ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated hace 3 semanas, 5 días
Last updated hace 3 semanas
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot
🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹
Last updated hace 1 mes, 1 semana
አልሀምዱ ሊላሂ ይገባው ምስጋና
ሀራሙን ከልክሉ ሀላሉን በሱና
ተጋቡ ብሎናል ትዳር ነው ሰኪና
ከጭፈራ ከዳንስ ከኽቲላጥ የፀዳ
ዘፈን ሳይሰማ መንዙማ ነሺዳ
የሰለፍዮች ሰርግ እንዲህ ነው ተረዳ
አይታወቅ ፎቶ ካሜራቪዲዮ
የኩፋር ሱናነው ቡፌም ይሁን ቨሎ
ደስታውም ሀዘኑም ሲሆን በስልምና
እንዴት ያስደስታል የነብዩ ሱና
በቁርአን በሀዲስ የታሰረ ኒካ
የእርዚቅ ሰበብ ነው ያመጣል በረካ
ሷሊህ ልጅ ወፍቆህ ምትክህን ተካ
መዲናንም ዘይር ከተጓዝክ መካ
የአሏህ ውሳኔ ደርሶ ያቀጠሮ
መሀባን አየነው ዛሬ ተሞሽሮ
የነስሬስ መቼ ነው ከርሞ ነው ዘንድሮ
አበባው አብቦ ለፍሬ ያብቃችሁ
ሞቅ ደመቅ ይበል በፍቅር ጎጇችሁ
ትዳርህ ላይ ፅና ውለድ መንታመንታ
ለአይንህ ማረፊያ ናቸው ጠንክር በርታ
በምትችለው አቅም አንድም ሳትሳሳ
ውለታህ ለመርከዝ መቼም አይረሳ
አሏህ ይቀበልህ ይክፈልልነን ካሳ
ደግሞ ወደ ቀልዱ እንመለስና
ትንሽ ፈታ እንበል ትንሽ እንዝናና
ከጫት ያሳብዳል የሰርግ ምርቃና
ለዛሬ አውፉ በሉኝ መሀባ ነው እና
አእንግዲህ መሀባ ለዚህ ቀን በቅተሀል
አሏህን አመስግን ይጨምርልሀል
ልብ ይኑርህ እንጂ ተዓ ዱድ ይቻላል
አይዞሽ ሙሽሪት እንዳትሸበሪ
አይደርብብሽም ፈሪ ነው አትፍሪ
ሁለተኛ አይደፍርም ሚስት ተጨማሪ
መህሬም ይሁነን ብትል የውሃ ቆጣሪ
አንቺንም በስተት እንዳይሆን አጣሪ
በይሆን የኡስታዝ ቤት ገና ሳይጨርሱ
ለሰርጉ ወሊማ መቅመሱ ባዲሱ
ኮሽታ ይፈጥራል ለእኛም ለነሱ
አለን ሜትሮ ሎጂ ለሰርጉ ለኡርሱ
ሚዘነንብ ይመስላል ዳመናው ንፋሱ
ያላገባህ አግባ አትበል ገናነኝ
ጊዜህን አትግደል እያልክ ምንም የለኝ
እርዚቅን ፈርታችሁ ከትዳር አትራቁ
መጋቢው አሏህ ነው ኻሊቁ ራዚቁ
ዘመኑ ከባድ ነው ስልኩ ኢንተርኔቱ
ይጠብቀን እንጂ አሏህ በእዝነቱ
ከመሀባ ይልቅ ሞቅ ያለው ዛሬ
እውነት ለመናገር ይመስለኛል ነስሬ
ምክኒያቱም ተከፍቷል አጥሩ እና ወንዙ
ጥሶት ሳይሻገር እንደጫት አይሱዙ
عمر
بارك الله لكما وبارك عليكما وجمع بينكما في خير
ስደት✈️ ስደት ✈️** ስደት
በናፍቆት ውቅያኖስ
በትዝታ መርከብ
በጭንቀት ማዕበል
በትካዜ ወጀብ
ስደተኛው ልቤ
ይከንፋል በሀሳብ
ትርፌ ድካሜ ነው
በናፍቆት መባባት
በትዝታ ረመጥ
መንደድ መሰቃየት
እንደኔ ከሆነ
የሁሉም ሰው ስደት
በጢሙ ይደፋ
በእናትሀገሬ በድህነት ልሙት**
ኡመር
**ኢድ ነው ብሉ ጠጡ
ከከትፎው ከቁርጡ
ዚክሩንም አትርሱ
አሏህ አስታውሱ
ለሙስሊሞች ምክሬ
ልዩ ቀን ነው ዛሬ
ወንጀልን እራቁ
በደስታ ቦርቁ
የአረፋ በዓል
ድምቀቱ ይለያል
ተቀበለሏሁ ሚና ወሚንኩሙ
አደራ አደራ ጫትን እንዳትቅሙ
ኡመር**
ጋብቻ እብደትን ከሚያሶግዱ አስባብ(ምክኒያቶች) ሲሆን ላጤነት ደግሞ ለእብደት ከሚዳርጉ ምክኒያቶች ነው ።
?ላጤዎች እኔ አይደለሁም ያልኩት
**በእንቁ ቀናቶች ባስርቱ ዙል ሂጃ
ወደ ሇላ ጥለህ የዱንያህን ሀጃ
ተሰነቅ ላኺራህ እንድት ወጣ ነጃ
ቤቱን ለመዘየር ሄደን ወደ መካ
እጃችን ካጠረ አቅሙ ካልተሳካ
ባለንበት ሆነን በምንችለው ዋጋ
ተካፋይ እንሁን ከወሩ በረካ
አንገትህን ለሰይፍ ሰጥተህ በጅሀድ
ከምትሞተው በላይ በአሏህ መንገድ
በነዚህ ቀናቶች መሰደቅ መስገድ
በላጭ ነው ወንድሜ ጠንክረህ ነግድ
አሏህን በማውሳት በተስቢህ በተክቢራ
ኸይር የተባለ ሁሉም መልካምስራ
እጅግ ተወዳጅ ነው ለመዳን ከኪሳራ
በዋዛ እንዳያልፈን ይህ ሰፊ መግፊራ**
ኡመር {عمر}
ቆንጆ ብትሆኚ ገዳይ በውበትሽ
ታምራለች እያሉ ሺ ወንድ ቢያደንቅሽ
እወቄ የኔ እህት ፀባይ ዲን ከሌለሽ
ሴም የሌለው ቀፎ ቁመና ብቻ ነሽ
ግን ባሁኑ ሰዓት ከኑሮ በላይ የተወደደውን ታውቃላችሁ እንትን ነዋ…………
ቆይ ሰው ማግባት አቆመ እንዴ!?? ባል ነው ወይስ ሚስት የጠፋው
ለሄዎቴ አዲስ ገፅ
አንድ ብየ ልግለፅ
በሰጠኸኝ እድል
ጌታየ ባንተ ፈድል
ሆኜ ተጠቃሚ
ወሩን ሙሉ ፇሚ
ነፃ ከሚወጡት
ከጅሀነም ቅጣት
ከሚገቡት ጀነት
ጌታየ ባን እዝነት
ታደገኝ ከእሳት
ነፍሴ ደካማናት
ቀኑን ከሚፆሙት
ሌቱን ከሚቆሙት
አድርገኝ ባንተ እዝነት
የፊርደውስ ባለቤት
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated hace 3 semanas, 5 días
Last updated hace 3 semanas
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot
🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹
Last updated hace 1 mes, 1 semana