ታሪካዊት ኢትዮጵያ [ History of Ethiopia ]

Description
ስለ ሀገር ብቻ ስለ ኢትዮጵያ

በዚች ድንቅ ሀገር እጅግ ብዙ ታሪክ ባላት
በተለይም በቀደምት ኢትዮጵያን የተፃፉ
የተለያዩ ታሪኮችን ለማግኘት
YOUTUBE : https://youtube.com/@Historical_Ethiopia
✅ጥያቄ ካለዎት❓ 👉 @Historical_Ethiopia_Discussion
✅ለቻናሉ መስራች አስተያየትዎን ለመስጠት @Abel_balehager_bot
Advertising
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 3 weeks, 1 day ago

Last updated 2 weeks, 3 days ago

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated 1 month ago

1 month ago
ታሪካዊት ኢትዮጵያ [ History of Ethiopia …
1 month ago
ታሪካዊት ኢትዮጵያ [ History of Ethiopia …
1 month ago
ታሪካዊት ኢትዮጵያ [ History of Ethiopia …
1 month ago
ታሪካዊት ኢትዮጵያ [ History of Ethiopia …
1 month ago
ታሪካዊት ኢትዮጵያ [ History of Ethiopia …
1 month ago
ታሪካዊት ኢትዮጵያ [ History of Ethiopia …
1 month ago
[**#አመሰግናለሁ**](?q=%23%E1%8A%A0%E1%88%98%E1%88%B0%E1%8C%8D%E1%8A%93%E1%88%88%E1%88%81) *****🙏******🙏***

#አመሰግናለሁ *🙏*🙏

ውድ የታሪካዊት ኢትዮጵያ ቤተሰቦች በ አስተያየት መስጫ (@Abel_balehager_bot ) ላይ የማይገባኝን ክብር ሰጥታችሁ ትልቅ አክብሮት ስለሰጣችሁኝ በእውነት እጅግ አድርጌ አመሰግናለሁ።
" በርታ ፣ጠንክር እንዳትሸበር " እያላችሁ ከጎኔ የምታበረታቱኝ ሁሉ ከልቤ አመሰግናለሁ 🙏
እንዲሁም በሀገርም ሆነ ከሀገር ውጪ ያላችሁ ውድ የታሪካዊት ኢትዮጵያ ቤተሰቦች እና ወዳጆቼ ላቅ ያለ ምስጋናዬን ላቀርብላችሁ እወዳለሁ 🙏
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር !!#አቤል_ባለሀገር ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር !!

YOUTUBE : https://youtube.com/@Historical_Ethiopia ጥያቄ ካለዎት 👉 @Historical_Ethiopia_Discussion የቴሌግራም ቻናል -** @Historical_Ethiopia

1 month ago
***💠*** ስለ ግእዝ ፊደላት

💠 ስለ ግእዝ ፊደላት

#ክፍል

ፊደል ማለት ፈደለ ከሚለው የግእዝ ግስ የወጣ ሲሆን ትርጉሙም ፦ ጻፈ ፣ ጽሕፈት ፣ አጻጻፍ ማለት ነው፡፡

የግእዝ ቋንቋ ልዩ የሚያደርገው የራሱ የሆነ ፊደል ስላለው ነው።

የፊደል ቅርጽ የተጀመረው በሄኖስ ዘመን ነው። ሄኖስ የሴት ልጅ ሲሆን የአዳም የልጅ ልጅ ነው። ነቢዩ እግዚአብሔርን በማገልገሉና በመገዛቱ የሕግ ማሰሪያ የሆነው የፊደልን አጻጻፍ በጸፍጸፍ ሰማይ እግዚአብሔር ገልጦለታል።

ፊደላቱ ፳፮ (26) ሲሆኑ በእብራይስጥ ቋንቋ አሌፋት በመባል ይታወቁ ነበር። ከጊዜ ወደ ጊዜ ግን ቅርጻቸውና ድምፃቸውን በመለወጥ ወደ ኢትዮጵያ የሳባና የግእዝ  ፈደላት በመባል ተሰይመዋል። እነሱም ፦👇👇

አ      የ        ቀ
በ      ከ       ረ
ገ      ለ       ሰ
ደ      መ      ተ
ሀ       ነ       ጰ
ወ      ሠ      ፐ
ዘ       ዐ
ሐ      ፈ
ኀ        ጸ
ጠ      ፀ

ፊደላቱን ከ አ  በ  ገ  ደ ... ወደ አሁኑ አቀማመጥ ያዘጋጁት የመጀመሪያው ሊቀ ጳጳስ አቡነ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን (324 ዓ.ም) ከአክሱም ሊቃውንተ ቤተክርስትያን ጋር በመሆን ነው፡፡

በድሮ ጊዜ ግእዝ ይጻፍ የነበረው ከቀኝ ወደ ግራ ነበር አሁን ግን ከግራ ወደ ቀኝ እንዲጻፍ አርገዋል።በመቀጠል አባ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን ግእዝ ቋንቋ ወደ አንድ ቤት ብቻ ነበር ወደታችም ወደ ጎንም የሚጻፈው። ወደ ጎን 6 ፊደል በመጨመር ባለ 7 ቤት እንዲሆን አድርገዋል፡፡
ምሳሌ፦ ከ'ሀ' 6ቱ 'ሁ፣ሂ፣ሃ፣ሄ፣ህ፣ሆ' ረብተዋል። ይህን ሲያረጉ ግን በዛው ቅርጹን ሳይለቅ ቅጥያዎችን ብቻ በመጨመር ፊደላቱን ሰርተዋል።

ሀ     ኀ     ገ
ለ     አ     ጠ
ሐ     ነ      ጰ
መ    ከ     ጸ
ሠ    ወ     ፀ
ረ      ዐ     ፈ
ሰ      ዘ     ፐ
ቀ      የ
በ      ደ

የግእዝ ቃላት ከላይ የተዘረዘሩት ፳፮ (26)ቱ ብቻ ናቸው ፡፡
በግእዝ ፈደላት ውስጥ እነ
'ሸ ፣ ቸ ፣ ኘ ፣ ጨ ፣ ጀ ፣ ዠ ፣ ቨ ፣ ኸ'
አይካተቱም ከግእዙ ላይ ያሉ ቃላትን በማሻሻል ለአማርኛው ፊደል የተጨመሩ ናቸው ፡፡

ይቀጥላል ....

#ምንጭ :- መሠረተ ግዕዝ

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር !!

YOUTUBE : https://youtube.com/@Historical_Ethiopia
ጥያቄ ካለዎት 👉 @Historical_Ethiopia_Discussion
የቴሌግራም ቻናል - @Historical_Ethiopia

1 month, 1 week ago
[#ግብፅና\_ሊቢያን\_የገዛው\_ኢትዮጵያዊ\_ንጉሥ\_ሻባካ](?q=%23%E1%8C%8D%E1%89%A5%E1%8D%85%E1%8A%93_%E1%88%8A%E1%89%A2%E1%8B%AB%E1%8A%95_%E1%8B%A8%E1%8C%88%E1%8B%9B%E1%8B%8D_%E1%8A%A2%E1%89%B5%E1%8B%AE%E1%8C%B5%E1%8B%AB%E1%8B%8A_%E1%8A%95%E1%8C%89%E1%88%A5_%E1%88%BB%E1%89%A3%E1%8A%AB)

#ግብፅና_ሊቢያን_የገዛው_ኢትዮጵያዊ_ንጉሥ_ሻባካ

ኢትዮጵያዊው ሻባካ የፒያንኪ 2ኛ የልጅ ልጅ ሲሆን በጥንታዊው ግብፅ አጠራር ሻባካ የሚለው "ካ" ሳይጨመር ሻባ ወይም ሳባ ማለት ነው። ካ ሲጨመር የሳባው ለማለት ሻካባ እንደተሠኘ ይነገራል።

ኢትዮጵያዊው ንጉስ ሻባካ የታህታይና የላዕላይ  ግብፅን እንዲሁም ሊቢያን ወደ ራሱ ግዛት አጠቃሎ ከደረበ በኋላ ልክ እንደ አያቱ(ፒያንኪ) ወደ ናፓታ በመመለስ ፋንታ በዚያው በግብፅ ሆኖ ማስተዳደር ጀመረ።የግብፅ የዋና ፈርኦንነት ስልጣንንም ያዘ።እህቱንም ሙሉ ስልጣን ሠጥቶ ከእርሱ በታች በላዕላይ ግብፅ በቴብ አነገሳት።

እርሷም ብልህና ሃይለኛ ስለነበረች ከሻባካ ቀጥለው በነገሱት 3 ነገስታት ዘመን እንደሞግዚት ሆና መላውን ግብፅ ለማስተዳደር ችላለች። በሻባካ ዘመነ መንግሥት ጊዜ ኢትዮጵያውያን በግብፅ ላይ 25ኛውን ስርወ መንግሥት መስርተው ማስተዳደር ችለዋል።

ንጉሥ ሻባካም ኢትዮጵያን ባስተዳደረበት የግዛት ዘመኑ በ12 ዓመት ቆይታው ይህን የመሰለ ግዙፍ ድርጊት ፈፅሞ እንደ አያቱ (ፒያንኪ) ኢትዮጵያን አግንኖ ነው ያለፈው።እርሱ ሲሞትም በሙሉ ስልጣን አነገሳት ያልናት እህቱ መንግስቱን ተረክባለች። እርሷም #ኒካንታ_ቅንዳኬ ወይም #ህንድኬ የተባለችው ናት።

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር !!

YOUTUBE : https://youtube.com/@Historical_Ethiopia
ጥያቄ ካለዎት 👉 @Historical_Ethiopia_Discussion
የቴሌግራም ቻናል - @Historical_Ethiopia

1 month, 1 week ago
ፊታዉራሪ ሀብተጊዮርጊስ ዲነግዴ(አባ መላ)

ፊታዉራሪ ሀብተጊዮርጊስ ዲነግዴ(አባ መላ)

ብዙ ነገር ካልተወራላቸው ጀግኖች መካከል ፊታውራሪ ሀብተጊዮርጊስ አንዱ ናቸው።

ፊታዉራሪ ሀብተጊዮርጊስ ዲነግዴ ከአባታቸዉ ከአቶ ዲነግዴ በተራና ከእናታቸዉ ከእመት ኢጁ አመዲና በ፲፰፻፵፮ ዓ/ም ተወለዱ።ሸዋን አንድ አድርጎ በማስተዳደር ዘመቻ ሰበብ በለጋነታቸዉ ዘመን ተማረኩ።በተማረኩት አካባቢም የተለያዩ የጦር አወራወር ስልት፣የጋሻ ምከታና የእርሻ ስራዎችን ተለማዱ ገና የ፲፰ ዓመት ወጣት ሳሉ ለእልፍኝ አሽከሮች በእልቅና ተሾሙ።ሀብተጊዮርጊስ ከዚህ ቀድሞ የትምህርት ዕድል ስላላገኙ ወደአንኮበር ቅዱስጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን በመሄድ ፊደልና ንባብ ከተማሩ በኋላ ወደ ምኒልክ እልፍኝ በመመለስ በቤተመንግስቱ ዉስጥ በባለሟልነት ስራ ተመድበዉ ስራቸዉን ማከናወን ጀመሩ። እድሜያቸዉ ለአቅመ አዳም ሲደርስ ወ/ሮ አልታየወርቅን አግብተዉ አንድ ልጃቸዉን ሙሉነሽን ወለዱ። ፊታዉራሪ ሀብተጊዮርጊስ በብልህነትና በአስተዋይነት ከዕለት ወደ ዕለት በቤተመንግስት ዉስጥ በሚያሳዩት የስራ ቅልጥፍናና አስተዋይነት ለአፄ ምኒልክ ይበልጥ ቅርብ ከመሆናቸዉም በላይ አንዳንድ ወታደራዊነክ ስራዎችን ይሰጧቸዉ ነበር። በመጀመሪያ በጦር አመራርነታቸዉ አድናቆትን ያተረፉት በእንግቦዉ ጦርነት ላይ ባሳዩት ጀግንነት ነበር። በጦር ስልት አዋቂነታቸዉና አመራራቸዉ ስለተወደዱ የጨቦንና በቻን ግዛት እንዲያስተዳድሩ ተሾሙ። የአድዋ ጦርነት ሲጀመር የባሻነት ማዕረግ ተሰጣቸዉ ። በዚያ ዉጊያ ላይ ከተሰለፉትና ኢትዮጵያን ከጠበቁ ጀግኖች መሀል አንዱ ናቸዉ። በ፲፰፻፹፰ዓ/ም ከአድዋ ጦርነት በኋላ በአፄ ምኒልክ የፊታዉራሪነት ማዕረግ ተሰጣቸዉ። አፄ ምኒልክ ስልጣኔን በኢትዮጵያ ለማስፋፋት ባደረጉት ያላቋረጠ እንቅስቃሴ የአዉሮፓን ስርዓት በመሻታቸዉ በሰዎች ዘንድ ተደራራቢ ስራ እንዳይኖር በማሰብ በኢትዮጵያ ዉስጥ የመጀመሪያ የሆነዉን 12 ሚኒስትሮችን ሹመት በመስጠት የአስተዳደሩን ሁኔታ ይበልጥ ፈር ለማስያዝ አዋጅ አስነገሩ። በአዋጁ መሰረት ፊታዉራሪ ሀብተጊዮርጊስ ዲነግዴ የመጀመሪያዉ የጦር ሚኒስተር ሆኑ። ፊታዉራሪ ሀብተጊዮርጊስ አባ መላ ከተባሉበት ምክንያት አንዱ ፦ በአፄ ምኒልክ ዘመን ሁለት የእንግሊዝ ዜጎች ያለ ፍቃድ ወደቦረና ግዛት በኬንያ በኩል ገብተዉ ተገድለዉ ስለተገኙ አዲስ አበባ ተቀማጭ የነበረዉ የእንግሊዝ መንግስት ቆንሲል ያለ አግባብ የእንግሊዝ ዜጎች ተገድለዉብናል ሲል አቤቱታዉን ለአፄ ምኒልክ ያመለክታል። አፄ ምኒልክም ጉዳዩን መክረን እንነግርሃለን ካሉ በኋላ ፊታዉራሪን ሀብተጊዮርጊስን አስጠርተዉ "እነዚህ እንግሊዞች በምን ምክንያት ነዉ የተገደሉት?" ብለዉ ቢጠይቋቸዉ ጃንሆይ ቆንስሉን ወደ እኔ ይላኩት አነጋግረዋለዉ ፤መልሱንም በቶሎ አሳዉቆታለዉ ብለዉ መለሱ። በዚህም መሰረት የእንግሊዝ ቆንሲል ወደ ፊታዉራሪ ሀብተጊዮርጊስ መኖሪያ ቤት ሄዱ። እንደተገናኙም 'ሰዎቻችን ያላአግባብ ተገድለዉብናልና ደማቸዉ የፈሰሰበት መሬት ይሰጠን አሉ' ፊታዉራሪ ግን በሀገራችሁ ይህን መሳይ ደንብ አለወይ? ብለዉ ጠየቁት። <አዎ> ብሎ መለሰ ቆንሲሉ። እንግዲያዉስ መልካም እኛም የአፄ ቴዎድሮስ ልጅ አለማዬሁ ቴዎድሮስ ከዚህ ሄዶ በሃገራችሁ ሞቷልና ለእኛ ሎንዶንን ስጡን ፤ እናንተ ይህንን ዉሰዱ ብለዉ ቃል አርቅቀዉ ፈርሙና በል ከዚህ ላይ ፈርም ቢሉት አልፈርምም ብሎ ሄደ። አፄ ምኒልክና እቴጌ ጣይቱም ከደስታቸዉ ብዛት የአባ መላን አንገት አቅፈዉ ሳሟቸዉ ። የእንግሊዙም ቆንሲል በሀብተጊዮርጊስ የነገር አካሄድ በጣም ተቆጥቶ ሴራዉ በመክሸፉ ተናዶ ነገሩን ደግሞ ሳያነሳ ቀረ ። ፊታዉራሪ ሀብተጊዮርጊስ ዲነግዴ /አባ መላ/ ለ፴፫ ዓመት ያህል በጦር አበጋዝነትና አስተዳዳሪነታቸዉ ክብራቸዉን እንዳስጠበቁ በ ፸፫ ዓመታቸዉ ታህሳስ ፫ ቀን በ፲፱፻፲፱ ዓ/ም አረፉ ። የሚገርመው ፀሎት ሲያደርሱ  አፄ ሚኒልክ በሞተበት ቀን ልረፍ ብለው ፀሎት ያደርሱ ነበረ እንደፀለዩት አፄ ሚኒልክ ባረፋበት ቀን እና እለት ታህሳስ ፫ ቀን አርብ እለት አረፉ የቀብር ስነስርዓታቸዉም በአራዳ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን እንዲያርፍ ተደረገ ።

ምንጭ፦ ፍፁም ወልደማሪያም 2006 ያልተዘመረላቸዉ እና 7 ክፍል አማርኛ መምህር መምሪያ
በተጨማሪም "ተፈሪ መኮንን ረዥሙ የሥልጣን ጉዞ በምኒልክ፣ በኢያሱና በዘውዲቱ ዘመን" ከሚለው በዘውዴ ረታ ከተፃፈው መፅሐፍ።

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር !!

YOUTUBE : https://youtube.com/@Historical_Ethiopia
ጥያቄ ካለዎት 👉 @Historical_Ethiopia_Discussion
የቴሌግራም ቻናል - @Historical_Ethiopia

We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 3 weeks, 1 day ago

Last updated 2 weeks, 3 days ago

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated 1 month ago