ሞዐ ሚዲያ- Moaa Media…✍

Description
የቤተ-አምሓራ ነፃ ህዝብ፣ የትግል ልሳን ነን፣ ይከተሉን፣ "ነፃ ሀሳብ ለነፃነት" መርኸ መስመራችን ነው!
Advertising
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated hace 3 semanas, 5 días

Last updated hace 3 semanas

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated hace 1 mes, 1 semana

hace 1 semana, 3 días

ጩኸታቸው ያልተሰማ 29 ወንድ ኢትዮጵያውያን ለባርነት፣ ለኩላሊት ልዋጭ እና ለግብረሰዶም ንግድ በይፋ ተሸጡ‼️****
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••

ከ29 በላይ ኢትዮጵያውያንን ወደ ሌላ ቦታ ሸጠዋቸዋል። ቀሪዎቹም ከፍተኛ ስጋት አለባቸው ” - በማይናማር ያሉ ኢትዮጵያውያን ወላጆች ኮሚቴ

በማይናማር የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ካሉበት አስቸጋሪ ሁኔታ የኢትዮጵያ መንግስት እንዲያስወጣቸው በተደጋጋሚ እየተማጸኑ እንደሚገኙ ይታወቃል።

የወላጆች ኮሚቴ በበኩሉ፣ “ ግብረሰዶም ወደማፈጸምበትና ኩካሊት እያወጡ የሚሸጡ ሰዎች ወዳሉበት ኮሎምቢያ ሊሸጧቸው እንደሆነ ሰምተናል ” ሲል ስጋቱን ገልጾልን ነበር።

ስለጉዳዩ ማብራሪያ የጠየቅነው ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ ልጆቹ ያሉበት ቦታ አዳጋች እንደሆነ፣ ከአገራቱ ጋር የሥራ ስምሪት አለመኖሩ ሁኔታውን አስቸጋሪ እንዳደረገው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ሲገልጽ መቆየቱ አይዘነጋም።

ከቶኪዮ ኤምባሲ ጋር እየተነጋገረ መሆኑንም ገልጾ የነበረው ሚኒስቴሩ ከዚያ በኋላ ላቀረብለት ጥያቄ፣ “ አዲስ መረጃ ካለ አሳውቃለሁ ” ቢልም እስካሁን ያለው ነገር የለም።

አሁንስ የኢትዮጵያውያኑ ጉዳይ ከምን ደረሰ ?

የወላጆች ከሚቴ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጠው ቃል፣ “ ከ29 በላይ የማሆኑ ኢትዮጵያውያንን ወደ ሌላ አገር ሸጠዋቸዋል። ቀሪዎቹም ከፍተኛ ስጋት አለባቸው ” ብሏል።

በመሆኑም ልጆቹ ካሉበት ስቃይ እንዲወጡ በኢትዮጵያ የሚገኙ የተለያዩ ተቋማት ጫና እንዲያደርጉ ቢሯዎቻቸውን እያንኳኳ በደብዳቤ ጭምር እየተማጸነ መሆኑን ገልጾ፣ መንግስት አሁንም ለጉዳዩ ትኩረት እንዲሰጥ ጠይቋል።

ኮሚቴው በዝርዝር ምን አለ ?

“ ምንም መፍትሄ የለም። እንዲያውም የተወሰኑ ልጆችን ወደሌላ ቦታ ሸጠዋቸዋልና ያን የሰሙ ልጆች በጣም ተረብሸዋል።

ወደ ኮሎምቢያ እየሸጧቸው ነው ስለተባለ ተጨናንቀዋል። በየቀኑ ‘ምን አዲስ ነገር አለ?’ ነው የሚሉን። እኛም ውጪ ጉዳይን አሳስበን መፍትሄ በመጥፋቱ አሁን የሃይማኖት ተቋማትን እየተማጸንን እንገኛለን።

ልጆቹን በማይናማር ከነበሩበት ቦታ አንስተው ወደ ሌላ ቦታ እየሸጧቸው ነው። ይሄ ነው ችግር የሆነው። በየጊዜው አዲስ ነገር ነው የሚሰማው በጣም ይጨንቃል።

ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴርን በተደጋጋሚ ብንጠይቅም ምንም አዲስ ነገር የለም። አሁንም ተሰባስበን ልንሄድ ነው። የሃይማኖት ተቋማት ጫና እንዲያደርጉ እየተማጸንን ነው።

ዱኣ አድርጉ፤ ጾም ጸሎት ይታወጅ ብለን እየጠየቅን ነው።

ሀገራቱንም፣ ህዝብንም፣ ቤተሰብንም መጥቀም የሚችሉ የተማሩ ልጆቻችን ስቃዬ ላይ እያሉ ውጪ ጉዳይ ሰምቶ ዝም ከማለት ያስቸገረው ነገር ካለም ለጠቅላይ ሚኒስቴር ጽሕፈት ቤት እንዲያቀርቡልን እንጠይቃለን።

ጠቅላይ ሚኒስቴር ጽሕፈት ቤትም ሄደን ነበር ለቅሬታ ሰሚ ክፍል ጥያቄያችንን በኢሜይል እንድናስገባ ነው የነገሩን። ግን በኢሜይል ብቻ አስገብተን አንቀመጥም ደብዳቤም እንወስዳለን ” ብሏል።

(ጉዳዩን እስከ መጨረሻው የምንከታተለው ይሆናል)
Tikvah
https://www.facebook.com/profile.php?id=61571637893418

27/04/2017 ዓ.ም
ሞዐ ሚዲያ
https://t.me/Moamediamoresh

hace 1 semana, 3 días

ሰበር ዜና!

የስናን አባጅሜ ፋኖ ከጠላት በማረከው ሞርተር ጥቃት መክፈቱ ተሰምቷል።

የአማራ ፋኖ በጎጃም የ6ኛ ክ/ጦር አካል የሆነው የስናን አባጅሜ ብርጌድ ከቀናት በፊት በማረካቸው ሁለት ሞርተሮች ዛሬ ታህሳስ 27/2017 ዓ/ም ከረፋድ ጀምሮ በአገዛዙ ወታደሮች ላይ ጥቃት መክፈቱን መረብ ሚዲያ የክ/ጦሩ አዛዥ የሆነው ፋኖ እስቲበል ዓለሙ በማህበራዊ ትስስር ገፁ ማስነበቡን ለመመልከት ችሏል።

የመረብ ሚዲያ

https://www.facebook.com/profile.php?id=61571637893418

27/04/2017 ዓ.ም
ሞዐ ሚዲያ
https://t.me/Moamediamoresh

hace 1 semana, 3 días

ጅል ጋዜጠኛው አርቲስቷን እንዲህ ሲል ይጠይቃታል “እንዴት አዲስ አበባ ተወልደሽ አድገሽ “አማራ ነኝ” ትያለሽ?”

አርቲስቷም ስትመልስ እንዲህ ትላለች “ማንነት ህያው ነው። እንደፈለክ ልትቀይረው የምትችለው ነገር አይደለም። የነዛ ሐገር ያቆሙ አናብስት አርበኛ ልጆች ከሆኑት አንዟ  ኩሩ አማራ ነኝ!” " አማራ ነኝ" ማለት አዲስ አበቤ ነኝ ማለትም ነው። የአዲስ አበባ አባቷም፣ እናቷም አማራ አይደለምዴ?
"የአዲስ አበባ ልጅ ነኝ" ማለት፦ የጣይቱ እና የሚኒሊክ ልጅ ነኝ ማለት እንጅ፣ ሌላ አይደለም።
👇
👇
https://vm.tiktok.com/ZMkUxHrLw/ https://vm.tiktok.com/ZMkUxHrLw/

https://www.facebook.com/profile.php?id=61571637893418

27/04/2017 ዓ.ም
ሞዐ ሚዲያ
https://t.me/Moamediamoresh

hace 1 semana, 6 días
ሞዐ ሚዲያ- Moaa Media…✍
hace 1 semana, 6 días

በላስታ ቡግና ወረዳ ለከፋ ችግር ለተጋለጡ ወገኖች የመጀመሪያ ዙር ድጋፍ ማድረጉን ወሎ ቤተ አምሐራ - Wello Bete Amhara  የልማት እና የበጎ አድራጎት ድርጅት አስታወቀ።

በሰሜን ወሎ ላስታ ቡግና ቆብ ቀበሌ ለሚገኙ ለ1840 ወገኖቻችን ወይም ለ460 አባውራ 230 ኩንታል ጥራቱን የጠበቀ የስንዴ ዱቄት የ ወሎ ቤተ አምሐራ - Wello Bete Amhara  የልማት እና የበጎ አድራጎት ድርጅት በቦታው ተገኝቶ ፈልፈሊት እና ዘብሎ ቀበሌወች ኗሪ ለሆኑ ለችግር ለተጋለጡ ወገኖች ድጋፍ ተደርጓል ብሏል ድርጅቱ በማህበራዊ ትስስር ገፁ ባወጣው መረጃ።

ከላሊበላ ከተማ የቡግና ወረዳ አይና 56 ኪሎሜትር የሚርቅ ሲሆን በወረዳው 4 የሰብዓዊ ድጋፍ መስጫ ቦታወች /ቆቡ ፣ ብርኮ፣ አይና ፣ ቅዱስ ሀርቤ/ የተለዩ ቀበሌወች ሲሆን ድርጅታችን አስቸጋሪ መንገዶችን በማለፍ ከወረዳው ማዕከል 38 ኪሎሜትር ርቀት በምትገኘው ቆብ /አጠቃላይ 94 ኪሎሜትር ከላሊበላ ፈታኝ ፒስታ መንገድ / በማለፍ ለዘብሎ እና ፈልፈሊት ቀበሌ  1840 ወገኖቻችን /460 አባውራ/ ለአንድ አባውራ 50 ኪሎ  የ1ኛ ዙር የሰብዓዊ ድጋፍ ማድረስ ተችሏል ብሏል።

የገንዘብ ድጋፍ ያደረጉት የሁልግዜም የችግር ደራሽ የሆኑት በካናዳ ሀገር የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ECNAS National ሲሆኑ ድርጅቱ ደግሞ ዱቄት በመግዛትና ስርጭት በመፈፀም ድጋፉን አድርሷል።

እንደ ጀርመን ሬዲዮ ዘገባ /DW/ ከሆነ ለችግር የተጋለጡ" ከ70ሺ በላይ ወገኖች ያሉ ሲሆን" አሁንም ቢሆን ለከፍተኛ ችግርና ርሃብ የተጋለጡ ከችግሩ ስፋት አንፃር ድርጅታችን 2ኛ ዙር ድጋፍ ለማድረስ ከወዲሁ ዝግጂት እያደረገ መሆኑን እየገለፅን በአይነት እና በገንዘብ መደገፍ እንደሚቻል አስታውቋል።

-ድጋፍ ለማድረግ
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1000347415891 "ወሎ ቤተ አምሐራ በጎ አድራጎት ድርጅት" ብሎ ድጋፍ ማድረግ ይቻላል።

@የወሎ ቤተ አምሐራ የልማት እና የበጎ አድራጎት ድርጅት              
"የወሎን መልካም እሴት እናስቀጥላለን"
https://t.me/Moamediamoresh

hace 1 semana, 6 días

ቀን 24/04/2017ዓም
            ቀኝ ጌታፐዮፍታሔ ንጉሴ ክፍለ ጦር
                  ጎጃም አማራ!!!
~~~~¡~~¡¡

የአማራ ፋኖ በጎጃም በቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ፮ኛ ክፍለ ጦር አባል ብርጌዶችና የድል ውሏቸው።

እንደሚታወቀው ቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሴ ክፍለ ክፍለ ጦር በየቀኑ ጀብድ መስራት ልማዱ ቢሆንም የተለመደ ተግባሩን ዛሬም በጠላት ላይ ሲያሳይ ውሏል።
ከሰሞኑ በደብረ ኤልያስ ከተማ አስደማሚ ጀብድ መፈፀሙን ተመልክተናል።በየቀኑ ለምን እንደሚዋጉ የማያቁና ምንም የውጊያ ልምድ የሌላቸውን ለአቅመ ጦርነት ያልደረሱ ወጣቶችን ከእየ ስራ ቦታቸው እያፈነ እያመጣ ለደም ግብር ወንበሩ ማፅኛ እንዳደረጋቸው እሙን ነው።
በዛሬው እለት በደብረ ኤልያስ ፣በጮቄ ተራሮች፣በመስታዎት ከባቢዎች አባል ብርጌዶቻችን ከፍተኛ ተጋድሎ በማድረግ ላይ ናቸው።
በተደረገው ውጊያ በጡሀቱ ደብረ ኤልያስ ከተማ ወሽቆ የተቀመጠውን የአብይ አህመድ ቡድን የቀስተ ደመና በርጌድና የኢንጅነር ክበር ተመስጌን ብርጌድ በጋራ ሆነው በቤተክርስቲያን ከባቢ መሽጎ የሚገኘውን የደም ግብር አስጠባቂ የብርሐኑ ጁላ ወንበር ጠባቂ ወሮበላ ቡድን ድባቅ መትተው ሙትና ቁስለኛ አድርገውት ወጥተዋል።
በሌላኛው የድል ዜና ደግሞ ስናንአባ ጅሜ  አይበገሬው በተደጋጋሚ ብዙ ድሎችን አጣጥሟል በ24/04/2017 ዓ.ም የተገኘው ግን ይለያል። በቃ ይለያል አልሁህ!!!!!
በጥቅሉ ወደ ስናን አባጅሜ አናብስቶች መሄድ ይቻላል መመለስ ግን ፈፅሞ አይቻልም እጅግ ጥቂቶቹ ፈጣሪ በታምሩ ከሚያወጣቸው በስተቀር!!!
በተጋጣሚዎች መካከል አሸናፊው የሚለየው እና የሚታወቀው ከዚህ በታች በዕጃችን በገቡት ንብረቶች ብቻ አይገበሬነታችን አሳይተናል!
የጠላት  ኃይል ቁስለኛ  ያለው አይመስለኝም። የአስከሬኑን ቁጥር ራሱ መከላከያ ነኝ  ባዩ ቆጥሮ ቢነግረን ይመረጣል።
ጥሻው ሁሉ አስከሬን ገደሉ ሁሉ ሙት ነው።አርሶ አደሩ በነፍስ ወከፍ ታጥቆት የተረፈው በተዋጊ ፋኖዎች እጅ ተቆጥሮ ገቢ የተደረገው ደግሞ ከዚህ እንደሚከተለው ነው።
የነፍስ ወከፍ ክላሽ     =ሰማንያ( 80)
መትረየስ ወይም ብሬን     = ሁለት(2)
የቡድን መሳሪያ ሞርተር  = ሁለት(2)
በእያንዳንዱ የነፍስ ወከፍና የቡድን መሣሪያ በኩል የተማረከውን የተተኳሽ መጠን  ለጊዜው ቆጥረን መጨረስ ስላልተቻለ ከውጊያ መልስ የምናሳውቅ ይሆናል።
በየሔደችበት ድልን መቀዳጀት ልማዷ የሆነችው የንጉስ ተክለሐይማኖት ብርጌድ ከትናንት ጀምሮ በደባይ ጮቄ እየተደረገ ባለው ውጊያ ከፍተኛ ጀብዱ እያስመዘገበች ቢሆንም ዛሬም በረቡ ገበያ ያለውን ጠላት ከስናን አባ ጅሜ በርጌድ ጋር በመሆን ድግ አመድ እያደረጉት ይገኛሉ።
በሁሉም የዛሬ ውጊያዎች የነፍስ ወከፍ መሣሪያ ከእነ ተተኳሹ በእያንዳንዱ በርጌድ እየተማረከ ይገኛል።
እንመክራለን
እናሰለጥናለን
እንዋጋለን
ድልን እንቀዳጃለን
ህዝባችንን እናስተዳደራለን።የአማራ ፋኖ በጎጃም የእየለት ተግባሩ ይሔው ነው።
የሌለን ሲመስላቸው በዝተን የምንታይ ታምር በተግባር የምናሳይ የምድር ድሮኖች የቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሴ ክፍለ ጦር አባል ፋኖዎች።
አዲስ ምክክር አዲስ ድል
አደስ አብዮት አዲስ ድል
አዲስ ትውልድ
አዲስ አስተሳሰብ
አዲስ ተስፋ
በወንበዴዎች ወንበር የማይናውዝ አዲስ ትውልድ በክንዳችን እና በአንደበታችን እንፈጥራለን።

የአማራ ፋኖ በጎጃም የቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሴ ፮ኛ ክፍለ ጦር ቃል አቀባይ መ/ር ፋኖ ታደገ ይሁኔ(ሸርብ)

ታሕሳስ 24/04/2017 ዓ.ም
https://t.me/Moamediamoresh

hace 2 semanas, 4 días

ሰበር ዜና!

የአማራ ፋኖ በወሎ በቀጠለው የህልዉና ተጋድሎ ላስታ አሳምነው ኮር ተከዜ ክፍለጦር እና ጥራሪ ክፍለጦር በጋራ ባደረጉት ተጋድሎ ታላቅ ድል ተጎናፅፈዋል::

ላስታ አሳምነው ኮር ከተቆጣጠራቸው አካባቢዎች አንዱ በሆነው ኩልመስክ ቀጠና ለማጥቃት ሶስት ሬጅመንት ከመካናይዝድ ጋር ያሰለፈው የአብይ አህመድ ዙፋን ጠባቂ ሰራዊት በፋኖ ኮማንዶ ዘላለም ሲሳይ የሚመራው ተከዜ ክፍለጦርና በአርበኛ ሻለቃ ብርሃን አሰፋ የሚመራው ጥራሪ ክፍለጦር ባደረጉት ብርቱ ትንቅንቅና ተጋድሎ በርካታ ሙትና ቁስለኛዉን ይዞ የተመለሰ ሲሆን ጠላት አሁንም ኩልመስክ ላይ ተከቦ ይገኛል::

ከራያ ቆቦ ተኩለሽና አካባቢው በበርካታ ተደጋጋሚ የደፈጣ ጥቃት ተሰላችቶና መፈናፈኛ አጥቶ ወደ ጊዳን ወረዳና ኩልመስክ የገባው ጠላት ቀጠናዉን ከአመት በላይ ተቆጣጥረው በሚገኙት የላስታ አሳምነው ኮር አሃዶች ጥራሪ ክፍለጦርና ተከዜ ክፍለጦር ተቀብለው እያስተናገዱት ይገኛሉ::

ኩልመስክና ሃሙሲት አካባቢ በተደረገው ጠንካራ ዉጊያ የጠላት ሰራዊት የተረፈረፈ ሲሆን 17 ሙትና 29 ቁስለኛ ሁኗል፤ ቀሪው የጠላት ኃይልም ኩልመስክ ላይ ከበባ ውስጥ ገብቶ እጅ ስጥ እየተባለ ይገኛል፤ ተጋድሎው ታህሳስ 18/2017 ዓ.ም ንጋት ጀምሮ እስከ ምሽት 1:00 ድረስ በጀግኖቹ ተከዜ ክፍለጦር እና ጥራሪ ክፍለጦር ትንቅንቅ የቀጠለ ሲሆን አሁንም የገባው ጠላት በማይወጣበት ሁኔታ ተከቦ ይገኛል::

ቅዱስ ላሊበላ ከተማና ቀጠናው ላይ ፖለቲካዊና ወታደራዊ ድል ለማግኘት የቋመጠው የምርኮኛው ብርሃኑ ጁላ ጦር በተለያየ አቅጣጫ ወደ ቅዱስ ላሊበላ ከተማ ሬሽን ለማስገባት ቢሞክርም የአማራ ፋኖ በወሎ ዋና አዛዥ ዋርካው ምሬ ወዳጆ በሰጠው ትዕዛዝ መሰረት በመጣበት አቅጣጫ ሁሉ እንደ እባብ እየተቀጠቀጠና እየተደመሰሰ ይገኛል።

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ድል ለፋኖ
ድል ለአማራ ህዝብ
የአማራ ፋኖ በወሎ
ወሎ ቤተ-አምሐራ
ታህሳስ 19/2017 ዓ.ም
https://t.me/Moamediamoresh

hace 2 semanas, 4 días
hace 2 semanas, 4 días

የአርበኛ ዘመነ ካሴ መልዕክት‼️**

"ህዝባችን ውሻየን ሽጨ ቀበሮ ገዛው እንዳይለን እንጠንቀቅ:: ህዝባችን ማንገላታት የጀመርን ቀን ጫካውም ውቅያኖሱንም ይክደናል:: ህዝብን የምትበደሉ ካላችሁ ቆም ብልችሁ አስቡ:: የወጣነው ህዝብን ልንታደግ ነው:: "

በዚህ መልእክት ለአርበኛው የደረሱ፣ የሚያውቃቸው በዙ ነገሮች አሉ። በዚህ መሰረት ይሄን ድርጊት የፈጸሙ፣ እና በተለያዩ ዮጠናዎች አለመግባባትን የፈጠሩ አመራሮች ያለአንዳች ቅድመ ሁኔታ እርማት ይውሰዱ።

አጥፊው ከሳሽ የሚሆንበት አጋጣሚ፣ ብዙ ጫጫታዎች ይከሰታሉ። ስለዚህ አጋጥሞ በመስማት ያስፈልጋል። ቅጣት የሚያስፈልገውን በድርጅታዊ ቅጣት፣ በእርቅ የሚያልቀውን በእርቅ መቋጨት ያስፈልጋል። ችግር የሆነው ከአንድ አንድ አጥፊዎች ጋር የድረረጅቱ የበላይ አመራሮች ጭምር መከታነትና ከጀርባ አለን ባይነት የሚፈጠር በመሆኑ ውሉ እንዳይገኝ ወይንም እንዳይፈታ አድርጎታል።

ሌላው ይቅርና ችግር አለ በተባለበት ቦታ ጊዜን አጣቦ ቢቻል አባላቱን ባይቻል ግን የብርጌድና የሻለቃ አመራሮችን አግኝቱ ችግሩን ከአንደበታቸው ሰምቶ መፍታት እንዲቻል ከዚህ በኋላ ጊዜ አለመስጠት ነው። ታላቁ አቢዮተኛ አርበኛ አሁንም እንደጀመርከው የአንተን ማገርነት፣ ዋልታነት፣ መሰሶነት የሚጠይቅ ትግል ነው ያለው። በአንተ አንድ ቃልና ሐቀኛ ሽምግልናና ተግሳጽ የሚስተካከል ችግር አመት እያስቆጠረ ሌላ ችግር እየፈጠረ ብርጌድ እስከመበተን እየደረሰ ነው።

ይሄን መልእክት በአስቸኳይ ወደ መሬት በማውረድ ቢቻል በአካል ተገኝተህ፣ ባይቻል ግን የበታች ወንድሞችህ ከአለህበት ድረስ እየተገኙ ችግሮችን እንድትፈታላቸውና ለዐማራ እንዲሞቱ እንድትፈቅድላቸው የሚፈልጉ የሚለምኑ ብዙ ናቸው !!
18/04/2017 ዓ**/ም
https://t.me/Moamediamoresh

hace 3 semanas, 4 días
ሞዐ ሚዲያ- Moaa Media…✍
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated hace 3 semanas, 5 días

Last updated hace 3 semanas

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated hace 1 mes, 1 semana