? አዳም ረታ ?

Description
ቀንዎን ያሳምሩ
?የአዳም ረታ እና ሌሎችም እውቅ ደራሲያን ስራዎች
?ግጥሞች
?የአማርኛ መፅሀፍት በ pdf
? አዝናኝ እና ቁምነገር አዘል ፅሁፎች
?ሙዚቃዎች እና ሌሎችም የምትፈልጓቸውን አንድ ላይ በ አዳም ረታ ያግኙ።
? የመፃህፍት ጥቆማ

@AdamuReta
@AdamuReta
@AdamuReta

For cross promotion contact

@isrik

@isrik
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 2 months, 3 weeks ago

Last updated 2 months, 2 weeks ago

ይህ ስለ Manchester United መረጃዎችን የሚያገኙበት የ Telegram ቻናል ነው 🇪🇹
--------------------------------------------------------------
☞︎| ስለ ማንቸስተር ዩናይትድ ትኩስ መረጃዎች
☞| ቀጥታ ስርጭቶች ከየስታድየሞቹ
☞| የዝውውር ዜናዎች
☞| ስለ ማንችስተር ዩናይትድ ታሪኮች

📩 ለማስታወቂያ ስራ DM :- @Marcoabdu

Last updated 1 month, 2 weeks ago

3 months, 1 week ago

ደራሲ የሚፅፈው በዚህና በዚህ ውስጣዊ ግፊትና ውጫዊ ኤክስፔክቴሽን ነው። አንባቢም አንዳንዴ ደጅህ የቆመ ነዳያን ነው። ወጣ ብለህ የሆነ ነገር ከጓዳህ ቆርሰህ ካልመፀወትከው እንቅልፍ አያስተኛህም። ዕረፍት ይነሳኻል።

ደራሲ አንዳንዴ ከሩህሩኋ ነፍሱ የተነሳም ቤት ያፈራውንም ይፅፋል። የደረስክበትንም ያጎርስሃል። ያለችውን ቤሳም ይሰጥሃል። የሥጦታ ፈረስ ነች። ወይ የማርያም ፈረስ። ጥርሶቿን ገልጠህ አታይም። አመስግነህ፣ መርቀህ ትቀበላለህ። የአዳም አንዳንድ በመጨረሻ ያነበብኳቸው ድርሰቶች እንደዚያ የመሠሉኝ ጊዜ ነበር። እንደ ምፅዋት። ("ምፅዋት" ደሞ አሪፍ ርዕስ ሆነብኝ?! የሰማህ ላልሰማ አሰማ!)።

በነገራችን ላይ በእኛ ሀገር፣ በአማርኛ ብቻ ስለተፃፈ እንጂ፣ የአዳም ረታ የግራጫ ቃጭሎች ህፃን መዝገቡ፣ በማንኛውም መስፈርት፣ በግሌ በዚህች አጭር ዘመኔ ካነበብኳቸው የየትኛውም ዘመን በዓለም የታወቁ መሠል ይዘት ካላቸው ሊትሬቸሮች የሚያስከነዳና የሚልቅ እንጂ የሚያንስ አይደለም።

አዳም ያለውን ሁሉ የኢማጂኔሽን ኃይል አንጠፍጥፎ ህፃኑን መዝገቡን ለመፍጠር ያዋለው ሁሉ ይመስለኛል። ልክ የግሪኩ ፕሮሜቲየስ ከአማልክቱ ላይ እንደምንም ሠርቆ፣ ተጋግጦ፣ ነፍሱን ሸጦ፣ የማይገባበት ገብቶ በሰው ልጅ ልብ ውስጥ የአማልክቱን ፍም ጨመረበት እንደሚሉት ይሆንብኛል የህፃኑ መዝገቡ ገፀባህርይ አፈጣጠር።

አዳም ያንን ህፃን የፈጠረው እንደ ፕሮሜትየስ በመሠለ፣ ተወዳዳሪ በማይገኝለት የሰውልጅ ፍቅርና የመፍጠር ፍላጎት ተመርቶ መሆን አለበት። ወሰኖችን ሁሉ ጥሶ ነው መዝገቡን አምጦ የወለደው።

ከዚያ በፊትም፣ ከዚያ በኋላም የነበሩ ልማዳዊ የአፃፃፍ መንገዶችን ሁሉ የሚጠረማምስ፣ እስከ ጠብታው የተንጠፈጠፈ የመፍጠር አቅም ነው በመዘገቡ ካራክተር ውስጥ እንደ ተራራ ገዝፎ የሚታየው። እስካነበብኩት፣ እና እስከማውቀው ይረስ፣ አዳም ለኢትዮጵያችን ብቻ ሳይሆን ለዓለምም ያበረከተው አስገራሚና ዘለዓለማዊ ገፀባህርይ ህፃን መዝገቡ ይመስለኛል። That kid is so vivid!

የአዳም የምናብ ህፃን መዝገቡ፣ አንድ ህፃን ብቻ አይደለም። ብዙ ሰው ነው። ዓለም ነው። አንዴ አውቀኸው ዕድሜህን ሙሉ ልትረሳው አትችልም። የአዳም ስነፅሑፋዊ የምናብ ልህቀት ከፍታ የታየበት እጅግ አስደናቂ የፈጠራ በረከት ነው።

ጂኒየሱ አዳም ረታ፣ ጂኒየስን ህፃን ፈጥሮ ሰጠን። ጂኒየሱ የትምህርት ቤት፣ የክፍልውስጥ ጂኒየስ አይደለም። እውነተኛው፣ በየጓዳው፣ በየህይወት ፈርጁ ቤክኖ የሚቀረው፣ ብርቁ፣ በፍለጋ የሚገኘው ኢትዮጵያዊ ጂኒየስ ነው በጌራጫ ቃጭሎች ውስጥ የተሰጠን።

በነገራችን ላይ አዳም ረታ ግራጫ ቃጭሎችን ሁለት ቦታ ከፍሎ ህፃኑን መዝገቡ፣ እና ፖሊሱን መዝገቡ በአኔድ ሽፋን ሥር ማስቀመጡ ትልቅ ስህተት መስሎ የሚሰማኝ እኔን ብቻ ይሆን? እላለሁ።

የሁለቱ የተለያዩ ገፀባህርዮች በአንድ መፅሐፍ በደባልነት እንዲኖሩ ማድረጉ ፍፁም ስህተት ነበር ብዬ አስቤያለሁ ደጋግሜ። ደሞ ህፃኑ አድጎ... ምናምን ዓይነት ተረት-ተረት ትልቁን ድንቅ ምሥል ወደ ተራ ትረካነት ያወርደዋል። በበኩሌ ህፃኑ መዝገቡ ከማንም ጋር መደባለቅ አልነበረበትም ባይ ነኝ። መዝገቡ በራሱ monumental character ነው። ተከታይና ተቀፅላ ደባል የማያሻው ምሉዕ ፍጡሩ ነበር። ነው።

አዳም ረታ ለሁለተኛው መዝገቡ የመረጠለት የትረካ መጓጓዣ የከተማ ፖሊስነትን ነበር። ምርጫውን አደንቃለሁ። ፖሊሶች በየሰፈሩ፣ በየመንገዱ ሲንቀዋለሉ የማያዩት፣ የማይታዘቡት፣ የማይጠረጥሩት ነገር የለም። በፖሊስ ዓይን በኩል እያደረግክ ብዙ ነገሮችን ልትፅፍ ትችላለህ። ሰፊና ተዘዋዋሪ vehicle ነው የመረጠው አዳም።

በመጀመሪያው ህፃኑ መዝገቡ ተለክፈን ስለምንቀር ኋለኛው ፖሊሱ መዝገቡ ተጋርዶብን ይቀራል እንጂ፣ በፖሊሱ መዝገቡ ውስጥ አዳም የተጠቀማቸው surreal ምናቦችና ትረካዎች፣ ህፃኑንና አዋቂውን መዝገቡን ለማገናኘት የተጠቀመባት ወደ ሠማይ ተወርውራ ተሰውራ የምትቀር የባልጩት ድንጋይ፣ ሙጃሌያሞቹ የመርካቶ ስውር ቅዠታዊ ገፀባህርያት፣ የአዲስ አበባ የዕለት ትዝብቶች፣ ብዙዎቹ ድንቅ ነበሩ።

ግን ከህፃኑ መዝገቡ ጋር የአዋቂው መዝገቡ ባንድ ላይ መጠረዝ በክትፎ ላይ ገንፎ እንደመጨመር ዓይነት ይሆናል። ሁለቱም ለየብቻው ድንቅ ነው። አብሮ መሆኑ ጭማሪውን በሙሉ ልብህ እንዳታጣጥመው ያደርግሃል። የጠገበ አንጀትህ ይኮራብሃል። ትዕግሥትህ ይሟጠጣል።

እና ደሞ የህፃኑ መዝገቡ አስደናቂና ገበገፅ የማይገመት ጥልቅነት፣ በአዋቂው ፖሊስ ላይ የለም። ፖሊስ ጥልቅ ሊሆን እንደማይችል ካላመንን በስተቀር፣ ወይ አዳም የምናቡን ነፋስመውጫን የሚያውቃትን ያህል አዲሳባን አያውቃትም ካላልን በስተቀር፣ የፖሊሱ መዝገቡ ገፀባህርይ ሥዕሉ ግልፅ አይደለም።

ፖሊሱ ልክ በመንገድህ እንደምታገኘው ፖሊስ፣ ዩኒፎርሙን ብቻ አስታውሰህ፣ የምትዘነጋው ነው። ስሙንማ አታስበውም። አዋቂው መዝገቡ ተነቦ የሚረሳ ነው። ምናልባት ለብቻው ቢያደርገው ኖሮ (ኖሮ የሚል ቃል ባልወድም!) ምናልባት አዋቂው መዝገቡም፣ እንደ ህፃኑ ለሁሌ የሚታወስ ኗሪ ገፀባህርይ መሆን ይችል ነበር።

ባጠቃላይ አዳም ረታ ባለ ኢማጂኔሽን ደራሲ ነው። ድርሰትን የደረቅ እውነታዎች ነፀብራቅ ብቻ ሳይሆን፣ ያፈተለኩ፣ ታሪካቸው ያልተነገረ ሕልሞችና ቅዠቶችም መናገሪያ ልሣን መሆኑን አዳም በሥራዎቹ አሳይቶናል። ብዙ ሰጥቶናል። ገና ብዙ አቅምም አለው።

አዳምን ገና ጨርሼ አላነበብኩትም። ሰውን ጨርሰህ ልታነበው ትችላለህ ማለቴ አይደለም። የፃፋቸውን ሁሉ አላነበብኩም። አነባለሁ። አይቀርም። እሱም ጨምሮ መፃፉ አይቀርም። በረከቱ ብዙ ነው። ተፅዕኖው ብዙ ነው አዳም።

አስማትም ነገር ሳይመስጠው አይቀርም። ይሄ የዕፀ-መሰውር ሃሳብ ሳይወሰውሰው አልቀረም። በአዳም ዓለም ወደ ላይ ተወርውራ የምትጠፋ ጠጠር አለች። ተወርውራ እንደተሰለበች የምትቀር ቀለበት አለች። ዛሬ ታይቶ ነገ የሚጠፋ፣ የሚሰወር ሙሉ ሰፈር አለ።

ሽሮሜዳና ነፋስመውጫ፣ የእንጀራእናት እና እንጀራና መረቅ፣ ማስቲካና ፓስቲ፣ የሴትልጅ ክብረትና ክስረት አለ በአዳም ዓለም ውስጥ ተነባብሮ። ደራሲው ምንምን ነገር ክስረት አይለውም። ስኬትም አይልም። አይፈርድም። አይደመድምም።

አዳም ያየውን፣ የሰማውን፣ ያለመውን እንድታይ፣ ያየው የተኖረው የተፈሳው እንዳያመልጥህ፣ ከአብዮቱ ፎቶዎች ውስጥ ተረስቶ የቀረውን ያንተንና የቢጤዎችህን ምስል ያመጣልሃል። ሁሉን ይነግርሃል። ፍርዱን ይተውልሃል። የተጋነነውን ሰዋዊ ያደርገዋል። ሰዋዊው ላይ አስማተ መለኮት ይጨምርበታል። እንባዎች ላይ ጥቂት ፈገግታን ይዘራል። ጉልበታም ደራሲ ነው አዳም። ሕልመኛም።

ያልተነበቡት እንዲነበቡ፣ ያልተፃፉትም ሽፋን ለብሰው እንዲቀላቀሉን ከልብ እመኛለሁ። ይህ የአዳም ምስል ድንቅ ነው። ከለር ጨመርኩለት። እንደ ብዕሩ። የአንድ ዘመን መልክ ነው። እና የብዙ እሳቦቶች ሰው ግርማ (the face of one person, with millions of imagination)!

ረዥም ዕድሜና ጤና በረከቱን ሁሉ አብዝቶ እንዲሰጠው ለደራሲያችን ተመኘሁ! ለእኛም! ለከነማዎች!???

ፈጣሪ ኢትዮጵያችንን ይባርክ!

መልካም ጊዜ!

©Assef Hailu

@AdamuReta

3 months, 1 week ago

ጥቂት ሃሳቦች ስለ አዳም . . .

__ ? ___

አዳም ረታ ባለ ምጡቅ አድማስ ደራሲ ነው። የሚያከራክር አይመስለኝም። ብዙ እጅግ የተለዩ፣ እንደ ዋዛ የማታልፋቸው፣ ደስ የሚል ግላዊ ነፃነትና የማሰብ ከፍታ የሚታይባቸው፣ እይታዎች አሉት።

አዳም ሲፅፍ የረጋ ዕለታዊ ክንውኖችን በሚያሳዝንም፣ አንደርድሮ በሚወስድም የልጅነትና የወጣትነት ትዝታ እያዋዛ መከተብ ይችልበታል። በሺህዎች ኪሎሜትርና በብዙ ዓመታት ርቀት ከተመላለሰባቸው አፈሮችና ቀዬዎች ርቆም፣ የማይደበዝዝ የትውስታ መነፅሩ አንባቢን የሚያስደንቅ ነው።

በዚህ ውክቢያ በበዛበት ዓለም፣ በዚህ ከአሁን ሩጫ አልፎ ስለ ትናንት ይቅርና ስለ ነገ ማሰብ በተሳነን "የአሁንነት ኃይል" የዘመኑ መፈክር በሆነበት በዚህ የፈጣን ሎተሪ ጊዜ፣ አዳም ረታ ጊዜ ይሰጣል ማለት ነው ያለፈባቸውን ዳናዎች ለማሰብ፣ ለመቁጠር፣ የቀረፃቸውን ትውስታዎች በአርምሞ ለመመንጠር። ለራሱነቱ እና በዕድሜ በዘመኑ ለተኖሩ እያንዳንዳቸው ሰዎች ጊዜና ቁብ ይሰጣል ማለት ነው።

አዳም በሰጠን ገፆች በኩል ስለሚገልፃቸው ነገሮች እያነበብኩ፣ እና ገፁን ገልጬ ባነበብኩት ቁጥር፣ እሱ የቱ ጋር ነበር ይሄ ሲሆን? ነፍሱ የት ጋር ነች የደራሲው? እያልኩ ማሰቤ አልቀረም። በተለይ የዚያን ትውልድ ነገሮች እያስታወሰ አሊያም እያለመ ሲፅፍ።

ሳስበው አዳም ገና ኪነሻው ጀምሮ ይሄ ፖለቲካ የሚባለው ነገር፣ ብዙውን ሰዋዊ ነገራችንን እንዳስረሳን የነቃ፣ ነቅቶም የተበሳጨ ይመስለኛል። የኔና የሰፈሬ ልጆች ታሪክ እዚህ ውስጥ የታለ? ብሎ የጠየቀና የሚጠይቅ ይመስለኛል።

የመገዳደልና የመቧደን ታሪኮች፣ ከታሪካችን ሁሉ ገዝፈው ከወጡበት የ60ዎቹና የ70ዎቹ ኢትዮጵያ ውስጥ፣ እርሱ አብረውት ቀንን ያሳለፉ ጓደኞቹን፣ በየሰፈሩ ውስጥ ቁራሌው እያሉ የጮሁ ድምፆችን፣ የሻይ ቤቶቹን የተለየ የሻይቅጠልና የፓስቲ ሽታዎች፣ የወዳደቁትን ቆሼዎችና የየመንደሩን ውሪ ሁሉ ፈልጎ ያጣ ይመስለኛል።

የያ ዘመን የአብዮቱና የሥርነቀል ተራማጆቹ ፍትጊያ ታሪክ፣ ብዙውን ወርቃማ የጓዳ እፍታዎች ጣዕም በትላልቅ የዘመቻ ድንኳኖች የጋረደበት ይመስለኛል። ወይም በአሜሪካን ሽጉጥ ያዳፈነበት። በኡዚ የቀበረበት፣ ወይም ከጃፓን መጥቶ በቦክስ በሚማታው አስተማሪ የረመረመበት አድርጎ ሳያስበው እና ሳይበሳጭ የቀረ አይመስለኝም።

አዳም በ70ዎቹ የፃፋቸውን በየመሐሉ በገፆች ላይ ብቅ ካደረጋቸው የማልረሳቸው የእሱን የግሉን ሰዋዊ ነፍስ አጥብቃ የምትሻውን፣ በከበባት ግርግር ትንፋሽ ያጠራትን ነፍሱን ደጋግሜ አይቻታለሁ።

በአንድ ቦታ ላይ አዳም፣ ከሰፈሩ ልብስ-ሰፊና የእድር ድንኳን የመጣችን በጂንስ የተጣፈች ጨርቅ፣ ታፍሶ በሄደባት የወታደሮች ማሠልጠኛ ካምፕ ውስጥ፣ በጀርባው በተንጋለለበት የድንኳኑን ጣሪያ ሲያይ፣ እንደ ድሪንቶ ከየቦታው በተዋጣ ልብስ በተሰፋው ድንኳን ላይ፣ ያቺን የሰፈሩን ልብስ-ሰፊ የጂንስ ቅዳጅ ያያታል። እና ርንደ እብድ ብቻውን ከትከት ብሎ ይስቃል።

አዳም ያኔ። እና አዳም አሁን። ሳስበው በሀገሪቱ የግሩፕ ፎቶ ውስጥ፣ የራሱን ፎቶ ፈልጎ ያጣና የተናደደ ሰው ነው። ለዚያም ነው የእኔና የጓደኞቼ፣ የሰፈርቸኞቼ፣ የረሰዉም የዝንቡም፣ የቅምቀማውም የዝምዘማውም ታሪክ ይኸውና ብሎ ሆን ተብሎ የተዘነጋበትን ሰዋዊ ታሪክ፣ ሳይፃፉ ከነቀሩት የየጊዜው ቅዠቶችና ውሎዎች ጋር ደግሞ ደጋግሞ ሲፅፍ የምናየው።

በዚህ ነገሩ አዳም ከእርሱ መፅሐፎች ለንባብ መብቃት በኋላ ለተከተሉት፣ ከደረቅ መንቻካ የፖለቲካ ድርሳኖች ወጣ እና ጠለቅ ብለው፣ ሰብዓዊ ሰበዞችን እየመዘዙ ብቅ ማለት ለጀመሩት የዚያ ዘመን ድርሳን ከታቢዎች የመጀመሪያው ፋና ወጊ፣ ዓይን ገላጭ፣ እና ቢቀበሉትም ባይቀበሉትም የእይታና የትውስታቸው ቀስቃሽ፣ አርዓያ የሆናቸው ይመስለኛል።

በተለያየ ንጥል ማስታወሻዎች በስማበለው ከምሰማውና በቃል ከወዳጆች ከሚጠረርልኝ የቃል መነባንቦች አልፌ፣ የአዳም ረታን የቀደሙትን የብዕር እፍታዎች ማህሌትንና ሎሚ ሽታን አላነበብኩም። የኋለኞቹን ስንክሣሮቹን የስንብት ቀለማትንና አፍንም አላነበብኩም። እስከዛሬም ግራጫ ቃጭሎቹ ላይ ነኝ።

ከግራጫ ቃጭሎች እና ድሮ ሀገር ውስጥ እያለ ከፃፋቸው አጭሬዎች በቀር ዘልቆ ቀልቤን የሠረቀብኝ፣ ኢማጂኔሽኔን የጠለፈብኝ፣ ወይ ጎኔን በብዕር ጫፍ የነደፈኝን አንድም ሌላ የአዳም ኪታብ ስለማግኘቴም እርግጠኛ አይደለሁም። ምናልባት መረቅ! መረቅ ጥሩ የግራጫ ቃጭሎች ዓይነት አይረሴ ነፍስ ያለበት ምግብ ነው። ጣዕም ያለው። የተለየ። እና የማይረሳ።

አንዴ በግራጫ ቃጭሎች ከተነደፍኩ ወይም ከተለከፍኩ በኋላ፣ ከአዳም እፍታዎች መሐል አለንጋና ምሥርን፣ ከሠማይ የወረደ ፍርፍርን፣ ይወስዳል መንገድ ያመጣል መንገድን፣ ሕማማትና በገናን፣ እና መረቅን በተለያየ ጊዜ አንብቤያለሁ። ግን ውስጤ የቀሩ ትውስታዎች ኢምንት ናቸው ብል እውነቴን ነው።

ብዙ መፅሐፎች (ሳገኝ እና አፍታ ሲገኝ) አነባለሁ። በሩጫም በጡጫም አነባለሁ። ብዙ አነባለሁ። እና ብዙ አረሳለሁ። ተገልጠው የሚከደኑ፣ እና የሚረሱ ብዙ መፅሐፍትን አንብቤያለሁ። አንብቤ የማላስታውስበት ምክንያት አንድም ትውስታዬ ረግቦ ይሆናል። አንድም ደግሞ የሚታወስ የተለየ ነገርን በውስጤ አትመውብኝ ስላላለፉ ይሆናል። ግምቴን ነው የምፅፈው።

እና የአዳምን መፅሐፍት ከግራጫ ቃጭሎች አንስቼ እስከተወሰነ ጊዜ ተከተልኩ። ግን የተለየ፣ የፈነጠቀ፣ የጠረመሰ ነገር አላየሁም። እንደ ምርቃት፣ ቅቅሉን ከበላህ በኋላ መረቅ እንደሚመጣልህ ዓይነት፣ መረቅን ጣል አድርጎልኛል። በተረፈ አንብቤ የጣልኩት የበዛብኝ ወቅት እንደነበረ ትዝ ይለኛል።

የግድ መፃፍ አለብህ ተብሎ የሚፅፍ ፍርደኛ ሁሉ የመሠለኝ ወቅት ነበር አዳም። አንዱን ባለ ብላክ ኤንድ ዋይት ገፅ መፅሐፉን እያነበብኩ።

ለምን አይታገስም ትልቁ ዳይኖሰር የመሠለ ሃሳብና ገፀባህርይ በአካል በአምሣል ቤቱ ገብቶ ዳንኪራውን እስኪጨፍርበት ድረስ? ምንድነው ችኮላው መፅሐፍ ለማዝነብ? ያልኩበት አጋጣሚ ነበር። እያነበብኩ ነው ግን እንዲህ የምለው። ለራሴ።

ደግነቱኮ የማይነበብ ነገር አይፅፍም አዳም። ግን በግራጫ ቃጭሎች ላይ ያየሁትን ያንን ከዓለም የገዘፈውን የህፃን መዝገቡን ከፍታ፣ በሌሎች ባነበብኳቸው ሥራዎቹ ላይ አላገኘሁም። እና ተውኩት። አፍ እና የስንብት ቀለማት በዓይኔ ላይ እየዋለሉ፣በጓደኞች እጅ እየተንገዋለሉ፣ እና እያማሩኝም፣ ሌላ ጊዜ እያልኩ የቀጣኋቸው (ለዛሬ ይለፈኝ አመሠግናለሁ፣ ብዬ ያለፍኳቸውም) ለዚያ ይመስለኛል።

ግን ደራሲ የሚፅፈው ህይወትን፣ ምናብን፣ ሕልምንና ቅዠትን ጭምር ነው። ማንኛውም ድርሰት የሆነ እንደ ዛር በል በል ብሎ በደራሲው ብዕር ላይ አዶከብሬ የረገጠ የአንድ ወይም የሌላ ፃፍ ፃፍ የሚል ውቃቢ የጎበኘው ነው። መፃፍም ጠኔ ነው። ይሞረሙራል። ብዕርም ልፍሰስ የሚል ቀለም አለው። ሃሳብም እንደ ሐምሌ መብረቅ ደጋግሞ ብልጭ ይላል። ሞገዱ አያስተኛም። ጭቅጨቃው አያስቦዝንም። እና ደራሲ ይፅፋል።

መፃፍ ሥራው ስለሆነ አይደለም ደራሲ የሚፅፈው። ብዙውን ጊዜ በውስጣዊው የነፍሱ ርዕደ-መሬት ግፊት መጠን ነው። እንደ ማግማ ነው የድርሰት ሃሳብ። ይፈልቃል፣ ይንተከተካል በውስጥህ። አውጥተኸው መገላገል አለብህ። ያንን የእሣተ ገሞራ ፍንጥቅጣቂም ደግሞ የሚጠብቁ የተራቡ ዓይኖች፣ የተጠሙ ነፍሶች አሉ። ስለ እመ ብሩሃን የሚሉ ደጅህ ቆመው።

3 months, 1 week ago

ዓለም ዘጠኝ ዓለም በቃኝ
( ©እስራኤል )

በአፈኛ አንደበት ፥ ስሜን ሳላጎድፍ
ዘምቼ ሳልማርክ ፥ ወይ ጦሜ ሳልገድፍ
በነገስታት መንበር ፥ ተሹሜ ሳልነ'ግስ
ተጠርጌ ሳልወድቅ ፥ ልክ እንደ ግሳንግስ
መብቴን ለማስጠበቅ፥ ሹመኛ ሳልሞግት
ወይ ጥገት አስሬ ፥ ጠዋት ሳላልብ ግት
በአንገቴ ላይ ገመድ ፥ በደረቴ ሳንጃ
አጣማጅ አጥቼ ፥ ሆኜ ባልፍ ቀንጃ
እንደዚህ ባለ ፍርድ ፥ ለሞት ድግስ ቢያጩኝ
ዘብጥያ ጥለውኝ ፥ ጠጉሬን ካልላጩኝ
አቦ ምኑን ኖርኩኝ።
በአማላጅ ልመና ፥ ተነጥፎልኝ ኩታ
ሰርክ እጅ ካልነሱኝ ፥ ለእግዚሐር ሰላምታ
በመላ በጥበብ ፥ ለፍርድ በአደባባይ
አንዱን በተናጠል ፥ ሌላውን በጉባይ
እንደ አርያም መንግስት ፥ፍትህ እያሰፈንኩኝ
አንዴ ርትዕ ሆኜ ፥አንድየ እየበደልኩኝ
በነቃፊ ምላስ ፥እየተወደስኩኝ
በአፋቸው ሾተል ፥ካልተተረትርኩኝ
አቦ ምኑን ኖርኩኝ።

ጠፈር እንደሚያደምቅ ፥
እንደ ሶ'ብይ ሳቅ፣
በየአውራጃው ሁሉ ካልተወደስኩበት ፥
በተሰጠኝ አህላቅ፣
በዕምነት ተቀብዬ በክብር ካልመለስኩኝ
የወሰድሁትን ሃቅ፣
ዘመን በዘመን ላይ፥ ኮተቱን ቢደርብ
እንደ ንስር ሳል'ከንፍ ፥ እንደ አሳ ሳልሰ'ርብ
እንደ ጉልበተኛ ፥ደዌ ካልደቆሰኝ
ጎርሼ ለማደር ፥ ቤሳ ካላነሰኝ
አንጀቴ ካልላላ ፥ ትንንሹ ነገር
ሆዴን ካላባሰኝ፤
የሰው ፊት አይቼ ፥ ዕድሌን ካልረገምሁ
ካልተሸማቀቅሁኝ ፤
አቦ ምኑን ኖርኩኝ።

@AdamuReta
@AdamuReta

@getem
@getem
@getem

3 months, 2 weeks ago

ባሕሩ ቀኜ

??❤️

ደርባባ ?

@AdamuReta
@isrik

3 months, 2 weeks ago

ደራሲ - ብርሃኑ ዘርይሁን

የቴዎድሮስ እንባ

@AdamuReta
@isrik

3 months, 2 weeks ago

የታንጉት ምስጢ

ደራሲ - ብርሀኑ ዘሪሁን

ዘውግ - ልብወለድ ( ታሪካዊ )

የህትመት ዘመን - 1958

የገፅ ብዛት - 228

በሀገራችን ከተፃፉ ታሪካዊ ልብወለዶች መሀከል እጅግ ተወዳጅ ከመሆኑም በላይ አንዳንዶች የአማርኛ ስነፅሁፍ ማስተርፒስ ይሉታል። በሀገራችን በአፄ ቴዎድሮስ ህይወት ዙሪያ ከተፃፉት 2 ታሪካዊ ልብወለዶች ( አንድ ለናቱ & የታንጉት ምስጢር ) የተሻለ ቦታ የሚሰጠውም ይህ መፅሀፍ ነው።

@AdamuReta
@isrik

3 months, 3 weeks ago

" ሰዎች የደበቁትን ጎዶሎ ነገር አለማየት ትልቅነት ይመስለኝ ነበር ለካ ያለንን ውድ ነገር አለማሳየት ይበልጣል "

ሁለተኛው እትብት

በኃይሉ ሙሉጌታ

@AdamuReta
@isrik

3 months, 3 weeks ago

ለካ ሁሉ ነገር አይወጣም ከሚዛን
ከፍ ዝቅ አይልም ፥ ምንም ዳኛው ቢካን
ሁለት ስህተት ፥ ሁለት እውነት ፥ ለአንድ ቦታ
ያለ አጥፊ የሚከሰት ግድፈት አለ
  ከላይ ሲታጭ ለይሁንታ ።

ሲጠቋቆሙ ቢውሉ ፥ የማይፈታ ከስሩ
ችሎቱ ማይደመደም ፥ ማንንም እማኝ ቢጠሩ ።

          ምሕረት ዘነበ

3 months, 3 weeks ago
4 months ago

That May evening as we headed back home, tipsy but still clear-eyed, I saw Tebareki at the corner of the field where girls usually gathered to play games. She was picking up pebbles and throwing them at something I could not see. As she leaned over to pick up another pebble, her dress rode up. Although she tried to pull it back down, I saw her big thighs.
She straightened up, rubbed her hands together to clean off the dust, and ran back to her home; her light summer dress showing her shapely butt. Her smooth legs mesmerized me, finally making me realize that I was in love with this young woman with whom I had grown up most of my life. This realisation, and the memory of Almaz’s prophecy made me trip… For the first time in my life, I believed in fortunetelling and this belief scared me.

@AdamuReta
@isrik

We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 2 months, 3 weeks ago

Last updated 2 months, 2 weeks ago

ይህ ስለ Manchester United መረጃዎችን የሚያገኙበት የ Telegram ቻናል ነው 🇪🇹
--------------------------------------------------------------
☞︎| ስለ ማንቸስተር ዩናይትድ ትኩስ መረጃዎች
☞| ቀጥታ ስርጭቶች ከየስታድየሞቹ
☞| የዝውውር ዜናዎች
☞| ስለ ማንችስተር ዩናይትድ ታሪኮች

📩 ለማስታወቂያ ስራ DM :- @Marcoabdu

Last updated 1 month, 2 weeks ago