቀርቀሪያ ዘግቶ ወደ አብሬት አቀና...

አህመድ ጉርባም አብሬት እንደደረሰ ጌትዋና ዝያራ ቤት መሆናቸውን ስለተረዳ ወደዝያራ ቤት በመሄድ እጃቸውን ስሞ የጎተራውን ቁልፍ አስረከባቸውና "ያ ቆጮ አይበላም ያላቹት ልጅ የታል?" ብሎ ጠየቃቸው...

ጌትዋናም የጎተራውን ቁልፍ መልሰው እየሰጡት "ያማስ የኛ እና የአንተ ሚስጥር ነው... ያልኩህ ልጅ እናቱ ሌላ ቦታ አግብታ እየኖረች ነው... እኛ ጋር ልትገባ ገና ሶስት አመት ይቀራታል... እስከዛ ይህም ቁልፍ አንተ ጋር ይሁን ጎተራውም አመት ሞልቶ አዲስ ዘር ሊታጨድ ሲል ያለፈውን ለደረሳ ስንቅነት እያውልክ ስራህን ቀጥል..." አህመድ ጉርባ ይህንን ትዛዝ ተቀብሎ እጅ ስሞ ወደ መጣበት ዳግም ተመለሰ...

አህመድ ጉርባ እንደተናገረው "ጌትዋና ባዘዙኝ ሁኔታ ሶስት አመት ከቆየሁ በሃላ አንድ ቀን አስጠሩኝ... ወደ አንድ እልፍኛቸው ገባሁ እጃቸውን ዘየርኩኝ... ከጎናቸው መልከመልካሞቹ እሜት ዘሃራ(የጌኔ አዲ) ተቀምጠዋል... ገና የጌትዋና እና የእሜት ዛሃራ ኒካህ የታሰረ ቀን ነው... 'አህመድ ያልኩህ ልጅ እናት እሷ ናት የጎተራውን ቁልፍ አስረክባት...' የሚል ትእዛዝ ሰጥተውኝ ቁልፉን ለእሜት ዛህራ አስረከብኩኝ..."

ይህ የፅሁፍ ከዚህ በሃላ:-
ክፍል-4 ስለ አወላለዳቸው
ክፍል-5 ስለ አስተዳደግና የቂርአት ሂወታቸው
ክፍል-6 ስለ ሂወታቸው በአጭሩ
ክፍል-7 ለሙስሊሙ እንዲሁም ለሌላው ማህበረሰብ ስላበረከቷቸው አስተዋጽኦች
ክፍል-8 ስለ ኪታቦቻቸው
ክፍል-9 ስለ ስንብታቸው የሚያወሩ 6 ክፍሎች ይኖሩታል...

ይቀጥላል!!!
አላበቃሁም!!!

3 months, 3 weeks ago

ወደ ቀልባቸው ምልስ አሉና እሜት ዛህራ ሶስቴ የታላቁን የአብሬት ሸህ ስም ጠሩ "ዝናዎን ሰምቻለው፣ ስራዎን ሰምቻለው ሰው እንደሚሎት ከሆናቹ ለዚህም ቢሆን መላ አታጡም..." ለመጀመሪያ ግዜ ከአብሬትዮቹ ጊያሳ ጠየቁ...

ብዙም ሳይቆይ የኒካዋ ቀን በደረሰችበት አጥብያ በአፄ ኃይለሥላሴ ክስ ቀርቦበት ሊያገቡት የነበረው የባላቸው ወንድም ታሰረ... 'እድሜ ይፍታህ' ተፈረደበት...

እሜት ዛህራም ይህንን ሲያዩ የሟች ባላቸውን ንብረት በአደራ ለዘመዶቻቸው ሰተው 'ለአባቴ ቁርአን አስቀራለሁ...' በማለት ከሁለት ሴት ልጆቻቸው ጋር ወደ ኧዣ አገና ወረዱ... ያው የሴትነት ወጉ ይዟቸው ኖሮ እንጂ ራሳቸው ለአብሬትዮቹ ሽምግልና ቢልኩ ደስ ይላቸው ነበር...

ገና የአባታቸው እልፍኝ ከመግባታቸውም ዳግም አጎታቸው ሸህ አህመድ ድባባ ከአብሬትዮቹ ሽምግልና ተልከው መጡ...

እሜት ዛህራ በአሁን የአጎታቸው አመጣጥ ምክንያቱ ግልፅ ስለነበር... ለትልቅ እንግዳ የሚቀርበውን ዱክቸ አሰርተው አበሏቸው...

ሸህ አህመድ ድባባ ይህንን ሲያዩ የወንድማቸው ልጅ እንቢታቸውን ወደ እሺታ መቀየራቸው ገባቸው... ሆኖም በአብሬትዮቹ የተላከ አንድ ደብዳቤ ነበርና እሱን ደብዳቤ አነበቡላቸው...

ደብዳቤው ሲነበብ ቆመው ሰሙ... ጉንጭ በእንባ ራሰ...

ሳይቀመጡም በቆሙበት "ለሸሆቹ እሜት ዛህራ አንድ ልመና አላት... ይህንን ልመና እሺ ያላቹ እንደሆን እሷም ለጋብቻው እሺ ብላለች ብላቹ ንገሩልኝ..."

ሸህ አህመድ ድባባ መስማማታቸውን አንገታቸውን ነቅንቀው ገለፁ...

እሜት ዛህራም ቀጠሉ "የእኔና የእናንተ ነገር ተነግሮኛል መጀመሪያውንም ማብቂያውንም አውቀዋለሁ... ስለዚህ የእኔ ልመና በዱንያ ብቻ ሳይሆን በአሄራም የእርሶ ሚስት እንድታረጉኝ ነው..." አቤታቸውን አሰሙ...

የዛኑ ቀን ሸህ አህመድ ድባባ ለአብሬትዮች የእሜት ዛህራን ልመና አደረሱ አብሬትዮቹም መስማማታቸውን ገለፁ...

ከወራት በሃላ እሜት ዛህራ አቦ ሐምዛ ኢዳቸውን ጨርሰው ወደ አብሬት በመውረድ ሸህ አህመድ ድባባ ወኪላቸው ሆነው ከሸህ ሰይድ ባኡ ሳሊስ ጋር ኒካህ ታሰረ...

እሜቴ የእርሶን ሸፈአ እንጂ ለችግሬ ወጥቼ ወርጄ ሌላን ዘዴን አላገኘሁም...

አላበቃሁም!!!
ይቀጥላል!!!

6 months ago

አሚሩና መንገደኛው

የሰራዊት ሁላ አምላክ የሆነው አላህ(ሱ.ወ) ስራው እጅግ ነው በግልፅ ከከውነው በድብቅ የሰራው እጅግ ይበልጣል...

በዘረጋው ከውን ላይ ሁላ ቋሚ የማይቀያየር አንዲትም የለም... ቋሚ የነገራቶች መለዋወጥ ብቻ ነው... ዛሬ የተወለደ ነገ ጎልማሳ፣ ከነገ ወዲያ አዛውንት፣ ከዛም አፈር ነው...
ያ የሰራዊቱ አምላክ አላህ(ሱ.ወ) ግን የፈጠራቸውን በሰማያትም ሆነ በምድር ካሉ የአንዳቸውን ባህሪ አልወረሰም... ቋሚ ሳይለውጥ ዘውታሪ እሱ ብቻ ነው... ቦታን ከመፍጠሩ ፣ ወቅትን ከማስገኘቱ ፣ አቅጣጫዎችን ከመከፋፈሉ በፊት እንደነበረው ሳይለወጥ ዛሬም ላይ አለ ፣ ከዚህም ወዲያ እንዲያውም ይሆናል...

እናም የጌታውን ጓዳ ዘልቆ ስላየ ስለ አንድ የሱፍዮች አባት ላጫውትህ...
ይህ ሰው ከዘመናት በፊት እንደነበሩ እንደ ሀቂቃ ሱፍዮች ስምህ ማነው ካልከው "ሙሳፊር(መንገደኛ)" ከማለት የዘለለ የስም እንኳ ባለቤት መሆንን ነብሳቸው ላይ ሀራም ካረጉ የአላህ ወዳጅ ነበር...
ብቻ ከሊማው ስለ አምላኩ አላህ(ሱ.ወ) ለሰዎች ማስተማር መናገር ነው...
እናማ የሚስሩ አሚር የነበረው አብድ አል-ሐኪም ይህንን የጌታው ወዳጅ መቃብር ስፍራ ብቻውን ሲያወራ ያየዋል...

ትእይንቱ ስለገረመው ፈረሱን ከአጃቢዮቹ ጋር ወደ ሙሳፊሩ ያስጠጋውና ልጓሙን ይይዘዋል...
"አንተ እብድ ከሙታኖች መሐል ምን ትሰራለህ?" አሚሩ ጠየቀ...

"አሚር ሆይ ሰው ልጠይቅ ነው አመጣጤ..." ሙሳፊሩ መለሰ...

አሚሩና አጃቢዮቹ በሳቅ አስካኩ... "ከሙታን መሀል ማንን ፈልገክ መጣህ ታዲያ?" አሚሩ መልሶ ጠየቀ...

"አንድ ንጉስን በዚሁ በአንተ ግዛት ከፊትህ ንጉስ የነበረ በስልጣኑ ህዝቦቹን ሲበድል ኖሮ ያለፈ..." መለሰ ሙሳፊሩ...

"ታዲያ ምን ጠየከው...." አሚሩ...

"ያ የምትኮራበት ስልጣንህ አሁንም አለ ይሁን?? ብዬ ጠየኩት...
"አንድም በጉልበቱ ደካሞችን ይበድል የነበረ ጉልበተኛ ነበር...  እሱንም ጠየኩት ያጉልበትህ አሁንም አለ ይሁን?? ብዬ...
"አንድም በንብረቱ ምስኪኖችን አስታውሶ የማያውቅ ባለ ሀብት ነበር... እሱንም ሀምሳ የግመል ቅፍለት የማይሸከመው ንብረትህን እንዴት አደረከው ይዘከው ተሻገርክ ወይስ?? ብዮ ጠየኩት...
"አንድም አዋቂ፣ ጥበበኛ፣ ሙሁር ነበር... እሱንም ያ የምትኮራበት እውቀትህ አለ ይሁን?? ብዬ ጠየኩት...
"አንዲትም ቆንጆ መልከ መልካም ሴት ነበረች... እሷንም ጠየኳት ያ የምትኩራሪበት መልክሽ አሁንም አለ ይሁን??ብዬ...
"አንድም ዘመደ ቡዙ ሁሌ በወዳጆች የታጀበ ግለሰብ ነበረ... በዘመድ ወዳጆቹ በጣም የሚተማመን... እሱንም ጠየኩት ከዘመድ ወዳጆችህ ስንቶቹ አሁንም አሉ?? ብዬ..." ትንፋሹን መሳብ የከበደው ያህል እየቀዘፈ አይኑ ቀይ ሆኖ ወደ ሰማያት እየተመለከተ ሙሳፊሩ የተጠየቀውን መለሰ...

አሚሩና አጃቢዮቹ በሙሳፊሩ ምላሽ ልቦናቸው ተነካ... ሳቃቸው ወደ እንባና ኩርፊያ ተቀየረ...

አሚሩ መለሰና "ታዲያ ምን ብለው መለሱለህ..." ጠየቀ...

"ወዳጄ አፈር ክፉ ነው ማይወሰደው የለም ሁሉን ወስዶታል ብለው መለሱልኝ..." እጁን እያወራጨ መለሰ...

"ታዲያ የአላህ(ሱ.ወ) ወዳጅ አፉ በለንና የከጀልከውን ሁላ ንገረን የቀልብህን ሁሉ እንሙላው..." አሚሩ ከፈረሱ እየወረደ...

"ከጠየከኝማ እንዳንተ ያለ ምን ልስጥህ የሚል ሰው ስፈልግ ነበር..."

ይቀጥላል...

የሞቀ ቤት በቀዝቃዛው ቀብር ይለወጣል...
✍️በኸውላን ሠይድ

6 months, 1 week ago

?ከላይ የተለቀቁት ፒዲኤፎች አንዱ የአመት መጨረሻ ላይ ሌላኛው ድሞ የአመት መጀመሪያ ላይ የሚደረጉ ዱዓኦች ናቸው:: ዛሬ ከመግሪብ ቡኃላ የመጨረሻ አመት መዝጊያና መክፈቻ ነው::

@mededulhabib

6 months, 1 week ago
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated hace 3 semanas, 5 días

Last updated hace 3 semanas

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated hace 1 mes, 1 semana