ሐዋርያዊ መልሶች

Description
በክርስትና ላይ ለሚነሱ ጥያቄዎች ሐዋርያዊ መልሶችን ለማቅረብ የምንሞክርበት ቻናል..
YouTube፡ https://m.youtube.com/@apostolicanswers1
Advertising
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 2 months, 1 week ago

Last updated 6 days, 22 hours ago

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ ? @Esat_tv_comment_bot

??ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ??

Last updated 2 months, 3 weeks ago

4 days, 19 hours ago

ዌል ዌል😁😁

በሕይወት መጽሐፍ ስሙ የተጻፈ ሰው ስሙ ከዛ መጽሐፍ ላይ የማይደመሰሰው ድል ከነሣ ነው.. ልክ ጌታችን ለሰርዴስ ቤተ ክርስቲያን አባት መልእክትን ሲያስተላልፍ በሰርዴስ ስላሉ ሰዎች ሲናገር እንዲህ እንዳለው:

“ድል የነሣው እንዲሁ በነጭ ልብስ ይጐናጸፋል፥ ስሙንም ከሕይወት መጽሐፍ አልደመስስም..”
[ራእይ 3: 5]

——————//////—————-

“ወርሻለሁ.. ገብቻለሁ ወደ እረፍት” የሚል ንግግርም በጣም ጥንቃቄ ይፈልጋል.. መጽሐፍ እንዲህ ይላል:

“እንግዲህ እንደዚያ እንደ አለመታዘዝ ምሳሌ ማንም እንዳይወድቅ ወደዚያ ዕረፍት ለመግባት እንትጋ። “
[ዕብራውያን 4: 11]

ወደ እረፍት ለመግባት እንትጋ ነው ሚለው.. “ወርሻለሁ” የሚለው ላይም መጽሐፍ የሚለው ወራሾች ነን(እንወርሳለን) ነው እንጂ “ወርሰናል አለቀ” የሚል ዓይነት ነገር መጽሐፍ ቅዱስ ላይ አይቼ አላውቅም..

“ድል የሚነሣ ይህን ይወርሳል አምላክም እሆነዋለሁ እርሱም ልጅ ይሆነኛል።”
[ራእይ 21: 7]

@Apostolic_Answers

5 days, 8 hours ago

ጀማሪ ጴንጤ ትዝታው ሳሙኤል..

ወደ ቤተ ክርስቲያን እንድመለስ ታቦት መፈለጥ አለበት እያለ ነው.. በዚህ ንግግሩ ከመጽሐፍ ቅዱስ አንጻር ምን ያህል የክርስቶስ ጠላት እንደሆነ ይመልከቱ

https://vm.tiktok.com/ZMhK6pAxr/

———

6 days, 11 hours ago

“ለእኔ ሕይወት ክርስቶስ፥ ሞትም ጥቅም ነውና።”
[ፊልጵስዩስ 1: 21]

ቢኖር ክርስቶስን ያገለግላል ክብር ነው.. ቢገድሉትም ጌታን በመከራው መስሎት ወደ ዘላለም እረፍትና ክብር ይሸጋገራልና ለእርሱ ጥቅም ነው..

@Apostolic_Answers

1 week, 3 days ago

ዛሬ ቅደሴ ላይ ከተነበበው የቅዱስ ጳውሎስ መልእት ክፍል:

“እርሱም የማይታይ አምላክ ምሳሌ ነው። የሚታዩትና የማይታዩትም፥ ዙፋናት ቢሆኑ ወይም ጌትነት ወይም አለቅነት ወይም ሥልጣናት፥ በሰማይና በምድር ያሉት ሁሉ በእርሱ ተፈጥረዋልና ከፍጥረት ሁሉ በፊት በኵር ነው። ሁሉ በእርሱና ለእርሱ ተፈጥሮአል።”
[ወደ ቆላስይስ 1: 15-16]

ከጥቅሱ ላይ የተወሰኑ ነጥቦች:

  1. በሰማይ ያሉት ሁሉ በኢየሱስ ተፈጠሩ
  2. በምድር ያሉት ሁሉ በኢየሱስ ተፈጠሩ
  3. የሚታዩት ሁሉ በኢየሱስ ተፈጠሩ
  4. የማይታዩትም ሁሉ በኢየሱስ ተፈጠሩ
  5. ከፍጥረት ሁሉ በፊት በኩር(መጀመሪያ የተወለደ) ነው

ቅዳሴው ላይ ከጴጥሮስ መልእክት የተነበበ የሕይወት ምክር:

1ኛ ጴጥሮስ 1
13፤ ስለዚህ የልቡናችሁን ወገብ ታጥቃችሁና በመጠን ኖራችሁ፥ ኢየሱስ ክርስቶስ ሲገለጥ የምታገኙትን ጸጋ ፈጽማችሁ ተስፋ አድርጉ።
14፤ እንደሚታዘዙ ልጆች ባለማወቃችሁ አስቀድሞ የኖራችሁበትን ምኞት አትከተሉ።
15-16፤ ዳሩ ግን፦ እኔ ቅዱስ ነኝና ቅዱሳን ሁኑ፡ ተብሎ ስለ ተጻፈ የጠራችሁ ቅዱስ እንደ ሆነ እናንተ ደግሞ በኑሮአችሁ ሁሉ ቅዱሳን ሁኑ።
17፤ ለሰው ፊትም ሳያደላ በእያንዳንዱ ላይ እንደ ሥራው የሚፈርደውን አባት ብላችሁ ብትጠሩ በእንግድነታችሁ ዘመን በፍርሃት ኑሩ።

መልካም የጌታ ቀን@Apostolic_Answers

1 week, 4 days ago

ጋዲ ቅዱስ ሚካኤል ያደረገለትን ተአምር ተናግሮ ቪዲዮ ሰርቶ ቫይራል ሲወጣለት..

የቲክቶክ ስሙን.. “ጋዲሳ-ዘሚካኤል” ሎል

1 week, 5 days ago

ያው እኔ የሚጠቅማችሁን ነው ማጋራችሁ.. የዛሬው ደግሞ በጣም የተወደደ እና ትንሽ ብታበረታቱት በጣም አብዝቶ ሚጠቅመን ወንድም ነው ማርያምን.. ሁላችሁም ተቀላቀሉት.. እስቲ እንደተለመደው ሺህ እናስገባው

👇👇

@KidanZeIyesus@KidanZeIyesus

👆👆

2 weeks, 3 days ago

ዛሬ ቅደሴ ላይ ከተነበበው የቅዱስ ወንግል ክፍል..

“ሌላውም በእሾህ መካከል ወደቀ፥ እሾህም ወጣና አነቀው።”
[ማቴዎስ 13: 7]

ጌታ ቃሉን ወደ ልባችን ሲልክ ፍሬን እንድናፈራና ይበልጥ ወደ እርሱ እንድንቀርብ የሚያደርገን ነው.. ታድያ ግን በልባችን ውስጥ የዓለም የሆነው ምድራዊ አሳብ ሲነግስብን እርሱ እንደ እሾህ ይሆንና ወደ ልባችን የሚመጣውን የጌታን ቃል እንዳያፈራ ያደርገዋል.. ስለዚህም እንዲህ ያለው እሾህ ሊቆረጥ ይገባዋል..

እግዚአብሔር አምላካችን ፍሬን እናፈራ ዘንድ በጸጋው መልካም መሬት ያድርገን

መልካም የጌታ ቀን@Apostolic_Answers

2 weeks, 4 days ago

መዝሙር በጣም ሃሪፍ ነው..

ሻወር ስትወስዱ መጀመሪያ መዝሙሩን ክፈቱና እየሰማችሁ ውሰዱ🙄🙄

ስለዛ በየትኛውም ቦታ ይሰማል

2 weeks, 5 days ago

አቡነ በርናባስ ስለ ቅዱሳን ምልጃ🙄🙄

https://vm.tiktok.com/ZMhGNkKDD/

3 weeks, 4 days ago

እግዚአብሔር አምላካችሁ የሆነላችሁ እናንተ የተለያችሁ ምርጥ ሕዝቦች.. ይመቸን በስመአብ ጌታ ይመስገን የምር “አባ” ብለን የምንጠራው አምላክ ነው ያለን..

“አባ አባት ብለን የምንጮኽበትን የልጅነት መንፈስ ተቀበላችሁ..”
[ሮሜ 8: 15]

@Apostolic_Answers

We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 2 months, 1 week ago

Last updated 6 days, 22 hours ago

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ ? @Esat_tv_comment_bot

??ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ??

Last updated 2 months, 3 weeks ago