አርምሞ🧘🏽‍♂

Description
ጥቂት ምናኔ 🧘🏽‍♂️


©³ @thoughts_painting
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 2 months, 2 weeks ago

Last updated 2 months, 1 week ago

ይህ ስለ Manchester United መረጃዎችን የሚያገኙበት የ Telegram ቻናል ነው 🇪🇹
--------------------------------------------------------------
☞︎| ስለ ማንቸስተር ዩናይትድ ትኩስ መረጃዎች
☞| ቀጥታ ስርጭቶች ከየስታድየሞቹ
☞| የዝውውር ዜናዎች
☞| ስለ ማንችስተር ዩናይትድ ታሪኮች

📩 ለማስታወቂያ ስራ DM :- @Marcoabdu

Last updated 1 month, 1 week ago

1 month, 1 week ago

`ይህ ቻናል ያለምንም ላስተዋውቅልህ አስተዋውቅልኝ ድጋፍ ሳይደገፍ ለ7 ዓመታት ዘልቆ ቆይቷል። እናንተስ ምን ያህል አመት አብራችሁን ነበራችሁ?

በሚለቀቁትስ አርቲክል ምን ትምህርት አገኛችሁ?`

፦አርምሞ🧘🏽‍♂****

1 month, 1 week ago

¹ራስን የመግዛት ጥበብ `በዚህ አስተምህሮ ክፍሎች ፈጥረንለት ረጅም የመማማር ሂደት ይኖረናል። ይህም የነበረውን የምናፈርስበት ወይም የተሃድሶ መንገድ ነው። በመጀመርያ “ራስ” ማለት አዕምሮ፣ እኔነት፣ መሪነት እና ማንነት ነው። “መግዛት” ማለት ደግሞ ግዞት፣ ቁጥጥሮሽ፣ ስልጣን እና ማስተዳደር ነው። ሁለቱ ሲጣመሩ “ጥበብ” ይሆናሉ።

ነጮች ይህን መንገድDisciplineይሉታል። እሱም“You must be disciplined in thought.. word and deed.. Consciously train yourself to do those things that are good for you!”ሁላችንም በሁለት ነገሮች አንዱን መርጠን እንሰቃይ ዘንድ ምርጫ ተሰጥቶናል። የዲሲፕሊን ስቃይ ወይም የጸጸት እና የብስጭት ስቃይ። ራስን የመግዛት ዲስፕሊን ከሌለን አልያም ደግሞ ካልተለማመድን እራሳችንን መቆጣጠር አለመቻል ብቻ ሳይሆን በአዕምሮ ወጥመድ ውስጥ የወደቅን ምስኪን እስረኞች እንሆናለን።Control your mind. otherwise your mind will control you!ራስን መግዛት ማለት የአዕምሮ ስነስርዓት ሂደት ነው። እሱም ለሚሰማን እያንዳንዱ ስሜት የኛ ፈቃድ ሲታከል የሚፈጠረው ድርጊት ነው። አንድ ሰው ወደኛ መጥቶ ቢሰደበን ምን ይሰማናል? ስሜቱ የመጣው የሰደበንን ስድብ በመሆናችን ነው? ወይስ ያልሆነውን ሆናችኋል ብሎ ስለተሳደበ ነው?። የተሰደብነው ስድብን ከሆንን ይህ ስድብ ሳይሆን ትክክለኛ መገለጫችን ነው። ነገር ግን የሰደበንን ስድብ ካልሆንን ለምን እንናደዳለን ምክንያቱም አይደለንማ!። ስሜት በመሠረቱ ልጓም የሌለው ፈረስ ነው። ምክንያታዊነት የሌበት የውስጥ ፍላጎት ድርጊት ነው። ይህ ስሜትን ከላይ እንደጠቀስኩት ሎጂካሊ ጥያቄ ብንጠይቀው ከመቅጽበት ከአዕምሮአችን በኖ ይጠፋል።

አንድ ግለሰብ ቡድሃ ላይ ጠንካራ ውርፋቶችን ባዥጎደጎደበት ወቅት ቡድሃ ፈገግ አለና ሰውየውን እንዲህ በማለት ጠየቀው፦“ለአንድ ግለሰብ ገፀ በረከት ለማበርከት ብፈልግ እና ግለሰቡም ገፀ በረከቱን ሳይቀበል ቢቀር ያ ገፀ በረከት የማን ነው የሚሆነው?”

ግለሰቡም ለቡድሃ እንዲህ በማለት መለሰ:-“በእርግጥ የገፀበረከቱ የመጀመሪያ ባለቤት ለሆነው ሰው ይመስለኛል!።”

ቡድሃ፦ “እኔም ያንተን ገፀበረከት ለመቀበል ባልፈልግስ**...**

ቡድሃ አረፍተ ነገሩን በእንጥልጥተል ተወው። ግልፍተኝነት ያለው ቁጣ ከውጭ የመጣ የውስጥ ፍላት ስሜት ነው። ሌላ ሰው ባዶ ጀልባ ከሆነ ቁጣችን ግን ውስጣችን ነው። ሰለዚህም የመጀመርያው ህግ ዝምታ ነው!።

የምናወራው ነገሮች ምን ያህል አስፈላጊ ናቸው?። ከስራ ባልደረቦቻችን፣ ከጓደኞቻችን፣ ከቤተሰቦቻችን አልያም ከሌላ አንድ ሰው ጋር የምናወራው ነገር ምን ያህል አስፈላጊ ነው?። እርግጠኛ ነኝ ከአፋችን የሚወጣው የወሬ ጎርፍ ከ100/95% የማይጠቅም አሉባልታ ነው። የምናወጣው ቃል ምን እንደሆነ ማሰብ ስንጀምር ከምናወራው የማናወራው ግዜ ይበልጣል። አውሩ ተናገሩ የሚል ስሜታችሁን ለመግራት ከፈለጋችሁ ጥቃቅን አምሮቶችን መግደል በቂ ነው። ለምሳሌ ፊታችንን እየበላን ለማከክ እየፈለግን ግን ሆም ብለን አለማከክን መለማመድ። ይህ ተራ የሚመስለው ሂደት ወደ ትልቅ የስሜት መግራት ይመራናል። ዝምታ ትልቁ የመንፈስ እርካታ ነው። ይህ የመንፈስ እርካታ ጥንካሬ ስንመግበው ልዕለ መንፈሳዊነታችን ያንሰራራል። ታድያ ይህ መንፈሳዊ ከፍታ በምን መልኩ እንመግበዋለን..?`

ይ ቀ ጥ ላ ል..

1 month, 1 week ago

`ካለህ ላይ ስጥ ቢሆንም የጠቢብ ምክሩ፤ የዓለም ህግ ደግሞ እንዲህ ትላለች፦

-የማንንም እጅ እንዳትጠብቅ!`

1 month, 1 week ago

እነዚህ ሶስቱ እራስን የመግዛት ባህል ናቸው፦??‍♂**

¹ዝምታ
²ጾም
³እስፖርት**

1 month, 1 week ago
**Genes book** `ላይ ከተመዘገቡት እንግዳ ሞቶች …

Genes book `ላይ ከተመዘገቡት እንግዳ ሞቶች አንደኛው ይህ ነው፦

ነገሩ እንዲህ ነው ፖላንድ ውስጥ ሚስት ከባሏ ጋር ተጣልታ እሱም ካንቺ ጋር ያለኝ ነገር ሁሉ በቃኝ በማለት ትቷት ይሄዳል። በዚህ የተበሳጨችው ሚስት እራሷን በመስኮት ከአስረኛ ፎቅ ትወርውራለች። ባልየው በተመሳሳይ ሰዓት ከህንፃው እየወጣ ነበር። እናም ሚስት የባል ጀርባ ላይ ታርፋለች። እሷ በህይወት ስተርፍ ባልየው ግን ሞተ!` ???

1 month, 1 week ago

የሁሉንም አዛውንት ምክር እንደ እውነት አትቀበሉ፤ ደደቦችም ያረጃሉ!። ?

1 month, 2 weeks ago

`መምህሩ ያጋጠመውን ሁኔታ ለመወያየት ከተማሪዎቹ የአንዱን እናት ወደ ትምህርት ቤት ጋበዛትና እንዲህ አላት፦“ልጅሽ የማስታገሻ መድሃኒት እንደሚያስፈልገው እንድትረጂ እፈልጋለሁ። የትኩረት ችግር ላለባቸው እና ከመጠን በላይ እንቅስቃሴ ለሚያደርጉ ሰዎች የተዘጋጀ መድሃኒት አለ እሱን ስጪው። የምሬን ነው ልጅሽ ሁሌም በትምህርት ሰዓት ይበሳጫል። በዛ ላይ የትምህርቱን አሰጣጥ በጣም ይረብሸዋል። በዚህም ብዙ ግዜ ክፍል አይገኝም!።”

እናትየዋ የመምህሩን ሃሳብ ተቀበለች። ተማሪውም ተስማማ ነገር ግን በክፍል ጓደኞችሁ ፊት መድሃኒቱን መውሰድ እንደሚያሳፍረው አክሎ ተናገረ። መምህሩም ክኒኑን ለመውሰድ ካሳፈረው ወደ መምህራን ቢሮ ሄዶ እንዲጠቀም ነገረው።

ተማሪው ለአንድ ወር ያህል መድሃኒቱን መዋጥ ጀመረ። እናም በሚገርም ሁኔታ ለውጥ ማሳየት ጀመረ። መምህሩ እናቱን በድጋሚ ጠራ እና የልጇን ባህሪ እያዳነቀ መረጋጋቱ እና ትምህርቱ ምን ያህል እንደተሻሻለ ገለጸላት። እናትየዋ የአስተማሪውን ቃል በሰማች ግዜ ተደሰተችና በፈገግታ ወደ ልጇ ዞር ብላ እንዲህ አለችው፡- “ልጄ አሁን በፊት ካለህበት በእጥፍ ተሽለ እየተማርክ ነው። ስላደረግከው ለውጥ እና ስላሳካኸው ስኬት እስቲ እንደሚገባ በትንሹ ንገረኝ?”

ሕፃኑም ያ መረጋጋቱ ሳይለቀው እናቱን እንዲህ አላት፡- “ጉዳዩ በጣም ቀላል ነው ወደ መምህራን ቢሮ ሄጄ ለአስተማሪዬ ላጠፋውት ጥፋት ሁሉ ይቅርታ ጠየቅኩት። እና ምሳ ሰዓት ላይ ቡና የመጠጣት ልምድ ስለነበረው እንደምላከውና በዛ እንደምክሰው ነገርኩት። ስለዚህ ሁሌም ምሳ ሰዓት ሲልከኝ የሰጠሽኝን ማስተጋሻ ክኒን ቡናው ውስጥ መደባለቅ አልረሳም ነበር። ከዛ በኋላ እኔ እና አስተማሪዬ ጥሩ ሆነናል። እሱም ከበፊቱ በተሻለ መልኩ ተረጋግቶ ማስተማር ቀጥሏል!”

እና ምን ለማለት ነው ሌሎችን ለማከም አትሞክሩ አንዳንዴ የታመምነው እኛ ነን` ?

1 month, 2 weeks ago

`ለታፈሱት ወገኖቻችን መፅናናትን እመኛለሁ ? እስከመቼ ነው ቦዘኔ ጀለሶች አሉኝ ብዬ የማወራው። እስቲ እኔም በተራዬ ወግ ደርሶኝ 10 አለቃ እና 50 አለቃ ጓደኞች ነው ያሉኝ ብዬ ላውራ..

ቡኮውስኪ ምን ነበር ያለው፦“ችግር የለውም አንተ ዓለምን አድን፤ እኔ ደግሞ እንዴት እንዳዳንከው እጽፈዋለሁ” ጓዶችም አገራችንን ጠብቁ እኔ ደግሞ ተጋድሏችሁን በነጭ ሉክ አሰፍረዋለሁ። አዎ የእኔ ጣት ክላሽ መያዝ አይሆንለትም፤ ነገር ግን ከክላሹ የወጣውን እሳት የመጻፍ አቅም አለው!።`

1 month, 2 weeks ago
“Democracy don't rule the world. You'd …

“Democracy don't rule the world. You'd better get that in your head. This world is ruled by violence.But I guess that's better left unsaid!” ?

አንድ ቀን የአገራችንን ባንዲራ በትልቁ ዘርግተን እንሰቅላለን። አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ምልክታችን ከምድር በጸና አፈር ወደ ሰማይ ከፍ ከፍ ብሎ ይውለበለባል።
ያለምንም ዘር ኢትዮጵያ ትቅደም ?

1 month, 2 weeks ago
**‹‹**`ጦርነቱም ያበቃል መሪዎችም ይጨባበጣሉ። እኚህ ትልቅ …

‹‹ጦርነቱም ያበቃል መሪዎችም ይጨባበጣሉ። እኚህ ትልቅ እናት የተሰዋው ልጃቸውን ይጠብቃሉ፤ ያቺ ሴትም የምትወደውን ባሏን ትጠብቃለች፤ ህፃን ልጆችም ጀግና አባታቸውን ይጠብቃሉ። አዎ ማን አገር እንደሸጠ ባላውቅም፤ ማን ለአገራችን ዋጋ እንደከፈለ ግን አውቃለሁ!››―ማህሙድ ዳርዊሽ

We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 2 months, 2 weeks ago

Last updated 2 months, 1 week ago

ይህ ስለ Manchester United መረጃዎችን የሚያገኙበት የ Telegram ቻናል ነው 🇪🇹
--------------------------------------------------------------
☞︎| ስለ ማንቸስተር ዩናይትድ ትኩስ መረጃዎች
☞| ቀጥታ ስርጭቶች ከየስታድየሞቹ
☞| የዝውውር ዜናዎች
☞| ስለ ማንችስተር ዩናይትድ ታሪኮች

📩 ለማስታወቂያ ስራ DM :- @Marcoabdu

Last updated 1 month, 1 week ago