Unlock a World of Free Content: Books, Music, Videos & More Await!

ሐዋርያዊ መልሶች

Description
በክርስትና ላይ ለሚነሱ ጥያቄዎች ሐዋርያዊ መልሶችን ለማቅረብ የምንሞክርበት ቻናል

YouTube፡
https://www.youtube.com/channel/UCNR0pStqUuWVKs7elJMYmlQ
Advertising
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 2 days, 4 hours ago

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated 2 weeks, 5 days ago

Last updated 2 weeks, 5 days ago

1 month, 2 weeks ago

ዛሬ ቅዳሴ ላይ ከተነበበው የቅዱስ ጳውሎስ መልእክት

ወደ ገላትያ 5
14፤ ሕግ ሁሉ በአንድ ቃል ይፈጸማልና፥ እርሱም፦ ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ፡ የሚል ነው።

ተወዳጅ መልእክታትን የጻፈ ይህ ሐዋርያ “ሕግ ሁሉ በፍቅር ይፈጸማል” ይለናል.. በሌላ ክፍልም እንዲህ ይላል:

ወደ ሮሜ 13
9፤ አታመንዝር፥ አትግደል፥ አትስረቅ፥ በውሸት አትመስክር፥ አትመኝ፡ የሚለው ከሌላይቱ ትእዛዝ ሁሉ ጋር በዚህ፦ ባልንጀራህን እንደ ነፍስህ ውደድ፥ በሚለው ቃል ተጠቅልሎአል።

ለምን ነው እነዚህ ሁሉ ትእዛዛት ሌላውን ውደድ በሚለው ውስጥ የሚጠቃለለው..?? ምክንያቱም በምትወደው ሰው ላይ እነዚህን ሁሉ ትእዛዛት አትተላለፍምና ነው.. ለምሳሌ በምትወደው ሰው ላይ በውሸት አትመሰክርበትም፣ የምትወደውን ሰው አትገድልም.. ሌሎችንም እንዲሁ አትፈጽምም..

ስለዚህም ቀጣይ እንዲህ ይላል..

“ፍቅር ለባልንጀራው ክፉ አያደርግም፤ ስለዚህ ፍቅር የሕግ ፍጻሜ ነው።”

ወንድሙ ሐዋርያው ዮሐንስ ደግሞ እንዴት መዋደድ እንዳለብን ሲናገር: “ልጆቼ ሆይ፥ በሥራና በእውነት እንጂ በቃልና በአንደበት አንዋደድ።” ይለናል [1ኛ ዮሐንስ 3:18]

ስለዚህ እናንተን መውደዴ በሥራ ሊገለጥ ሊታይ ይገባዋል.. ጌታ እርስ በእርስ በእውነት እንድንዋደድ ይርዳን..

መልካም የጌታ ቀን😊🤗

@Apostolic_Answers

1 month, 2 weeks ago

ጥያቄው:

ክርስቲያኖች ብዙ ስንሆን አንድ ሥጋ ወይም አካል የሆንነው ከምን የተነሳ ነው..??

1 month, 2 weeks ago

ኧረ እኔ መልሳችሁን ሳየው ተሸማቀኩ አጠርኩ😁😁 እንደው ሌላ ሰው እንዳያይብን አጠፋሁት ሎል.. ከባቢሎን ምርኮ ተብሎ ሙሴ..?? ያውም የአሕዛብ ንጉሥ..??😭😭 አሮን..?? ፈርዖን..??😭😭

ለማንኛውም የፋርስ(Persia) ንጉሥ ቂሮስ(Cyrus) ነው..

እዝራ ምእራፍ 1 ብቻ አንብቡ..

3 months, 2 weeks ago

የእመቤታችንን እረፍቷን ማሰባችን በጣም መልካም ነው.. ወደ ካቶሊኩ ዓለም የተወሰነ ውዝግብ አለ ሞታለች አልሞተችም ከሚለው ጋር በተያያዘ.. ያው immaculate conception ከሚለው ትምህርታቸው ጋር ተያይዞ ጥቂቶች ሳትሞት ነው ያረገችው የሚሉም ስላሉ ማለት ነው.. እነርሱ ጋር ዶግማ የሆነው ማረጉዋ ነው..

እመቤታችን ምንም ኃጢአት ያላደረገች ፍጽምት ንጽሕት ብትሆንም እንደማንኛውም ሰው የአዳም ዘር ናትና ሞት ለእርሷም የሚገባ ሆነ.. ልጇ ወዳጇ ኢየሱስ ግን ሥጋዋን በመቃብር ሊተወው አልወደደም እና ወደ ሰማይ አፍልሶታል..

እመቤታችን ባለችበት ሆና አሁንም ስለ ደካሞች ስለ እኛ መጸለይን አታቋርጥብን.. እንኳን አደረሳችሁ ተወዳጆች..

3 months, 3 weeks ago

ነገረ ክርስቶስ ላይ በታሪክ ውስጥ በአባቶች ዘንድ ቴክኒካል የሆኑ ነገሮች ስላሉ ጥንቃቄ ይፈልጋልና በተለይ እኛ ሃገር ደግሞ የቃላት ውስንነት ይኖራል በጣም በዚህም ምክንያት ታሪካዊው ነገረ ክርስቶስ ሲጠና ትንሽ የሚያስቸግር ነገር ይኖራል..

እና ለአንባቢያን ብቻ የምትሆን አንድ ነገር ልናገር.. ነገረ ክርስቶስ ላይ "ከሁለት አካል" የሚለው አሳብ ላይ "አካል" የሚለው ምንድር ነው..?? የሚለውን መመርመር ይገባል.. ኬልቄዶንያውያኑ ሁፖስታሲስን እና ፕሮሶፖንን ሁሌም አንድ አድርገው ለ አካል(individual, ማንነት) ይሰጡታል.. ያው ፕሮሶፖን እንደዛ ነው.. ሁፖስታሲስ ግን ሁሌም individual(አካል) እንደማለት ሳይሆን የሆነ ባህሪ ቢኖር ያ ባህሪ የተገለጠበት ነገር(individuated የሆነበት አይደለም) ያ ነው ሁፖስታሲስ ብዙውን ጊዜ ነገረ ክርስቶስ ላይ.. ስለዚህም ማንነት(አካል) የሌለው ነገርም ባህሪ ይኑረው እንጂ ሁፖስታሲስ ይሆናል ማለት ነው.. ለምሳሌ ዲንጋይ..

ነገረ ክርስቶስ ላይ እኛ ሃገር "ከሁለት አካል" ስንል "አካል" ያልነው ፕሮሶፖንን ሳይሆንን ሁፖስታሲስን #ይመስለኛል.. ብዙ ጊዜ ደጋግሜ አይቼው possible የሆነ ያገኘሁት እና አሁን የደረስሁበት ነገር ይሄ ነው..

3 months, 3 weeks ago
5 months, 2 weeks ago

ኧኸ ሰዎች..

5 months, 2 weeks ago

ለእሼ ተዘመረ..??😬😬

https://vm.tiktok.com/ZM684Ljkc/

5 months, 2 weeks ago

ዛሬ ቅዳሴ ላይ ከተነበበው የቅዱስ ጳውሎስ መልእክት

ወደ ዕብራውያን 12
28፤ ስለዚህ የማይናወጥን መንግሥት ስለምንቀበል በማክበርና በፍርሃት እግዚአብሔርን ደስ እያሰኘን የምናመልክበትን ጸጋ እንያዝ፤

29፤ አምላካችን በእውነት የሚያጠፋ እሳት ነውና።

የማይናወጥን መንግስት እንቀበላለን አዎ.. ስለምንቀበል ምን እናድርግ..?? በማክበርና በፍርሃት እግዚአብሔርን ደስ እያሰኘን የምናመልክበትን ጸጋ እንያዝ..

ይህንን ባናደርግስ..??

"አምላካችን በእውነት የሚያጠፋ እሳት ነው"

ይቀጣል ወይም ያጠፋል ነው በብሉይ እንዲህ እንደተባለ:

ኦሪት ዘዳግም 4
23፤ አምላካችሁም እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር የተማማለውን ቃል ኪዳን እንዳትረሱ፥ አምላክህም እግዚአብሔር የከለከለውን በማናቸውም ቅርጽ የተቀረጸውን ምስል እንዳታደርጉ ተጠንቀቁ።

24፤ አምላክህ እግዚአብሔር የሚበላ እሳት ቀናተኛም አምላክ ነውና።

መልካም የጌታ ቀን

@Apostolic_Answers

7 months ago

ዛሬ ቅዳሴ ላይ ከተነበበው የጳውሎስ መልእክት ውስጥ

"በቀረውስ በጌታና በኃይሉ ችሎት የበረታችሁ ሁኑ።"
[ኤፌ 6:10]

ከላይ ጀምሮ በአንድ ቤተሰብ ውስጥ ያሉ ክርስቲያኖች እንዴት ሊኖሩ እንደሚገባ ወታደራዊ በሆነ መልኩ ይናገራቸውና : "በቀረውስ በጌታና በኃይሉ ችሎት የበረታችሁ ሁኑ።" ይላል.. ምክንያቱም ክርስቲያኖች የምርም ወታደሮች(ተዋጊዎች) ናቸውና.. ይህም ደግሞ መጋደላቸው ከደምና ሥጋ ጋር ሳይሆን ከክፋት መንፈሳውያን ሰራዊት ጋር እንደ ሆነ ቀጠል አድርጎ እዛው ክፍል ላይ ይነግራቸዋል..

ክርስቲያን ከሆንክ በቃ ውግያ ውስጥ ነህ.. ምናልባት ምንም ውግያ እያየህ ካልሆነ እጅ ሰጥተህ ተማርከህ ይሆናል..

አንድ ወታደር ሊዋጋ ሲወጣ ለመርታት በሚገባ ሊታጠቅ እንዲሁም ንቃት ሊኖረው ይገባዋል.. ውግያው ከክፋት መንፈሳውያን ሰራዊት ጋር ሲሆን ደግሞ እኚህ ሰራዊት የብዙ አመት ልምድ ስላላቸው(ቢያንስ የ7000 አመት) የእነርሱን ጦር የሚከላከል እንዲሁም ደግሞ የሚያጠቃ ሁነኛ የሆነ ትጥቅ ያስፈልግሃል..

ኢየሱስ: ጌታችን ኢየሱስ የዲያቢሎስን ሽንገላ የምንቃወምበት.. መልሰንም ደግሞ የምናጠቃበት ተዋጊያችን ነው.. ከእኛ የሚጠበቀው ይህንን ኢየሱስን መያዝ ነው.. እንዲዋጋልንም መፍቀድ ነው..

ስለዚህም የእግዚአብሔርን ቃል ወይም መልእክት መያዝ.. የእርሱን መንገድ እንድንከተል ያግዘናል.. እንዲሁም በእምነት ሆኖ መጸለይ..

ሁሌም ግን የነቃን እንሁን.. ለምንም አይነት ዲያቢሎሳዊ ወይም ሥጋዊ ሽንገላ(የሃጢአት አሳብ) እድል አንስጥ

መልካም የጌታ ቀን

@Apostolic_Answers

We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 2 days, 4 hours ago

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated 2 weeks, 5 days ago

Last updated 2 weeks, 5 days ago