ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated 2 months, 2 weeks ago
Last updated 2 months, 1 week ago
ይህ ስለ Manchester United መረጃዎችን የሚያገኙበት የ Telegram ቻናል ነው 🇪🇹
--------------------------------------------------------------
☞︎| ስለ ማንቸስተር ዩናይትድ ትኩስ መረጃዎች
☞| ቀጥታ ስርጭቶች ከየስታድየሞቹ
☞| የዝውውር ዜናዎች
☞| ስለ ማንችስተር ዩናይትድ ታሪኮች
📩 ለማስታወቂያ ስራ DM :- @Marcoabdu
Last updated 1 month ago
የትራምፕ የጤና ፖሊሲ እርምጃዎች ምንድን ናቸው?
የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ትራምፕ ስልጣን እንደተቆናጠጡ ከፈረሟቸው ፕሬዝዳንታዊ ትእዛዛት መካከል ጤናን የሚመለከቱ ስር ነቀል ፖሊሲዎች በዓለም አቀፍ ደረጃ መነጋገሪያ ሆነዋል። አሜሪካን ከአለም ጤና ድርጅት (WHO) ከማስወጣት እስከ ቁልፍ የጤና ኤጀንሲዎች እስከ መዝጋት ድረስ ሰፊ ክርክር አስነስተዋል።
1️⃣ ከዓለም ጤና ድርጅት (WHO) መውጣት፡
ፕሬዚዳንት ትራምፕ አሜሪካ ከዓለም ጤና ድርጅት ለመውጣት ሂደቱን የጀመሩት ድርጅቱ የዓለም ጤና ጉዳዮችን በተመለከተ ያለውን ቸልተኝነት በመንቀፍ ነው። ትራምፕ የዓለም ጤና ድርጅት የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመግታት አፋጣኝ እና ግልጽ ስራ ባለመስራቱ ለቫይረሱ መስፋፋት አስተዋጽኦ አድርጓል ብሎ ያምናል። የቻይና ፖለቲካዊ ጣልጋ ገብነት አለበትም ሲሉ ከሰዋል።
ይህ እርምጃ የአለም አቀፋዊ የበሽታ ልየታ፣ ክትትል እና ምላሽ አሰጣጥ ስርዓቶችን ያዳክማል በሚል ስጋት ፈጥሯል።
2️⃣ የአሜሪካ የጤና ተቋማትን ኮሚኒኬሽን መዝጋት፡
የአሜሪካ በሽታ መቆጣጠሪያና መከላከያ ማእከል እና የመድኃኒት ቁጥጥር ባለስልጣንን ጨምሮ ሁሉም የፌደራል ጤና ኤጀንሲዎች የውጭ ግንኙነቶችን እንዲያቆሙ ትእዛዝ ተላልፏል። ይህ ከዚህ በፊት ታይቶ የማያውቅ መመሪያ ሲሆን አዲስ የበሽታ ወረርሽኝ ሲነሳ ወቅታዊ መረጃዎችን ለተቀረው አለም መንግስታትና ህዝብ ለማሰራጨት መዘግየት ይፈጥራል የሚል ስጋትን ጭሯል።
3️⃣ የዲኢአይ (Diversity, Equity, and Inclusion, DEI) መታገድ
ይህ ፕሮግራም በአሜሪካ ተቋማት ውስጥ አካታችነት፣ እኩልነት እና ፍትሃዊነትን ለማስፈን የወጣ ፕሮግራም ሲሆን ትራምፕ እንዲቆም ፈርሟል። ይህ እርምጃ በተቋማት ስራ ውስጥ ፍትሃዊ አካታችነት እና እኩልነት ለማስፈን የሚደረግውን ጥረት ወደኋላ ሊመልስ ይችላል ሲሉ ብዙዎች ተችተዋል።
4️⃣ የሮበርት ኬኔዲ የጤና ሚኒስቴር ሆኖ መሾም፡
ይህ ሰው በክትባት እና አንዳንድ የጤና አሰጣጥ ስርአቶች ላይ አወዛጋቢ አቋም እንዳለው ስለሚታዎቅ ስራዉን እንዴት ይመራው ይሆን የሚል የሰላ ክርክር አስነስቷል።
ለታዳጊ ሃገራት ጤና ምን ተጽእኖ ያመጣል?
እነዚህ እርምጃዎች የአሜሪካ መንግስት በጤና ፖሊሲ ላይ ከፍተኛ ለውጥ እያሳየ መሆኑን አመላካች ናቸው። ይህ ፖሊሲ በአሜሪካ ድጋፍ የሚሰሩ በርካታ የጤና ዘርፎችን፣ ህክምናዎችና እና ዓለም አቀፍ የጤና ትብብር ስራዎች ላይ ችግር ሊፈጥር ይችላል ሲሉ የጤና ባለሙያዎች እና ተሟጋቾች ስጋታቸውን አንጸባርቀዋል።
ለብዙ ታዳጊ ሃገራት የጤና ወጪ ከፍተኛውን ድጋፍ የምታደርገው አሜሪካ ናት። ስለሆነም የዚህ ድጋፍ መቀነስ አስፈላጊ የጤና ፕሮግራሞች የገንዘብ እጥረት ያጋጥማቸዋል። ለምሳሌ
👉 የክትባት ዘመቻዎች፣
👉 ኤችአይቪ/ኤድስ፣
👉 ቲቢ እና
👉 ወባን መከላከል
የመሳሰሉት ፕሮግራሞች በአሜሪካ ድጋፍ ላይ ጥገኛ ናቸው። የአሜሪካ ገንዘብ ድጎማ ከቀነሰ እነዚህ ወሳኝ የጤና አገልግሎቶች አደጋ ላይ ሊወድቁ ይችላሉ።
እነዚህ ፖሊሲዎች በኢትዮጵያ ጤና አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ምን አንድምታ ይኖራቸዋል ብለው ያስባሉ? ሃሳብዎትን ያጋሩን!
ቴሌግራም @HealthifyEthiopia
YouTube https://www.youtube.com/@HealthifyEthiopia
ፕሬዝዳንት ትራምፕ - ዩናይትድ ስቴትስን ከዓለም ጤና ድርጅት (WHO) የመውጣት ሂደት የሚያስጀምረውን የሥራ አስፈፃሚ ትዕዛዝ (Executive Order) ፈረሙ።
አሜሪካ ለዓለም ጤና ድርጅት ከፍተኛ የገንዘብ ድጋፍ ከሚያደርጉ አገሮች ግንባር ቀደሟ እንደሆነች ይታወቃል።
ከዚህ ቀደም ፕሬዝዳንቱ "ድርጅቱ ቻይናን ለኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ተጠያቂ ማድረግ ሳይችል ቀርቷል" ካሉ በሗላ አክለውም ቻይን ለመቅጣት የሚወስዷቸውን እርምጃዎች ይፋ ሲያደርጉ “ቻይና የዓለም ጤና ድርጅትን ሙሉ በመሉ ትቆጣጠረዋለች” ማለታቸው ይታወሳል።
ቴሌግራም @HealthifyEthiopia
YouTube https://www.youtube.com/@HealthifyEthiopia
የእባብ መነደፍ አደጋ ( Snake Bite )
✅በአገራችን ካሉት እባብ አይነቶች ውስጥ መርዛማ የሆኑት ጥቂቶች ናቸው፡፡
✅ የብዙዎቹ ንድፊያ ለህይወት አያሰጋም::
ስለዚህ ከተነደፈ በጣም መርበትበት ወይም አላስፈላጊ መረበሽ ውስጥ መግባት አያስፈልግም፡፡ ነገር ግን መርዛማ አለመሆኑ እስኪጣራ ጊዜ ስለሚፈጅ አስፈላጊውን የመጀመሪያ እርዳታ ማድረግ ተገቢ ነው፡፡
በእባብ የተነደፈ ሰው ምን አይነት ምልክቶችን ያሳይል ?
ከንድፊያ በኋላ የእባቡ ጥርስ ያረፈባቸው ቁስሎች ይኖራሉ፣ አካባቢው ሊያብጥ ይችላል፡፡ የቆዳ ቀለምም በዚያ አካባቢ ሊለወጥ ይችላል፡፡ እንደ እባቡ አይነት ሌሎች ምልክቶች ማቅለሽለሽ፣ ማስታወክ፣ አይን ብዥ ማለት፣ ማላብ፣ መተንፈስ ችግር፣ የአፍ መኮላተፍ ፣ መዝለፍለፍ እና የአካል መንቀጥቀጥ ሊያስከትሉ ይችላሉ፡፡
✅ የመጀመሪያ ህክምና እርዳታ ምን እናድርግ ?
የተነደፈውን ሰው ከእባቡ ማራቅ።
የተነደእውን ሰው ማረጋጋት ፣ እንዲንጋለሉ ማድረግ፡፡
የባለሙያ እርዳታ ወዲያውኑ እንዲገኝ ማድረግ፡፡
መርዝን በአፍዎ ለመምጠጥ ሙከራ አያድርጉ፡፡ አይጠቅምም፡፡
የተነደፈውን የሰውነት ክፍል አለመነቃነቅ (መርዙን ስርጭት ለመቀነስ)፡፡
በረዶ ወይም ቀዝቃዛ ነገር ቁስሉ ላይ አያድርጉ፡፡ አይጠቅምም ሊጐዳ ይችላል፡፡
የመርዙን ስርጭት ለመቀነስ ከቁስሉ በላይ (በቁሰሉና በልብ መሃከል) በፋሻ በጣም ሳይጠብቅ ይሰሩት፡፡ (በጣም ከጠበቀ የበለጠ አደጋ ይደርሳል)::
ወደ ሐኪም ቤት መውሰድ ካለብዎ የተነደፈውን አካል እንዳይንቀሳቀስ ማድረግ::ይህም የእባቡ መርዝ ወደ ሰውነታችን በጡንቻዎች እንቅስቃሴ በሊንፋትክ ( lymphatic system ) እንዳይሰራጭ ይጠቅመናል።
እባቡን ከርቀት ፎቶ ማንሳት ( የእባቡን አይነት ለመለየት) ::
በእርግዝና ወቅት የሚከሰት የስኳር ህመም (gestational diabetes, GDM) የህክምና ግቦች ምንድን ናቸው?
በእርግዝና ወቅት የሚከሰት የስኳር ህመም እንዳለቦት ከታወቀ — አትደንግጡ። የስኳር ቁጥጥርን በአስተማማኝ ግብ ውስጥ ካስተካከሉ እናት ጤና፤ ልጅም ደህና መሆን ይቻላል።
ለጤናማ እርግዝና ስለስኳር ህክምናው ግቦች ጠንቅቆ ማወቅና መረዳት ይፈልጋል። ውጤታማ ህክምና የስኳር ቁጥጥር እቅድ ማውጣት እና ግልጽ የሕክምና ግቦችን በማዘጋጀት ይጀምራል።
የደም ስኳር መጠንን ጤናማ በሆነ ክልል ውስጥ መቆጠጠርን ያካትታል። በአለም አቀፋዊ የሕክምና መመሪያዎች የሚደገፉት የስኳር ግቦች እንዲህ ናቸው፡-
1️⃣ የባዶ ሆድ የስኳር መጠን፡ ከ70 እስከ 95 mg/dL
2️⃣ ከምግብ ከአንድ ሰዓት በኋላ የስኳር መጠን፡ ከ140 mg/dL በታች
3️⃣ ከምግብ ከሁለት ሰአት በኋላ የስኳር መጠን፡ ከ120 mg/dL በታች
እነዚህን ግቦች ማሳካት ለእናትም ሆነ ጽንስ ጤና ወሳኝ ነው። የጽንስ መፋፋትና ክብደት ከፍ ማለት (macrosomia)፣ ከምጥ ጋር የተያያዙ ችግሮች፣ የጽንስ መታፈን፣ ህጻኑ እንደተወለደ መተንፈስ መቸገር፣ ወዘተ ያሉ ተግዳሮቶችን ለመቀነስ ስኳርን እስከመጨረሻዋ ደቂቃ ድረስ ማስተካከል ይገባል።
እነዚህ ግቦች ለእያንዳንዷ እናት በሚመች መልኩ በትንሹ ሊለያዩ ይችላሉ። የእያንዳንዷን እናት ጤና፣ የአኗኗር ዘይቤ፣ የአመጋገብ ምርጫዎች እና ለመድሃኒት ያላትን ምላሽ ከግምት ያስገባ መሆን ይገባዋል። ይህን ከጤና ባለሙያው ጋር በመመካከር ማስተካከል ይችላሉ።
ስለ ጂዲኤም ጥያቄዎች አሉዎት? አስተያየትዎትን ይጻፉልን።
ቴሌግራም @HealthifyEthiopia
YouTube https://www.youtube.com/@HealthifyEthiopia
ለታይሮይድዎ ጤናማ አመጋገብ
የእርስዎ ታይሮይድ በልዩ ፍቅር የሚመርጠው ምግብ እንዳለው ያውቃሉ? ያለዚህ የምግብ አይነት ታይሮይድ በትክክል ላይሰራ ይችላል።
በዚህ ጽሁፍ ለታይሮይድ አስፈላጊ ስለሆነው አዮዲን እንነጋገራለን!
ታይሮይድ በጣም የሚወደው ምግብ አዮዲን ነው። አዮዲን ለታይሮይድ አስፈላጊ ነው። ያለ አዮዲን ወሳኝ ሆርሞኖችን ማምረት አይችልም።
ነገር ግን ሰውነታችን በራሱ የሚፈልገውን አዮዲን ሊያመርት አይችልም - የግድ ከምግብ ማግኘት አለበት።
በአዮዲን የበለፀጉ ምግቦች ምን ምን ናቸው?
1️⃣የባህር ምግቦች ዋነኛ የአዮዲን ምንጭ ነው።
2️⃣ በቂ አዮዲን ያለው አካባቢ የሚመረቱ አትክልቶች፣
3️⃣የወተት ተዋጽኦዎችን እና
4️⃣ በአዮዲን የበለጸገ ጨው ነው። በተለይ በግፊት ህመም፣ ልብ ህመም ወይም ኩላሊት ህመም ምክንያት ጨው የተከለከሉ ከሆነ ሌሎች የአዮዲን አማራጭ ምንጮችን መጠቀም ሊኖርብዎ ይችላል።
5️⃣ ለነፍሰ ጡር እና ለሚያጠቡ እናቶች ደግሞ ከምግብ ተጨማሪ የአዮዲን ሰፕሊመንት መወሰድ ይመከራል።
https://youtu.be/-1qYBN_DBac?si=M1Ctn0xYtx1diiA7
@HealthifyEthiopia
ሰው ሰራሽ ጥርስ አፍ ያሸትል???
ሰው ሰራሽ ወይም አርቴፊሻል ጥርስ የአፍ ሽታ ያመጣ ይሆን???
-መልሱ ሰው ሰራሽ ጥርስ በራሱ የአፍ ሽታ አያመጣም ነው...ታዲያ ይሄ ጥያቄ ለምን ተነሳ?
-የሰው ልጅ የተፈጥሮ ጥርስ ህይወት አለው። በውስጡ ደም ይዘዋወራል። ስርአተ ነርቭ አለው። የህመም ስሜት፣ የንዝረት ስሜት እንዲኖረው ያደርገዋል። የተፈጥሮ ጥርስ በዙሪያው ብዙ ህይወት ያላቸው አካላት አሉ የደም ዝውውር፣ ትንንሽ የምራቅ እቅጢዎች...እነዚህ ሁሉ ጥርሳችንን ከጉዳት እና መጥፎ ከሆኑ ጀርሞች ይከላከሉለታል። በዚህም የተነሳ የዛን ያክል ልናስተውለው የምንችለውን ያክል የአፍ ውስጥ ለውጥ ላይኖር ይችላል ማለት ነው።
-በሌላ በኩል ሰው ሰራሽ ጥርስ ህይወት አልባ እና ግኡዝ ነገር እንደመሆኑ ጤንነቱ እና ንጽህናው የሚወሰነው በኛ ድክመት እና ብርታት ብቻ ነው። በዚህም ምክንያት የሰው ሰራሽ ጥርስ በቀላሉ የምግብ የመሰብሰብ ባህሪ ስላለው ቶሎ እንድናስተውለው ያደርገናል።
-እኛ በጣም ጠንቃቆች እና ለአፋችን ንጽህና ትኩራት የምንሰጥ ከሆነ ያለምንም መታከት፣ ያለምንም መዘናጋት ወጥ በሆነ መልኩ በትገቢ እውቀት ቅሪቶችንአፋችንን እና ጥርሳችንን የምናጸዳው ከሆነ ፤ እኛ ለማጽዳት የተቸገርነውን ለሀኪም አማክረን ወጥ በሆነ ሁኔታ በ6ወር ወይም በአመት የምናጸዳ ከሆነ በየቀኑ በመስታወት እያየን የአፍ ንጽህናችንን ደረጃ የምንገመግም ከሆነ...ከላይ የተነሳውን ጥያቄ በራሳችን መመለስ እንችላለን።
https://youtube.com/@healthifyethiopia?si=KoaubEAd_8nX7Dqk
...ቸር ነገር ያሳየን ያሰማን...
ስለታይሮይድ/እንቅርት ሆርሞን መብዛት (hyperthyroidism) ህክምና ማወቅ ያለብን አራት ነገሮች?
ሃይፐርታይሮይዲዝም የሚከሰተው ታይሮይድዎ ከመጠን በላይ ሆርሞን ሲያመነጭ ነው።
የታይሮይድ ሆርሞን መብዛት ሁሉን ነገር ያፈጥናል - የልብ ምትዎ፣ የሜታቦሊዝምዎ መጠን፣ ጭንቀትዎም ጭምር ይንራል! እንቅልፍ ይነሳል፣ ጸባይ ያልተለምደ ብስጩ ያደርጋል።
ምግብ በደንብ እየበሉ ክብደት ግን መቀነስ ሊያስተውሉ ይችላሉ። አጥንት ያሳሳል። ጸጉር ያረግፋል።
የታይሮይድ ሆርሞን መብዛትን ለማስተካከል በርካታ የህክምና አማራጮች አሉት።
የታይሮይድ ሆርሞን መብዛት ህክምና ሲሰጥ መወሰድ ያለባቸው እርምጃዎች እንደሚከተለው መሆን ይኖርበታል
1️⃣ የሆርሞን ደረጃውን ማወቅ
2️⃣ የህመሙን መነሻ ምክንያት ማወቅ
3️⃣ ዘላቂ የህክምና መፍትሄውን በውይይት መወሰን ያስፈልጋል።
4️⃣ መድሃኒት ከተጀመረም ለውጡን መታየትና መድሃኒት ማስተካከል ወይም ሌላ አማራጭ መፈለግ ይመከራል።
የእንቅርት መድሃኒት (thyroxine) ትክክለኛ አወሳሰድ እንዴት መሆን አለበት?
የታይሮይድ መድሀኒትዎን እየወሰዱ ግን ምንም ጥሩ ስሜት አይሰማዎትም? እንግዲያውስ የታይሮክሲን መድሃኒት በትክክል እየወሰዱ ላይሆን ይችላል!
የታይሮይድ ሆርሞን ማነስ (Hypothyroidism) ብዙ ሰዎችን በተይም ሴቶችን የሚያጠቃ የሆርሞን መዛባት ችግር ነው። አንገታችን ላይ የሚገኘው ታይሮይድ ወይም እንቅርት የታይሮይድ ሆርሞኖችን በበቂ ሁኔታ ማማንጨት ሲቀንስ የሚከሰት በሽታ ነው።
የሃይፖታይሮዲዝም መንስኤዎች በርካታ ቢሆኑም ህክምናው ተመሳሳይ ነው። ዋና ህክምናው ያነሰውን ሆርሞን ታይሮክሲን በሚባል መድሃኒት መተካት ነው። ይህ የሆርሞን መድሃኒት ያነሱትን ሆርሞኖችን ይተካል።
የታይሮክሲን መድሃኒትዎን በየቀኑ በተመሳሳይ ጊዜ መውሰድ አስፈላጊ ነው። ታይሮክሲን መወሰድ ያለበት በባዶ ሆድ ብቻ ነው። በጣም ተመራጩ የታይሮክሲን መውሰጃ ሰዓት በጠዋት ከእንቅልፍዎ እንደተነሱ የመጀመሪያው የእለቱ ስራዎት ማድረግ ነው። ታይሮክሲን ከዋጡ በኋላ ቢያንስ ግማሽ ሰዓትና ከዚያ በላይ ምንም ምግብ መመገብም ሆነ ከውሃ ውጭ መጠጣት የለበትም። እኔ ጧት አይመቸኝም ቀን ወይም ማታ ነው የምፈልገው ካሉ ግን ታይሮክሲን መወሰድ ያለበት ከበሉ በኋላ ቢያንስ ለ4 ሰዓታት ራቅ ማለት አለበት ።
በተጨማሪም ሌሎች መድሃኒቶች ካሉዎት ሰዓታቸው ከታይሮክሲን ጋር መቀራረብ የለባቸውም ። በተለይም የጨጓራና የደም ማነስ መድሃኒቶች፣ ቫይታሚኖች እና ሌሎች የመሳሰሉ መድሃኒቶች ከታይሮክሲን ጋር ሲወሰዱ በትክክል እንዳይሰራ ሊያደርጉት ይችላሉ። ስለዚህ የእነዚህን መድሃኒቶች ከታይሮክሲን መውሰጃ ሰዓት ቢያንስ ለ4 ሰዓታት ለመለየት ይሞክሩ።
የታይሮክሲን መዳሃኒቱ መጠን በቂ መሆን አለመሆኑን ለመከታተል መደበኛ የታይሮይድ ሆርሞን ምርመራዎች ማድረግ ወሳኝ ነው። መድሃኒቱ እንደተጀመረ ወይም መጠኑ እንደተቀየረ በየ6-8 ሳምንቱ ምርመራ ማድረግ ይገባል። የታይሮይድ ሆርሞኑ በደንብ ተስተካክሎ ከተረጋጋ በኋላ ደግሞ በየ4-6 ወሩ ያለማቋረጥ መከታተል ይመከራል።
ያስታውሱ ታይሮክሲን ሲወስዱ ሁሌም በተመሳሳይ ሰዓት መዋጥ ይመረጣል።
ይህን መረጃ የእንቅርት መድሃኒት ለሚወስዱ ሼር ያድርጉ።
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated 2 months, 2 weeks ago
Last updated 2 months, 1 week ago
ይህ ስለ Manchester United መረጃዎችን የሚያገኙበት የ Telegram ቻናል ነው 🇪🇹
--------------------------------------------------------------
☞︎| ስለ ማንቸስተር ዩናይትድ ትኩስ መረጃዎች
☞| ቀጥታ ስርጭቶች ከየስታድየሞቹ
☞| የዝውውር ዜናዎች
☞| ስለ ማንችስተር ዩናይትድ ታሪኮች
📩 ለማስታወቂያ ስራ DM :- @Marcoabdu
Last updated 1 month ago