ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated hace 3 semanas, 5 días
Last updated hace 3 semanas
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot
🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹
Last updated hace 1 mes, 1 semana
አንድ ሰው በኢኽዋን ቫይረስ ከተለከፈ ቫይረሱ መጀመሪያ የሚያጠቃው የሚዛናዊነት ክንፉን ነው። የሳኡድ ነገስታቶች ብዙ ችግሮች ይኖሩባቸዋል ምንም ጥርጥር የለውም ይሁን እንጅ ከነ ስህታቸው ከኢራን፣ከቱርክ ጋ ግን ለንፅፅር የሚቀርቡ አይደሉም። አብዛሀኛዎቹ የሀገራችን ኢኽዋኖች አላህ ሂዳያ ይስጣቸው እንጅ ወይ ከታሪክ፣ ወይ ከፓለቲካው ወይ ከሸሪዓው በቂ እውቀት የላቸውም። በተለይ የሀገራችን ኢኽዋኖች የተካኑት ለሰው ስሜት የሚመቸውን እየመረጡ እንደ ጊዜው ዥዋዥዌ ማለት ነው
------------
የቀበሮ ባህታውያን
~
የዐረብ ሃገራት መሪዎች ብዙ ችግር እንዳለባቸው የሚታወቅ ነው። ለማንም #ጥፋት የምንከላከልበት ምንም አይነት ምክንያት የለም። ከመሆኑም ጋር ከነ ችግራቸው አላህ ይጠብቃቸው። አላህ መቃናትን ይስጣቸው። የሃገር መፍረስ በሊቢያ፣ በየመን፣ ... ሲጠቅም አላየንም። ሙዐመር አልቀዛፊን " ግ.ደ.ሉ.ት! ደሙ በጫንቃዬ ላይ ነው" እያሉ የቀሰቀሱት እነ ቀርዷዊ ናቸው። የኢኽዋን በጎች ግን ዛሬ "ጋዳፊን በሴራ ያስገደሉት ምእራባውያን ናቸው" እያሉ የአዞ እንባ እያነቡ የዋሆችን እየሸወዱ ነው። የቀበሮ ባህታውያን! "የቀበሮ ባህታዊ ከበግ መሀል ይፀልያል" አሉ።
ህሊና ቢስ ፍጡሮች ሆነው እንጂ እንዴት ነው የቱርክን፣ የኢራንን መንግስት የሚያወድስ አካል ሳዑዲን የሚያብጠለጥለው? በዚህ መጠን ነው በጭንቅላታችሁ ላይ የምትሸፍቱት?!
"ሳዑዲ ንጉሳዊ ናት" ብሎ ይከሳሉ። እና ቀጠር ያለው አስተዳደር የኺላፋ ስርአት ነውንዴ?! ሰርክ የምትቆዝሙለት የኦቶማን ቱርክ ስርአትስ ንጉሳዊ አልነበረም ወይ? ወይ ከታሪክ የሉ! ወይ ከሸሪዐ የሉ! ወይ ከህሊና የሉ! ቢያንስ አንዱ ጋ እንኳ እረፉ እንጂ!
"ሳዑዲ ሸሪዐ የለም" ይላሉ። የአቶማን ቱርክ ነው ሸሪዐ የነበረው? የኤርዶጋን ቱርክ ነው ሸሪዐ ያለው? ወይስ ኢራን? ወይስ ቀጠር? ወይስ ሙርሲ ነበር ሸሪዐ የዘረጋው? ወይስ ሃማስ ነው በሸሪዐ የሚያስተዳድረው? እስኪ አንድ ጥቀሱ።
በነዚህ ዲንን ሽፋን በሚያደርቁ ቆሻ .ሻ የቡድን ፖለቲካ በሚያራምዱ አካላት የተሸወዳችሁ አካላት ብትነቁ መልካም ነው። ቡድኑ ሁሌ ሙስሊሙ ላይ የሚደርሱ ወቅታዊ መከራዎችን ለቡድናዊ ትርፍ ለመጠቀም የሚተጋ የደም ነጋዴ ነው። እንጂ እያንዳንዱ የዐረብ ሃገራትን የሚኮንንበት ነጥብ በባሰ መልኩ ከሚከላከልላቸው መንግስታት ውስጥ ይገኛል። በገዛ ህሊናው ላይ የሸፈተ ሰው ካልሆነ በስተቀር ለኢራንና ለቱርክ የሚከላከል አካል ሳዑዲን ነጥሎ ከማብጠለጥል ጀርባ ያደፈጠ ኢኽዋናዊ ምክንያት እንዳለ አይጠፋውም። በመካከለኛው ምስራቅ ትልቁ የአሜሪካ የጦር ካምፕ ያለውኮ በቀጠር ነው። በቱርክም የአሜሪካ የጦር ካምፖች አሉ። ኢማራት የሂንዱ የአምልኮ ቦታ በመፍቀዷ የጮሁ ሰዎች ስለ ቀጠር ቤተ ክርስቲያን ግን ትንፍሽ የማይሉት ለምን ይመስላችኋል? ያደፈጠ ኢኽዋናዊ ቫይረስ ነው እንዲህ የሚያደርጋቸው።
ደግሞ በሃኒያ ሞት ደስታቸውን ገለፁ እያሉ ይከሳሉ። (በቅድሚያ እኔ እዚህ ውስጥ ራሴን አላስገባሁም።) ግን ደግሞ የኢኽዋን ቡድንኮ ሳዑዲ ላይ በሚደርሱ ፈተናዎች ሁሉ በመደሰት ነው የሚታወቀው። በኮሮና ጊዜ የሃገራችን ታዋቂ ኢኽዋኒዮች ሲቀባበሉት የነበረውን ፅሁፍ እናስታውሳለን። ፍልስጤማውያንም በንጉስ ዐብደላህ ሞት ሲደሰቱ ነበር። (አያይዤዋለሁ።) ከመቼ ወዲህ ነው ደግሞ የሞራል ሰባኪ የሆናችሁት? እኮ እናንተ!
ለማንኛውም እወቁ! እናንተ ስለ ሳዑዲ ከምታወሩት በላይ ስለ ኢራን፣ ቱርክ፣ ቀጠር፣ ስለ ሙርሲ የአገዛዝ ዘመን ብዙ ማውራት እንችላለን። ዝምታን የመረጥነው በሳዑዲ ለሚታዩ ክፍተቶች ሽፋን እየሰጠን እንዳይመስል ብለን ነበር። እንደ ቅዱስ ሲሰራራችሁ ግን በሚገባችሁ ቋንቋ ለማውራት እንገደዳለን።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor
Telegram
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
كناشة ابن منور
ለካ እንደዚህም አለ ጉድኮ ነው!!ከወደ fb ሰፈር የተገኘ አስገራሚ ነገር ነው!!
---------------
በትልቅ ሆቴል ውስጥ ሪሴፕሽን ሆኖ የሚሰራ የምንቀራረብ አንድ ጓደኛ ነበረኝ፡፡ በስራ ላይ ሳለ ከእለታት ባንዱ ቀን አንድ ቦርሳ የያዘ ሰው ይመጣና 9 ቁጥር ተይዞ እንደሆነ ይጠይቀዋል፡፡ ክፍሉም አልተያዘም ነበርና ቁልፍ ተቀበለ፡፡ ባለቦርሳውም ሰውዬ አስተናጋጁን 9 ቁጥር ሻማ፥ ቢላ፥ አፕል እና ብርጭቆ እንዲያመጣለት ጠየቀ፡፡ ወዳጄም እየተገረመ የተባለውን አቀረበለት፤ ሰውዬም እየሳቀ ወደ ክፍሉ ይገባል፡፡
ባጋጣሚ 9 ቁጥር ክፍል ጎን ያለው ሪሴፕሽኑ ክፍል ነበርና ጓደኛዬ ሌሊት ላይ በጣም አስደንጋጭ ነገር ሰማ፡፡ የእንሰሳት ጩኸት፥ ኡኡታ፥ የህፃን ልጅ ለቅሶ፥ የሚሰባበሩ እቃዎች ድምፅ፡፡ በዚህ የተረበሸው ጓደኛዬ እስኪነጋ ጠብቆ የተፈጠረውን ለማወቅ ጓጓ፡፡ ጠዋት ላይም ባለቦርሳው ሰውዬ በሙሉ ፈገግታ ቁልፍ ሲያስረክብና አስተናጋጁ ምን እንደተፈጠረ ለማየት ሮጦ ወደ ክፍሉ ሲገባ......ሁሉም ነገር ባለበት እንጂ የተቀየረ ነገር አልነበረም፤ አልጋው በስነስርአት ተነጥፏል፡፡ ብርጭቆውም፥ ቢላውም፥ አፕሉም ሻማውም ባሉበት ተቀምጠዋል፡፡ ይህም የሆነው ግንቦት አንድ ቀን ነበር፡፡ በ ነገሩ የተገረመው ወዳጄ ግራ እንደተጋባ ወራት አለፉት፡፡
ከአንድ አመት በኋላ በዚያው ተመሳሳይ ግንቦት አንድ ቀን ባለቦርሳው ሰውዬ ተመልሶ መጣ፡፡ በድጋሜም 9 ቁጥር አልጋ ተይዞ እንደሆነ ጠየቀው፡፡ በዚህም አመት ክፍሉ ስላልተያዘ ቁልፍ ተሰጠው፡፡ በድጋሜም 9 ቁጥር ሻማ፥ ብርጭቆ፥ ቢላ እና አፕል አምጡልኝ አለ፡፡ አመቱን ሙሉ ግራ የተጋባው ጓደኛዬም የማወቅ ጉጉቱ እየጨመረ የተባለውን አቀረበለት፡፡ በዚያም ሌሊት እነዛኑ የሚረብሹ ድምፆች ሰማ፥ የሚያለቅሱ ህፃናት፥ የእቃዎች መሰባበር እና የእንሰሳ ድምፆች፡፡ ሌሊቱን ሙሉ ወደ ክፍሉ የሚወጣ ወይ የሚገባ ሰው መኖር አለመኖሩን ሲከታተልም አነጋ፡፡ ሲነጋ ባለቦርሳው ሰውዬ እንደተለመደው ከፈገግታ ጋራ ቁልፍ ሲያስረክብ ጓደኛዬ ሮጦ ቢመለከት ምንም ነገር የለም፡፡ አልጋው ባግባቡ እንደተነጠፈ፥ እቃዎቹም ምንም ሳይነኩ በተቀመጡበት ነበሩ፡፡
በዚህ ባለቦርሳ ሰውዬ ሚስጥር እጅግ ግራ የተጋባው ወዳጄ አመቱን ሙሉ በጉጉት ሲጠብቅ ከረመና ግንቦት አንድ ደረሰ፡፡ እንደተለመደው ሰውዬው ከነቦርሳው መጣና 9 ቁጥር ክፍልን ያዘ፡፡ እንደተለመደው 9 ቁጥር ሻማ፥ ብርጭቆ አፕልና ቢላ ጠየቀ፡፡ እንደተለመደው ሌሊቱን ሙሉ አስፈሪ ድምፆች ሲሰሙ አደሩ፡፡ ሲነጋ እንደተለመደው ቁልፍ ሲያስረክብ 9 ቁጥር ክፍል ምንም አይነት ምልክት አልተገኘበትም፡፡ በዚህ ጊዜም አስተናጋጁ ይህንን ሚስጥር ከራሱ ከሰውዬው ሊጠይቅ ወሰነ፡፡
“አንድ ጥያቄ ልጠይቅህ ነበር “
“ጠይቀኝ” አለ ሰውዬው በፈገግታ::
“ለምንድነው ሁልጊዜ ግንቦት አንድ ብቻ የምትመጣው?
ለምንድነው ሁልጊዜ 9 ቁጥር ክፍልን የምትይዘው?
9 ቁጥር ሻማው አፕሉ ቢላውና ብጭቆውስ ምን ያደርጉልሃል?
ሌሊት ላይ የሚሰሙት አስፈሪ ድምፆችስ የሚመጡት ከየት ነው?”
አለና ጠየቀው፡፡
ሰውዬም እየሳቀ
“ለማንም የማትናገር እና ሚስጥር የምትጠብቅ ከሆነ እነግርሃለሁ” አለው፡፡
ጓደኛዬም “ለማንም አልናገርም ንገረኝ” ሲል መለሰ፡፡
ሰውዬም ለማንም እንዳይናገር አስማለና ሚስጥሩን ነገረው፡፡
.
እነሆ ጓደኛዬም ሚስጥር ጠባቂና መሃላውን አክባሪ በመሆኑ የባለ ቦርሳውን ሰውዬ ሚስጥር ምንነት ለኔም አልነገረኝም
Copied
ፅሁፉን አንድ ወንድማችን እስከመጨረሻው አንብቦት ሲናደድ ምን ሆነህ ነው ብየው ነገረኝና እኔም ለሚመከር ሰው ለማስተማሪያነት ይሆናል በሚል ላክልኝ ብየው ልኮልኝ ነው።
---------------
Anyway ምንም ለማይጠቅም ነገር ጊዚያቹህን ስለወሰድኩባቹህ too much sorry ብያለሁ የፅሁፉ ቁም ነገር የብዙዎቻችንን ንባብ ከዚህ የተለየ አይደለም ለማለት ነው። የአንዳንዶቻችን ነገር ይገርማል በተለይ አንዳንድ ወንድም እና እህቶች አላህ ይዘንላቸውና እንደዚህ አይነት ትርኪ ምርኪ ምንም ተጨባጭ የሌላቸውን ነገሮች ሲያነቡ አይሰለቻቸውም አንዳንዶቹማ ጭራሽ 20፣30 ተከታታይ ክፍል ያለውን ፅሁፍ ሁሉ ያነባሉ የሚገርመው ግን ትንሽ ረዘም ያሉ ዲናዊ ትምህርቶች ሲለቀቁ scroll scroll አድርገው ባላየ ያልፉታል.....
ኒካህ፡ ከነጭሳር ካምፓስ
السلام عليكم ورحمة الله وبركاته
አልፍ ሚልዮን መብሩክ አልፍ ሚልዮን መብሩክ አልፍ ሚልዮን መብሩክ!!!
?????????
? ባረከሏሁ ለኩማ .?
? .?
? ወባረከ አለይኩማ . ?
? .?
? ወጀመዓ በይነኩማ .?
? .?
? ፊኸይር .?
?????????
ትላንት ማለትም 27/11/2016 አ.ል
ውድ ወንድማችን ኡስታዛችን አሚራችን Dr ሚዕራጅ ሙራድ(7th year medicine) እና እህት ነዒማ ሸይኽ ሙሐመድ በሽር (Abaya Campus) ምሩቅ የኒካህ ፕሮግራም ተፈጽሟል።
ትዳራቹህን እንደ ዐልይ እና ፋጢማ በጣም ያማረ እና የሰመረ ትዳር ያድርግላችሁ ። ወልዳችሁ ከብዳችሁ ለኢስላምና ለኡመተል ኢስላም የሚለፉ ሷሊህ ልጆችን የምታፈሩበት ትዳር ያድርግላችሁ ብለናል!!!
???????????
???????????
በድጋሚ አልፍ ወአልፍ ወሚሊዮን፡ መብሩክ ብለናል ሙሽራችን Our Mentor!!!
ኪታብ በማስተማር ላይ ለተሰማራችሁ
~
1- ለተማሪዎችህ የሚማሩትን ኪታብ መምረጥ። አቅማቸውን፣ የጎደላቸውን፣ የሚያስፈልጋቸውን እንጂ እንዲሁ የጠየቁትን ሁሉ አትጀምር። ተማሪ ያላቅሙ ትልቅ ኪታብ መጀመር ሊፈልግ ይችላል። ተማሪው በጥሩ ደረጃ ላይ ካለ የጠየቀውን ብትቀበልም ችግር የለውም።
2- የምታቀርበው ትምህርት፣ የምትመልሰው ጥያቄ ታዳሚህን ያገናዘበ ይሁን። ሰፊ ህዝብ የሚታደምበት ደርስ ላይ የሚኖርህ አቀራረብ በ'ቂራአት' ገፋ ካደረጉ ተማሪዎች ጋር ከሚኖርህ ጋር በይዘቱም፣ በቋንቋውም፣ በመጠኑም ሊለይ ይገባል። ለምሳሌ ከመግሪብ እስከ ዒሻ መስጂድ ውስጥ የሚሰጥ ደርስ ላይ ጠለቅ ያለ ኺላፍ አትተንትን። ይሄ ማስተማር ሳይሆን ማደናገር ነው። ኺላፍ ጆሯቸውን ከመታቸው ተማሪዎች ጋር ስትሆን ደግሞ በተቻለ መጠን 'ራጂሕ' እና 'መርጁሑን' ባቅማቸው መጠን ለይተህ አቅርብ። ብዥታዎችን ግፈፍ። የምታቀርበው ነገር ግልብ ከሆነ ደርስህን ጣዕም ያጡበታል። ባጭሩ ትምህርት ታዳሚዎችህን ያገናዘበ ይሁን።
3- ተዘጋጅተህ ቅረብ። ቢያንስ ገረፍረፍ አድርገው። ተማሪዎችህ ፊት አትደናበር። በቅጡ ሳትይዝ ቀርበህ ሸርሕ ላይ በፍለጋ አትባዝን። የቀለም ትምህርት ላይ እንኳ አስተማሪዎች ተዘጋጅተው ነው የሚቀርቡት። የዲን ጉዳይ የበለጠ ጥንቃቄ ይፈልጋል።
4- ካ'ቅምህ በላይ ካልሆነ በስተቀር ቀሪ አታብዛ። ደርስ አታቆራርጥ። ይሄ የተማሪዎችን ሞራል በጣም ያቀዘቅዛል።
5- ተማሪዎችን አታሸማቅ። አንዳንዱ አስተማሪ ጥያቄዎችን በቅንነት አይረዳም። ሁሉ ነገር መፈታተን ይመስለዋል። ይሄ መሆን የለበትም። መፈታተን የሚፈልግ፣ ልታይ ልታይ የሚል፣ መጥፎ አቀራረብ ያለው ተማሪ ካለ እንዳስፈላጊነቱ በጥቅል ወይም በተናጠል ለይተህ ምከር። ካልሆነ ጠንከር አድርገህ ገስፀው። ነገር ግን ቁጣችን የራሳችን ድክመት መሸፈኛ ሊሆን አይገባም። በአስተማሪዎች ከባድ ባህሪ የተነሳ ስንት ደርስ ተበትኗል! ስንት ተማሪ ተሰናክሏል! ስንት የደዕዋ እንቅስቃሴ ተስተጓጉሏል!
6- ድንገት ያልገባህ ነገር ከገጠመህ ወይም የማታውቀው ጥያቄ ከተጠየቅክ አትደንግጥ። አንተ ሁሉን እንደማታውቅ ይታወቃል። አይቼ እመጣለሁ፣ አላውቀውም በል። እንጂ እርግጠኛ ባልሆንክበት በግምት እንዳትመልስ። አደራ!
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor
Telegram
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
كناشة ابن منور
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated hace 3 semanas, 5 días
Last updated hace 3 semanas
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot
🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹
Last updated hace 1 mes, 1 semana