ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated hace 3 semanas, 5 días
Last updated hace 3 semanas
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot
🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹
Last updated hace 1 mes, 1 semana
መምህር ኤስድሮስ የተባሉት ሊቅ ያስተማሩትን የመንፈስ ልጃቸዉን ሲመክሩ እንዲህ አሉት፡፡
"ልጄ ከመሃይም አትጣላ ፣ ደጋፊው ብዙ ስለሆነ ያሸንፍሃል"
"...አሜሪካ አእሮን እንዴት ማጠብ እንዳለባት ታውቃለች። ገና ምድሯን ስትረግጥ አሜሪካዊ የሆንክ ያህል እንዲሰማህ የሚያደርጉ ታላላቅ ሰዎች ያሉባት ሀገር ናት ።
እኛ ሀገር ውስጥ ደግሞ ባደክበት ቀየ ባደክበት ምድር ወዘ ልውጥ እየተባልክ ትኖራለህ።ለሀገርህ ባዳ ሆነህ ትሞታለህ።
አሜሪካን ሀያል ያደረጓት አሜሪካውያን ብቻ አይደሉም፤አምባገነን መሪዎቻቸው ያሳደዷቸው የሌሎች ሀገር ስደተኞች ጭምር ናቸው።
ኢትዮጵያ የተማረ ሰው አጥታ አይደለም፤የተማረ ስለማትወድ እንጂ። ግን ለለውጥ እራስን መስጠት ያስፈልጋል።
አየህ...ለውጥን የሚጠላ ኢትዮጵያዊ የለም።ለውጡ ሆዳቸውን ከሚያጎልባቸው ትቂቶች በቀር።
ችግሩ የለውጡ አካል ለመሆን የሚፈልግ የለም።በሌሎች ሞትና ደም ለመጠርቃት እና ኑሯቸውን ለማደላደል የሚመኙ ብዙ ናቸው።..."
- ኢንጅነር ሻጊዝ እና ዶ/ር ሚራዥ ወደ ሀገር (ኢትዮጵያ )ስለመመለስ ሲመካከሩ (ዴርቶጋዳ መፅሀፍ ላይ)
ያሳዝናል...የስንት ሰው ላብ መና ሆኖ ሲያድር 💔
"አይ መርካቶ.." እንዲል ሎሬቱ
ወዳጄ በእውቀቱ እንደፃፈው... #ሼር አድርጉት!
የሚያሳስበኝ
(በእውቀቱ ስዩም)
ዶስተየቨስኪይ የተባለ የሩስያ ደራሲ ልቦለድ ውስጥ የሚገኝ ኢቫን የተባለ ገጸባህርይ ” ሰውን አውሬ ብሎ መጥራት አራዊትን እንደ መስደብ ይቆጠራል ይላል ፤” ሰው የበጎነት አቅም ያለውን ያህል ፥ በጭካኔ የሚወዳደረው የእንስሳ ዝርያ የለም፤ አንበሳ ሚዳቆን የሚገድለው በልቶ ማደር ስላለበት ነው፤ ሳይቸግረው ያለ አላማ መሰሉን፥ የሚገድል፥ ብጤውን በማሰቀየት የሚደሰት ፍጡር ሰው ብቻ ነው፤
ልጅ ሆኜ በጎችን አሰማራ ነበር፤ ግልገል በግ የሚደፍር ትልቅ በግ አይቼ አላውቅም ፤ ወንዱ በግ ፥ደረሰች በግ ላይ ለመውጣት ራሱ ወቅት ይጠብቃል፤ ለርቢ መድረሷን አሽትቶ ካላረጋገጠ በቀር አይደርስባትም፤
የሰባት አመትዋን ሄቨንን ለመስማት በሚገዘገንን ጭካኔ ደፍሮ የገደላትን ሰውየ “ እንስሳ ፥ወይም አውሬ” ብሎ መጥራት ፍትሀዊ የማይሆነው ለዚህ ነው፤ እንዲህ አይነቱ ቀፋፊ ፍጡር የሚገልጽ ሌላ ቅጽል ተፈጥሮ መዝገበቃላት ውስጥ መካተት አለበት፤
ህግ ካለ ይህ ወንጀለኛ እንደ ምግባሩ ፍዳውን መቀበል ይገባዋል፤ እሱ ብቻ ሳይሆን ወንጀሉን ለመሸፋፈን የሞከሩ እና የዶለቱ ሁሉ ከቅጣቱ ድርሻቸውን ማንሳት አለባቸው፤
አስገድዶ ደፈራ በዋናነት የወሲብ ጉዳይ አይደለም፤ የፈሪዎች እና የግፈኞች “ሀይል “ መግለጫ ነው፤ ከጥቂት ዓመታት በፊት የሰባ ምናምን አመት ሴት የደፈረ ጎረምሳ በአስራት መቀጣቱን የሚገልጽ ዜና ማንበቤ ትዝ ይለኛል ፤ የሰባ አመት ባልቴት እና የሰባት አመት ሴት ሁለቱም ለሩካቤ የሚያሳስብ ነገር የላቸውም፤ ግን ሁለቱም አንድ የሚያደርጋቸው አቅም አልባ መሆናቸው ነው፤ ራሳቸውን ከደፋሪው መከላከል አይችሉም፤ ደፋሪዎች ብዙ ጊዜ ፈሪዎች ናቸው፤ ከሚበልጣቸው ጋራ ወይም ከእኩያቸው ጋራ ጉልበት እንደማይፈታተሹ ያውቁታል፤ በጉልበት የሚያንሳቸውን፤ ሀብት ስልጣን ወይም ወገን የለውም ብለው የሚያስቡትን ከማጥቃት ግን አይመለሱም፤ ብዙ ጊዜ የጥቃት ሰለባዎችን ስናይ ህጻናት፥ የቤት ሰራተኞች፥ እንግዶች፥ የመንገድ ዳር ተዳዳሪዎች ወይም በጦርሜዳ ላይ ያለ ታዳጊ የቀሩ ሴቶች ናቸው፤
ለወላጆች አንድ የጭንቅ ቀን ምክር አለኝ፤ ጨካኝ ፤ጭቦኛና ቀፋፊ ባህርይ ያላቸው ሰዎች
የትም እና መቼም ይኖራሉ፤ሰርሲ ላንስተር እንደተናገረችው Everywhere in the world they hurt little girls ."
ፈታኝ አለም ውስጥ እንደምንኖር አንርሳ፤ ሁሌም በህግ በፈሪሀ እግዚአብሄር እና በባህል በጭምት ፊት ተማምነህ መዘናጋት የለብህም፤የልጆችህ ወታደር መሆን አለብህ ፤ ልጆችሽን እንደ አይንሽ ብሌን ጠብቂ ! ቀላል እንዳልሆነ አውቃለሁ፤ግን ሌላ ምን አማራጭ አለ?
#ሼር አድርጉት
መጥፎ ሰው ማለት እየፈለከው የማይፈልግህ ሳይሆን ሳትፈልገው ፈልጎህ የመፈለግ ስሜት ከፈጠረብህ በኋላ የማይፈለግህ ሰው ነው።
ብዙ ሰዎች ማስታወቂያ በማህበራዊ ሚዲያዎቼ ላይ ስለጥፍ አያምርብህም፣ አንተ ጋር አይሄድም፣ አይመጥንህም ይሉኛል። አይመጥንህም ምን ማለት ነው?
የሰው ልጅ ስለ አንድ ሰው የሆነ ስዕል ይስላል፣ ከዛም ያ ሰው ከሱ ስዕል እንዲወጣ አይፈልግም። ዘመኑ ወደድንም ጠላንም በማህበራዊ ሚዲያዎች እየተመራ ነው ለዛም የተለያዩ ስራዎች ይሰራሉ። ማስታወቂያ አስገዳጅ አይደለም። መንገር፣ እዩልኝ፣ ሞክሩልኝ ብሎ መለፈፍ ነው። ፍላጎቱ ያለው አይቶ ይሞክረዋል፣ የሌለው ደግሞ ያልፈዋል። ይሄም የሚያሳየው አብዛኞቻችን ስለ ገንዘብ፣ ስለ ስራ እንዳልገባን ነው፣ ውጮቹ Financial Literacy ስለሚሉት ነገር ምንም እንደማናውቅ ነው። አቆማለሁ? በጭራሽ! ከችግርተኞች ላይ ፣ ከአደራ ላይ፣ ከሰው ላይ የወሰድኩት ምንም ነገር የለም። ወጣቶች፣ በጎን ስራ መስራት፣ ተስፋን ማየት አታቁሙ።
“አትደንግጡ፤ የተሰቀለውን የናዝሬቱን ኢየሱስን ትፈልጋላችሁ፤ ተነሥቶአል፥ በዚህ የለም፤ እነሆ እርሱን ያኖሩበት ስፍራ" ማርቆስ 16:6
እንኳን አደረሳችሁ!
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated hace 3 semanas, 5 días
Last updated hace 3 semanas
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot
🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹
Last updated hace 1 mes, 1 semana